#ደመወዝ
• " ደመወዝ በሰዓቱ እየተከፈለን ባለመሆኑ ቤተሰብ ለማስተዳደር አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ደርሰናል " - ሰራተኞች
• " በዚህ ወር ለሰራተኛ ደመወዝ ለመክፈል 9 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር የሚያስፈልግ ቢሆንም አሁን ላይ 8 ሚሊየን ብር ብቻ ነው የተገኘው " - ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ት ቤት
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ በሚገኘው የካፋ ዞን ፤ ጌሻ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ በአግባቡ እየተከፈላቸው እንዳልሆነ ገልፀዋል።
ሰራተኞቹ ፤ የወርሃዊ ደመወዝ በአግባቡ አለመከፈሉ ለችግር እየዳረጋቸው መሆኑን አመልክተዋል ፤ በዚህ ሳቢያ ህይወታቸውን ለመግፋት ፈተና እንደሆነባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል።
የወረዳው ኮሚኒኬሽን በበኩሉ ፤ በየወሩ በተደጋጋሚ ደምወዝ በአግባቡ ባለመከፈሉ ምክንያት የመንግስት ሰራተኞች #ለአላስፈላጊ_ወጪዎች እና #ችግሮች መዳረጋቸውን እንደገለፁ አሳውቋል። ገልጿል።
" በተያዘው የበጀት አመት አንድም ቀን ደመወዝ በጊዜው ተከፉሎ አያውቅም " ያሉት ሰራተኞቹ " ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሩ እየተባባሰ መጥቷል " ብለዋል።
የመንግስት ሰራተኞቹ ያለፈው የህዳር ወር ደመወዝ እስከ ትላንት ታህሳስ 12 ቀን ድረስ እንዳልተከፈላቸዉ ገልፀው " ቤተሰብ ለማስተዳደር አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ደርሰናል " ብለዋል።
" ቀጣይም የሚከበረውን #የገናን_በዓል ለማክበር ደመወዝ በወቅቱ የማይገባ ከሆነ ለከፋ ችግር ልንዳረግ እንችላለን " ሲሉ ስጋታቸውን ጠቁመዋል። ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ዘላቂ መፍትሔ እንዲያበጅለትም ቅሬታ አቅራቢዎች ጠይቀዋል።
የጌሻ ወረዳ ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ፅህፈት ቤት ፤ " የሰራተኞችን ቁጥር ታሳቢ ያላደረገ በጀት ከዞኑ መለቀቁ ለችግሩ መባባስ ምክንያት ነው " ሲል አሳውቋል።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ የሆኑት አቶ ታደሰ ቆጭቶ ፤ " ችግሩ ከዞን የሚለቀቀው ደመወዝ ሰራተኛውን ያመጣጠነ አለመሆኑ ነዉ " ያሉ ሲሆን በተለይም ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ ደመወዝ እየተለቀቀ እንዳልሆነና በዚህ ወር ለሰራተኛ ደመወዝ ለመክፈል 9 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር የሚያስፈልግ ቢሆንም አሁን ላይ 8 ሚሊየን ብር ብቻ ማግኘት እንደተቻለ ተናግረዋል።
ኃላፊው "አሁን ላይ ችግሩን በጊዜያዊነት ለመፍታትና ከመማር ማስተማር ጋር ተያይዞ መስተጓጐል እንዳይፈጠር ለመምህራን ብቻ ደመወዝ መክፈል ተችሏል " ያሉ ሲሆን " የሌሎችን ሰራተኞች ችግር ለመፍታት ከሚመለከተው አካላት ጋር እየተወያየን ነው " ብለዋል።
በሌላ በኩል በተመሳሳይ በዞኑ በ " ገዋታ ወረዳ " ያሉ የመንግስት ሰራተኛ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ባለፉት በርካታ ወራት ደመወዝ በአግባቡ እየገባላቸው እንዳልሆነ ጠቁመዋል።
