TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Tigray

በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመረ የሁሉም ክልል ፕሬዜዳንቶችን ጨምሮ የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችን ያቀፈ ልዑክ ትግራይ ይገኛል።

ይኸው ልዑክ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ፋብሪካዎች በአካል ተመልክቷል።

የልዑክ ቡድኑ ሰማያታ የእምነበረድ እና ሼባ ሌዘር ኢንድስትሪ የቆዳ ፋብሪካን የደረሰባቸውን ከፍተኛ ውድመት እንዲመለከቱት ተደርጓል።

በተለይ ሼባ ሌዘር 100% ውድመት የደረሰበት መሆኑና ተጠግኖ እንኳን ስራ ላይ የሚውል ንብረት እንዳይቀር ተደርጎ መውደሙ ይታወቃል።

1200  ሰራተኞች የነበሩት ሸባ ሌዘር ውድመቱን ተከትሎ ሰራተኛው ደመወዝ አጥቶ ፣ ተቸግሮ ተፈናቅሏል።

በተመሳሳይ ሰማያት እምነበረድ ፋብሪካ እጅግ ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት ፋብሪካ ነው።

ከዚህ ቀደም ፥ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን አመራሮች የሸባ ሌዘር እና ሰማያት አምነበረድ ፋብሪካዎችን ከጎበኙ በኃላ የደረሰው ውድመት ሙሉ በሙሉ 100% መሆኑና ሌላ አዲስ ማሽን ካልመጣ በስተቀር አንድም ተጠግኖ ስራ ላይ የሚውል አንድ ብሎ እንኳን እንዳልቀረ መግለፃቸው አይዘነጋም።

ፎቶ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በታንዛኒያው የ " ሰላም ንግግር " ላይ እነማን እየተሳተፉ ነው ? በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለው) መካከል ትላንት የሰላም ንግግር በታንዛኒያ ከፊል ራስ ገዟ ዛንዚባር ተጀምሯል። ኢጋድ ይሄ የሰላም ንግግር ወደ ፖለቲካ ስምምነት እንደሚያመራ ተስፋ እንዳለው በቃል አቀባዩ በኩል ገልጿል። ለመሆኑ የታንዛኒያ የሰላም ንግግር ተሳታፊዎች / ተደራዳሪዎቹ እነማን…
#Update

በታንዛኒያ እየተካሄደ የሚገኘው የመንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ኦነግ ሸኔ እያለ የሚጠራው) የሰላም ንግግር ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።

ቢቢሲ ለድርድሩ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች አገኘሁት ባለው መረጃ ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ልዩነታቸውን በሰላም ለመቋጨት በሚያደርጉት ውይይት #ኬንያ እና #ኖርዌይ በዋነኛ የአሸማጋይነት ሚና እየተጫወቱ እንደሆነ ገልጿል።

እየተካሄደ ባለው ውይይት አጀንዳዎችን የመቅረጽ ውይይቶች እየተካሄዱ እንደሆነም ተነግሯል።

ማክሰኞ የጀመረው ውይይት በሳምንቱ መጨረሻ ይጠናቀቃል የሚል ዕቅድ ተይዞ እንደነበር የተሰማ ቢሆንም ሊራዘም እንደሚችል ቢቢሲ ከስፍራው ዘግቧል።

ለውይይቱ መራዘም በዋነኝነት በኦሮሚያ ክልል ያሉ ጥያቄዎች በጣም ውስብስብ እና በቀላሉ እልባት ሊደረስባቸው ስለማይችሉም እንደሆነ ተመላክቷል።

እስካሁን ሁለቱ ወገኖች ውይይቱ እንደሚካሄድ ከመናገር ውጪ ዝርዝር መረጃዎችን ያልሰጡ ሲሆን ውይይቱ እየተካሄደበት ያለችው ዛንዚባር አስተዳደሮች ዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል።

የዛንዚባር ባለሥልጣናት ውይይቱ እየተካሄደ እንደሆነ ቢያረጋግጡም የድርድሩ አካል እንዳልሆኑ እና ከአዘጋጅነት የዘለለ ሚና እንደሌላቸው አመልክተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከትግራይ ክልል ወደ አዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ክልል የሚደረገው የየብስ ትራንስፖርት ዛሬ በይፋ መጀመሩ ተገልጿል።

ይህ የተገለፀው ፦
👉 የአማራ ክልል የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን
👉 የአፋር ክልል የትራንስፖርት እና መንገድ ቢቶ
👉 የፌዴራል የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።

የአማራ ክልል የትራንፖርት እና የሎጀስቲክስ ባለስልጣን ምን አለ ?

- በአማራ ክልል አቅጣጫ ዛሬ 4ኛ ቀኑን የያዘ የሕዝብ ትራንስፓርት የሙከራ ጉዞ  ወደ አዲስ አበባ ተደርጓል።

- ሶስት (3) የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች በአማራ ክልል በኩል ጉዞ አድርገዋል።

- ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ ይፋዊ ጉዞ ጀምሯል።

- የአማራ ክልል መንግሥት ለማንኛውም የትራንፓርት እና ሰላማዊ እንቅስቃሴ ድጋፍ ያደርጋል።

- የክልሉ ሕዝብ ለሰላማዊ እንቅስቃሴ በጎ አመለካከት ያለው በመኾኑ ጉዞው ላይ ችግር አያጋጥምም።

የአፋር ክልል የትራንፖርት እና መንገድ ቢሮ ምን አለ ?

