TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ነዳጅ
የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በሁለት ቀናት 43 ሺህ የኤሌክትሮኒክ የነዳጅ የግብይት ልውውጥ መካሄዱን አሳወቀ።
ሚኒስቴሩ ይህን ያሳወቀው ለብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ / ኢብኮ በሰጠው ቃል ነው።
ሚኒስቴሩ ምን አለ ?
- በ2 ቀናት ብቻ 43 ሺህ የኤሌክትሮኒክ የነዳጅ የግብይት ልውውጥ ተካሂዷል። በዚህም 80 ሚሊዮን ብር የሚሆን ሽያጭ ተካሂዷል።
- አፈፃፀሙ ከቀን ወደ ቀን መሻሻሎች እየታዩበት ነው።
- ለዝግጅት የተሰጠውን ጊዜ በአግባቡ ባለመጠቀም ከነዳጅ ማደያ ቀጂዎች በኩል የመተግበሪያው አጠቃቀም ውስነት፣ የሰው ሀይል ቁጥር ማነስ እና አንዳንድ አሽከርካሪዎች መተግበሪያው ሳይኖራቸው ለአገልግሎት መቅረባቸው ፤ የአገልግሎት አሰጣጡ እንዲስተጓጎልና ሰልፍ እንዲፈጠር አድርጓል። አሁን ላይ አፈፃፀሙ ከቀን ወደ ቀን መሻሻሎች እየታዩበት ነው።
- አንዳንድ አሽከርካሪዎች በቂ ነዳጅ እያላቸው የክፍያ ስርዓቱ በቴክኖሎጂ መደገፉን ተከትሎ በመደናገጥ የመሰለፍ ሁኔታ በግንዛቤ እጥረት የተፈጠረ በመሆኑ እርምት ሊወሰድበት ይገባል።
- ነዳጅ የሚገዙት እና የሚሸጡት አካላት ልምድ እያገኙ ሲሄዱ በአንድ ሳምንት ውስጥ ችግሩ ይቀረፋል።
- ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ በክልሎች ጭምር የነዳጅ ግብይቱ በኤሌክትሮኒክስ መካሄድ ይጀመራል። አሁን ያጋጠሙ ችግሮች እንዳይደገሙ ከወዲሁ ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በሰፊው እየተሰራ ነው።
#የንግድ_እና_ቀጠናዊ_ትስስር_ሚኒስቴር
@tikvahethiopia

⛽️ " አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ሆነ ብለው የነዳጅ ዕጥረት ያጋጠመ ለማስመሰል መሞከራቸውን በክትትል ደርሼበተለሁ " - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን
⛽️ " ከአዲሱ የዲጂታል ስርዓት ጋር በተያያዘ የተሽከርካሪዎቻቸውን የነዳጅ ታንከር #በመሙላት፣ ግዥ የሚፈጸሙ አሽከርካሪዎች ለነዳጅ እጥረት መንስዔ እየሆኑ ነው " - የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ሆነ ብለው የነዳጅ ዕጥረት ያጋጠመ ለማስመሰል መሞከራቸውን በክትትል ደርሼበታለሁ አለ።
" በሀገር ውስጥ በቂ የነዳጅ አቅርቦት አለ " የሚለው ባለስልጣን መ/ቤቱ ይህ እየታወቀ የነዳጅ ዕጥረት ይከሰታል የሚሉ አዋኪ መልዕክቶች ሆነ ተብለው የሚነዙ መሆኑን ሕብረተሰቡ ይገንዘብ ሲል አሳስቧል፡፡
በቀጣይ በነዳጅ ማደያዎች ላይ የአገልግሎት አሰጣጥ መዘግየት እና ዕጥረት መፍጠርን የመሳሰሉ ችግሮች በሚፈጥሩ አካላት ላይ ክትትል በማድረግ አስተማሪ እርምጃ እወስዳለሁ ሲልም አስጠንቅቋል።
በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ፤ ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም የሚያስችል አካውንት ካለመክፈት ጋር የተያያዘ እንጅ የነዳጅ ዕጥረት አይደለም ሲል አሳውቋል።
የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር ፥ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጠው ቃል ፤ ከአዲሱ የዲጂታል ስርዓት ጋር በተያያዘ የተሽከርካሪዎቻቸውን የነዳጅ ታንከር #በመሙላት፣ ግዥ የሚፈጸሙ አሽከርካሪዎች ለነዳጅ እጥረት መንስዔ እየሆኑ ነው ብሏል።
አሁንም ቢሆን ወደ ዲጂታል የግብይት ሥርዓቱ የማስገባቱ ሥራ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሊፈጠር የሚችለውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ ተጨማሪ የነዳጅ አቅርቦት ያስፈልጋል ብሏል።
የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር ፥
" አሁን የሚታየው መጨናነቅ የተወሰኑ ቀናት ሊቀጥል የሚችል ቢሆንም እንኳን መጨናነቁን ለማስቀረት የግድ መንግሥት በቂ ነዳጅ ወደ ከተማው እንዲገባ ማድረግ ይገባዋል " ያለ ሲሆን " ይህንን ካላደረገ ዕድሉን አግኝተው ነዳጅ የሚቀዱ ተገልጋዮች፣ ከፍላጎታቸው በላይ እየቀዱ የሚቀጥሉ ስለሚሆን የነዳጅ አቅርቦቱ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል " ብሏል።

#እንድታውቁት
በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የተደረገው የዲጅታል የነዳጅ ግብይት ከነገ ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ #በመላ_ሀገሪቱ ተግባራዊ መደረግ ይጀምራል።
ነገ በመላው ሀገሪቱ በሚጀምረው የዲጂታል የነዳጅ ግብይት በሁሉም ክልሎች ያሉ ነዳጅ ማደያዎች ቅድመ ዝግጅት ሲያደርጉ ነበር።
የዲጂታል ነዳጅ ግብይት ከነገ ጀምሮ በሁሉም ተሽከርካሪዎች እና በሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ ይሆናል።
እንዴት በዲጂታል መንገድ የነዳጅ ግብይት ማካሄድ ይቻላል ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ አብሯቸው ከሚሰራቸው ኢትዮ ቴሌኮም / ቴሌብር ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ኤግል ላይን ቴክኖሎጂ / ነዳጅ / በኩል የነዳጅ ግብይቱን በተመለከተ ተከታዩን መልዕክት ያስተላልፋል።
#ቴሌብር
- በቴሌ ብር ነዳጅ ለመቅዳት ወደ ነዳጅ ማደያ ስትሄዱ በቅድሚያ ፤ የቴሌብር ሱፐርአፕን ከ onelink.to/75zfa5 በማውረድ ወይም *127# በመደወል የቴሌብር አካውንት በቀላሉ ክፈቱ፤
- ከቴሌብር ጋር በተሳሰሩ 20 ባንኮች ከሚገኝ የባንክ አካውንታችሁ፤ በየነዳጅ ማደያዎቹ በተመደቡ የቴሌብር ወኪሎች ወይም የአገልግሎት ማዕከሎች አማካኝነት ገንዘብ ወደ ቴሌብር አካውንትዎ ማስተላለፍ ይችላሉ፤
- የነዳጅ ማደያ ሠራተኞች ስልክ ቁጥርና የሚከፍሉትን የገንዘብ መጠን ሞልተው ሲጨርሱ በስልክዎ በሚደርስዎ የማረጋገጫ መልዕክት ላይ የገንዘብ መጠኑ ትክክል መሆኑን በማየት የሚስጥር ቁጥር ማስገቢያ ሳጥኑ ውስጥ የሚስጥር ቁጥር (ፒን) በማስገባት ያረጋግጡ፡፡
በመጨረሻም ክፍያው መፈጸሙን የሚያረጋግጥ አጭር መልዕክት የሚደርስዎ ሲሆን ከቴሌብር ሱፐርአፕም ደረሰኝ ማግኘት ይችላሉ፡፡
#ነዳጅ_መተግበሪያ
በነዳጅ ከነገ ጀመሮ በመላ ሐገሪቱ በሚገኙ 1100 በላይ የነዳጅ ማድያዎች ነዳጆን መቅዳት ይችላሉ።
- አንድ ጌዜ በሲቢኢ ሞባይል ባንኪንግ አካውንቶን Link አርገው የሚጠቀሙበት፤
- በነዳጅ STANDBY( ፈጣን) ፈጣን አግልግሎት የሚያገኙበት ነው።
ከPLAY STORE እና APP STORE አውርደው ፣ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ ፦
For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj
For iOS:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926
#CBE_BIRR
በሲቢኢ ብር ነዳጅ ሲቀዱ ሁለት አማራጮች አሉ።
የመጀመሪያው ፦
ራስዎ ወደ ሲቢኢ ብር መተግበሪያዎ ‘Quick Pay’ በመግባት ‘Fuel Payment’ የሚለውን የአገልግሎት አማራጭ መርጠው አስፈላጊውን መረጃ በማስገባት ክፍያ ፈጽመው ነዳጅ የሚቀዱበት ነው፡፡
ሁለተኛው ፦
ለነዳጅ ቀጂ ባለሙያው ሲቢኢ ብር የተመዘገቡበትን ስልክ ቁጥር ߹ የሰሌዳ ቁጥርዎን እና የሚቀዱትን ነዳጅ የገንዘብ መጠን አሳውቀው በሚደርስዎት አጭር መልእክት መሠረት የገንዘብ መጠኑን ትክክለኛነት አረጋግጠው ክፍያውን በመፈፀም ነዳጅ የሚቀዱበት አማራጭ ነው።
የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለመጫን ወይም ለማዘመን ፦
ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
ለአፕል ስልኮች ፦
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

የነዳጅ ግብይት #በመላው_ሀገሪቱ በ " ዲጅታል " መንገድ ብቻ እንዲሆን በተላለፈው ውሳኔ መሰረት ዛሬ ግንቦት 1/2015 ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።
በክልሎች የነዳጅ ጉዳይ ከተነሳ አይቀር ...
በክልል ከተሞች ላይ #ነዳጅ በተለይም ቤንዚን እንደልብ ማግኘት የማይታሰብ ነው። ነዳጅ ሲገኝም ለሰዓታት ረጃጅም ሰልፍ መሳለፍ እና መንገላታት አይቀሬ ነው።
እንደ #ሀዋሳ ያሉ ትልቅ ከተሞች ውስጥ ነዳጅ በወረፋ ብቻ ሳይሆን በሳምንት ለተወሰነ ቀን ብቻ ነው መቅዳት የሚቻለው (ለከተማው ነዋሪ - በኩፖን) ። ይህም የሚከናወነው በታርጋ " #ሙሉ እና #ጎዶሎ ቁጥር " ነው የሚከናወነው። ማደያዎችም ከተመደበላቸው ተሽከርካሪ ውጭ ማስተናገድ አይችሉም።
" እንግዳ ነኝ ፤ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ አይደለሁም " ለሚሉት ደግሞ የነዳጅ ማደያዎች የሚኖሩበትን ከተማ የነዋሪ #መታወቂያ በማየት እንደሚቀዱ ለመረዳት ተችሏል።
ከምንም በላይ የሚገርመው እጅግ በርካታ ማደያዎች ባሉበትና አሁንም እየተሰሩባት ባለው ከኢትዮጵያ ግዙፍ ከተሞች አንዷ ሀዋሳ በየዕለቱ ነዳጅ የሚሸጡት እጅግ ውስን ቁጥር ያላቸው ማደያዎች ናቸው።
ይህ በእንዲህ እያለ ግን በከተማው ነዳጅ በጥቁር ገበያ ከፍ ባለ ብር እንደጉድ ነው የሚቸበቸበው። ሀዋሳ ብቻ ሳይሆን በሀዋሳ ዙሪያ ጭምር ነው ይህ የሚሆነው።
የከተማው የአስተዳደር አካላት ይህንን እያወቁ መፍትሄ እየሰጡ እንዳልሆነ ከተገልጋዮች ቅሬታ ይቀርባል።
እጅግ በጣም ብዙ ተሽከርካሪዎች በሌሉበት እና በርካታ ማደያዎች ባሉበት ከተማ ነዳጅ ለማግኘት በዚህ ደረጃ መቸገር ከምን የመጣ ነው ?
ከሰሞኑን በሀዋሳ ከተማ ስላለው የነዳጅ ግብይት ጉዳይ የሲዳማ ክልል ንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ በድሶ አዲሳ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።
ምን አሉ ?
አቶ በድሶ አዲሳ ፦
" ችግሩ አለ ፤ ይህ የሆነው በቀን ከ3 ሚሊዮን ሊትር የማይበልጥ ቤንዚን ስለሚቀርብ በአገር ደረጃ የቤንዚን እጥረት በመኖሩ ነው።
ለዚህም ሲባል ተሸከርካሪዎችን በየቀኑ በተለያዩ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች መድበን ነው እንዲቀዱ የምናደርገው።
ችግሩ ያለው ቤንዚን ላይ ነው የነዳጅ ማደያዎችም ቤንዚን ለማግኘት አንድ ወር ይጠብቃሉ።
ነዳጅ በጥቁር ገበያ ሀዋሳ ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባም ይሸጣል ፤ ለዚህ ተብሎ ከሌላ ቦታ የሚገባ ነዳጅ አለ።
እንደዚህ ዓይነት ተግባር የሚፈጽሙ የተወሰኑ ማደያዎች መኖራቸው ታውቆም እርምጃ የተወሰደባቸው አሉ።
ግብይቱ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ሲሆን ችግሩ ይቀረፋል። "
ነዳጅ ለማግኘት የመቸገር ጉዳይ በሀዋሳ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሻሸመኔ፣ በሌሎችም ከተሞች ያለ ጉዳይ ነው።
እንደ ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን መረጃ ከሆነ " በሀገር ውስጥ በቂ የሆነ የነዳጅ አቅርቦት አለ " ነገር ግን በክልል ከተሞች ያለው ነዳጅ ለማግኘት የመቸገር ጉዳይና የጥቁር ገበያው ነገር መፍትሄ የሚያሻው ነው።
@tikvah_eth_BOT @tikvahethiopia