TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ሀዉልቶች ነገር⬇️

እዉነት እንነጋገር!

ከወዲያ እና ከወዲህ ተመሳሳይ ድምፅ! ሀሳብ የሌለበት ንትርክ! አሁን ክርክሮች ስለሀዉልቶች ሆኗል። ግማሹ የአኖሌ ሀዉልት እንዲፈርስ ይጠይቃል። ሌላዉ ደግሞ በምኒልክ ሀዉልት ላይ አተኩሯል። ይህ ጫወታ የማን እንደሆነ ይታወቃል። የእሳትና ጭድ ፖሊሲ አካል ይመስላል። ሀዉልት ሟቾችን ይመለከታል። ጠላት ሆን ብሎ ትኩረታችንን ወደ ሟቾች ይስባል። በመሀሉ የኗሪዎች ጉዳይ ተዘንግቷል። ስለሞቱት እያለቀስን የአሁኑን እና የወደፊቱን ትዉልድ በጅምላ እንዳንገድል ያሰጋል። በ21ኛ ክፍለ ዘመን በዝህ ደረጃ መታለላችን ምን ይባላል? ሌላ ጋ መማሪያ የሆነ ታሪክ እኛ ጋ ለምን የግጭት መነሻ ይሆናል? ሰዉ እንዴት በገዛ እጁ በተከለዉ ሀዉልት ሰለባ ይሆናል?

እዉነት እላለሁ፦

ሰዉ ከሀዉልት ይበልጣል!
ልብ ያለዉ ልብ ይበል!
ሠላም!

#ታዬ_ደንዳዓ #TayeDendea (የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ ሀላፊ )
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TayeDendea

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ታዬ ደንደአ ከስልጣን መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ተሰምቷል።

ለሚኒስትር ዴኤታው የተፃፈው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፊርማ ያረፈበት ደብዳቤ ፦

" ከመስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነዉ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እያመስገንኩ ከታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከኃላፊነት የተነሱ መሆኑን አስታዉቃለሁ። " ይላል።

ደብዳቤው ከራሳቸው አቶ ታዬ ገፅ የተገኘ ነው።

ይህ ተከትሎ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ታዬ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተችተው ፅፈዋል።

አቶ ታዬ ፤ " ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ " ብለው ባሰራጩት ፅሁፍ " የተናገሩትንና የፃፉትን የመደመር እሳቤ አምኜ ተከተልኩዎት። አሁን ግን በተናገሩት የማይኖሩ ብቻ ሳይሆን በሰዉ ደም የሚጫወቱ አረመኔ መሆንዎን ተረድቻለሁ። " ብለዋል።

" እዉነት መስሎኝ በሀገር ህልውና ስም ሲያካሄዱ የነበረዉንና ኢትዮጵያውያንን ከማገዳደል አልፎ ሀገሪቷን ያደቀቃትን ከንቱ ጦርነት ሳዳምቅልዎ በነበረበት ወቅት ሲያወድሱኝ ነበር። " ያሉት አቶ ታዬ " ዛሬ ነገሩ ገብቶኝ የወንድማማቾች መገዳደል ይቆም ዘንድ ለሰላም በመወገኔ ከስልጣን አነሱኝ። " ብለዋል።

" ለወንበርና ለመኪና በመገዛት ኦሮሞን በኦሮሞ ለማጥፋትና ኦሮሞን ከወንድሞቹ ጋር ለማጣላት የሚጫወቱትን ቁማር እያየሁ ዝም ባለማለቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ። " ያሉት አቶ ታዬ " ስለነበረን አጭር ቆይታ አመሰግናለሁ። እስካለሁ ድረስ ለሰላምና ለህዝቦች ወንድማማችነት የማደርገዉ ትግል ይቀጥላል " ሲሉ ፅፈዋል።

ምንም እንኳን አቶ ታዬ ከስልጣን መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ አያይዘው ብስጭታቸውን ቢገልጹም ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

አቶ ታዬ ደንደአ በተለያየ ጊዜ እሳቸው ያሉበትን መንግሥት በመተቸት ይታወቃሉ።

@tikvahethiopia