TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
"... የ2ኛው ዓመት የውሃ ሙሌት #ነሃሴ መጨረሻ ላይ ይጠናቀቃል" -ኢንጅነር ጌዲዮን አስፋው

የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪና የባለሙያዎች ቡድን ሰብሳቢ ኢ/ር ጌዲዮን አስፋው ለኢዜአ በሰጡት ቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት እየተከናወነ ያለው ሶስቱ አገሮች በፈረሙት የመርህ ስምምነት መሰረት መሆኑን አሳውቀዋል።

ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን እ.ኤ.አ. በ2015 በመሪዎቻቸው አማካኝነት በሱዳን ካርቱም የህዳሴ ግድቡን ድርድር አስመልክቶ የመርሆች ስምምነት ተፈራርመዋል።

የመርህ ስምምነቱ አስር አንቀጾችን ያካተተ ሲሆን የሶስቱንም አገሮች ፍትሃዊና ምክንያታዊ የውሃ አጠቃቀም ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም ኢትዮጵያ ፣ ግብጽ እና ሱዳን በተስማሙት የመርህ ስምምነት መሰረት ሁለተኛው ዙር የግድቡ የውሃ ሙሌት እየተከናወነ ኢንጅነር ጌዲዮን አስፋው ገልፀዋል።

በታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ላይ የሶስቱ አገሮች ባለሙያዎች የተስማሙባቸው ነጥቦች የተቀመጡ መሆኑን አስታውሰው አገሮቹ በዚሁ መሰረት መስማማታቸውን አስረድተዋል።

ግብጽና ሱዳን በመርሆች ስምምነት ውስጥ ሁለት ጥናቶች እንዲካሄዱ የሚያስቀምጥ ቢሆንም ግብጽ እና ሱዳን ጥናቱ እንዳይካሄድ ሲያስተጓጉሉ ነበር ብለዋል።

አገሮቹ ስምምነቱን ከተፈራረሙ በ15 ወር ውስጥ ሁለት (2) ጥናቶችን ማከናወን እንዳለባቸው ቢያስቀምጥም ጥናቶቹ እንዳይካሄዱ ግብጽና ሱዳን በያዙት ግትር አቋም ሳይሳካ ቀርቷል ነው ያሉት።

አለም አቀፉ ማህበረሰብ ግብጽ እንዲሁም ሱዳን የግድቡን ውሃ ሙሌት በተመለከተ የሚሰጡትን የተዛባ መረጃ ሊመረምር እንደሚገባም ገልጸዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/ENA-07-07

#ኢዜአ

@tikvahethiopia