የባለፈው ህዳር ወር ደመወዝም እስካሁን እንዳልገባ ገልፀው ፤ " ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሩ ከመፈታት ይልቅ እየተባባሰ ነው የሄደው፤ ለምን ይህ ይሆናል ? ብለን ስንጠይቅ የተለያየ ምክንያት ነው የሚሰጠን " ብለዋል።
ዛሬ በስልክ ያነጋገርነው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የሆነ አንድ መምህር ባለፉት በርካታ ወራት ለአንድም ቀን ደመወዝ በአግባቡ እየገባ እንዳልሆነና በዚህ ምክንያት የትምህርት ስርዓቱ ላይ መስተጓጎል እንደተፈጠረ አመልክቷል።
መምህሩ ፤ " ለበርካታ ወራት በሰዓቱ ደመወዝ ገብቶ አያውቅም ፤ ግፋ ቢል 15 ቀን 13 ቀን ወስዶ ነው እየገባ ያለው። የዚህ ጉዳይ ምክንያት ምንድነው ተብለው ሲጠየቁ ከፋይናንስ በጀት ተቀንሶ እየገባ መሆኑና ለሴክተር ሰራተኞች / ለመምህራን ማዳረስ እንደማይቻል ተብሎ ነው እየተነገረ ያለው። ለዚህ መፍትሄ አጥተን ነበር እንደአጋጣሚ ዛሬ ለመምህራን ደመወዝ እየገባ እንደሆነ እየተነገረ ነው ገና የህዳር ወር ፤ በዚህ ደመወዝ በአግባቡ አለመከፈሉ ምክንያት ትምህርትም ተስተጓግሎ ነበር ፤ እስከዚህ ድረስ ነው የችግሩ ስፋት " ብለዋል።
እኚሁ መምህር ፤ ዛሬ ሀሙስ ታህሳስ 13 የህዳር ወር ደመወዝ እየገባ እንደሆነ የሰሙት የመምህራንን ብቻ እንደሆነ ለሴክተር ሰራተኞች ገና መፍትሄ እየተፈላለገ ስለመሆኑ እንደሰሙ ገልፀዋል።
በወረዳው ደመወዝ በአግባቡ አለመግባት ሰራተኛውን ለችግር እና ለተለያዩ ወጪዎች እየዳረገው መሆኑ ተገልጿል ፤ ችግሩ እጅግ አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚፈልግም መልዕክታቸውን የላኩ ሰራተኞች አስገንዝበዋል።
@tikvahethiopia

በደቡብ ክልል፤ ወላይታ ዞን ዉስጥ በጤና ስርዓት ላይ ያለው ችግር እንዲፈታ የፌደራል መንግስት አስቸኳይ የእርምት እርምጃ ይውሰድ ሲሉ የጤና ባለሞያዎች ጠየቁ።
ባለሞያዎቹ ይህን የጠየቁት ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት የፅሁፍ መልዕክት ነው።
መልዕክታቸውን የላኩ የጤና ባለሞያዎች፤ በዞኑ የጤና ዘርፍ ላይ ያሉ አመራሮች ቸልተኝነት የተነሳ የህክምናዉን አገልግሎት እንደ ሌሎች አካባቢዎች ግዜዉን የሚመጥን አልሆነም ብለዋል።
ባለሞያዎቹ እንደሚሉት የደንገተኛ ቀዶ ህክምና ከአንድ ሆስፒታል (ኦቶና) ዉጭ ማግኘት የማይታሰብ ሆኗል።
መድኃኒት፣ የምርመራ መሳሪያ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች በበቂ ሁኔታ የለም የሚሉት ባለሞያዎቹ፤ ባልተሰራ ነገር "የዉሸት ሪፖርት" እንድናቀርብም እንገደዳለን ሲሉ ገልጸዋል።
ሌላው ባለሙያዎች የሰሩበት #ደመወዝ እና #ጥቅማጥቅም ባለማግኘታቸዉ ችግር እያጋጠማቸው እንደሆነ ጠቁመዋል።
በዞኑ የተለያዩ ሆስፒታሎች የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች ከደመወዝና ጥቅማጥቅም ጋር በተያያዘ ስራ ለመስራት ስለመቸገራቸውም አስረድተዋል።
ያለውን ችግር ለበላይ አካላትና ለሚዲያ እንዳይገለፅ ጫና እንደሚደርስ እንዳንድ ባለሞያዎችንም እስከ ማሰር የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል።
በዞኑ የፋይናንስ ችግር ሳይሆን የመልካም አስተዳደር ችግር ጎልቶ እንደሚታይ አሳውቀዋል።
የጤና ሚኒስቴር፤በዞኑ የሚታየው ችግር እንዲፈታ፣በተለይም በወላድ እናቶች ላይ እያደረሰ ያለው ችግር እንዲቀረፍ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።
በዞኑ አብዛኞቹ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ላይ ችግሩ አለ ያሉት የጤና ባለሞያዎቹ በዚህም ስራ መስተጓጎሉን አመልክተዋል።
ስለጉዳዩ ከዞን ጤና መምሪያ ምላሽ እና ማብራሪያ ለማግኘት ለአንድ አመራር ስልክ ብንደውልም ስልኩ አልተነሳም።
@tikvahethiopiaBOT

#AxumUniversity
አክሱም ዩኒቨርስቲ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሳቢያ የደረሰበት ጉዳት 15 ቢሊዮን ብር እንደሚገመት ማስታወቁን " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።
ላለፉት 19 ወራት ትምህርት መስጠት አቁሞ የቆየው ዩኒቨርስቲው፤ ሊያከናውነው ላቀደው ዳግም ግንባታ የድጋፍ ጥሪ አቅርቧል።
የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ገብረእየሱስ ብርሃነ የሰጡት ቃል ፦
- ዩኒቨርስቲው በጦርነቱ ሳቢያ በደረሰበት #ውድመት እና #ዘረፋ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር የሚያስችሉት ቁሳቁሶች እና መሳሪያዎች አጥቷል።
- ሙሉ ለሙሉ የተዘረፉ እና ከወደሙ የዩኒቨርስቲው ንብረቶች ውስጥ ኮምፒውተሮች፣ የላብራቶሪ መሳሪያዎች፣ ሰርቨሮች እና የቢሮ በሮች ይገኙበታል።
- ዩኒቨርስቲው ከጦርነቱ በፊት የነበሩት 60 ገደማ ተሽከርካሪዎች ተዘርፈው እና ተቃጥለው አሁን በስራ ላይ የሚገኘው #አንድ_መኪና ብቻ ነው።
- በጥር ወር ላይ በተደረገ ዳሰሳ የደረሰው ውድመት 15 ቢሊዮን ብር ይደርሳል።
- ጉዳት የደረሰባቸውን ንብረቶች በተወሰነ መልኩ በመተካት ወደ ስራ ለመግባት ታቅዷል።
- ለሚያከናውነው ዳግም ግንባታ እና ጥገና ስራ የገንዘብ እና የማቴሪያል ድጋፍ እንዲደረግልን ጠይቀናል። የድጋፍ ጥሪው ለዓለም አቀፍ እና ለሀገር በቀል አጋር ድርጅቶች፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ነው።
- ዩኒቨርስቲው የሚያገኘውን ድጋፍ በፌደራል መንግስት ከሚመደበለት በጀት ጋር በማጣመር በአጭር ጊዜ ውስጥ የመማር ማስተማር አገልግሎቱን ለመስጠት ታቅዷል።
- ቁሳቁሶችን በተወሰነ መልክ ቅድሚያ እየሰጠን ካስገባን፤ የግዢ ሂደቱ ፈጣን ከሆነ፤ ተማሪዎችን #በሶስት_ወር ውስጥ ማስገባት እንችላለን። በትግራይ ክልል የሚኖሩ እና ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት ያቋረጡ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን ትምህርት ማስጨረስ ላይ ትኩረት ይደረጋል።
አክሱም ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ከፌደራል መንግስት በጀት ባይለቀቅለትም፤ በስሩ ለሚገኘው የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 43 መምህራንን ለመቅጠር ከ2 ሳምንት በፊት ማስታወቂያ አውጥቷል።
የቅጥር ሂደቱ የሚፈጸመው በትምህርት ሚኒስቴር ተፈቅዶ፣ በጀት ሲለቀቅ መሆኑ ተገልጿል።
ከፌደራል መንግስት የሚለቀቀው በጀት፤ ለዩኒቨርስቲው ሰራተኞች ደመወዝ ለመክፈል እና ትምህርት ለማስጀመር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
#አራት_ሺህ ገደማ የሚሆኑት የዩኒቨርስቲው መምህራን እና ሰራተኞች ከሐምሌ 2013 ዓ.ም. ወር ጀምሮ #ደመወዝ_አለማግኘታቸውን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።
Credit : www.ethiopianInsider.com

