TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#SifanHassen

ብርቱና ጠንካራዋ አትሌት ሲፋን ሀሰን በቡዳፔስት በምን ያህል ርቀቶች ተካፈለች ? ምን ውጤት አስመዘገበች ?

አትሌት ሲፋን ሀሰን ፦

🇳🇱 1,500 ሜትር ማጣርያ
🇳🇱 10,000 ሜትር ፍፃሜ
🇳🇱 1,500 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ
🇳🇱 1,500 ሜትር ፍፃሜ
🇳🇱 5,000 ሜትር ማጣሪያ
🇳🇱 5,000 ሜትር ፍፃሜ ሮጣለች።

አትሌቷ በድምሩ በሁሉም ውድድር 24,500 ሜትር ሮጣለች።

ከተሳተፈችባቸው ውድድሮች በ1,500 ሜትር የነሃስ እንዲሁም በ5,000 ሜትር የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። በ10000 ሜትር ፍፃሜ ውድድሩን ለመጨረስ ጥቂት ሲቀራት ወድቃ ድል ሳይቀናት ቀርቷል።

ሲፋን ከዚህ በፊት በቶኪዮ ኦሎምፒክ በ1,500 ሜትር ፣ 5,000 ሜትር እና 10,000 ሜትር ርቀቶች ላይ በመሮጥ ሁለት ወርቅ እና አንድ ነሀስ አሳክታ ነበር።

በርካቶች የአትሌት ሲፋን ሀሰን ብርታ እና ጥንካሬን ፣ ለማሸነፍ ያላትን ከፍተኛ ፍላጎት እና ጥረት እያወደሱ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

የወንዶች ማራቶን ውድድር በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በታምራት ቶላ ፣ ፀጋዬ ጌታቸው ፣ ልዑል ገ/ስላሴ እና ሚልኬሳ መንገሻ ተወክላለች።

ከሀገራችን አትሌቶች አሁን ላይ ወደፊት መውጣት የቻለው አትሌት ልዑል ገብረስላሴ ብቻ ሲሆን ከኡጋንዳ አትሌት ጋር ባለድል ለመሆን እየተፋለም ነው።

ታምራት ቶላ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

1 ሰዓት ከ53 ደቂቃ መሮጥ ችለዋል።

@tikvahethsport    
ኢትዮጵያ በልዑል ገብረስላሴ የነሃስ ሜዳሊያ አገኘች❤️

🥇የኡጋንዳው አትሌት ኪፕላንጋት በአንደኛ ደረጃ አጠናቋል። 🇺🇬

🥈አትሌት ማሩ ተፈሪ ከእስራኤል ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ጨርሷል። 🇮🇱

🥉የሀገራችን ልጅ ልዑል ገብረ ስላሴ ሶስተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል። 🇪🇹

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ በልዑል ገብረስላሴ የነሃስ ሜዳሊያ አገኘች❤️ 🥇የኡጋንዳው አትሌት ኪፕላንጋት በአንደኛ ደረጃ አጠናቋል። 🇺🇬 🥈አትሌት ማሩ ተፈሪ ከእስራኤል ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ጨርሷል። 🇮🇱 🥉የሀገራችን ልጅ ልዑል ገብረ ስላሴ ሶስተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል። 🇪🇹 @tikvahethiopia
ፎቶ፦ በወንዶች ማራቶን ውድድር አትሌት ልዑል ገብረ ስላሴ 3ኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ለሀገሩ የነሃስ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

ሌሎች ኢትዮጵያውያን ፤ አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ 6ኛ ፣ አትሌት ፀጋዬ ጌታቸው 17ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

የባለፈው አመት የዓለም ሻምፒዮን ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምራት ቶላ ውድድሩን አቋርጧል።

አትሌት ታምራት ውድድሩን ለማቋረጥ የተገደደው ባጋጠመው ከባድ የጨጓራ ህመም ምክንያት እንደሆነ ለ " ልዩ ስፖርት " ተናግሯል።

በስፍራው የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ስፖርት ባልደረባ አትሌቶች በቡዳፔስት ያለውን ከፍተኛ ሙቀት መቋቋም አቅቷቸው ሲወድቁ እንደነበር ገልጿል።

ከውድድሩ ፍፃሜ በኃላ የተነሱ ፎቶዎችን ከላይ ይመልከቱ።

#ማስታወሻ ፦ ዛሬ ምሽት 3000ሜ መሰናክል ሴቶች ፍፃሜ እና 5000 ወንዶች ፍፃሜ ይካሄዳል።

@tikvahethiopia
#MoE

የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን ከአሁን በኋላ በካድሬነት ሳይሆን በብቃታቸው ብቻ እንደሚመረጡ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ይህንን ያለው ነሐሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 30ኛውን ዓለም አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ምን አሉ ?

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" የትምህርት ቤቶች አስተዳዳሪዎች ከአሁን በኋላ የሚመረጡት በካድሬነት ሳይሆን፣ ባላቸው ብቃትና ችሎታቸው ላይ መሠረት ተደርጎ ይሆናል።

በዚህ መሠረት በአገር አቀፍ ደረጃ በብቃታቸውና በችሎታቸው የተመዘኑ 1,600 የትምህርት አስተዳዳሪዎች ሥልጠና ተሰጥቷቸዋል። ይህ ዓይነቱ አሠራር ቀጣይነት ይኖረዋል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሳደግ ሥራ በተጨማሪ የመምህራንና ርዕሳነ መምህራን ብቃትና ችሎታ ማጎልበት ትኩረት ተሰጥቶበታል፡፡

ትኩረት ካገኙ መሠረታዊ ጉዳዮች ትምህርት ቤቶችን በግብዓትና በጥራት ከማሻሻል ባሻገር ክህሎት፣ ብቃትና ችሎታ ባላቸው ርዕሳነ መምህራን እንዲተዳደሩ ማድረግ ትልቁን ድርሻ ይይዛል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻል በተጨማሪ በዕውቀት ተማሪዎቻቸውን ተወዳዳሪ ማድረግ የሚችሉ መምህራንን ማብቃት ከተያዙ ግቦች መካከል አንዱ ነው።

ባለፉት 30 ዓመታት የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ጥራት ወርዷል ፤ በኑሮ ለተሻሉ ደግሞ የግል ትምህርት ቤቶች የሚማሩበት ሥርዓት ተዘርግቷል።

ይህ ዓይነት አካሄድ በዜጎች መካከል በኑሮ ደረጃ ከተፈጠሩ ልዩነቶች አልፎ በትምህርት ዘርፍ ላይ መታየቱ ትልቅ ክስረት ነው። ይህ አካሄድ በአገር አቀፍ ደረጃ አደገኛ ሁኔታዎች የሚፈጥር ነው ፤ በየትኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በገንዘብ ዕጦት ሳቢያ የትምህርት ጥራት ሊጓደልባቸው አይገባም።

ትምህርት የአገር የሉዓላዊነት እሴት መለኪያ ነው ፤ በዚህ ጉዳይ ለዓመታት የተቀለደበት ዘርፍ ነው አሁን እርስ በርስ መነጋገር የማይቻልበት ሁኔታ ላይ መደረሱ የችግሩ ማሳያ ነው።

የትምህርት ዘርፍ መሠረታዊ መርሆዎች ሁለት ናቸው ፤ ዜጎች በብሔራቸውና በሃይማኖታቸው ሳይታዩ እኩል ጥራት ያለው ትምህርት የማግኘት መብታቸውን ማረጋገጥ አንደኛው ነው።

የትኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች ከሁሉም እኩል ተወዳዳሪና ተፎካካሪ የሚሆኑበትን የትምህርት ሥርዓት በመዘርጋት፣ አሁን ያለውን የኢፍትሐዊነት ችግር በዘላቂነት መፍታት ይቻላል።

በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉ ከአሥር ዓመታት በኋላ ትምህርት ቤቶች እንደ አሁኑ የፀብ (የረብሻ) መፍለቂያ ሳይሆኑ የመወዳደሪያና የብቃት ማጎልበቻ ይሆናሉ፡፡

ከዚህ በኋላ እንደ ከዚህ ቀደሙ ዲግሪ እንደ ከረሜላ የሚታደልበትን አሠራር አስቀርቶ፣ በብቃት እና በችሎታ ብቻ ዜጎች ማዕረግ የሚያገኙበት ሥርዓት በዘላቂነት ይዘረጋል። "

Via Reporter Newspaper

@tikvahethiopia