TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
ኤርፖርት ... በፎቶው 👆 ላይ የምትመለከቷቸው አቶ ነቢዩ ሲራክ ይባላሉ ፤ በአንደኛው ፎቶ ላይ አብሯቸው የሚታየው ልጃቸው ነው። ትላንት ምሽት ለስራ ወደ ውጭ ሀገር የሚሄደውን ልጃቸውን ለመሸኘት ቦሌ ኤርፖርት በነበሩበት ወቅት አንድ የኢሚግሬሽን ሰራተኛ ልጃቸው ላይ ፍፁም ከስነምግባር ያፈነገጠ ተግባር መፈፀሙን ገልጸዋል። ልጃቸው ምንም እንኳን በሱዑዲ አረቢያ ተወልዶ ቢያድግም አማርኛ አቀላጥፎ የሚናገርና…
#ቦሌኤርፖርት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰሞኑን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከመንገደኞች አገልግሎት አሠጣጥ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ቅሬታዎች እየተነሱ መሆኑን እንደተገነዘበ ገልጿል።

አየር መንገዱ ከደንበኞቹ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች እና አስተያየቶች ከፍተኛ ትኩረት የሚሠጥ በመሆኑ ሂደቱን በጥሞና ሲከታተል መቆየቱን አመላክቷል።

በመሆኑም እየተሰሙ ያሉ ቅሬታዎችን መርምሮ መፍትሄ ለመስጠት አየር መንገዱ በአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ አገልግሎት ከሚሰጡ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ቅሬታዎችን የማጣራት ስራ እየሠራ መሆኑን አሳውቋል።

ይህንንም ተከትሎ በማጣራቱ ሥራ ላይ በሚገኙ ውጤቶች ላይ በመመርኮዝ ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ በፍጥነት እንዲወሠድ ይደረጋል ብሏል።

በቦሌ ኤርፖርት ውስጥ በሚሰሩ የተለያዩ ህገወጥ ተግባራት እና ከስነምግባር ያፈነገጡ ድርጊቶች በርካቶች ተማረው ድምፃቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል።

በተለይ በኢሚግሬሽን ፣ በፍተሻ ቦታዎች ላይ በተጓዦች ላይ በአንዳንድ ሰራተኞች የሚፈፀሙ ከስነምግባር ያፈነገጡ ድርጊቶችን ተከትሎ የአየር መንገዱ ስም በተደጋጋሚ ይነሳል።

በቅርቡም አንድ አባት ልጃቸውን ወደ ውጭ ለመሸኘት በተገኙበት ወቅት ልጃቸው በኤርፖርት ኢሚግሬሽን ሰራተኛ ማንገላታት፣ ማመናጨቅና ፓስፖርትም እስከመወርወር የደረሰ ተግባር መፈፀሙ ይታወሳል።

ይህ የአንድ ሰው ገጠመኝና በማህበራዊ ሚዲያ የወጣ ይሁን እንጂ በተለይ በተለይ በቦሌ ኤርፖርት በአንዳንድ  ፦
- ስነምግባር በጎደላቸው
- የገዛ ዜጋቸውን በማያከብሩ
- ስራቸውን አክበረው በማይሰሩ፣
- ገንዘብ እና ጥቅም በሚያሳድዱ ሰራተኞች ስንት ዜጎች ተበድለው ፣ አንብተው ፣ የሚጮኹበት አጥተው ፣ መፍትሄ ተነፍገው ፣ መፍትሄ ፍለጋ የሚሄዱበት አጥተው ይሁን ? የሚል ጥያቄ አስነትቷል።

ተቋማት ፤ ሰራተኞቻቸው #ከህዝቡ በሚሰበሰብ ገንዘብ ደመወዝ እንደሚከፈላቸው በአግባቡ እንዲያወቁት በማድረግ ህዝብን #ጎንበስ ብለው ማስተናገድ እንዲለምዱ ፣ ሙስና እና ጥቅምን እንዲፀየፉ የማድረግ #ግዴታ አለባቸው።

@tikvahethiopia
ቀኑን ሙሉ ደስ ደስ እያልዎት እንዲውሉ የደስታ ሰዓት ጥቅልን እነሆ!

የደስታ ማለዳ፣ የደስታ ምሳ፣ የደስታ ሌሊት እና እሁድን በደስታ የተሰኙ ልዩ ጥቅሎችን ከ 5 ብር ጀምሮ አቅርበናል!

