#Mekelle
በጦርነት የተጎዱ የትግራይ ኃይል አባላት በዛሬው ዕለት በመቐለ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።
ሰልፈኞቹ
✔ የ 85ቱ፣ 93 ቱ በ2015 ደገሙት፤
✔ ድምፃችን ይሰማ ፤
✔ ለህዝብ እንጂ ለግለሰብ አልታገልንም፤
✔ ተጠቅመው ጥለውናል፤
✔ መንግሰት ያየ ፍትህ ያየ ፤
የሚሉና ሌሎች መፈክሮች እያሰሙ በመቐለ ዋና ዋና መንገዶች ድምፃቸው አሰምተዋል።
ይህንን ዘገባ እስከተጠናከረበት ድረስ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የተሰጣቸው መልስ የለም።
ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ፓሊስ ስነ-ስርዓት በማስከበር መሳተፉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከቦታው ዘግቧል።
Via @tikvahethiopiatigrigna (መቐለ)
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Mekelle
" መንግስት ያልፈቀደው ሰልፍ የቀሰቀሱና የተሳተፉ ከ49 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል " - ፓሊስ
" ከሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፉ ጋር በተያያዘ ከ150 በላይ ሰዎች በፓሊስ ተደብድበው ታስሯል" - የተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲ አመራር
የመቐለ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ወልዳይ መውጫ ጳጉሜን 2 / 2015 ዓ.ም በከተማው ሮማናት አደባባይ በተፎካካሪ ፓርቲዎች ሊካሄድ የተጠራው ሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፍ በማስመልከት ዛሬ ጳጉሜን 3 ለክልሉ ሚድያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፤ መንግስት ያልፈቀድው ሰልፍ የቀሰቀሱና የተሳተፉ ከ49 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውለናል ብለዋል።
" ሁሉም ሰው ከህግ በታች እንጂ ከህግ በላይ አይደለም " ያሉት የፓሊስ አዛዡ " ፖሊስ መንግሥት ያልፈቀደውን ሰልፍ ማድረግ አትችሉም ብሎ ቢያስጠነቅቅም ፤ ለ20 ደቂቃ ያህል በአምቢተኝነት ከፓሊስ ጋር ለመጋጨት የሞከሩ ነበሩ " ብለዋል።
ፓሊስ ከጳጉሜን 1 /2015 ዓ.ም ረፋድ ጀምሮ በመንግስት ያልተፈቀደው ሰልፍ እንዳይቀሰቅሱና እንዳይመሩ ለተፎካካሪ ፓለቲካ ፓርቲ አመራሮች ምክር መሰጡትንና ፤ ምክሩ ችላ ብለው ከሰዓት በኋላ 10:30 አከባቢ አመራሮቹ ሰልፉ እንዲካሄድ የሚቀሰቅስ ወረቀት ሲለጥፉ እጅ በፈንጅ ተይዘው በቁጥጥር ስር ውለዋል ፤ በተጨማሪ ጳጉሜን 2 / 2015 ዓ.ም ጠዋት ሰልፉ ለማስተባበርና ለመሳተፍ የተገኙ ቀሪ አመራሮች መያዛቸው ገልፀዋል።
ፓሊስ የተሰጠው ህግ የማስከበር ሃላፊነት መሰረት በማድረግ ግርግር ለመፍጠር የሞከሩ በደቂቃዎች በመቆጣጠር የመቐለ ከተማ እንቅስቃሴ ከወትሮ የተለየ የፀጥታ ስጋት እንዳይታይባት ማድረግ መቻሉንና ፤ ህዝቡ ያልተፈቀደውን ሰልፍ ለማደረግ የመኮሩ ጥቂቶች ሰርአት እንዲይዙ የማድረግ ሚናው በመወጣቱ አመስግነዋል።
የውድብ ናፅነት ትግራይ (ውናት ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ አለምሰገድ አረጋይ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለምልልስ በበኩላቸው " ፓሊስ ሰልፉ ለመታደም በመጡ ድብድባ ፤ ማንገላታትና ባጠቃላይ ኢ-ሰብአዊ የሆነ ግፍ ፈፅመዋል " ብለዋል።
" ፓሊስ 50 ሊቀመናብርትና የማእከላይ ኮሚቴ አመራሮች የሚገኙባቸው ከ150 በላይ ሰዎች አስረዋል " ያሉት አቶ አለምሰገድ ፤ የዓረና ሉአላውነትና ለዴሞክራሲ ሊቀመንበር ዓምዶም ገ/ስላሴ ፣ የባይቶና ግዚያዊ አስተዳዳሪ ኪዳነ አመነ ከታሳሪዎች መካከል ናቸው ብለዋል።
" ይህን መሰል አፈና ሊቆም የሚችለው ገዢው ፓርቲ ህወሓት ከስልጣኑ ሲነሳ ነው " ያሉት አመራሩ ህዝቡ ትግሉ አጠናክሮ እንዲቀጥል መልእክት አስተላልፈዋል።
የግዚያው አስተዳደሩ ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጳጉሜን 1/2015 ዓ.ም ለሚድያዎች በሰጡት ሰፊ ቃለመጠይቅ "... ሰልፍ ማድረግ መብት ነው : ቢሆንም በክልሉ ካለው ከባድ የፀጥታ ስጋት አንፃር ስልፉ ማካሄድ አስቸጋሪ ነው " ማለታቸው ይታወሳል።
መረጃውን የመቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው ያደረሰን።