#ጥቆማ
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፤ በ2014 ዓ.ም እና 2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የዩኒቨርስቲ መግቢያ መቁረጫ ውጤት ያመጡ እና በፖሊስ የሙያ ዘርፍ ሀገራቸውን ለማገልገል #የሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደሚፈልግ አሳውቋል።
ተቋሙ ለ4 አመታት በ " ፖሊስ ሳይንስ ዲግሪ " አስተምሮ በመኮንንነት (ረዳት ኢንስፔክተር ማዕረግ) በማስመረቅ በተለያዩ የፌደራል ፖሊስ የስራ ክፍሎች አስመድቦ ለማሰራት እንደሚፈልግ ነው የገለፀው።
በተጨማሪ በ "ፎረንሲክ ሳይንስ ዲግሪ" አስተምሮ በመኮንንነት (ረዳት ኢንስፔክተር ማዕረግ) በማስመረቅ በፎረሲክ ምርመራ የላብራቶሪ ሙያተኝነት (ኤክስፐርት) በማስመደብ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በተቋሙ በ " ፖሊስ ሳይንስ ዲግሪ " ለመማር የሚያስፈልጉ የመመልመያ መስፈርቶች ከላይ በምስሉ የተዘረዘሩ ሲሆን ከነሱም ውስጥ ፦
- አመልካቾች ከማንኛውም ወንጀል ነፃ ስለ መሆኑ ከሚኖርበት ወረዳ ፖሊስ ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
- ለፖሊስ አካል ብቃት ስልጠና ብቁ የሆነ አካላዊ አቋምና አዕምሮ ጤንነት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል።
- በ2014 ዓ/ም እና 2015 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር መቁረጫ ውጤት ያላቸው የትምህርት ማስረጃቸውንም ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የ #ሪሚዳል_ትምህርት ወስደው የማለፊያ ውጤት ያመጡ ከሆነም ማስረጃ ማቅረብ አባቸው።
- አመልካቾች እድሜያቸው ከ18 እስከ 28 ዓመት መሆን አለበት።
- ቁመት ለወንድ 1.65 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴት 1.55 እና ከዚያ በላይ፣
ሲሆን የተስተካከለ የሰውነት ክብደት 18.5-24.9 kg/m) ያለቸው ሊሆኑ ይገባል።
- ከተመረቁ በኋላ 7/ሰባት/ አመት በተማረበት የፖሊስ ሙያ በየትኛውም የአገሪቱ ክልልና የፖሊስ የስራ መደቦች ላይ ተመድቦ ለመስራት ፍቃደኛ መሆን አለበት።
- ሴት አመለካቾች ከእርግዝና ነፃ መሆን አለባቸው።
- ሁሉም አመልካቾች ከዚህ በፊት የፖሊስ ወይም የመከላከያ ሰራዊት ስልጠና ያልወሰዱ መሆን ያለባቸው ሊሆኑ ይገባል።
ለ " ፎረንሲክ ሳይንስ ዲግሪ " ከላይ ያሉት አብዛኛው መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆነው ፦
- ዜግነት #ኢትዮጵያዊ
- የ12ኛ ክፍል #በተፈጥሮ_ሳይንስ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በ2014 ዓ/ም እና በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን መቁረጫ ውጤት ያላቸው
- በተፈጥሮ ሳይንስ የሪሚዳል ትምህርት ወስደው የማለፊያ ውጤት ያመጡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሊሆኑ ይገባል።
በሁለቱም የዲግሪ ትምህርት ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን የሚቀላቀሉት በራሱ በተቋሙ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና ማለፍ ሲችሉ ብቻ ነው።
የት እና እስከመቼ መመዝገብ ይቻላል ?