በቴሌብር ሲገዙ ከ 10% ስጦታ ጋር እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል፣ አርዲ ቻትቦት ወይም በ*999# ያገኟቸዋል!


#Ethiotelecom #RealizingDigitalEthiopia
#ደመወዝ

➡️ " አሁን ላይ ከኑሮ ወድነቱ ጋር ተደምሮ የደመወዝ መዘግየት እየፈተነን ይገኛል " - ሰራተኞች

➡️ " ችግሩ ይቆያል የሚል እምነት የለኝም " - የድርጅቱ አመራር

ደቡብ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በበጀት ምክኒያት መፈተን ከጀመረ እንደቆየ የድርጅቱ ሰራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

በዚህም ምክኒያት " ደሞዝ እየዘገዪ ተቸግረናል " የሚሉት ሰራተኞቹ " በ28 ሲገባ የነበረዉ ደሞዛችን እስከ አስራአምስትና አስራ ስድስት ቀናት መዘግየት ጀምሯል " ብለዋል።

የስልክ እና አንዳንድ ወጭዎች ከተቋረጡ መቆየታቸውን ያነሱ ሲሆን አሁን ላይ ከኑሮ ወድነቱ ጋር ተደምሮ የደሞዙ መዘግየት እየፈተናቸዉ መሆኑን አስረድተዋል።

ድርጅቱ ከአራቱ ክልሎች ማለትም ፦
* ከሲዳማ
* ከደቡብ ኢትዮጵያ
* ከደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ
* ከመአከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚበጀት ገንዘብ እንደሚንቀሳቀስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹት አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አመራር " አሁን ላይ ይህ በጀት በአግባቡ ባለመለቀቁ ምክኒያት የደሞዝም ሆነ የውስጥ ስራ ማስኬጃ እጥረቶች ሊከሰቱ ችለዋል " ብለዋል።

" ችግሩ ይቆያል የሚል እምነት የለኝም " ሲሉም ተናግረዋል።

አመራሩ አክለው ፤ " ደሬቴድ ይፈርሳል፤ ይሰነጣጠቃል " የሚሉ ወሬዎች እንደነበሩና አሁን ላይ በአራቱ ክልል በጀት እየተንቀሳቀሰ ማህበረሰቡን በማገልገል እንዲቀጥል አቅጣጫ በመቀመጡ  የህልዉና ችግር እንደሌለበትና በጀትም የመለቀቁ ጉዳይ ብዙ የሚያደክም አይደለም ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

መረጃዉ አዘጋጅቶ የላከው የሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ጵጥሮስ " አቋቁመናል ካሉት ውስጥ ሶስቱ #መታሰራቸውን የእንቅስቃሴው አስተባባሪ ነኝ ያሉ ዲያቆን አክሊሉ ዓለሙ የተባሉ ግስለሰብ ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል ተናግረዋል። ሶስቱ አባቶች የታሰሩት " መንበረ ጴጥሮስ " አቋቁመናል የሚል መግለጫ ከሰጡ በኃላ ሸገር ከተማ አስተዳደር በሚገኘው ቢሯቸው እንደሆነ እኚሁ አስተባባሪ ተናግረዋል። …
#Update

" የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ጴጥሮስ መስርተናል " በሚል መግለጫ የሰጡትና በእስር ላይ የነበሩት አባቶች ከእስር ተለቀቁ።

" መንበረ ጴጥሮስ መስረተናል " ያሉት 10 አባቶች እና ሌሎች አብረዋቸው የነበሩት አስተባባሪ ግለሰቦች በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ለአንድ ወር ከ18 ቀን ከታሰሩ በኃላ ትላንት እያንዳንዳቸው በ5000 ብር ዋስ ከእስር መፈታታቸውን ቪኦኤ ሬድዮ ጠበቃቸውን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

እንዳ ጠበቃቸው ገለጻ ፖሊስ የተጠረጠሩበት ወንጀል ብሎ ያቀረበው ፦
1ኛ.  " ያልተፈቀደ መግለጫ ሰጥታችኃል "
2ኛ. " ሃይማኖትን ከሃይማኖት ጋር አጋጭታችኃል "
3ኛ. " ህዝብን በመንግስት ላይ እንዲነሳሳ አድርጋችኃል " የሚል ነበር።

በሸገር ከተማ ሆነው " መንበረ ጴጥሮስ መስርተናል " የሚል መግለጫ በሰጡ በሰዓታት ውስጥ የታሰሩት የሃይማኖት አባቶቹ በዋስ ከእስር ተለቀዋል።

