TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
@samcomptech

አዳዲስ ላፕቶፕች ገብተዋል!!!!

ለተማሪዎች፣ ለቢሮ ሰራተኞች፣ ለጌመሮች፣ ለቪዲዮ ኢዲተሮች ፣ ለግራፌክስ ስራዎች ፣ ለዴዛይነሮች አዳዴስ  ላፕቶፕች እና ስልኮች  በቅናሽ እና ከአንድ አመት ዋስትና ጋር እናቀርባለን።
🔵 @samcomptech

በሚገርም ፍጥነት ፣ ቅለት እና ከ 10 ሰሀት በላይ የባትሪ ቆይታ ያላቸዉ  ዘመናዊ ላፕቶፖችም አሉን።

ቴሌግራም ላይ ሁሉም ዝርዝር አለ በመቀላቀል  የሜፈልጉትን ይምረጡ  ።
🔵https://yangx.top/samcomptech 🔵 
🔼@sww2844

ስልክ፤ 0928442662 / 0940141114
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ፎቶ ፦ በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ለዓመታት የትጥቅ ትግል ሲያካሂዱ የነበሩ የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቃናቄ (ጉህዴን) ታጣቂዎች ትላንት በገነተ ማሪያም ቀበሌ እርቀ ሰላም በመፈጸም ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀላቸውን ክልሉ አሳውቋል።

ምን ያህል ታጣቂዎች እንደተመለሱ በይፋ የተባለ ነገር የለም።

የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ለሜሳ ዋውያ፣ በነበረው አለመረጋጋት የተዘጉ መንገዶችና የመሰረተ ልማቶችን በአጭር ጊዜ ሙሉ በሙሉ  ወደ መደበኛ ስራዎች እንዲገቡ ይሰራል ብለዋል።

የማንዱራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቤዋ ቡልት በበኩላቸው ፤ ለተመላሾች የእርሻ ትራክተሮችና የወርቅ ማውጫ ማሽን ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

ታጣቂዎች ተመለሱ ሲባል ይህ የመጀመሪያ ነው ?

የጉህዴን ታጣቂ አባላት የትጥቅ ትግል አቁመው ወደ ሰላማዊ ሕይወት ተመለሱ ሲባል ይህ የመጀመሪያ አይደለም።

የመንግሥትን " የሰላም ጥሪ " የተቀበሉ ከ380 በላይ ታጣቂዎች በሚያዝያ 2014 እጅ ሰጥተው ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለሳቸውን በወቅቱ ተነግሮ ነበር።

ይሁን እንጂ በሐምሌ 2015 ለተሐድሶ ሥልጠና ዝግጅት ላይ የነበሩ ታጣቂዎች በመተከል ዞን በግልገል በለስ ከተማ ከሚገኝ ካምፕ ከነ ጦር መሣሪያቸው ወደ ጫካ መመለሳቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረው ነበር።

ከክልሉ መንግሥት የሰላም ሥምምነት የተፈራረመው ጉህዴን በተደጋጋሚ የታጠቀ ኃይል እንደሌለው ሲያስታውቅ ቆይቷል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ስድስት ገደማ ዓመታት የተቀሰቀሱ ተደጋጋሚ ግጭቶች ብርቱ ሰብዓዊ እና ምጣኔ ሐብታዊ ጉዳት ማስከተሉን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" እርዳታው ከተላከ ከአንድ ሳምንት በላይ ሆኖታል እስካሁን ግን ቦታው ላይ አልደረሰም " - ቀይ መስቀል

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ላጋጠመው ድርቅ እርዳታ ቢልክም እስካሁን ቦታው ላይ አልደረሰም።

እርዳታው ቦታው ላይ ያልደረሰው በፀጥታ ችግር ነው ብሏል።

የማህበሩ የፕሮግራም ኃላፊ አቶ ድረስ ደስይበለው ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፤ እርዳታው ከተላከ ከሳምንት በላይ እንደሆነ ጠቁመዋል።

" ምግቡ ከእኛ ከወጣ ከሳምንት በላይ ሆኖታል " ያሉት አቶ ድረስ " እስካሁን ግን እዛ አልደረሰም " ሲሉ ተናግረዋል።

" በየቦታው እየቆመ ባሰብነው ልክ መሄድ አልቻለም ፤ አሁን የደረሰው ባህር ዳር ነው እርዳታው ከሄደ ግን ከሳምንት በላይ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ችግሩ ከፀጥታ ጋር የተገናኘ ነው ብለዋል።

ከተላከ ሳምንት የሞላውና በፀጥታ ችግር መንገድ ላይ የቆመው እርዳታ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበትና 2600 ሰዎችን ተደራሽ የሚያደርግ እንደሆነ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በአማራ ክልል ካለው ድርቅ ጋር በተያያዘ ማህበሩ በሰሜን ጎንደር 3 ወረዳዎች ረሃብ እንደተከሰተ በደረሰው መረጃ 4450 በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች እርዳታ ተደርጓል ብሏል።

የተደረገው እና መንገድ ላይ የቆመው ድጋፍ የምግብ ዱቄት እና በአንዳንድ ቦታዎች ዘይትንም ያካተተ እንደሆነ ተጠቁሟል።

@tikvahethiopia
#USA

" ፕሬዜዳንት በሆንን በአንድ ሳምንት ውስጥ ቲክቶክን እናግዳለን " ያለቱ የሪፐብሊካን እጩዎች !

የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ በ2024 ይካሄዳል።

የሪፐብሊካን የፕሬዜዳንታዊ እጩዎች ቢሮ በገቡ በመጀመሪያው ሳምንት " #ቲክቶክ " የተሰኘውን መተግበሪያ እንደሚያግዱ ገልጸዋል።

እጩዎቹ ሰሞኑን በነበረ ክርክር መድረክ ላይ ነው ይህን የገለፁት።

እጩዎች የቻይናን መረጃ መሰብሰብን ለመዋጋት አንዴ ፕሬዜዳንት ሆነው ወደ ነጩ ቤተመንግስት ይግቡ እንጂ " ቲክቶክ" ን እስከወዲያኛው እንደሚያግዱት ገልጸዋል።

ክሪስ ክርስቲ የተባሉ የሪፐብሊካን እጩ ምን አሉ ?

እኚህ እጩ " ቲክቶክ " መረጃዎችን ከመሰብሰብ ባለፈ በመላው ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የወጣት አሜሪካውያንን አእምሮ እየበከለ ነው ብለዋል። " ይህንን የሚያደርጉት ደግሞ ሆን ብለው ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ቲክቶክ " በአልጎሪዝሙ አሰቃቂ፣ ያልተገቡ፣ ከፋፋይ፣ አፍራሽ ፣ የወጣቶችን አእምሮ የሚበክሉ ጉዳዮችን ከፍተኛ ደረጃ ወደ ተጠቃሚው እንዲገፋ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

ይህም ቻይና አሜሪካንን ለመከፋፈል ይበልጥ እየተጠቀመችበት ያለ ተግባር ነው ሲሉ ከሰዋል።

የሪፐብሊካኑ ሰው የቀድሞው ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው " ቲክቶክን ማገድ " በተመለከት ብዙ ሲናገሩ እንደነበር ነገር ግን መተግበሪያውን ማገድ ሲገባቸው ያን አለማድረጋቸው የሚያስወቅስ እንደሆነ ገልጸዋል።

እሳቸው ፕሬዜዳንት ሆነው በመጡ በመጀመሪያው ሳምንት ቲክቶክን እንደሚያግዱ አሳውቀዋል።

ሮን ዴሳንቲስ የተባሉ እጩ ደግሞ " የአሜሪካን ህዝብ ለመጠበቅ ስንል ቲክቶክን የማገድ እርምጃ እናሳያችኃለን " ብለዋል። ፕሬዜዳንት ሆነው ሲመጡም ይህንን እንደሚያደርጉትን ገልጸዋል።

ቲም ስኮት የተባሉት እጩ ፤ " እኛ ማድረግ ያለብን ቲክቶክን ማገድ ነው ፤ አለቀ !! " ብለዋል።

በቀድሞው ፕሬዝደንት ትራምፕ ቲክቶክን ለማገድ ሁለት ጊዜ ሲሞከር አይተናል ያለቱ ስኮት ፤ ነገርግን በፌደራል ፍርድ ቤቶቻችን እንዳይፈፀም ተደርጓል ሲል አስታውሰዋል።

ቲክቶክን ማገድ ካልተቻለ በመተግበሪያው ላይ ያለውን የቻይናን ተፅእኖ መኖር እንደወዲያኛው #ማስወገድ ነው ብለዋል።

ባይትዳንስ የተሰኘው ኩባንያ ንብረት የሆነው " ቲክቶክ " ከዚህ ቀደም በተለይም ግላዊ መረጃን በመበዝበዝ እና ከቻይና መንግሥት ጋር የተቆራኘ ነው በሚል ከፍተኛ ወቀሳ ሲደርስበት ነበር ፤ ኩባንያው የቻይና መንግሥት መረጃውን እንደማያገኝበትና ቻይና ያለው ቲክቶክ ከሌላው ዓለም ፈፅሞ የተለየ መሆኑን ደጋግሞ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። መግለጫውን የሰጡት የክልሉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው አቶ ኃይሉ አዱኛ ሲሆኑ ታንዛኒያ ውስጥ እየተካሄደ ነው ስለተባለው የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድር ተጠይቀው ቀጥተኛ ምላሽ ሳይሰጡ አልፈዋል። አቶ ኃይሉ ፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም በክልሉ ዘላቂ ለሰላም እና ደህንነት እንዲሰፍን ፅኑ…
" ድርድሮች መፍትሔ ይዘው የሚመጡት ሁሉን አቀፍ፣ ግልጽነት የተላበሱና በአግባቡ የሚመሩ ሲሆኑ ብቻ ነው " - የ5 ፓርቲዎች የጋራ መግለጫ

መኢአድ ፣ ኢህአፓ ፣ የዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲና እናት ፓርቲ ዛሬ ከጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

ፓርቲዎቹ ምን አሉ ?

- ማንኛውም የሚደረጉ ድርድሮችና ዉይይቶችን የኢትዮጵያ ሕዝብ በይፋ ሊያውቃቸው ይገባል።

- ግልጽ ያልሆኑና ከመጋረጃ ጀርባ የሚደረጉ ድርድሮችና ስምምነቶች ከመድረኩ እንደተወጣ ጥያቄ የሚያስነሱ መሆናቸዉ እንዳለ ሆኖ ዉለዉ አድረዉ ወደ ከፋ ጥፋት አገርንና ሕዝብን እንደሚወስዱ ከቅርብ ጊዜ ታሪካችን የምንረዳዉ ጉዳይ ነዉ፡፡

ለምሳሌ ፦

* " ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጋር ከአምስት ዓመታት በፊት አስመራ ላይ ተደረገ " የተባለዉና የኢትዮጵያ ሕዝብ በግልፅ ምንነቱን ያላወቀዉ ኋላም " የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት " ብሎ ራሱን ለሚጠራዉ ታጣቂ ኃይል መፈጠር ምክንያት እንደሆነ የሚነገረዉ ድብቅ ስምምነት አንዱ ነው።

* ፕሪቶሪያ ላይ የተደረገዉና እርሱን ተከትሎ ናይሮቢ ላይ በፌደራል መንግሥት እና በሕወሃት መካከል የተደረጉ የተሸፋፈኑ ድርድሮችና ተደረሰባቸዉ የተባሉ ስምምነቶች ዛሬም ድረስ ጥያቄ የሚያስነሱና ወደፊትም ጥያቄ በማስነሳት የሚቀጥሉ ናቸዉ።

- ለፖለቲካዊ ጥያቄ ፖለቲካዊ መፍትሄ ብቻ ሊሰጥ ይገባል። ለዚህም ግልፅነት የተላበሰ ድርድር ብቸኛ አማራጭ ነው።

- ከጥቂት ቀናት ወዲህ በመንግሥትና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል ድርድር እየተደረገ ነዉ " በተባለዉና የፌዴራል መንግሥት ድርድሩ ስለመታሰቡም ሆነ ስለመጀመሩ እንዲሁም የድርድሩ ተሳታፊዎችን ማንነት ባልገለፀበት ሁኔታ ላይ መረጃዎች መደመጣቸው የተደበላለቀ ስሜትና ከፍተኛ #ስጋት_አንዲሰማን አድርጓል፡፡

- አብዛኛዉ የኦሮሚያ አካባቢ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚንቀሳቀስበት በመሆኑ በተሰነዘሩ የተለያዩ ዘግናኝ ጥቃቶች በግንባር ቀደምነት የአማራ ማኅበረሰብ ለአሰቃቂ ጅምላ ጭፍጨፋ መዳረጉ የማይታበል ሐቅ ሲሆን፤ ቀን በብልጽግና ማታ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ቀንበር ሥር ወድቆ የመከራ ህይወት እየገፋ ለሚገኘዉ የኦሮሞ ማኅበረሰብም ከመከራዉ ቀንበር የሚገላገልበት የተስፋ ጭላንጭል የሚፈጥር በመሆኑ የፖለቲካ ልዩነቶች በድርድር እንዲፈቱ ዛሬም ጽኑ ፍላጎታችን ነው።

- ድርድሩ እየተካሄደበት ያለዉ መንገድ የተሸፋፈነ መሆን፣ ለድረድሩ ምክንያት የሆኑ አጀንዳዎች ይፋ አለመደረጋቸው እና ከአገራችን ሕዝብ ጀርባ እየተከናወነ የሚገኝ ድርድር መሆኑ፣ ሠላም የራቀዉ ህዝባችንን ተስፋ መልሶ የሚያጨልም የጎራ ድርድር እንዳይሆን ያለንን ስጋት እንገልጻለን።

- የአገራችን ጉዳይ በመጠነ ሰፊ ችግሮች የተሞላ ሆኖ ሳለና ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ባሻገር ድርድሩ ሁሉን አቀፍ መሆን ሲገባዉ የተድበሰበሰና ቁንጽል መሆኑ ያሳስበናል።

(ከፓርቲዎቹ የተላከው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

NB. ምንም እንኳን መንግሥትም ይሁን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው) በታንዛኒያ ዳሬሰላም ለሰላም ድርድር መቀመጣቸውን እስካሁን በይፋ ባያሳውቁም / ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ ባይሰጡም ፤ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የዲፕሎማቲክ ሰዎች ግን የሰላም ድርድር እየተካሄደ መሆኑን አሳውቀዋል። ድርድሩ እየተመራ ያለውም በጦር አዛዦች ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ለዓመታት ተቋርጦ የነበረው ከግልገል በለስ - ድኋንዝ ባጉና - ድባጤ የመወስደው መንገድ ክፍት እንዲሆን መደረጉን የመተከል ዞን አስታወቀ።

የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ለሜሳ ዋውያ ፤ በአካባቢው በነበረው የጸጥታ ችግር ለዓመታት ተቋርጦ የነበው መንገድ አገልግሎት ጀምሯል ብለዋል።

መንገዱ ወደ አገልግሎት የተመለሰው በተደረገው የሰላም ስምምነት መሆኑን ጠቁመዋል።

በማንዱራ ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጉህዴን ታጣቂዎች ትላንት የሰላም ስምምነት ማድረጋቸውን የገለፁት አስተዳዳሪው ይህን ተከትሎ መንገዱ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አሳውቀዋል።

መንገዱ ክፍት እንዲደረግ የሀገር ሽማግሌዎች እና ከፍተኛ አመራሮች ከሰላም ተመላሾች ጋር ውይይት ማድረጋቸውም ተመልክቷል።

ከዚህ ባለፈ ከፍተኛ አመራሮች በአካባቢው የሚገኙ የቱኒ ዳዱሽ እና የገሰስ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ምልከታ ያደረጉ ሲሆን ተቋማቱ ውስጥ ምንም አይነት የመማሪያ ቁሳቁስ ባለመኖሩ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ ፤ የነበሩ መምህራ አሁን ያለውን ሰላም ተጠቅመው ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

መረጃው ከክልሉ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#TecnoPhantomVFlip5G

ዘመኑ የደረሰበትን የመጨረሻ ቴክኖሎጂ ከፋሽን ጋር አጣምሮ የያዘውን ፋንተም ቪ ፍሊፕ 5ጂ ምርጫዎ ያድርጉ ።

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#PhantomVFlip#TecnoMobile #TecnoEthiopia
#SafaricomEthiopia

ሰላም ድሬ! በኦአይ ብራይት ኢንተርናሽናል ኮሌጅ አካባቢ ፈጣኑ ኔትወርክ መጥቶልናል። የ07 ኔትዎርክን በመቀላቀል ማርሻችንን ወደ ፈጣኑ ያልተገደበ ኢንተርኔት ፍጥነት ያለው 4G ኔትዎርክ እንቀይር።

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://yangx.top/Safaricom_Ethiopia_PLC

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
የበርካታ ስደተኞች ደብዛቸው ጠፋ።

ከቀይ ባሕር ዳርቻ ስደተኞች የጫነች ጀልባ ሰጥማ አብዛኞቹ ከአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሆኑ ስደተኞች ደብዛቸው መጥፋቱን የየመን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ጀልባዋ 75 ስደተኞች እንደጫነች ትላንት እሁድ መስጠሟን የየመን የባሕር ድንበር ጠባቂ ኃይል አሳውቋል።

ከስደተኞቹ መካከል 26 ሲተርፉ የቀሩት 49 ሰዎች የገቡበት አይታወቅም ተብሏል።

የጠፉትን ስደተኞች ለማግኘት ዛሬ ሰኞ ፍለጋ እየተካሔደ ነው ተብሏል።

የየመን መንግሥት የሚቆጣጠረው " ሳባ " የዜና ወኪል ጀልባዋ በኃይለኛ ንፋስ ሳቢያ ስትሰምጥ #ሴቶች እና #ሕጻትን ጨምሮ የጫነቻቸው ስደተኞች ወደ ባሕር መውደቃቸውን ስማቸው ያልተጠቀሰ የየመን ባሕር ድንበር ጠባቂ ኃይል ባለሥልጣን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

የተሻለ ገቢ እና የሥራ ዕድል ፍለጋ ወደ ባሕረ ሰላጤው ሀገራት ለማምራት የሚሞክሩ የአፍሪካ ቀንድ ሰዎች የጫነ ጀልባ በቀይ ባሕር ዳርቻዎች የመስጠም አደጋ ሲገጥመው የአሁኑ የመጀመሪያው አይደለም።

በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በየዓመቱ ከኢትዮጵያ፣ ከጅቡቲ እና ከሶማሊያ በየመን በኩል አድርገው ሳዑዲ አረቢያን ወደመሳሰሉ ሀገራት ለመጓዝ ጥረት ያደርጋሉ።

መረጃው የዶቼቨለ ሬድዮ / አሶሼትድ ፕሬስ / ሳባ ነው።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በእኛ ክልል ደረጃ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው የሚታሰሩ ሰዎች የሉም " - አቶ ወንሰንየለህ ስምዖን (የሲዳማ ክልል ኮሚኒኬሽን ኃላፊ) የሲዳማ ክልል መንግሥት በሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ) ለሚቀርበው ክስ ምላሽ ሰጠ። ክልሉ ምላሽ የሰጠው በኮሚኒኬሽን ቢሮው አማካኝነት ነው። የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ ምንድነው ያለው ? (አቶ ገነነ ሀሰና - የፓርቲው የፅ/ቤት ኃላፊ / ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ…
#Update

" የቢሮ ቁልፍ ተሰብሮ ዶክመንት ተዘረፈብኝ " ያለው የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ የክልሉን መንግስት በመክሰስ ለምርጫ ቦርድ የአቤቱታ ደብዳቤ ጻፈ።

ፓርቲው ከሳምንት በፊት ተሰብሮብኛል ያለዉን ቢሮና የተዘረፈውን ዶክሜንት በተመለከተ ለምርጫ ቦርድ ከማሳወቅ ባለፈ ጉዳዩ ባፋጣኝ እንዲጣራለት ጠይቋል። 

የፓርቲዉ  ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገነነ ሆሳና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሀዋሳው ቤተሰብ አባል ባሳወቁት መሠረት  ፤ አሁን ላይ የፓርቲዉን ቢሮ ቁልፍ በመቀየር የተቆጣጠረው የቀድሞ አባልና በዲስፕሊን ግድፈት የተባረረ ግለሰብ ከምርጫ ቦርድ እዉቅና አለኝ ማለቱን ተከትሎ ጉዳዩ እንዳሳሰባቸዉ ገለጸዋል።

በመሆኑም ምርጫ ቦርድ በነዚህ ጉዳዮች ላይ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ እርምጃ እንዲወስድ በደብዳቤ መጠየቁን አሳውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፓርቲው የክልሉ መንግስት በተለያየ ጊዜ የሚያደርስበትን ጫናና ወክቢያ እንዲያቆም ጠይቋል።

የታፔላዎች መነሳትና መጥፋት፣ የአባላት ያለፍርድቤት ትእዛዝ መታሰር ተጠናክሮ መቀጠሉን ፓርቲው ገልጿል።

በመሆኑም ምርጫ ቦርድ አስፈላጊዉን ምርመራ አድርጎ ፈጣን  ማስተካከያ በማድረግ ጫናዉን እንዲያስቆምለት በጻፈዉ ደብዳቤ ጠይቋል።

ከቀናት በፊት የሲዳማ ክልል መንግሥት ኮሚኒኬሽን ፓርቲው በክልሉ ላይ የሚቀርበው ክስ እና ወቀሳ መሰረተቢስ ውንጀላ ነው ማለቱ ይታወሳል።

ከዚህ በተጨማሪ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች እንደታሰሩ ፤ በክልሉ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው የሚታሰሩ ሰዎች እንደሌሉ አሳውቆ ነበር።

መረጃዉ የሀዋሳ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia