" የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ቀጣዩን ድርድር በማፋጠን ህዝቡ ለተጠማው #ሰላም ቅድሚ ሊሰጡ ይገባል " - ኦፌኮ
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) በ2014 ዓ.ም 2ተኛ ጠቅላላ ጉባኤን አካሂዷል፤ በመደበኛ ስብሰባውም የተለያዩ ነጥቦችን የያዘ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
በዚህም ፦
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በኦሮሚያን ጨምሮ በአጠቃላይ በመላው ሀገሪቱ እየሞከረ ያለውን እርቅና ድርድር በመርህ ይደግፋል ብሏል።
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 5 ዓመታት በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነሰ) መካከል የተፈጠረው ጦርነት መነሻው ፖለቲካዊ አለመግባባት በመሆኑ በሰሜን ኢትዮጵያ እንደተደረገው ጦርነት ሁሉ በሰላም እና በእርቅ እንዲቆም ደጋግሞ ጥሪ ማቅረቡን ኦፌኮ አስታውሷል።
በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በሰላማዊ መንገድ ድርድር መጀመራቸውን በደስታ እንደሚቀበል የገለፀው ፓርቲው የሁለቱ ወገኖች የመጀመሪያው ዙር ድርድር መጠናቀቁን ተከትሎ ቀጣዩ ድርድር በማፋጠን ህዝቡ ለተጠማው ሰላም ቅድሚ እንዲሰጡ አሳስቧል።
የሰላም ድርድሩ ከተኩስ አቁም ስምምነት ባለፈ የኦሮሞን ህዝብ በሚመለከቱ ውስብስብ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ቀሪ የኦሮሞ የፖለቲካ ሃይሎችን ማሳተፍ እንዳለበት መረዳት ያስፈልጋልም ሲል አስገንዝቧል።
ከዚህ ባለፈ ኦፌኮ ፤ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የመንግስት ታጣቂዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ እያደረሱ ያለው ህገወጥ ግድያ እስራትና ንብረት ማውደም፤ እንዲሁም በፓርቲው ደጋፊዎች፣ አባላት እና አመራሮች ላይ እየደረሰ ያለው እስራት ፣ ግድያ፣ ደብዛማጥፋት በአፋጣኝ እንዲቆም ጠይቋል።
በተለያዩ ስም የመንግስት ካድሬዎች ያለ ደረሰኝ የሚሰበሰብ ገንዘብ እንዲቆም፤ ከመንግስት እና ከገዢ ፓርቲው ጋር ግንኙነት ያላቸው ቡድኖች ህገ ወጥ ንግድን ቁጥጥር እንዲደረግበትም ኦፌኮ ጠይቋል።
ሌላው ኦፌኮ በመግለጫው የዋጋ ንረትን በተመለከተ ያነሳ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የዋጋ ንረት በህዝብና በኢኮኖሚ ላይ ላደረሰው ጉዳት ገዢው ፓርቲ ሙሉ ኃላፊነት ሊወስድ ይገባል ብሏል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የዋጋ ንረት በገዢው ብልፅግና ፓርቲ የተሳሳተ ውሳኔ ምክንያት መሆኑን ፓርቲው (ኦፌኮ) ገልጿል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የግንቦት 2015 ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤ ባለ 10 ነጥብ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል። ዛሬ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጥቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ ምን አለ ? ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያኗ አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት እና መንፈሳዊ ዕድገት ትኩረት በመስጠት ለቤተ ክርስቲያናን እና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን ማሳለፉን አሳውቋል።…
#ሰላም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ግጭቶች እና አለመግባባቶች በውይይት ይፈቱ ዘንድ የሰላም ጥሪ አቀረበች።
ይህን ጥሪ ያቀረበችው የ2015 ዓ/ም የግንቦት ርክበ ካህናት ጉባኤ መጠናቀቁን ተከትሎ ትላንት በሰጠችው መግለጫ ነው።
ቤተክርስቲያኗ በሀገራችን በአንዳንድ ቦታዎች የሚታዩትን አላስፈላጊ ግጭቶች የዜጐች መፈናቀል፣ ስደት ተወግዶ ሁሉም ዜጋ በሀገሩ በእኩልነት፣ በሰላምና በፍቅር ተከባብሮ በአንድነት እንዲኖር፤ ለማድረግ ግጭቶችና አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ የሰላም ጥሪ አስተላልፋለች።
ከዚህ በተጨማሪ ፤ ቤተክርስቲያኗ በመላው ዓለም ጦርነት ባለባቸው ሀገራት ሁሉ ሰላም እና ዕርቅ እንዲሰፍን ተመኝታለች።