ለእስር ተዳርገው ከነበሩት መካከል ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን " ማዕረጋቸውን ገፍፌዋለሁ " ያለቻቸው አባ ገብረማርያም ነጋሳ፣ አባ ወልደ ኢያሱስ ኢፋ እንዲሁም አባ ወልደኢየሱስ ተስፋዬ እንደሚገኙበት መናገሩ የሚዘነጋ አይደለም።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን   " መንበረ ጴጥሮስ "  አቋቁመናል ብለው መግለጫ በሰጡበት ወቅት በሌላቸው ክህነት መግለጫ እንደሰጡና ድርጊቱንም እንደምታወግዝ ገልጻ ፤ በሕገወጥ ድርጊታቸው ቀጥለዋል ያለቻቸውን ቡድኖች  በፍርድ እንደምትጠይቅ አሳውቃ ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ለጥንቃቄ " በፎሬክስ ትሬዲንግ የኦንላይን ስራ ትርፋማ እናደርጋችኋለን " የሚል የፌስቡክና የቴሌግራም ማስታወቂያ በሚያስነግሩ የተደራጁ ቡድኖች መጭበርበራቸውን ተበዳዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።  እነዚህ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገጾች ስያሜአቸው ከፎሬክስ ትሬዲንግ ጋር የተያያዘ ሲሆን " ትሬድ እናደርጋለን ትርፋማ ትሆናላችሁ " የሚል ቃል በመግባት ከሰዎች ገንዘብ እያስላኩ የማጭበርበር ስራ…
#በድጋሜ⚠️

ውድ ቤተሰቦቻችን ጥንቃቄ አድርጉ።

በሀገራችን ያለውን ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ጫናን ለመቋቋምና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ብዙ ሳይደክሙ በርካታ ገንዘብ ለማግኘት በሚደረግ ጥረት በርካታ የሀገራችን ልጆች ደክመው በላባቸው ያገኙትን ፤ ከቤተሰብም ለስራ በሚል የተቀበሉትን ብር በኦንላይን አጭበርባሪ ዘራፊዎች በየዕለቱ እየተበሉ ይገኛል።

ከዚህ ቀደም መላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በኦንላይን ከሚደረጉ የማጭበርበር ስራዎች እራሳችሁን እንድትጠብቁ የአደራ ማሳሰቢያ መላክችን ይታወሳል።

አሁንም ሰዎች በመቶ ሺህ የሚቆጠር ብራቸውን እየተበሉ ይገኛል።

እባካችሁን በ " ዋትአፕም " ይሁን በ " ቴሌግራም " አድራሻችሁን አግኝተው የሚያናግሯችሁን የማታውቋቸውን ሰዎች መልዕክት አትመልሱ።

" በተለያየ ኦንላይን ስራ ፣ በፎሬክስ ትሬዲንግ እና በሌሎችም በትንሽ እና በማያደክም ስራ ትርፋማ እናደርጋችኋለን ፤ ይሄን ይሄን ስራ ስሩ በዚህ አካውንት ገንዘብ አስገቡና እኛም መልሰን ትርፉን እናስገባለን " የሚሉ አጭበርባሪዎች ተንሰራፍተዋልና ተጠንቀቁ።

በነገው ዕለት ከዚህ ጋር በተያያዘ ስላጋጠመ ክስተት እናጋራችኃል። ለአሁኑ ግን ምናልባት " ይሄን ስራ ስሩና ትርፋማ ትሆናላችሁ ፤ ገንዘብ ላኩና ትርፉን እንልካለን " በሚል እያባበሉ ገንዘብ እድትልኩ የሚጠይቋችሁን ሰዎች ከማናገር ተቆጠቡ፤ ምንም ገንዘብም አትላኩላቸው።

@tikvahethiopia
ግሎባል ባንክ

መልዕክቱን ያጋሩ፣ ከ1ሺህ ብር ጀምሮ ተሸላሚ ይሁኑ!
የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል

1. በመጀመሪያ ቀጣዩን የቦት ሊንክ ይጫኑ፡- https://yangx.top/global_bank_referral_bot?start=476862805
2. START የሚለውን ይጫኑ፣
3. JOIN CHANNEL የሚለውን ይጫኑ፣
4. ወደ መጀመሪያው ቦት ይመለሱ፣
5. CONTINUE የሚለውን ሲጫኑ የመጋበዣ ሊንክዎን ያገኛሉ፣
6. መልዕክቱን ቢያንስ ለ50 እና ከዚያ በላይ ወዳጅ ዘመድዎ ሼር ሲያደርጉ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በየሳምንቱ ከአንድ ሺ ብር ጀምሮ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ያበረክታል፡፡

ሽልማቱ በየሳምንቱ ለተሸላሚዎች ይደርሳል፡፡
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ናቸው፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን
" ጥሪ መቀበያው ከእውቅናችን ውጭ ለ7 ወር ተቋርጦ ነበር " - የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ህዝቡ የሚደርስንበትን አስተዳደራዊ በደል የሚያሳውቅበት ነጻ የስልክ ጥሪ መቀበያ 7502 ከእውቅና ውጪ ለባለፉት 7 ወራት ተቋርጦ እንደነበር ገለጸ።

ተቋሙ አገልግሎቱ በመቋረጡ ለተፈጠረው እንግልት ይቅርታ ቢጠይቅም እንዴት ? በምን ? ለምን ? ከእውቅና ውጭ አገልግሎቱ እንዲቋረጥ ተደርጎ እንደነበር ያለው ነገር የለም።

በአሁን ሰአት 7502ን ጠግኖ በድጋሚ ማሰራት ባለመቻሉ የነጻ ስልክ ጥሪ መስመሩን ለመቀየር መገደዱን አሳውቋል።

በዚህ መሰረት ማንኛውም ዜጋ በመንግስት አስፈጻሚ አካላት እና በግል ተቋማት በተለይ በሽርክና በተቋቋሙ የግል ተቋማት የሚደርሱ #የአስተዳደር_በደል እንዲሁም ከመልካም አስተዳደር ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችን በነጻ የስልክ ጥሪ 9503 ማቅረብ ይችላል ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#በድጋሜ⚠️ ውድ ቤተሰቦቻችን ጥንቃቄ አድርጉ። በሀገራችን ያለውን ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ጫናን ለመቋቋምና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ብዙ ሳይደክሙ በርካታ ገንዘብ ለማግኘት በሚደረግ ጥረት በርካታ የሀገራችን ልጆች ደክመው በላባቸው ያገኙትን ፤ ከቤተሰብም ለስራ በሚል የተቀበሉትን ብር በኦንላይን አጭበርባሪ ዘራፊዎች በየዕለቱ እየተበሉ ይገኛል። ከዚህ ቀደም መላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ…
ውድ ቤተሰቦቻችን ፤ ትላንትና ምሽት ከላክንላችሁ የድጋሜ የጥንቃቄ መልዕክት በኃላ በርካታ ሰዎች በኦንላይን የማጭበርበር ስራ ገንዘባቸው ተዘርፎ የውሃ ሽታ መሆኑን አመልክተዋል።

ለአብነት ከ150 ሺህ ብር እስከ 300 ሺህ ብር ከዚህም ከፍ ሲል እስከ 470 ሺህ ብር በቀናት ውስጥ የተጭበረበሩ ሰዎችን መልዕክት ተቀብለናል።

አጭበርባሪዎቹ ፦
* " የኦንላይን ስራ እናሰራችኋለን፣ "
* " የፎሬክስ ትሬዲንግ ስራ እናሰራለን "
* " በትንሽ ብር ኢንቨስት በማድረግ ያለ ብዙ ድካም ትርፋማ ትሆናላችሁ "
* " ይሄን ያህል ገንዘብ ላኩና ስራ ሰርታችሁ የከፈላችሁትን በእጥፍ አግኙ " በማለት በተደራጀ መልኩ በዋትሳፕና በቴሌግራም የማጭበርበር ስራ የሚሰሩና የበርካቶችን ገዘንብ እየዘረፉ በመሆኑ በድጋሜ ከየትኛውም የማታውቁት ሰው " ስራ እናሰራችሁ " በሚል የሚመጣላችሁን የዋትስአፕና ቴሌግራም መልዕክት አትመልሱ።

ሰዎች እንዴት እየተጭበረቡ እንደሆነ በቀጣይ ይናቀርባለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hawassa በፀጋ በላቸው ላይ የጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰው ኮንስታብል የኋላመብራት ወልደማርያም በ16 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል። የህግ አማካሪና ጠበቃ እንዲሁም በፆታዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩት አበባየሁ ጌታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ ውሳኔው የከተማውን ገፅታ የሚያበላሽ እንደሆነ ስለታሰበ ነው መፍትሄ ያገኘው ብለዋል። አበባየሁ ጌታ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው…
" ፍርዱ ለሚዲያ 16 ዓመት ከተባለ በኃላ ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዳለ ሰምቻለሁ " - ጸጋ በላቸው

