TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
“ ... 1,500 ካ/ሜ ግሪን ኤርያውን 12 ወጣቶች መጥተው አጠሩት ” - ቅሬታ አቅራቢዎች

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አካባቢ በሚገኘውና በ1979 ዓ/ም ለ “ አዲስ አበባ 100ኛ ዓመት ቤት ሥራ ማኀበር ” ተሰጥቶ ነበር የተባለ 1500 ካ/ሜ መሬት የመከነ ማስረጃ ባቀረቡ ሰዎች መታጠሩን ማኅበሩ ገለጸ።

ቦታው በ1979 ዓ/ም ለማኀበሩ ከተሰጠ ጊዜ ጀምሮ “ የአዲስ አበባ 100ኛ ዓመት ግሪን ኤሪያ ” እየተባለ ይጠራ እንደነበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል።

“ በፊት የአዲስ አበባ 100ኛ ዓመት ግሪን ኤሪያ ነበረ። በኋላ ‘ የአካባቢው ማህበረሰብ ይጠቀምበት ’ ተባለ ” ብሏል።

በዚህም የማኀበሩ አባላት በግንብ እንዳሳጠሩት ፣ ጥበቃም ቀጥረው ጥበቃ ያስደርጉለት እንደነበር ፣ ቦታው ላይ የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት የሚመለከታቸውን አካላት ቢጠየቅም ፣ “ ለጊዜው ቆዩ ስንወስንላችሁ ትሰራላችሁ ” ተብለው እየጠበቁ እንደነበር ገልጿል።

ይህ በሆነበት ግን ወጣቶች መጥተው ቦታውን እንዳጠሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገልጸዋል።

ማኀበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ “ ጥበቃውም ሰሞኑን ጥሎ ሄደ አስገድደውት ይሁን ተስማምቶ ይሁን አናውቅም። ልክ እሱ እንደሄደ 1,500 ካሬ ግሪን ኤሪያውን 12 ወጣቶች መጥተው አጠሩት ” ብሏል።

ማኅበሩ እጄ ላይ አሉ ያላቸውን ዶክመንቶችም ልኳል።

“ ‘አረንጓዴው እንዳይሸፈን’ ብለውን እኛ ባጭሩ በግንብ አጥረን ከላይ ብረት አድርገንበት ነበር ” ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎች ፥ “ አሁን ግን እነርሱ ሙሉ ለሙሉ #በቆርቆሮ ግጥም አድርገው አጠሩት ” ብለዋል።

አክለው “  2 ጊዜ ፎርጂድ ካርታ አሰርተውበት የማኀበሩ ተጠሪዎች ሂደው አምክነውታል በ2011 እና በ2014 ዓ/ም ” ሲሉ አስታውሰው፣ ቦታውን ያጠሩት ወጣቶች ለደንቦች ያቀረቡት በ2011 ዓ/ም ማኀበሩ ያመከነውን ሰነድ እንደሆነ፣ ማኀበሩ ከቦታው የምስክር ወረቀት ሁሉ እንዳለው አስረድተዋል።

ግሪን ኤሪያው በማኀበሩ አማካኝነት ፦
- መብራትና ውሃ እንደገባለት፣
- ወይራ፣ ፅድ የመሳሰሉ አገር በቀል እፅዋቶች እንደለሙበት፣
- ህጻናትም በየወቅቱ እየገቡ #የሚናፈሱበት አረጓዴ መናፈሻ እንደሆነ የገለጹት ቅሬታ አቅሬቢዎቹ፣ “ ይሄ እያለ ነው ሰዎቹ መጥተው ያጠሩት ” ብለዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ ጉዳዩን መንግሥት ትኩረት እንዲሰጠው የጠየቁ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩኩ ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ ለማግኘት ወደ ክፍለ ከተማው ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

አዋኪ ድርጊት በሚፈፀምባቸው ንግድ ቤቶች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

ሰሞኑን በቦሌ ክፍለ ከተማ ከ3 ሺህ 80 የሺሻ ዕቃ እና 80 ኪሎ ግራም አደንዛዥ ዕፅ ተይዞ መወገዱን ገልጿል።

በህጋዊ ንግድ ሽፋን ሺሻ እና አደንዛዥ ዕፅ ሲጨስባቸው ከተገኙ ቤቶች ነው ይሄ የተያዘው።

ፖሊስ በሰጠው መረጃ በድንገተኛ ቁጥጥር ከተደረገባቸው መካከል ፦
- መኖሪያ ቤቶች
-  ፔንሲዮኖች፣
- ማሳጅ ቤቶች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ይገኙበታል፡፡

ይህ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለይም በአዲስ አበባ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ያለው አዋኪ ድርጊት እጅግ ትኩረት የሚሻ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ የደረሰው መልዕክት ያስረዳል።

በተለይ ተማሪዎች፣ ህፃናት፣ የወለዱ እናቶች፣ ቀን ስራ ደክመው የሚገቡ በርካታ ዜጎች ባሉባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ብዙ አዋኪ ድርጊቶች በመኖራቸው ትኩረትን ያሻል።

የግል መኖሪያ ቤቶች ለሺሻ ማጬሻ ፣ ለመጠጥ መጠቻ፣ ለሲጋራ ማጬሻ እየዋሉ ማህበረሰቡ እንደሚታወክ ተጠቁሟል።

ምሽት ላይም ቢሆን ከጭፈራ ቤቶች የሚወጣው ድምጽ ማህበረሰቡን ሰላም የሚነሳ በመሆኑ ቁጥጥር እንዲደረግ ተጠይቋል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

" የስፖርት ውርርድ / የቤቲንግ ቤቶች #ሊታገዱ ይገባል " ሲል የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አሳሰበ።

ሚኒስቴሩ ዛሬ የ9 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለተ/ም/ቤት አቅርቦ ነበር።

በዚህ ወቅት ፤ " የወጣቶች ሱሰኝነት በሀገር ደረጃ እየተባባሰ መጥቷል ፤ በተለይ አሉታዊ መጤ ልማዶች እና አደንዛዥ ዕጽ እንደ ሀገር እየተስፋፋ መጥቷል " ሲል ገልጿል።

ይህም ብዙ ወጣቶችን እያሳጣን ነው ሲል አስረድቷል።

ወጣቶች ሰብዕና ግንባታ ላይ ተግዳሮት እየፈጠረ ከሚገኘው አንዱ የስፖርት ውርርድ እንደሆነ ያመለከተው ሚኒስቴሩ " የስፖርት ውርርድ ለሀገሪቱ ከሚያስገባው ገቢ አኳያ ብቻ መታየት የለበትም " ብሏል።

" ' ስፖርት ቤቲንግ ' ላይ ያሉት፣ ካሁን በፊት የወጡት መመሪያዎች፣ ደንቦች፤ ጥናትን መሰረት አድርገው ሊታገዱ ይገባል " ሲል ገልጿል።

ፓርላማውም በዚህ ረገድ እገዛ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስቧል።

" ገቢ አንድ ነገር ነው። ሀገር ገቢ ማግኘት አለባት " ያለው መ/ቤቱ ነገር ግን ፦

➡️ በወጣቶቹ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያስከተለ ስለሆነ፣

➡️ ብዙ ወጣቶች እያሳጣ ስለሆነ፣

➡️ ብዙ ቤተሰብም #እየፈረሰ ስለሆነ ሊታገድ እንደሚገባ ገልጿል።

በህ/ተ/ም/ቤት የጤና ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፤ " ብሔራዊ ሎተሪ ከገቢ ጋር አይቶታል። በዚህም በኩል ደግሞ ሌላ ችግር እየፈጠረ ነው " ያለ ሲሆን " ተማሪዎች ዩኒፎርማቸውን እያወለቁ የስፖርት ውርርድ ቤት ይገባሉ። ስለዚህ መቼ ያጥኑ። አእምሮአቸው ሊጎዳ ስለሚችል ጥንቃቄ ተደርጎ መሰራት አለበት " ብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስፖርት ውርርድ ላይ በተሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ በቅርቡ የወሰደውን እርምጃ " ጥሩ ስራ " ሲል አወድሷል።

በሌሎች አካባቢዎች በተሞክሮ ሊወሰድ ይገባል ሲል ጠቁሟል።

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴርም ፤ ከስፖርት ውርርድ ጋር በተያያዘ ያለውን የወጣቶች ሁኔታ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ አድርጎ እንዲያየው እና ጠንካራ ክትትል እንዲያደርግ መክሯል።

ከዚህ ቀደምም የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የስፖርት ውርርድ / ቤቲንግ / ' #ቁማር ' ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጾ እንዲታገድ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ግን ፤ " ቤቲንግ " ' #ጨዋታ ' እንጂ ' ቁማር ' ነው ብሎ እንደማያምን ገልጾ ነበር። ቤቲንግ አትራፊና ብዙ ወጣቶች ስራ እንዲያገኙ ያደረገና በከፍተኛ ሁኔታ ገንዘብ እንዲንቀሳቀስ የሚያደርግ መሆኑንም አስረድቶ ነበር።

በስርዓት እንዲመራም መመሪያዎች ወጥተውለት እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ " እኛ ጨዋታውን አቅርበናል ተጫዋቹ ደግሞ በኃላፊነት መጫወት አለበት " ሲል ነበር የመለሰው።

@tikvahethiopia
#ATTENTION🔔

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ ወላይታ ዞን ባሉ ወረዳዎች ያሉ መምህራን ከደመወዝ ጋር በተያያዘ ስራ እንዳቆሙ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አማኑኤል ጳውሎስ ፦

" ... ጉዳዩ ስር የሰደደና የቆየ ነው። አሁን ላይ ' በተራበ አንጀታችን መስራት አልችልም ' በሚል መምህራኑ ስራ አቁመዋል።

በፐርሰንት እየተቆራረጠ የሚከፈላቸው ደመወዝ በዚህ ወር ለ16 ቀን ዘግይቷል።

ከደመወዝ በላይ የሌሎች ጥቅማጥቅሞች ፥ የወዝፍ ደሞዝ ፣ ከደረጃ እድገት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የደሞዝ ጭማሪና የእርከን ጭማሪ መቅረት ፈተና ሆኖባቸዋል። "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ መረጃዎችን ይልካል።

ከዚህ ቀደም ወላይታ ዞን ስለሚገኙ መምህራን ቅሬታ የቀረበ ፦ https://yangx.top/tikvahethiopia/86484?single

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
📱 ባይትዳንስ ' #ቲክቶክ ' ን #ለአሜሪካ ከመሸጥ አሜሪካ ውስጥ #ቢዘጋው እንደሚመርጥ ሮይተርስ ለኩባንያው ቅርብ የሆኑ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘገበ።

ኩባንያው በ' ቲክቶክ ' ጉዳይ እስከመጨረሻው ያሉትን የህግ አማራጮችን ተጠቅሞ እንዳይታገድ ማድረግ ካልቻለ ፤ ለአሜሪካ ከመሸጥ ይልቅ እስከመጨረሻው #መዝጋት ይመርጣል ተብሏል።

አሁን ' ቲክቶክ ' የሚሰራበት #አልጎሪዝም ለኩባንያው እንደ ዋናው ነገር እንደሚቆጠርና በዚህ አልጎሪዝም መተገበሪያውን የመሸጥ እድሉ እጅግ ሲበዛ አነስተኛ እንደሆነ የኩባንያው ምንጮች ገልጸዋል።

በዚህም ፤ ለአሜሪካ ገዢ ከመሸጥ አሜሪካ ውስጥ እስከወዲያኛው ድረስ መዝጋትን እንደሚመርጥ ተጠቁሟል።

አሜሪካ ' ቲክቶክ ' እንዲሸጥ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ገደብ አስቀምጣለች ካልሆነ ግን እስከ ወዲያኛው እንዲታገድ ሕግ አጽድቃለች።

በርካታ ጉዳዩን የሚከታተሉ የዘርፉ ሰዎች አሁን ባለው የአሜሪካ አቋም 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ' ቲክቶክ ' እስከ ወዲያኛው ድረስ የመወገዱ ነገር እውን መሆኑ አይቀርም ብለዋል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የወራቤ - ቦዠባር አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት እየተሰራ ይገኛል። ለዚህ መንገድ ግንባታ 2.77 ቢሊዮን ብር በጀት የተመደበለት ሲሆን 41.3 ኪ.ሜ ርዝመት አለው። የተቀመጠው የሙሉ በሙሉ ግንባታ የማጠናቀቀያ ጊዜ ሁለት ዓመት ነው ተብሏል። የአስፓልት መንገዱን የግንባታ ፕሮጀክት ወስዶ እየሰራ ያለው የአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ በተያዘለት በጀት ፣ ጊዜ እና የጥራት ደረጃ…
#Update

የመንገዱ ፕሮጀክት እንዴት እየሄደ ነው ?

የወራቤ ቦጆበር አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት በፍጥነት እየተከናወነ አይደለም።

ይህ መንገድ የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት በአሁኑ ሰዓት እየገነባቸው ከሚገኙ የአስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች አንዱ ነው።

የመንገድ ስራው በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ የሶስተኛ ወገን ችግሮች እና የአየር ሁኔታው ፈተና እንደሆኑ ተገልጿል።

ድርጅቱ መንገዱን ቶሎ ሰርቶ ለማስረከብ ሙሉ ዝግጅት አድርጎ የገባ ቢሆንም የሶስተኛ ወገን ችግሮች ለፍጥነቱ እንቅፋት እንደሆኑ አመልክቷል።

ምንም እንኳን የሶስተኛ ወገን ችግሮችን መፍታት በዋናነት የተቋራጩ ተግባር ባይሆንም ከባለደርሻ አካላት ጋር በመተባበር  የተወስኑ አካባቢዎችን ችግሮች በመፍታት ስራው ማስቀጠል ቢቻልም አሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ አልተፈታም።

እነዚህ የሶስተኛ ወገን ችግሮች ምን እንደሆኑ በዝርዝር አልተገለጸም።

ከዚህ በተጨማሪ መንገዱ የሚገነባበት አካባቢ የበልግ ዝናብ የሚያገኝ መሆኑ ለመንገድ ስራ ምቹ አይደለም ተብሏል።

የመንገዱን ጥራት አስጠብቆ ለመስራት ዝናብ የሌለባቸውን ቀናት እየጠበቁ መስራት የግድ በመሆኑ በፍጥነት ፕሮጀክቱ እንዳይሄድ ማድረጉን አሳውቋል።

#AmharaRoadWorksEnterprise

@tikvahethiopia
በምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር #ታንዛኒያ ለሳምንታት በዘለቀ ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ የጎርፍ አደጋ እና የመሬት መንሸራተት 155 ሰዎች ሲሞቱ ፤ 236 ሰዎች ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀገሪቱ ጠ/ሚ ቃሲም ማጅዋሊ ተናግረዋል።

በዚህ ሳምንት በጎረቤት #ኬንያ በደረሰው የጎርፍ አደጋ በትንሹ 35 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል። 40,000 ሰዎች  ደግሞ ከቤታቸው እንዲፈናቀሉ ሆነዋል።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ🚨

በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል የሶማሌና አጎራባች ክልሎች የሜትዮሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል አሳውቋል።

በቀጣይ 10 ቀናት ውስጥ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር ስለሚችል #ጥንቃቄ እንዲደረግ ተብሏል።

የማዕከሉ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘሪሁን ሀ/ማርያም ለሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፥ " በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በሀገር ደረጃ የተሰራው ትንበያ እንደሚያሳየው በቀጣይ 10 ቀን ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር ይችላል የሚል ነው " ብለዋል።

" በጎርፍ ይጠቃሉ ተብሎ የሚጠበቁት በሰሜኑ ላይ #ከድሬዳዋ ጀምሮ #በጭናቅሰን እስከ #ጅግጅጋ ድረስ ነው " ብለዋል።

" በብዛት በኦሮሚያ ሃይላንድ በቀርሳ ፣ በቁልቢ ከፍታ ቦታዎች ላይ ከሚዘንበው ዝናብ ጋር ተያይዞ በተለይ #ድሬዳዋ ላይ ብዙ ዝናብ ከተማው ላይ ሳይዘንብ ጎርፍ የመምጣት እድል አለው። በተመሳሳይ #ጅግጅጋ ላይ ጎርፍ ሊከሰት ይችላል " ሲሉ ገልጻዋል።

ዋቢ ሸበሌ፣ ከኢሚ፣ ጎዴ፣ ቀላፎ፣ ሙስታይል ወደታች ያለው አካባቢ ጎርፍ ሊመጣ የሚችልበት እድል ስላለ አሁን ላይ ባለው ሁኔታ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይፈልጋል ተብሏል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገር ውስጥ በረራ በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረ ገልጿል።