- በአፋር ክልል በኩል በመጀመሪያው ቀን ብቻ ሁለት የሙከራ ጉዞዎች የተደረጉ ሲሆን ትራንስፖርት ከተጀመረ ዛሬ 6 ቀናት ተቆጥረዋል።

-  ክልሉ ማንኛውም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሰላማዊ እንዲኾን ያግዛል።  መንግሥት ብቻ ሳይኾን ሕዝቡም ሰላማዊ አንቅስቃሴውን ይደግፋል።

- ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ ይፋዊ የየብስ ትራንፖርት ጀምሯል።

የትራንፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ምን አለ ?

- ተቋርጦ የነበረው የየብስ ትራንፖርትን ለማስጀመር ሁለት የጥናት ቡድን በአማራ ክልል በኩል እና በአፋር ክልል በኩል በመላክ ጥናት ተደርጓል።

- በሁለቱም ክልሎች በኩል 19 የሙከራ ጉዞዎች ከአዲሰ አበባ ትግራይ ክልል እና ከትግራይ ክልል አዲስ አበባ ተደርጓል።

- ከዛሬ ጀምሮ  ይፋዊ የየብስ ትራንስፖርት ተጀምሯል።

የትግራይ ክልል የትራንፖርት ቢሮ ኀላፊዎች በአየር ትራንፖርት #መዘግየት ምክንያት በአዲስ አበባ በተሰጠው የጋራ መግለጫ ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል።

#አሚኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና  ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡

ፈተናው ልክ እንደባለፈው አመት በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ የፈተና ችግሮችን ዘርዝረው ለቀጣዩ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ2015 ዓ.ም ፈተናን ለማስፈፀም ልዩ ልዩ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑንና የተፈታኞች መረጃ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን  አብራርተዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍና አመለካከቱን ለመቀየር፣ ብቁና አገር ተረካቢ ትዉልድ ለመፍጠር አሁን ያለው ባለድርሻ አካል ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ በአንክሮ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በ2016 ዓ.ም የሚካሄደው ፈተና እንደአካባቢው ሁኔታ ኦን ላይን እንደሚሆን ገልጸው የእለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡

ምንጭ፦ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@tikvahethiopia
አቶ ግርማ የሺጥላ ተገደሉ።

የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ዛሬ በሰሜን ሸዋ " መሀል ሜዳ " ላይ በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል።

የአቶ ግርማን ግድያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል። " ብለዋል።

ዶ/ር ዐቢይ የግድያውን ሁኔታ በተመለከተ #ዝርዝር_መረጃ ባይሰጡም " ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባህል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳብ የተለየንን ሁሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሣት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው " ሲሉ ገልጸውታል።

" ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ፣ ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች የፈጸሙት አስነዋሪና አሰቃቂ ተግባር፣ ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው። " ሲሉ አክለዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ ግርማ የሺጥላ ተገደሉ። የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ዛሬ በሰሜን ሸዋ " መሀል ሜዳ " ላይ በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል። የአቶ ግርማን ግድያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል። " ብለዋል። ዶ/ር ዐቢይ የግድያውን ሁኔታ በተመለከተ #ዝርዝር_መረጃ…
" አቶ ግርማ የሺጥላን ጨምሮ አምስት ሰዎች ተገድለዋል " - የአማራ ክልል መንግስት

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ባወጣው የሀዘን መግለጫ በአቶ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈፀመው ግድያ ዛሬ ከሰዓት በኋላ፤ የመንግሥትና የድርጅት ሥራዎችን ሠርተው ከመሃል ሜዳ ወደ ደብረ ብርሃን ሲመለሱ በመንዝ ጓሳ ላይ መሆኑንና ግድያው የተፈፀመው በታጠቁ ኢ-መደበኛ ኃይሎች እንደሆነ ገልጿል።

ከእሳቸው በተጨማሪ በግል ጥበቃዎቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ላይ ጥቃት መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን እስካሁን #የአምስት_ሰዎች ሕይወት ስለማለፉ መረጃው እንደደረሰው ክልሉ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

ክልሉ በመግለጫው፥ "ይህንን የሽብር ሥራ እየሠሩ ያሉ እንዲህ አይነት ኃይሎች ላይ የክልሉ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል፡፡ የጥቃቱን አድራሾችም ለሕግ ያቀርባል " ብሏል።

አክሎም፥ "የጥፋት ኃይሎች ከዚህ በላይ ዓላማ ያላቸው እና ክልሉን የማፍረስ ተልዕኮ ይዘው የሚንቀሳቀሱ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በኋላ የክልሉ መንግሥት እንደማይታገስ እና ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ እናረጋግጣለን " ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia