TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#ወልቂጤ - " በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። ቤቶች ተቃጥለዋል " - የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር - " በቦታው አድማ የመበተን ሥራ እየተሰራ ነው " - የጉራጌ ዞን ፓሊስ ኮሚሽን - " ግጭቱ እንዲባባስ በሚፈልጉ አካላት ንብረት ወድሟል፣ በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል " - የጉራጌ ዞን ኮማንድ ፓስት አዲስ በተዋቀረው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማና ቀቤና…
#Update

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማና በቀቤና ልዩ ወረዳ በተቀሰቀሰው ግጭት ንጹሐን መገደላቸውንና ነዋሪዎችና ባለስልጣናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

ሥሜ ባይጠቀስ ያሉ አንድ የቀቤና ልዩ ወረዳ ነዋሪ " ሰሞኑን ሁለት የቀቤና ወጣቶች ተገድለዋል " ብለዋል።

ሌላኛው የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ ደግሞ " አንድ የወልቂጤ ሰው በወጣቶች ተገድሏል " ሲሉ ገልጸዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ የቀቤና ልዩ ወረዳ ባለስልጣን በሰጡት አጭር ቃል፣ " ሰዎች እየተገደሉ ነው። መንግሥት አስቸኳይ መፍትሄ ይስጥ " ብለዋል።

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ባለሥልጣን በግጭቱ የንጹሐን ሕይወት ማለፉን አረጋግጠዋል።

ባለሥልጣኑ በሰጡት ቃል፣ " ሁለት ወጣቶች ከጸጥታ ኃይል በተተኮሰ ጥይት ሞተዋል። አንድ ሰው በወጣቶች ተገድሏል " ነው ያሉት።

አክለውም፣ " ቅዳሜ ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ሁለት የቀቤና ወጣቶች ከጸጥታ ኃይል በተተኮሰ ጥይት ሞተዋል። እሁድ ጥቅምት 4 ቀን 2016 ዓ.ም በአመጹ ከጉራጌ አንድ ሰው በወጣቶች ተግድሏል። ዘረፋ ቤት ማፍረስ ቤት ቃጠሎ በከፍተኛ ደረጃ ቀጥሏል " ብለዋል።

በቁጥር ባይታወቅም የቆሰሉ ሰዎች እንዳሉ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደተቋረጠ፣ የጸጥታ ኃይሉ ግን ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ሌሎች የመረጃ ምንጮች ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ " ከቀቤና ልዩ ወረዳ መጥተው ቤት አቃጥለዋል፣ ንብረት ዘርፈዋል፣ ፌደራል ፓሊስ በመሳሪያ መትተው ገድለዋል። ከተማውና የዞኑ ፓሊስ አቅሙን እንዳይጠቀም ተደርጓል። ልዩ ኃይል እረብሻ ያለበትን ሥፍራ ትቶ መሀል ከተማ ላይ አስለቃሽ ጭስ ማኅበረሰስቡ ላይ ወርውሯል። በተጨማሪም የዞኑን ፓሊስ ኮማንደር ጠጄን አግተውታል፣ ብዙ ወጣቶች ተደብድበዋል" ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣን የኮማንደር ጠጄን እገታ በተመለከተ በሰጡት ምላሽ ፣ " ጉዳት ደርሶበታል መሬት ለመሬት ተጎትቶ በወጣቶቹ ሲደበደብ ነበር። እገታው የሚለው መረጃ እኔ ባለኝ መረጃ ልክ አይደለም " ነው ያሉት።

ለሰው ሕልፈተ ሕይወት ምክንያት የሆነው ግጭት ከምን ጥያቄ የተነሳ እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሲጠየቁም፣ የሚከተሉትን ሦስት ጭብጦቹ ዘርዝረዋል።

- የቀቤና ልዩ ወረዳ ውስጥ በ24 ቀበሌ  የሚኖሩ ብሄራቸው ጉራጌ የሆኑ የሕዝብ ክፍሎች በዚህ አንካለልም ማለታቸው ተከትሎ አለመግባባት አለ።

- የቀቤና ልዩ ወረዳ መቀመጫ ወልቂጤ መሆን የለበትም የሚሉ የጉራጌ ተወላጆች ወልቂጤ ከተማ መስተዳድር  በጉራጌ የሚተዳደር አንድ መዋቅር የዞኑ መቀመጫ ጭምር ነው በማለት ያነሳሉ።

- ቀቤና ልዩ ወረዳ ደሞ የወልቂጤ ከተማ መስተዳድር በዙሪያው ባለው ቀበሌ ላይ የተሠመሰረተ በመሆኑ ከዚህ የትም ወጥቼ የልዩ ወረዳ መቀመጫ አልመሰርትም ብሎ ያምናል።

ከእነዚህ መሠረታዊ ኮዝ በመነሳት በወጣቶች መካከል ግጭት ተነስቶ ነው ለአጠቃላይ ሞት፣መንገድ መዘጋት፣ ንብረት መውደም ዘረፋ እንዲፈፀም  ምክንያት የሆነው " ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ አደረጉት በተባለ ውይይት፣ አራቱ መዋቅሮች የአካባቢያቸውን ሰላምና የሕዝቦችን ደኅንነት ተቀናጅተው በጋራ ማስጠበቅ ሲገባቸው ወደ ሁከትና ብጥብጥ በመግባታቸው ከተጠያቂነት የማያድን በመሆኑ ከድርጊቱ ወጥትው በአስቸኳይ ማስቆም እንዳለባቸው ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ጥቅምት 4 ቀን 2016 ዓ.ም በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል።

https://telegra.ph/Tikvah-10-16

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ #ቻይና

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ቻይና አቅንተው በቻይና ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ናቸው።

ከጠ/ሚ ፅ/ቤት በወጣ መረጃ የቻይናው ጠ/ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ለዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ይፋዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በኃላም የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል። በዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የምጣኔ ኃብት ትብብር ግንኙነት ማጠናከሪያ መንገዶች ላይ መክረዋል ተብሏል።

ከሁለትዮሽ ውይይቱ በመቀጠል ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ጠ/ሚ ሊ ኪያንግ በተገኙበት በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ መስኮች 12 ያህል የትብብር ስምምነቶች እና ሁለት የፍላጎት ሰነዶች ተፈርመዋል።

ዶ/ር ዐቢይ በቻይና ይፋዊ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ ከአራት ዓመት በኃላ ሲሆን በቀጣይ በሚካሄደው 3ኛው የቤልት ኤንድ ሮድ አለም አቀፍ ትብብር መድረክ ላይም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፎቶ፦ #PMOffice

@tikvahethiopia
የእህቱ ልጅ በሆነ የሰባት አመት ህፃን ላይ የግብረሰዶም ወንጀል የፈፀመ ተከሳሽ በፅኑ እስራት መቀጣቱ ተገለጸ።

ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመው በሰኔ ወር 2014 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በተለምዶ ማሪያም ወንዝ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚኖርበት ቤት ውስጥ ነው።

የ37 ዓመት ዕድሜ ያለው ተከሳሹ እና የተከሳሹ እህት በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን ተከሳሹ ሰው የሌለበትን አጋጣሚ ጠብቆ የሰባት ዓመት ዕድሜ ያለው የእህቱን ልጅ በስለት በማስፈራራት የግብረ ሰዶም ወንጀል ፈፅሞበታል።

ፖሊስ በቀረበለት ጥቆማ መነሻነት ተከሳሹን ተከታትሎ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ አስፈላጊ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ በአቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰረትበት አድርጓል፡፡

የተከሳሹን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ጥፋተኝነቱን በማረጋገጥ ሰሞኑን በዋለው ችሎት በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

ወላጆች ልጆቻቸው ለእንደዚህ አይነት ወንጀል ሰለባ እንዳይሆኑ ዕድሜያቸውን መሰረት በማድረግ አስቀድመው በግልፅ መወያየት እና ተገቢውን ክትትልና ጥበቃ ማድረግ እንደሚኖርባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን ያስተላልፏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የትግራይ አካባቢዎች ከፍተኛ የሃዘን ድባብ ውስጥ ናቸው። ጥቅምት 2 በይፋ የታወጀው የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት ተከትሎ የክልሉ ከተሞችና ገጠሮች በከፍተኛ የሃዘን ድባብ ውስጥ ይገኛሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በትግራይ ያለው የሃዘንና የመርዶ ስነ-ሰርአትና ተዛማጅ ጉዳዮች አፈፃፀም በሚከተለው ሪፓርታዥ አጋርቶናል።  ዓርብ ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ በክልሉ…
#ትግራይ

የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ስነ-ሰርዓት ከታወጀ ዛሬ 3ኛ ቀኑ ሲሆን ፤ ሌላ ጊዜ በሳምንታዊ የሰኞ ገበያዋ ከመላ ክልሉ ፣  ከዓፋርና የአማራ ክልል አዋሳኝ አከባቢዎች በመጡ ገበያተኞች ትድምቅ የነበረች መቐለ የንግድ ተቋማትዋ ተዘግተው ፣ መኪኖች መንቀሳቀስ አቁመው ጭር ማለትዋ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል። 

በሌላ በኩል ፤ በውጭ አገራት የሚኖሩ የትግራይ ዳያስፓራ ማህበረሰብ የክልሉ የሰማእታት የሃዘንና የክብር ስነ-ሰርአት በማስመልከት ሃይማኖታዊ ፀሎትና ሌሎች ዝግጅቶች ማከናወናቸውን ያገኘናቸው መረጃዎች ያሳያሉ።

በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ፦
- በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ፣
- በኔዘርላንድ ፣
- በጀርመን ሙኒክና ፍራንክፈርት ከተሞች ፣
- በእንግሊዝ ለንደን፣
- በስዊድን ስቶክሆልም ከተማ ፣
- በአሜሪካ ዋሽንግተን ደሲና አከባቢዋ ፣
- በአረብ አገራትና በሌሎች የሚኖሩ የትግራይ ዳያስፓራ አባላት ሰማእታት የሚዘክር የፀሎት ፣ የሻማ ማብራትና የተለያዩ ስነ-ሰርአቶች አከናውነዋል።

በተያያዘ ዓለም አቀፍ የትግራይ ማሕበረሰብ ሙሁራንና ባለሞያዎች ማህበር (GSTS)  የሰማእታት የሃዝንና የክብር ቀን ስነ-ሰርዓት አስመልክቶ ባወጣው የፅሁፍ መግለጫ የተሰማው ጥልቅ ሃዘን በመገለፅ  ሰማእታቱ የተሰውለት የትግራይ ድህንነትና ግዛታዊ አንድነት እንዲከበር ከመታገል ጎን ለጎን የሰማእታቱ ቤተሰቦች ለማቋቋምና ትግራይ መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩሌ እወጣለሁኝ ብሏል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ከሰሞኑን የባህር በር ጉዳይ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።

ጉዳዩ ክብደት እንዲያገኝ ያደረገው ደግሞ በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ መነሳቱ ነው።

አንዳንዶች ጉዳዩ መነሳቱን እና መነጋገሩን ሲያደንቁ ሌሎች ደግሞ " ጊዜውን የጠበቀ አይደለም ፤ አጀንዳ ለመስጠት ነው ፤ በቅድሚያ የሀገር ሰላምና የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ይቀድማል " በሚል ተቃውመዋል።

ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምንድነው ያሉት ?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የህዝብ እንደራሴዎችን ሰብሰበው የሰጡት ማብራሪያ በቴሌቪዥን ጣቢያዎች ተሰራጭቶ ነበር።

በዚህም የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አንስተዋል።

- ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ፍላጎትን በግልፅ አስቀምጠዋል።

-  የሕዝብ ቁጥሯ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የሄደው እና ከቀይ ባሕር እና ከሕንድ ውቅያኖስ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ሃሳብ የሕልውና ጉዳይ ነው መሆኑን አመልክተዋል።

- ቀይ ባሕር እና አባይ ኢትዮጵያን የሚበይኑ፣ ከኢትዮጵያ የተቆራኙ ለኢትዮጵያ ዕድገት እና ጥፋት መሠረት እንደሆኑ በመግለፅ ከዚህ ርዕሰ ጉዳይ መሸሽ እንደማይስፈልግ ገልጸዋል።

- ለባህር በር መተላለፊያ መገኘት ኤርትራ፣ ጂቡቲ እና ሶማሊላንድ አማራጮች ሊሆኑ እንደሚችሉ በማንሳት ይህ የኢትዮጵያ ፍላጎት ሊሳካባቸው የሚችልባቸውን #ከግጭት_ውጪ ያሉ አማራጮችን አስረድተዋል።

ይህም ፦

የታላቁ ሕዳሴ ግድብን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮ ቴሎኮም ጨምሮ በትልልቅ የአገሪቱ ተቋማት ውስጥ ድርሻ መስጠት እና የመሬት ልውውጥ ማድረግ እንደሚቻል ነው።

- በአጠቃላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ የባህር በር ጉዳይ ከመነጋገር ከመመካከር መሸሽ እንደማያስፈልግ አስገንዝበዋል።

የሰሞኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ነጥሎ ስለ አንድ ሀገር ትኩረት ያላደረገ ቢሆንም ከኢትዮጵያውን አልፎ #ኤርትራውያንም ስለጉዳዩ አስተያየት ሲሰጡበት ተስተውሏል።

አንዳንዶች ስርዓት ባለው መልኩ ቢሰራበት እና እስካሁን ያልተፈቱ ችግሮች ተፈተው መግባባት ላይ ተደርሶ ቢሰራበት መላው ኤርትራውያንን እና ኢትዮጵያውያንን የሚጠቅም ጉዳይ እንደሆነ ሲያነሱ ሌሎች ደግሞ በፍፁም ይህ ጉዳይ ለውይይትም ሆነ ለንግግር ሊቀርብ አይገባም ባይ ናቸው።

ዛሬ ደግሞ የኤርትራ መንግስት ሰሞነኛው አጀንዳ ስለሆነው የውሃና የባህር በር ጉዳይ " ሰም ያልጠቀሰ " አጭር መግለጫ አሰራጭቷል።

የኤርትራ መንግስት ማስታወቂያ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአስመራ ያወጣው ስም ያልጠቀሰው አጭር መገለጫ " በቅርቡ ጊዚያት ስለ ውሃ እና የባህር በር የመሳሰሉ ርእሰ ጉዳዮች የተባለና ' ተብለዋል ' የተባለው መጨበጫ የለውም። ይህም ያላስገረመው ታዛቢም የለም "  ይላል። 

ስም ያልጠቀሰው ይህ አጭር መግለጫ የኤርትራ መንግስት እንደ ሁልግዜው ይህንን ወደ መሰሉ የባህር በር እና ተያያዥ ጉዳይ መድረኮች የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ገልጿል።

" ይህን መሰል ነገር እንደማንታደም ደጋግመን እናረጋግጣለን " ያለው የኤርትራ መንግስት መግለጫ " ሁሉም አስተዋዮች እና ተቆርቋሪዎች በዚህ እዳይቆጡ " ሲል አክለዋል።

መግለጫው በግልፅ ስለ የትኛው አካልና በየትኛው አካል ስለተነሳ ጉዳይ እንዲሁም ስለየትኛው መድረክ እንደሚያወራ ግልፅ ያለው አንዳች ነገር የለም።

@tikvahethiopia
በችሎት ላይ ፤ ዳኞች ፊት 7 ዓመት ሙሉ በትዳር አብራው የኖረችውን ሴት አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በጩቤ ወጋግቶ የገደለው ግለሰብ " እድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል " ይለናል ተከታዩ ከኢቢሲ የተገኘ መረጃ።

ወንጀሉ የተፈፀመው በቀን 21/11/2015 ዓ.ም ረፋድ 5 ሰዓት ላይ ነው።

የተፈፀመበት ቦታ ደግሞ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን የበደኖ ወረዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ውስጥ ሲሆን በአቶ ደረጀ ሰይፉ እና በወ/ሮ ትዕግስት ልኬለው መካከል በፍትሐ ብሔር የተወሰነ #የፍቺ_ሂደት እና #የንብረት_ክፍፍል ውሳኔ አፈፃፀም ሂደትን ለመስማት በተጠራ ችሎት ላይ ነው።

በዕለቱ ተከሳሽ አቶ ደረጀ ሰይፉ ሆን ብሎ እና ተዘጋጅቶበት በብብቱ ስር ይዞ በገባው ጩቤ የቀድሞ ባለቤቱ የነበረችውን ትዕግስት ልኬለውን እዛው ፍርድ ቤት ደጋግሞ በመውጋት በአሰቃቂ ሁኔታ #ገድሏታል

አቃቤ ህግ ተከሳሽ ደረጀ በባለቤቱ ላይ ከፈፀመው የግድያ ወንጀል በተጨማሪ ፦
- በወቅቱ በቁጥጥር ስር ሊያውለው የነበረን የፖሊስ አባል ለመግደል ሙከራ አድርጓል፣
- ችሎትን ተዳፍሯል፣
- የመንግስት ስራን አስተጓጉሏል የሚሉ ክሶችን መስርቶበታል።

ተከሳሽ ደረጀ ከባለቤቱ ትዕግስት ጋር ለ7 ዓመታት በትዳር የቆዩ ቢሆንም በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ፍቺ ለመፈፀም በመስማማት የንብረት ክፍፍል ውሳኔ አፈፃፀምን ለመከታተል በችሎቱ በተገኙበት ወቅት ወንጀሉ መፈፀሙን አቃቤ ህግ አስረድቷል።

ዛሬ በዋለው ችሎት ተከሳሽ የመከላከያ ምስክር እና የቅጣት ማቅለያ እንዲያቀርብ በታዘዘው መሰረት የመከላከያ ምስክር ማቅረብ አለመቻሉ ፤ ከ14 ዓመታ በታች የሆኑ የ4 ልጆች አባት እና አስተዳዳሪ መሆኑን በቅጣት ማቅለያነት አቅርቧል።

ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከሰማ በኋላ ፦
- አንደኛ ባለቤቱ ላይ በፈፀመው የግድያ ወንጀል፣
- ሁለተኛ ተከሳሽ ከዚህ ቀደም የወንጀል ሪከርድ ያለበት በመሆኑ
- ሶስተኛ ወንጀሉን የፈፀመው በችሎት ፊት በመሆኑ አቃቤ ህግ ባቀረበው የእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል።

ይህንን መረጃ ከተመለከቱ በኃላ የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጉዳይ አስደንጋጭ እንደሆነባቸውና ፍርዱ በቂ ነው ብለው እንደማያምኑ ሲገልጹ ተመልክተናል።

- ችሎት ውስጥ እሷ እስልትገደል (ያውም ተደጋግሞ ተወግታ እስክትገደል) ድረስ ፖሊስ ምን ይሰራ ነበር ?
- እሷን እና እሱን አንድ ላይ ካላስቀመጧቸው እንዴት ደርሶ ሊገድላት ይችላል ?
- እዛው ዳኞች ፊት የተፈፀመ ወንጀል ላይ ለመወሰን እስከዛሬ ለምን ቆየ ? የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ፍትህ ካለ በዚህ ወንጀል ገዳይ ብቻ ሳይሆን ይህን መከላከል ያልቻሉ ሁሉ ሊጠየቁ ይገባል ፤ ግለሰቡ የሞት ፍርድ እንጂ እስራት አገባውም ነበር የሚሉ አስተያየቶች ተሰጥተው ተመልክተናል። ቅጣቱ ያበሳጫቸውም ብዙ ናቸው።

@tikvahethiopia