" ጉዳዩ ለቢሮዉም ሆነ ለኔ አዲስ ነው " - ወ/ሮ ወይንሸት ብርሀኑ

በሀዋሳ ከተማ የዳሽን ባንክ ሰራተኛ ከሆነችዉ ጸጋ በላቸዉ ጋር በተያያዘ በጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ  የነበረው ኮንስታብል የኃላመብራት ወ/ማርያም " ለብዙዎች አስተማሪ ይሆናል " በተባለ መልኩ የ16 አመት ጽኑ እስራት እንደተፈረደበት ይታወሳል።

ይሁንና ይህ ለሚዲያ የተገለጸው ፍትህ ከተበዳዩዋ እውቅና ውጭ በሆነ መልኩ የእስራት ፍርዱ ከ16 አመት ወደ 10 መቀነሱን እንደሰማች በሶሻል ሚዲያ ባስተላለፈችዉ በዕንባ የታጀበ ቅሬታ ገልጻለች።

ወይዘሪት ጸጋ ፤ ጉዳዩን ለማወቅ ብዙ ድካም እንደነበረዉና በመጨረሻ የሰማችዉ ጉዳይ እጅግ እንዳሳዘናት በመግለጽ አቤቱታዋን አሰምታለች።

ጸጋ ፤ " የፍርድ ሂደቱ በጥሩ ሂደት ሄዶ ፍርድ ቤት 16 ዓመት ተፈርዶበታል በሚል ለኔ ውሳኔ ሰጥቶኝ ነበር ፤ አሁን ግን እኔ በማላውቅበት ሁኔታ የፍርዱ ውሳኔ ይግባኝ ብሎ #እንደተስተካከለ ሰምቻለሁ፤ ይህ ውሳኔ መቼ እንደተላለፈ አልተነገረኝም ለግል ጉዳዬ የውሳኔ ወረቀት እንዲሰጠኝ  በተደጋጋሚ ወደ ፍርድ ቤት በምደውልበት ጊዜ ምላሽ እየተሰጠኝ አልነበረም ጉዳዩን አጥብቄ በተደጋጋሚ ስጠይቅ ውሳኔው በይግባኝ እንደተስተካከለ ተነገረኝ " ስትል አስረድታለች።

ውሳኔው አሁን ላይ ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዳለ የገለፀችው ጸጋ ፤ በድርጊቱ እጅግ እንዳዘነችና ካሳለፈችው የስቃይ ሁኔታ ጋር በፍፁም እየሚገባ እንዳልሆነ በእምባ ታጅባ ገልጻለች።

ከዚህ ባለፈ ህዝብ የማያውቀው ብዙ ነገር እንደተፈፀመ ፤ ከጠለፋው እገታ ከተለቀቀች በኃላ በማታውቀው ምክንያት ታስራ እንደነበር አመልክታለች።

ፍርዱ ለሚዲያ 16 ዓመት ከተባለ በኃላ ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዳለ ገልጻ ፤ " ይህ አይነት ተግባር ለቀጣይ ምን እንደሚያስተላልፍ አላውቅም " ብላለች።

ውሳኔው ተግቢና ትክክል እንዳልሆነ ፤ በድብቅ ሊሆን እንደማይገባው፣ እንዲከላከሉም ሊደረጉ እንደሚገባ አስገንዝባለች።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን በተመለከተ ጥያቄ ያቀረበላቸዉና የጸጋን ጉዳይ ሲከታተለዉ በነበረዉ የሀዋሳ ከተማ ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ውስጥ የሴቶችና ህጻናት መብትና ደህንነት ማስጠበቅ ቡድን መሪ የሆኑት ወይዘሮ ወይንሸት ብርሀኑ ጉዳዩ ለቢሮዉም ሆነ ለእርሳቸዉ አዲስ መሆኑን ገልጸዋል።

ወይዘሮ ወይንሸት ፤ ጉዳዩን እንደሚከታተሉትና የተፈጠረዉን ጉዳይ እንደሚያጣሩ በመግለፅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃል ገብተዋል።

መረጃዉን አጠናቅሮ የላከዉ የሀዋሳዉ ቲኪቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነዉ።

@tikvahethiopia