እየተጠናቀቀ ባለው በዚህ በጀት አመት የአገር ውስጥ ተጓጓዦች ቁጥር 3.5 ሚሊየን ይደርሳል፡፡

ይህ መጠን ከ2015 ዓ.ም በጀት አመት አንጻር የ34.6 በመቶ ጭማሪ ይኖረዋል።

በቀደመው አመት በአገር ውስጥ በረራ የተስተናገዱት ተሳፋሪዎች 2.6 ሚሊየን እንደነበሩ " ካፒታል ጋዜጣ " አየር መንገዱን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገር ውስጥ በረራ በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረ ገልጿል። እየተጠናቀቀ ባለው በዚህ በጀት አመት የአገር ውስጥ ተጓጓዦች ቁጥር 3.5 ሚሊየን ይደርሳል፡፡ ይህ መጠን ከ2015 ዓ.ም በጀት አመት አንጻር የ34.6 በመቶ ጭማሪ ይኖረዋል። በቀደመው አመት በአገር ውስጥ በረራ የተስተናገዱት ተሳፋሪዎች 2.6 ሚሊየን እንደነበሩ " ካፒታል ጋዜጣ " አየር መንገዱን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።…
' በረራው እንዴት ጨመረ ? '

" ስለ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ በረራ መጨመር የሚገልጸውን መረጃ በእጅ ስልኬ ላይ ደረሶኝ አየሁት።

እንዲያው ዝም ብሎ የሀገረ ውስጥ በረራ ጨመረ ብሎ የሚታለፍ መስሎ አልተሰማኝም።

በእርግጥ አየር መንገዳችን ገቢ ማግኘቱ እጅግ የሚያስደስት ቢሆንም ሰዎችን በዚህን ያህል ልክ የአየር ትራንስፖርት እንዲጠቀሙ ያደረጋቸው ምንድ ነው ?  ብሎ ጥናት ማድረግ ይገባል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀገራችን የየብስ ትራንስፖርት ማድረግ እኔን ጨምሮ ብዙ ሰዎችን የሚያሰጋ ሆኗል።

በተለያየ ጊዜ የሚሰማው የእገታ ወንጀል ፣ ጥቃት ሰዎች ቅርብ ከተሞች ሳይቀር በአየር እንዲጓዙ እያደረጋቸው ነው።

ለአብነት እኔ ከዚህ ቀደም ለስራ የግል መኪናዬን ይዤ ከከተማ ውጭ እስከ ድሬዳዋ ድረስ እየነዳው ሄጄ እመለስ ነበር ዛሬ ላይ ያን ለማድረግ አልችልም። የሆነ ነገር ብሆንስ ብዬ እፈራለሁ ስለዚህም በየጊዜው የአየር ትኬት መቁረጥ ግድ ብሎኛል።

እኔ ስላለኝ ነው ይህ ያደረኩት አቅሙ የማይፈቅድ ደግሞ የግዴታ ሆኖበት የየብስ ይጠቀማል።

እኔ እንኳን የማውቀው ብዙ ሰው ተቸግሮም ቢሆን በአየር ትራንስፖርት ለመጠቀም ሲገደድ ብዙ ጊዜ አይቻለሁ።

ወደ ሰሜኑ ክፍልም ብንመለከተ ካለው ጸጥታ ጋር በተያየዘ ሰዎች ከየብስ ትራንስፖርት ይልቅ አቅማቸው ባይፈቅድ እንኳን ተቸግረው የአየር ትራንስፖርት ይጠቀማሉ።

ስለዚህ የሀገር ውስጥ በረራ ቁጥሩ የመጨመሩ ብቻ ሳይሆን በዚህ ልክ እንዴት ሊጨምር እንደቻለ ምክንያቱ ቢታወቅ ጥሩ ነው ባይ ነኝ። "

(Ato Solomon K. Tikvah Family Addis Ababa)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION🔔 በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ ወላይታ ዞን ባሉ ወረዳዎች ያሉ መምህራን ከደመወዝ ጋር በተያያዘ ስራ እንዳቆሙ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አማኑኤል ጳውሎስ ፦ " ... ጉዳዩ ስር የሰደደና የቆየ ነው። አሁን ላይ ' በተራበ አንጀታችን መስራት አልችልም ' በሚል መምህራኑ ስራ አቁመዋል። በፐርሰንት…
#Wolaita

" መምህራኑ በተራበ አንጀት አንሰራም በማለት ስራ አቁመዋል " -  የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን ማህበር

" መምህራኑ ወደስራ ያለተመለሱት የሙያ ማረጋገጫ ፈተና ላይ በመሆናቸዉ ነው " - የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ

ከሰሞኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች መምህራን ከደሞዝ ጋር በተያያዘ ስራ ማቆማቸው ተነግሯል።

መምህራኑ በተለያየ ጊዜ ደሞዝ ሲዘገይና ሲቆራረጥ መቆየቱ ለስራቸው እንቅፋት ለህይወታቸውም አደጋ መሆኑን በመግለጽ ለሚመለከታቸዉ አካላት በተለያየ መልኩ ለመግለጽ ሲሞክሩ መቆየታቸውን ይገልፃሉ።

ከነዚህ መምህራን ውስጥ አንዱ የሆኑት መምህር አሸብር ፤ እርሳቸዉና በዳሞት ገሌ ወረዳ ያሉ መምህራን በደሞዝ መቆራረጥና የእርከን ጭማሪ እጦት ምክኒያት ምሬት ውስጥ እንደገቡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በተደጋጋሚ የግማሽ ወር ደሞዝ ሲወስዱ መቆየታቸዉን የሚገልጹት መምህር አሸብር አሁን ላይ ጉዳዩ ለመምህራን በህይወት የመኖርና ያለመኖር መሆኑን ገልጸዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመምህራን ማህበር ፕሬዚዳንቱ አቶ አማኑኤል ጳውሎስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በተደጋጋሚ " ችግሩ ይቀረፍ " በማለት በደብዳቤም ሆነ በውይይት ባለስልጣናትን ስናናግር ቆይተናል ብለዋል።

ጉዳዩ ስር የሰደደና የቆየ መሆኑን ገልጸው አሁን ላይ መምህራኑ " በተራበ አንጀታችን መስራት አልችልም " በሚል ስራ ማቆማቸዉን ገልጸዋል።

መምህራን በፐርሰንት እየተቆራረጠ የሚከፈላቸዉ ደሞዝ በዚህ ወር ለ16 ቀን መዘግየቱን ተከትሎ ስራ እንዳቆሙ አስረድተዋል።

" ችግሩ ከደሞዝም በላይ የሌሎች ጥቅማጥቅሞች ማለትም የወዝፍ ደሞዝ ፣ ከደረጃ እድገት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የደሞዝ ጭማሪና የእርከን እድገት መቅረት ፈተና ሆኖባቸዋል " ብለዋል።

በሌላ በኩል አሁን ላይ እንደ ሶዶ ባሉ ከተሞች ብቻ ደሞዝ መከፈሉ ወረዳ ላይ ካሉ መምህራን በላይ የገጠር ተማሪ ወላጆችን ልጆቻችን በዚህ ምክኒያት ከትምህርት ራቁ በሚል እያናደደ መሆኑን በመግለጽ ይህን አሳሳቢ ችግር የዞኑም ሆነ የክልሉ መንግስት በአፋጣኝ ሊቀርፈዉ እንደሚገባ አቶ አማኑኤል ጳውሎስ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመምህራኑን ቅሬታ ተከትሎ ምላሽ እንዲሰጡ የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊዉ አቶ ታደሰ ኩማን አነጋግሯል።

እሳቸውም ፤ " ነገሩ እንደሚባለዉ ሳይሆን ክፍያዉ የዘገየዉ በ8 መዋቅሮች ብቻ ነው " ብለዋል።

" አሁን ላይ ደሞዙ በመከፈሉ ችግሩ ተቀርፏል " ሲሉ ገልጸዋል።

ለቀናት የዘገየዉ ደሞዝ ከተከፈለ በኋላ መምህራን በአመጽ ሳይሆን በነበረባቸዉ የሙያ ማረጋገጫ ፈተና ምክኒያት ወደስራ አለመግባታቸውን አስረድተዋል።

ከዚህ ዉጭ አንዴ ብቻ በተፈጠረ የደሞዝ እጥረት ለአንድ ወረዳ ብቻ ስልሳ ፐርሰንት እንደተከፈለ በመግለጽ ከዛ ውጭ ምንም አይነት የደሞዝም ሆነ የጥቅማጥቅም ችግር እንደሌለ ምላሽ ሰጥተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia