TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#EthioTelecom

ኢትዮ ቴሌኮም የ " ኢ-ሲም " አገልግሎት መጀመሩን ገልጿል።

" ኢ-ሲም " በቀላሉ ከስልክ ቀፎ ጋር በማናበብ ብቻ የሞባይል ስልክ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል አዲስ ቴክኖሎጂ ሲሆን ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ፤ " ቸርችል ጎዳና " በሚገኘው የፕሪሚየም አገልግሎት ማዕከሉ ማግኘት እንደሚቻል አሳውቋል።

በቅርቡ ፤ በሁሉም የአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቹ አገልግሎቱን መስጠት እንደሚጀምር ገልጿል።

የኢ-ሲም አገልግሎት የሚሰጣቸው ጥቅሞች ምንድናቸው ?

- ቀላል እና ብቁ የኔትወርክ ግንኙነት፤

- በአንድ ስልክ ከአንድ በላይ የአገልግሎት ቁጥር መጠቀም የሚያስችል፤

- ሲም ካርድ እየቀያየሩ መጠቀምን ያስቀራል፤

- ላፕቶፕ ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት የመሳሰሉትን በቀላሉ ለማገናኘት ፣ ለአምራቾች፣ አከፋፋዮች እና አገልግሎት ሰጪዎች፣ ለትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች እንዲሁም የተለያዩ ዲጂታል ዲቫይሶችን በቀላሉ በማገናኘት ቀልጣፋ አገልግሎት የማግኘት ፍላጎት ላላቸው ሁሉ የቀረበ መሆኑን ኢትዮ ቴላኮም ገልጿል።

በኢ-ሲም የሚሰሩ ስልኮች የትኞቹ ናቸው ?

#Samsung

📱Samsung Galaxy S20
📱Samsung Galaxy S20+
📱Samsung Galaxy S20 Ultra
📱Samsung Galaxy S21
📱Samsung Galaxy S21+ 5G
📱Samsung Galaxy S21+ Ultra 5G
📱Samsung Galaxy S22
📱Samsung Galaxy S22+
📱Samsung Galaxy Note 20
📱Samsung Galaxy Note 20 Ultra 5G 
📱Samsung Galaxy Fold
📱Samsung Galaxy Z Fold2 5G
📱Samsung Galaxy Z Fold3 5G
📱Samsung Galaxy Z Flip

#iPhone

📱iPhone XR
📱iPhone XS
📱iPhone XS Max
📱iPhone 11
📱iPhone 11 Pro
📱iPhone SE 2 (2020)
📱iPhone 12
📱iPhone 12 Mini
📱iPhone 12 Pro
📱iPhone 12 Pro Max
📱iPhone 13
📱iPhone 13 Mini
📱iPhone 13 Pro
📱iPhone 13 Pro Max
📱iPhone SE 3 (2022)

#Google

📱Google Pixel 3a XL
📱Google Pixel 4
📱Google Pixel 4a
📱Google Pixel 4 XL
📱Google Pixel 5
📱Google Pixel 5a
📱Google Pixel 6
📱Google Pixel 6 Pro.
📱Google Pixel 3 XL
📱Google Pixel 2 XL

#Huawei

📱Huawei P40
📱Huawei P40 Pro
📱Huawei Mate 40 Pro

#Motorola

📱Motorola Razr 2019
📱Nuu Mobile X5
📱Gemini PDA
📱Rakuten Mini

#Oppo

📱Oppo Find X3 Pro
📱Oppo Reno 5A
📱Oppo Reno6 Pro 5G

#eSIM #DigitalSIM #EthioTelecom

@tikvahethiopia
#iPhone #Apple

የአፕል የገበያ ድርሻ ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ በ200 ቢሊዮን ዶላር ቀነሰ።

ከሰሞኑን የቻይና መንግሥት የአፕል ምርት የሆነውን #አይፎንን ማገዱ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ተዘግቧል።

እገዳው ምናልባት ከደህንነት ጋር ሊያይዝ ይችላል ተብሏል።

ይህን እገዳ ተከትሎ የአፕል የገበያ ድርሻ ለ2 ተከታታይ ቀናት ቅናሽ ማሳየቱ ተነግሯል።

የድርጅቱ የድርሻ ገበያ ከ6 በመቶ በላይ የቀነሰ ሲሆን ይህም ማለት በ200 ቢሊዮን ዶላር ባለፉት ሁለት ቀናት ቀንሷል።

ቻይና የአፕል ምርቶች ሦስተኛዋ ትልቁ ገበያ ስትሆን ከዓመታዊ ገቢው 18% የሚገኘውም ከቻይና ገበያ ነው።

ግዙፉ የአፕል ምርቶች አምራች የሆነው ፎክስኮን በርካታ የአፕል ምርቶችን የሚሠራው በቻይና ነው።

ዋል ስትሪት ጆርናል እንደዘገበው የማዕከላዊ ቻይና መንግሥት ሠራተኞች አይፎን ለሥራ እንዳይጠቀሙና መ/ቤት ይዘውም እንዳይሄዱ ታግደዋል።

ብሉምበርግ እንደዘገበው ዕገዳው በመንግሥት የሚተዳደሩ ተቋሞችን እንዲሁም መንግሥት የሚደግፋቸውን ተቋሞችም ይጨምራል።

ስለዘገባዎቹ ከቻይና መንግሥት የተሰጠ ምላሽ የለም።

ይህ በቻይና መንግሥት ይፋ የተደረገው ዕገዳ የተጣለው አይፎን 15 ከመውጣቱ ከ5 ቀናት በፊት ነው።

አፕል የዓለም ትልቁ የስቶክ ገበያ ያለው ሲሆን፣ ገበያው ወደ 2.8 ትሪሊዮን ዶላር ይደርሳል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia