TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" ቲክቶክ " ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ አቤቱታ ቀረበ።

የኬንያ ፓርላማ " #ቲክቶክ " የተሰኘው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ እንዲያግድ አቤቱታ እንደቀረበለት የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

" ወጣቶች ትምህርታቸውን ትተው የ 'ቲክቶክ' ቁራኛና የአዕምሮ ህመምተኛ እየሆኑ ነው " የሚለው አቤቱታው ፓርላማው አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቋል።

የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዋታንጉላ፣ " ሁከትን እና የጥላቻ ንግግርን የሚያበረታቱ " እና " የብልግና " እና " መረን የለቀቀ ጾታዊ ይዘት " ያላቸው የ " ቲክቶክ " ተንቀሳቃሽ ምስሎች " በኬንያ ባሕላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች ላይ አደጋ ደቅነዋል" በማለት አቤቱታውን ደግፈው መናገራቸው ተዘግቧል።

የኬንያ ፓርላማ በአቤቱታው ላይ ውሳኔ ባይሰጥም ፤ የመጀመሪያ ውይይት ግን እንዳደረገበት ተጠቁሟል።

ኬንያ በአፍሪካ በቲክቶክ ተጠቃሚዎች ብዛት ቀዳሚ ናት።

Credit : WazemaRadio
Video Credit : Citizen TV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቲክቶክ " ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ አቤቱታ ቀረበ። የኬንያ ፓርላማ " #ቲክቶክ " የተሰኘው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ እንዲያግድ አቤቱታ እንደቀረበለት የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። " ወጣቶች ትምህርታቸውን ትተው የ 'ቲክቶክ' ቁራኛና የአዕምሮ ህመምተኛ እየሆኑ ነው " የሚለው አቤቱታው ፓርላማው አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቋል። የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዋታንጉላ፣ " ሁከትን እና የጥላቻ ንግግርን…
#ቲክቶክ

የኬንያ ፓርላማ " ቲክቶክ ይታገድ " የሚል አቤቱታ ከቀረበለት በኃላ የፓርላማው አፈጉባኤ በቲክቶክ " ሁከትንና የጥላቻ ንግግርና የሚያበረታቱ እንዲሁም የብልግና እና መረርን የለቀቁ ፆታዊ ይዘት ያላቸው ቪድዮዎች እየተሰራጩ ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች ላይ አደጋ ደቅነዋል የሚለውን ሃሳባቸውን የተመለከቱ በርካታ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት " የኢትዮጵያ ሁኔታስ ? " በሚል አስተያየታቸውን በመልዕክት መቀበያ ልከዋል።

እንዚህ አስተያየቶች መተግበሪያው በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ፦
- በከፍተኛ ደረጃ ወጣቱን የመተግበሪያው ሱሰኛ በማድረግ ፤
- ተማሪዎችን በማዘናጋት ፤
- በብሄር፣ በሃይማኖት ጥላቻ ስድብ እንዲበራከት
- የብልግና ንግግሮች እንዲስፋፉና እንዲለመዱ በማድረግ፣
- በእርዳታ ስም ማጭበርበሮች እንዲስፋፉ
- ከምንም በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ በህግም በሃይማኖትም ፍፁም አፀያፊ የሆነውን የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት እንዲስፋፋ በማድረግ በአንፃሩን ይህን የሚቃወሙ ወጣቶችን ከመተግበሪያው በማውረድ በሀገሪቱ ባህል እና ሃይማኖት ላይ ከፍተኛ አደጋ መደቀኑን አንስተዋል።

በአንፃሩ ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች መተግበሪያው የራሱ ጉድለቶች ቢኖሩትም ፦
- በርካታ ወጣቶች በመተግበሪያው ገንዘብ እንዲያገኙ በማድረግ ህይወታቸውን እንዲቀይሩ ፣
- ችሎታ ያላቸው ችሎታቸውን እንዲያጎለብቱና እንዲያስተዋውቁ በማድረግ፤
- ሚዲያ ያላገኙ ወጣቶች በአንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ብቻ ብዙሃን ጋር እንዲደርሱ በማድረግ
- የታመሙ እንዲረዱ ፤ የተቸገሩ ወገኖች እንዲደረስላቸው ፣
- ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለወገናቸው ፣ ግድ የሚሰጣቸው ወጣቶች ድምፃቸው እንዲሰማ በማድረግ፣
- ፖለቲከኞች ፣አክቲቪስቶች የኔ የሚሉትን ወገን እንዲያነቁና ስለ ወቅታዊ ሁኔታ እንዲገነዘቡ በማድረግ፣
- በድካም የዛሉ ሰዎች በአሥቅኝ ቪድዮችን እንዲዝናኑ፣
- የውይይት ባህል፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ልምድ እንዲጎለብት በማድረግ
- ሃሳብ ኖሯቸው ተደራሽ ያልሆኑ ወጣቶችን በቀሉ በማስተዋወቅ ከፍተኛ በጎ አስተዋውፆ ማድረጉን አንስተዋል።

ይህን አስተያየቶች ከተመለከትን በኃላ ብዙሃኑ የመተግበሪያው ተጠቃሚ ምን ይላል ? ያሚለውን በግልፅ በይፋዊ መንገድ ለማወቅ Poll ያዘጋጀን ሲሆን ከታች ይለጠፋል👇

@tikvahethiopia
" ቲክቶክ " የተሰኘው ማህበራዊ ሚዲያ በሀገራችን ኢትዮጵያ ጥላቻን ፣ ሁከትን ፣ ብልግናን ፣ ከባህልና ሀይማኖት ያፈነገጡ ድርጊቶችን እንዲስፋፉ እያደረገ ነው ብለው ያስባሉ ? ወይስ ሰዎች እንዲተጋገዙ ፣ ባህልና ሃይማኖት እንዲጠነክር ፣ የመረዳዳት ባህል እንዲጎለበት ፣ ሃሳብን በነፃነት መግለፅ እንዲለመድ እያደረገ ይገኛል ብለው ያስባሉ ?
Anonymous Poll
74%
ጥላቻና ሁከት፣ እርስ በእርስ አለመከባበር ፣ ብልግና ፣ ከባህል እና ሃይማኖት ያፈነገጡ ድርጊቶች እንዲስፋፉ እያደረገ ነው።
26%
እርስ በእርስ የመረዳዳት ባህል እንዲጎለበት ፣ ባህልና ሃይማኖት እንዲጠነክር ፣ ሰላምና ፍቅር፣ መከባበር እንዲስፋፋ እያደረገ ነው።
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አሁን

የነባሩ ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን በወልቂጤ እያደረገ ነው።

ነባሩ ክልል ስያሜውን ወደ " ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " የሚለውጥ ሲሆን ፦
- ህገ መንግስት ማሻሻያ ረቂቅ ሰነድን መርምሮ ማፅደቅ፣
- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ ረቂቅ አዋጅ ቀርቦ ውይይት በማድረግ ማፅደቅ
- ልዩ ልዩ ሹመቶችን መስጠት የምክር ቤቱ ዋና ዋና አጀንዳዎች መሆናቸውን የደ/ሬ/ቴ/ድ ዘግቧል።

ከነባሩ ክልል / ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጋር ተያይዞ የተቋማት መቀመጫዎች ጉዳይ የሰሞኑን አነጋጋሪ ጉዳይ እንደነበር ይታወሳል።

በተለይም በከምባታ ጠምባሮ ዞን በኩሉ ድልድሉ ፍትሐዊ አይደለም በሚል ተቃውሞ ተነስቶ ነበር። ከምስርታው ጉባኤ በፊት በህዝቡ ዘንድ ለተነሱ ቅሬታዎች ምላሽ እንዲሰጥ ተጠይቆ ነበር።

የዞን ምክር ቤቱም ድልድል የሠራው የጋራ ኮሚቴ በፍትሐዊነት የቢሮዎች ምደባን አላደረገም በሚል የፍትሃዊነት ጥያቄ ያነሳ ሲሆን በክፍፍሉ ጉዳይ የፌዴራሉ አካል ጣልቃ እንዲገባ በመስማማት ይህንን የሚጠይቅ ደብዳቤ በፅሁፍ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስገብቷል።

በሌላ በኩል ፤ 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል ለመደራጀት በተስማሙት መሠረት አዲሱ የ " ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል " የምስረታ ጉባኤ በጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ፎቶ ፦ ደ/ሬ/ቴ/ድ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እገዳው ተራዘመ። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከርን እስከ እሮብ ነሐሴ 3/2015 ዓ.ም ማገዱ ይታወቃል። ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት እግዱ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን አሳውቋል። ክልከላው የፀጥታና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን የማያካትት ሲሆን ፤ የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እግዱ እሰኪነሳ በትዕግስት እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። ይህንን…
#AddisAbaba

ምክንያቱ በግልፅ ይፋ ባልተደረገበት " ላልተወሰነ ጊዜ " የታገዱ በሞተር ስራ የሚተዳደሩ ዜጎች ቅሬታቸውን ገለፁ።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከርን መጀመሪያ እስከ ነሐሴ 3/2015 ዓ.ም ማገዱ ፤ ከዛም በኃላ እግዱ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳል።

በከተማዋ ሞተር ለምን እንደታገደ በቢሮው በኩል እስካሁን የተሰጠ ማብራሪያም ይሁን ገለፃ የለም።

በሞተር በመንቀሳቀስ ስራ ተሰማርተው የሚገኙ በርካታ ወጣቶች እገዳው በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ በመሆኑ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ቃላቸውን የላኩ በዚህ ስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ፤ " የአዲስ አበባ ሞተር ሳይክሎች እገዳ እስከመቼ ነው የሚቀጥለው ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

በሞተር ተንቀሳቅሶ በሚሰራ ስራ ከራሳቸው አልፎ ቤተሰብ እያስተዳደሩ እንደነበር የገለፁት ሞተረኞቹ በእገዳው ምክንያት ስራ ለማጣትና የዕለት ጉርሳቸውን ለማጣት መገደዳቸውን አመልከተዋል።

" በሞተር ሳይክል በተገቢው እና ህጋዊ መንገድ ስራቸውን የሚሰሩ ወጣቶች እንዳሉ ሁሉ ዝርፊያና የቅሚያ ወንጀል የሚፈፅሙና ህጋዊ ያልሆኑ አሉ ይህን መንግስት ጠንካራ ህግና ደንብ አውጥቶ የመቆጣጠር ግዴታ አለበት፤ እርምጃም ይውሰድ " ብለዋል።

ሞተረኞቹ የተጣለው እገዳ ብዙ ወጣቶችን ወደ ስራ አጥነት እያስገባ መሆኑን በመረዳት እና በርካታ የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ላይ ጫና እያዳደረ በመሆኑ በአስችኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
  
@tikvahethiopia
#ሰላም

" እርቅ ይውረድ ! የሰው ደም መፍሰስ ይብቃ ! ሰላም ይታወጅ ! ምድሪቱንም እናሳርፋት ! " - ቅዱስነታቸው

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ አባታዊ የሰላም ጥሪ አቅርበዋል።

ቅዱስነታቸው ካስተለለፉት መልዕክት የተወሰደ ፦

" ከአካላዊ ጦርነት እስከ ቃላት ውርወራ ብዙ ጥላሸት የመቀባባት ሰለባ ሆነው የወደቁት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ልጆቻችን ትምህርት ሆነውን ልባችን ዘንበል ባለማለቱ ለወደፊት ሊመጣ የሚችለው ሲታሰብ እጅግ ያስፈራልና በዐራቱም ማዕዘን ነፍጥ አንሥታችሁ ያላችሁ በሙሉ ያነገባችሁትን ገዳይ መሣርያ አውርዳችሁ ለሰላምና ለዕርቅ ቅድሚያ በመስጠት ለአንዲት አገራችሁ ሕልውና ተገዢዎች እንድትሆኑ፤ መንግሥትም ልበ ሰፊ ሁኖ ሁሉንም ለውይይት እንዲሰበስብ በጽኑ እንለምናለን።

በኢትዮጵያ ምድር ላይ ያላችሁ ሽማግሌዎች ሽምግልናችሁ ለዚህ ቀን ካልሆነ ለመቼም አይሆንምና በአገሩም ሽማግሌ የለም ወይ? መባሉ በሰማይ በምድር ያስወቅሳልና ልጆቻችሁን እንድትመክሩና እንድታስታርቁ ከዛሬ ጀምሮም ለሰላም ጠበቆች ሁናችሁ እንድትቆሙ አበክረን እንጠይቃለን።

በውጭ አገር የምትኖሩም #እናንተ_በሰላም_አገር_እየኖራችሁ ዘመዶቻችሁ በእሳት ሲጠበሱ ዝም ብሎ ማየት ስለማይገባ እስከአሁን ስታደርጉት እንደቆያችሁት ሁሉ አሁንም ለሰላሙ ብርቱ ጥረት እንድታደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

በተጨማሪም ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ግጭት ባለባቸው አከባቢዎች ሰላም እንዲሰፍን የበኩላቸውን ጥረትና እገዛ እንዲያደርጉ፣ ቤተ ክርስቲያንን የምንመራ ውሉደ ክህነትም መፍትሔ መሆን ሲገባን የችግሩ አካል ሆነዋል እየተባልን ነውና ውስጣችንን አጥርተን ለወገኖቻችን በአስታራቂነት ለመድረስ ጊዜው አሁን ስለሆነ ዛሬ እንድንነሣሣ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን። "

ቅዱስነታቸው ዛሬ ባወጡት አባታዊ የሰላም ጥሪ ፤ " አሁን ያለው ችግር ወደ ቀጣይ አመት እንዳይሻገር ገትተነው ቀጣዩን አዲስ ዓመት በሰላም ለመቀበል እንችል ዘንድ ከጉልበት ሳይሆን ከልብ ሽብረክ በማለት እርቅ ይውረድ ! የሰው ደም መፍሰስ ይብቃ ! ሰላም ይታወጅ ! ምድሪቱንም እናሳርፋት ! " በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA #UAE

የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ / UAE ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ መግባታቸው ተሰምቷል።

ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል ተብሏል።

በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከተለያዩ የመንግስት የስራ ኃፊዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው ነው፤ ከዚህ ቀደም የአቡዳቢ አልጋ ወራሽ በነበሩትበት ወቅት በ2018 በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው ነበር።

መረጃው አልአይን ኒውስ ነው።
Photo : PM Office Ethiopia

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ፖሊስ ከቡሄ በዓል ጋር በተያያዘ ርችት መተኮስ ክልክል ነው አለ።
  
የቡሄ በዓልን ምክንያት በማድረግ በየአካባቢው በሚከናወነው የችቦ ማብራት ስነ ስርዓት ወቅት ርችት መተኮስ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ፖሊስ ፤ የፀጥታ ስራውን በአግባቡ ለመምራት እና ለመቆጣጠር  እንዲሁም  አጋጣሚውን በመጠቀም ሊፈፀሙ የሚችሉ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል ሲባል ርችት መተኮስ መከልከሉን አመልክቷል።

@tikvahethiopia
በአቢሲንያ ባንክ ደሞዝ ለሚከፈላቸው ሰራተኞች ደሞዝ ባይደርስም ደሞዛቸውን ቀድመው መበደር የሚችሉበት አስደሳች ዕድል ከአቢሲንያ ባንክ! የአፖሎ የሞባይል መተግበርያን አሁኑኑ ያውርዱ!

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

#Apollodigitalbank
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
መጣና ባመቱ፥
ኧረ እንደምን ሰነበቱ

ክረምቱ አልፎ ወደ ብርሃን መሻገራችንን በሚያበስረው፤ በህጻናት ውብ ዜማ እና የጅራፍ ድምጽ የሚደምቀው ቡሄ ሌላ ድምቀት የሆነውን ቡሄ የሞባይል ጥቅል በ20% ቅናሽ እንዲሁም በቴሌብር ከ10% ስጦታ ጋር ለራስዎ ይግዙ፤ በስጦታ ያበርክቱ!

እንዲሁ እንዳለን አይለየን!
ለዓመቱ በሰላም ያድርሰን!

መልካም ቡሄ!

(ኢትዮ ቴሌኮም)