TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
"ኢትዮጵያን በዚህ ሰአት #እያደማት ያለው ከአብራኳ የወጣ #እውቅና ፈላጊ የፌስቡክ አክቲቪስት እና የዩትዩብ ጡረተኛ ዜጋዋ ነው።"

©አዲሲቷ ኢትዮጵያ እኔ ነኝ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክሱም ዩኒቨርሲቲ‼️

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ግጭት እንዳይፈጠርና የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊ እንዲሆን  አስተዋጽዖ ላበረከቱ አካላት #እውቅና ተሰጠ።

ዩኒቨርሲቲው በእስከ ዛሬው የመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ግጭት ያልተፈጠረበትና ተማሪዎች በሰላም ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በማድረግ ምሳሌ መሆን ችሏል።

ይህ እንዲሆን የበኩላቸውን ላበረከቱ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ነው ዛሬ እውቅና የተሰጣቸው።

እውቅና የተሰጣቸው የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የዞኑና የከተማው የተማሪዎች የወጣቶች ኮማንድ ፖስት፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች መሆናቸው ታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በሶስት ካምፓሶች የሚማሩ ከ14 ሺህ በላይ ተማሪዎች ሲኖሩት ከነዚህ መካከል አራት ሺዎቹ ዘንድሮ የገቡ ናቸው።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia