TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ከ7.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጥቶበታል የተባለ ፊልም ሊመረቅ ነዉ።

የሲዳማን ህዝብ ባህላዊ የግጭት አፈታት እና የውይይት ባህልን በሰፊዉ ይዳስሳል የተባለው " አፊኒ " የተሰኘ ፊልም የካቲት 2 እና 3 በሀዋሳ ከተማ እንደሚመረቅ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

ፊልሙን በፋይናንስ የደገፈው የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ መሆኑንም ለመረዳት ተችሏል።

የፊልሙ ደራሲና ተዋናይ የሆኑት አቶ እለፋቸዉ ብርሀኑ (ልኡል) ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ " ፊልሙ የሲዳማ ባህላዊ የግጭት አፈታትና የንግግር ባህል የሆነዉን አፊኒ በዓለም ላይ የማስተዋወቅ አቅም ያለዉ ነው " ብለዋል።

ለዚህም ሲባል የፊልሙን ደረጃ ዓለማቀፍ ለማድረግ ታስቦ መሰራቱን ገልጸዋል።

" ፊልሙ በፋይናንስ በሰዉ ኃይልና በቴክኒክ የተሟላ ሆኖ መሰራቱ አስደስቶኛል የሚሉት " አቶ እለፋቸው "  ለዚህም ከ7.5 ሚሊየን ብር በላይ ወጥቶበታል " ብለዋል።

" ተዋናይ ግሩም ኤርሚያስ እና ተዋናይ አማኑኤል የመሳሰሉ አርቲስቶች የሲዳማን ውብና አስተማሪ የግጭት አፈታት ባህል የሚገልጽ የድርሰት ሀሳብ ውበትና ጉልበት ሰጥተውታል " ሲሉም አክለዋል።

በሌላ በኩል ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የምርቃቱን ጉዳይ እና በማህበራዊ ሚዲያ ተመድቧል እየተባለ ስለሚነገረው በሚሊዮኖች ገንዘብ መጠን ጠይቋል።

አቶ እለፋቸው ብርሃኑ ፤  " ከፊልሙ ተዋንያን ባለሙያዎችና ፊልሙን በፋይናንስ ከደገፈዉ የክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የተወጣጡ የምረቃ ኮሜቲ አባላት በቅርቡ ተቋማዊ ገለጻ ያደርጋሉ " ያሉ ሲሆን ለጊዜዉ ፊልሙ የካቲት 2 እና 3 ከመመረቁ ዉጭ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

መረጃዉ የሀዋሳዉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነዉ።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን በጨረታ ለሽያጭ አቅርቧል።

ኮርፖሬሽኑ ፤ " ያለብኝን የፋይናንስ እጥረት በመፍታት ተጨማሪ ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቼ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንድችል ከዲዛይን ግንባታ ቢሮ ጋር በመሆን በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው #የተጠናቀቁ
➡️ 3,146 የመኖሪያ ቤቶችን
➡️ 306 የንግድ ቤቶችን በድምሩ 3,452 ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሬ በሽያጭ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ " ሲል አሳውቋል።

ማንኛውም ለጨረታ የቀረቡ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን ለመግዛት የሚፈልግ ሁሉ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ከ27/05/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 20/06/2016 ዓ.ም ድረስ ቅዳሜን እስከ 11፡00 ሰአት እና እሁድ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ማታ 1፡30 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይችላል ተብሏል።

የሰነድ መሸጫ ቦታ ከላይ ባለው ሰንጠረዥ ተመላክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ማግኘቱን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📣 ሰምተዋል?

በማንኪያ ሲሉ በጭልፋ ፤ በጭልፋ ሲሉ በአካፋ!

👉 ከጥር 6 እስከ መጋቢት 22 ድረስ ከሚጠቀሙት ፓኬጅ ከፍ ካሉ በእኛ ወጪ ወደ ቀጣዩ ትልቅ ፓኬጅ ለአንድ ወር ከፍ ይላሉ!

ይህ አገልግሎት ክፍያ ከፈፀሙ ከ48 ሰዓት በኋላ ተግባራዊ ይሆናል።

*ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን 

የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!

👇👇👇
https://bit.ly/2WDuBLk

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #StepUp
#CBE

በአዲስ መልክ!
****
የነበሩትን አ
ሻሽሎ፣
በርካታ አዳዲስ ነገሮችን አካቶ፣
ለአጠቃቀም ቀሎ፣
ፍጥነት እና ምቾት ጨምሮ፣
በአዲስ መልክ በቀረበው የሲቢኢ ብር መተግበሪያ ይጠቀሙ!
****

አሁኑኑ ወደ
Google Play ወይም App Store በመግባት የሲቢኢ ብር መተግበሪያዎን ያዘምኑ/ ይጫኑ!
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr

• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

*** 
የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!  
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh  
• Telegram፡- https://yangx.top/combankethofficial
#Amhara

ዛሬ በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች የውይይት መድረኮች ሲካሄዱ መዋላቸውን ከመንግሥታዊ የዜና አውታሮች የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።

ውይይቶቹ የተመሩት ከፌዴራል እና ከሌሎች የሀገሪቱ ክልል በመጡ ከፍተኛ ባለስልጣናት ነበር።

በዋነኝነት ትኩረት ያደረገው በክልሉ ያለውን ችግር ለማዳመጥና የመፍትሄ ሃሳቡን ከህዝቡ ለመረዳት ነው ተብሏል።

ባለስልጣናት በነዚህ መድረኮች ላይ ክልሉ በሰላም እጦት በሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ እየከፈለ ስላለው ዋጋና እየደረሰ ስላለው ጫና ሲናገሩ ተደምጠዋል።

መንግሥት ለዘላቂ ሰላም ጥረት እያደረገ መሆኑንና ይህንንም ህዝቡ ሊደግፍ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ጥያቄዎችን በሃይል አማራጭ ለመፍታት መሞከር ውጤት እንደሌለውና ክልሉን ወደ ባሰ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ እንደሚከት ጠቁመው ፤ ሰላማዊ መንገድ መከተል ዓይነተኛ መፍትሄ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ለጥያቄዎች ከትጥቅ ትግል ይልቅ በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋብ።

በተለይ በባህር ዳር ነበረ የውይይት መድረክ የክልሉ ህዝብ በተደጋጋሚ የሚያነሳቸው ፦
የወሰንና የማንነት፣
የፍትሃዊ ተጠቃሚነት
ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በሰላም የመኖር መብት ሌሎች ጥያቄዎች ታውቀው ያደሩ መሆናቸውና በቀጣይ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ መንግስት እየሰራ ነው ብለዋል።

ዛሬ ውይይት እንደተደረገባቸው ከተሰሙት አንዷ በሆነችው ደሴ የተገኙ ተሳታፊዎች ፤ የእርስ በእርስ ግጭቱ እያደረሰ ካለው ጉዳት በተጨማሪ፦
የኑሮ ውድነት
የሥራ አጥነት
የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና ሌሎችም ተዳምረው ህብረተሰቡን ለከፍተኛ እንግልት መዳረጉ ተነስቷል።

የአማራ ህዝብ #አንኳር ጥያቄዎች በተገቢው ጊዜ እና ፍጥነት መመለስ ባለመቻሉ ዛሬ ለተደረሰው የሰላም እጦት ምክንያት መሆናቸውን ተሳታፊዎች አንስተዋል።

በመንግሥትና በታጣቂ ኃይሎች መካከል ሀቅ ላይ የተመሰረተ በእውነትም ሀገርን ከትርምስ ሊያወጣ የሚችል ውይይት ማድረግ እና ክልሉም አሁን ካለበት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማውጣት እንደሚገባ ተነስቷል።

ዛሬ በተመሳሳይ ጊዜ ውይይት ተደርጎባቸዋል ከተባሉ ከተሞች መካከል ባህር ዳር፣ ደሴ፣  ወልድያ፣ ደባርቅ፣ ደብረ ታቦር፣ እንጅባራ፣ ሰቆጣ ከተሞች ይጠቀሳሉ።