ማመልከት የሚቻለው እስከ ጥቅምት 22/2016 ዓ/ም ድረስ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ነው።
ተማሪዎች በአካባቢያቸው በሚገኝ በሁሉም የክልል እና የከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽኖች በአካል በመገኘት መመዝገብ ይችላሉ።
ለመዝገባው የትምህርት ማስረጃቸውን የ8ኛ ፣ የ10ኛና 12ኛ ክፍል ካርድ እና ትራንስክርፕት ኦርጅናል ከማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ ጋር ይዘው መቅረብ አለባቸው።
#ደመወዝ / #ክፍያን በተመለከተ ፦
ዕጩ መኮንኖች በትምህርት ላይ በሚቆዩበት ጊዜያት ከ3 ወር የሙከራ (recruit) ጊዜ ቆይታ በኋላ እስከሚመረቁ ድረስ የኪስ ገንዘብ/ደመወዝ ታስቦ ይከፈላቸዋል ተብሏል።
ስልክ ካስፈለጋችሁ ፡ 0116735564
(ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮችን ከላይ በምስሉ ያንብቡ)

አዲስ አበባ ሥራ አጦች📈
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ አጦች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ።
በመዲናዋ የሥራ አጦች ቁጥር በመቶኛ እየጨመረ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱትሪ ልማት ቢሮ የሥራ ዕድልና የሥነ ምግብ ዋስት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍስሃ ጥበቡ ሰምቷል።
ለሥራ አጦች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ረገድ ያሉ ተግዳሮቶች ምን እንደሆኑ እንዲያስረዱ ከቲክቫህ ኢትዮጵያና ሌሎች ሚዲያዎች ጥያቄ የቀረበላቸው ኃላፊው ተከታዮችን ነጥቦች አንስተዋል።
- ሥራ አጡ በጣም ሰፊ ነው።
- አዲስ አበባ የአገሪቱ ዋና ከተማ እደመሆኗ መጠንና አጎራባች አካባቢ ካለው የጸጥታ ችግርም አንፃር በመደበኛም ሆነ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ወደ ከተማ ውስጥ በሰፊው የሚገቡ አሉ። እዚህም የከተማውን ማህበረሰብ ከሥራ ዕድልም አንፃር የሚሻሙ ናቸው።
- የከተማው ወጣት አለ። የከተማው ሥራ አጥ የሥራ ዕድል በጥራትም በስፋት እዲፈጠርለት ይፈልጋል፤ በዚህ መካከል እኛ መፍጠር የምንችለው የሥራ እድል እና ከተማ ውስጥ ያለው የሥራ አጦች ቁጥር አይጣጣምም።
- የራሱ የከተማው ነዋሪ አለ፣ በተለያየ ምክንያት ወደ ከተማ ውስጥ የሚገባም አለ። እነዚህን ሁለቱን አጣጥሞ የሚጠበቀውን ያክል የሥራ ዕድል መፍጠር በጣም ፈታኝ ነው።
- የሥራ አጥ ቁጥሩ አምና ስንጀምር ስብጥሩ በጣም ዝቅተኛ ነበር። ወደ 17 በመቶ አካባቢ የነበረው አሁን አድጎ ወደ 22 ነጥብ 8 በመቶ ደርሷል የሥራ አጥ ቁጥር ምጣኔው።
- እኛ በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ወደ አንድ ድርጅት እናወርዳለን ብለን ነው እየሰራን ያለነው ነገር ግን እየጨመረ ነው የሚያሳየው። የዚህ መጨመር ምክንያቱ የተለያየ ቢሆንም አንደኛው ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር ያለመቻልን ያሳያል።
- እኛ እየፈጠርን ያለነውና የሥራ ስምሪት ውስጥ የሚገባው ሥራ አጥ ቁጥሩ ሰፊ ነው ይሄ አልተመጣጠነም።
- የሰው ሀይላችን እስኪልድ ማን ፓወር አይደለም በጣም የሰለጠነ ብቁ ሞያተኛ የሆነ የሰው ሀይል እጃችን ላይ የለም።
- የሰው ሀይላችን ሥራ አጡ በተለይ የትምህርት ደረጃው ዝቅተኛ ነው፤ ይህን ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ ያለው የሰው ኃይል አሰልጥኖ የክህሎትና የሙያ ባለቤት አድርጎ ወደ ኢንስትሪዎቹ ማስተሳሰርን ይጠይቃል።
በሌላ በኩል ፤ ሥራ ያገኙ ሰዎች ቀጣሪ ኢንዱስትሪዎች የሚከፈላቸው #ደመወዝ_በጣም_አነስተኛ በመሆኑ የቤትና ኪራይና አስቤዛ እንኳ ማሟላት እንደማይችል በተደጋጋሚ ቢገልጹም መፍትሄ እያገኙ እንዳልሆነ፣ ሥራ አጥ የሆኑትም የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ይደመጣል።
ይህንን በተመለከተ አቶ ፍስሃ ምን አሉ ?
" ኢንዱስትሪዎቹ የሚከፍሉት ደመወዝ ዝቅተኛ ነው የእነርሱ ምክንያት ደግሞ እምታቀርቧቸው ሰዎች ሙያቸው ከዚህ በላይ አያስከፍልም የሚል ጥያቄ ያነሳሉ " ብለዋል።
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን ማብራሪያ ያገኘው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኅዳር 8 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ኅዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አዘጋጅቶት በነበረው የውይይት መድረክ ለተገኙት አቶ ፍስሃ ጥበቡ ጥያቄ አቅርቦ ነው)
ጥንቅሩ በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።