በአማራ ክልል ከተሞች በነበሩት መድረኮች ላይ ፦ የሶማሌ ፣  የኦሮሚያ ፣ የሲዳማ ፣ የሐረሪ፣ የቤኒሽንጉል ጉሙዝ ክልሎች ፕሬዜዳንቶች እንዲሁም የአዲስ አበባ ከንቲባ ተገኝተው ነበር።

የሀገር መከላከያ ፣ የገንዝብ ፣ የሥራ እና ክህሎት ፣ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሮችን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል አመራሮችም ተገኝተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

ከዚህ ቀደም በክልሉ ከተሞች መሰል የውይይት መድረኮች ሲዘጋጁ የነበረ ቢሆንም በአንድ ጊዜ በዚህ ልክ ከፍተኛ እና የክልል አመራሮች ወደ ክልሉ ከተሞች ውይይት ሲቀመጡ ይህ የመጀመሪያ ነው።

የአማራ ክልል በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ቦታዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይል እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚካሄዱ ግጭቶች ከግጭቱ ተሳታፊዎች ባለፈ ንፁሃን ሰለባ እያደረጉ፣ ወጥቶ ለመግባት ፣ ለንግድ ፣ ለቱሪዝምም ትልቅ እንቅፋት እየሆኑ እንዳለ በተደጋጋሚ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
#Hawassa

" ተማሪው ላይ ጾታዊ ትንኮሳ ፈጽሟል " በሚል #የተጠረጠረው ርእሰ መምህር በቁጥጥር ስር እንዳሚገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

በሀዋሳ ከተማ ታቦር አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወስጥ አንዲት ተማሪ ርእሰ መምህሯን " ጾታዊ ትንኮሳ ፈጽሞብኛል " በሚል ክስ መመስረቷን ተከትሎ ፖሊስ ተጠርጣሪዉን ግለሰብ ከስራ ገበታዉ ድረስ በመሄድ በቀን 20/05/2016 ዓ/ም በቁጥጥር ስር ማዋሉን ለማወቅ ተችሏል።

የሀዋሳ ከተማ ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ሀላፊዋ ወይዘሮ ፍሬህይወት ወልደጻዲቅ ጉዳዩን በተመለከተ ከቲክቫህ ኢትዮጽያ የሀዋሳው አባል ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ፤ " የተጠቂዋ ቤተሰቦች ጉዳዩን ይዘዉ ቅድሚያ ለማመልከት የመጡት ወደእኛ ቢሮ ነበር " ያሉ ሲሆን ጉዳዩን ወደ ህግ እንዲወስዱት በማድረግ ማንኛዉንም የህግ ከለላና አስፈላጊ ድጋፎችን ሊሰጡ እንደሚችሉ ቃል ገብተው አንዳበረታቷቸው ገልጸዋል።

ከዚህ በኋላ ክሱ ተመስርቶ ተጠርጣሪዉ በህግ ጥላ እንደዋለና ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የገለፁት ኃላፊዋ " አሁን ላይ የሀዋሳ ከተማ ትምህርት መምሪያ መረጃዎችን አጠናክሮ የክስ ሂደቱን ከኛ ጋር ለመደገፍ እንቅስቃሴ ላይ ነው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዉ በትምህርት ቤት ውስጥ ሲያዝ የነበረዉን ሁኔታ እና ድርጊቱን በተመለከተ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር የሚያውቀዉ ነገር እንዳለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የትምህርት ቤቱ ምክትል ርእሰ መምህር አቶ ሀንዳሞ ፈይሳ ፤ በወቅቱ ተጠርጣሪው ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብለዉ መሄዳቸውን ፤ አሁን ላይ በህግ ቁጥጥር ስር ከዋሉ ሳምንት እንዳለፋቸው ገልጸዋል።

ክስ አቅራቢዋ ተማሪ ከትምህርት ገበታዋ ደጋግማ በመቅረቷ ምክንያት " ወላጅ አምጭ አታምጭ " በሚል ከሚመለከታቸዉ መምህራኖቿ እና ከተጠርጣሪው ርእሰ መምህር ጋር ስትጨቃጨቅ እንደነበር የሚያስታዉሱት አቶ ሀንዳሞ ፤ ይህ ጉዳይ ለእርሳቸውም ሆነ ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ #አስደንጋጭ እና ግራ ያጋባ መሆኑን አስረድተዋል።

ፖሊስ አስፈላጊዉን ማጣራት አድርጎ እዉነቱ ላይ እስኪደርስ እየጠበቁ መሆኑንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የሐዋሳዉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነዉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር ረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው አስተያየት እንዲሰጥ መድረክ መመቻቸቱን አሳውቋል። የትምህርት ሚኒስቴር : - 1ኛ. የአጠቃላይ ትምህርት የመምህራን የደረጃ እድገት የአፈጻጸም መመሪያ፣ 2ኛ. የር/መምህራን፣ የም/ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የምልመላ መረጣና ምደባ የአፈጻጸም መመሪያ፣ 3ኛ. የቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕጩ ምምህራን…
#Update

ትምህርት ሚኒስቴር  በረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት ለመስጠት ለሀሙስ የተጠራው ስብሰባ ወደ አርብ የካቲት 1/2016 ዓ.ም ጠዋት 3:30  ሰዓት መሸጋገሩን አሳውቋል።

ማንኛውም አስተያየት መስጠት ከሚፈልግ ሰው በሰዓቱ መገኘት ይችላል ተብሏል።

መመሪያዎቹ ፦

1ኛ. የአጠቃላይ ትምህርት የመምህራን የደረጃ እድገት የአፈጻጸም መመሪያ፣

2ኛ. የር/መምህራን፣ የም/ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የምልመላ መረጣና ምደባ የአፈጻጸም መመሪያ፣

3ኛ. የቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕጩ መምህራን ምልመላና መረጣ የአፈጻጸም መመሪያ፣ የሚሉ ናቸው።

@tikvahethiopia
#WSU

“ አንድ ዓመት መዘግየት በጣም ከባድ ነው። ግዴታ መማር እንዳለብን አስጠንቅቀውናል ” - የወላይታ ሶዶ ዩኒበርሲቲ ተማሪዎች

“ የተማሩበት ታይም ምን ያህል ነው? ተብሎ መወሰን አለበት” - የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የ4ኛ ዓመት ተማሪዎች በዚህ ዓመት መመረቅ ሲገባቸው “ አላወቅነውም ” ባሉት ምክንያት ለምረቃ አንድ ‘ዓመት ትጨምራላችሁ’ ተብለው እየተገደዱ መሆኑን አማረው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ለምን የእናንተ ብቻ ዘገዬ ወይም አንድ ዓመት ጭማሪ ተደረገ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል።

* ስኬጁሉ ላይ ነው ችግራቸው። በኮሮና ምክንያት 2013 ዓ/ም ሁሉም ግቢዎች ተማሪዎቻቸውን የጠሩት ሰኔ ወር ላይ ነበር። እኛም ከሁሉም ግቢ እኩል ነበር የገባነው (ሰኔ 26)። ወዲያውኑ (45 ቀናት አቆይቶ) አስወጣን (ከግቢ) ምንም ባላወቅንበት መንገድ። አንድ ሲሚስተር ጨርሰን መወሰጣት ሲገባን ሚድን ፈትኖ አስወጣን። 

* በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ሚዲ የወሰድነውን ሁለት ሲሚስተር አድርጎ በአጠቃላይ አስተማረ። ሙሉ 3 ሲሚስተር ነበር ማስተማር የነበረበት ግን አንዱን ዓመት በሁለት ሲሚስተር ብቻ አደረገ። ስህተቱን የሰሩት እዚሁ ላይ ነው።

* ሬጅስተራር ላይ የሰፈረው “4ኛ ዓመት ናችሁ” ነው የሚለው። እኛ የምንማረው ግን ገና ሦስተኛ ዓመት ሁለተኛ ሲሚስተርን እየጀመርን ነው። ሌሎች ግቢዎች ግን አሁን 4ኛ ዓመት ሁለተኛ ሲሚስተርን እያስተማሩ ነው። የእኛ ሙሉ 3 ሲሚስተሮች ወደ ኋላ ቀርቷል ማለት ነው።

* ‘ወደ ኋላ ቀረን’ ብለን ስናመለክት ‘#አስተካክላለሁ’ ብሎ ‘3 ሲሚስተር አስተምራለሁ’ ካለ በኋላ ሁለት ሲሚስተር አስተማረና ካፌ ዘጋ። እንደዛ እየተደረገ አንድ ዓመት ባከነ። የእኛን የአንድ ዓመት በጀት ለምን እንደፈለጉት አናውቅም። ከሌሎች ግቢዎች በሚለይ ሁኔታ በሚያስጠላ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው።

የሚል ማብራሪያ በአንድ ተወካያቸው በኩል ሰጥተዋል።

“ ሌሎች ግቢዎች የእኛን ባቾች በዚህ ዓመት ያስመርቃሉ። የእኛ ግን በዚህ ዓመት አይደለም” ያሉት ተማሪዎቹ፣ “ በዚህ ሳምንት ክላስ አልገባንም። ነገር ግን ግዴታ በቀጣይ ሰኞ መግባት እንዳለብን ተነግሮናል። ግዴታ መማር እንዳለብን አስጠንቅቀውናል። ” ሲሉ አስረድተዋል።

አክለውም፣ “ አንድ ዓመት መዘግየት በጣም ከባድ ነው። ሙሉ 3 ሲሚስተር አስተምሮ ሰኔ ላይ ይፈትነን (እንመረቅ) አንልም። ቢያንስ ስለ Exit exam የሚሆኑ ኮርሶችን ወደዚህ አሸጋሽገውልን Exist ተፈትነን ቀጣዩን አንድ ሲሚስተር እንድንወስድ ያድርጉን። አንድ ዓመት ከመዘግየት ግማሽ ዓመት መዘግየት ይሻላል ብለዋል ” ሲሉ አሳስበዋል።

ቅሬታውን በተመለከተ ምን ምላሽ እንዳለው ለመጠየቅ ወደ ዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮሽ የተደረገው ሙከራ ባይሳካም፣ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ኀብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ ፍሬው ተክሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ስኬጁል ላይ የተቀየረ ነገር የለም። ያልተጣራ መረጃ እንጂ በእኛ ፔጅ ላይ የተለጠፈ አይደለም ” ሲሉ አስተባብለዋል።

ተማሪ ፍሬው፣ “ የሚመረቁት መቼ ነው? ለሚለው የተማሩበት ታይም ምን ያህል ነው? የሚለው መወሰን አለበት” ያሉ ሲሆን፣ የዘንድሮ ተማሪዎቹ በቀጣይ ዓመት ነው የምትመረቁት ተብለዋል ወይስ አልተባሉም? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄም ቀጥኛ መልስ በመስጠት ፋንታ፤ “በእስኬጁል መሠረት ነው እኮ ይሄ ውሳኔ” ብለዋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
Unleash your entrepreneurial spirit with the Jasiri Talent Investor Programme! We're seeking visionary entrepreneurs ready to create high-impact businesses that will shape the future. Our fully-funded 13-month program is uniquely designed to support your growth journey, providing the resources to foster Market-Creating Innovation and find the perfect product-market fit. With a focus on competency and a comprehensive support system, we're here to help you overcome any barriers to success. Apply for Cohort 6 now at jasiri.org/application and start building your venture with us. #JasiriTalentInvestor #Entrepreneurship #Innovation #BusinessGrowth #ApplyToday
የሁለተኛ እና የሶስተኛ  ዙር ተረክ በM-PESA የባጃጅ አሸናፊዎቻችን ሽልማታቸውን ተረክበዋል!

አዲስ አበባ፣ አምቦ፣ ጅማ፣ ሰንዳፋ እና አዳማ እንኳን ደስ አላችሁ!

ቀጣይ በM-PESA የተዘጋጀው ምርጥ ሽልማት ማን የሚውስደው ይመስላቹዋል?

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ ቀጣይ እድለኛ አሸናፊዎች እንሁን።

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ: https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether