TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray
በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ከዚህ ቀደም ህወሓት የከባድ መሳሪያ ትጥቅ እንደፈታና ለሀገር መከላከያ እንዳስረከበ መነገሩ ይታወሳል።
ትላንት ደግሞ መካከለኛ እና ቀላል የቡድን መሳሪያዎችን በመፍታት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እንዳስረከበ ተነግሯል።
ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ተወካይ ኮሎኔል ጉደታ ኦፍካ ምን አሉ ?
" በሶስተኛ ዙር የመሳሪያ ርክክብ ሞርታር ዲሽቃ መሰል በርካታ የቡድን መሳሪያዎችን ተረክበናል።
ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ነው የሚገኘው ፤ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በትግራይ ክልል ባለው መንግሥት ከፍተኛ የትብብር መንፈስ ነው ያለው። ጥሩ ሂደት ነው ያለው ማለት ይቻላል። "
የትግራይ ኃይሎች ተወካይ ኮሎኔል ሙልጌታ ገብረክርስቶስ ምን አሉ ?
" በተደረገው የሰላም ስምምነት መሰረት ትጥቅ የማውረድ ስራ እየተሰራ ነው።
ባለፈው ከባድ መሳሪያዎችን አስረክበናል። አሁን ደግሞ መካከለኛ እና ቀላል የቡድን መሳሪያዎችን የማስረከብ ስራ ጀምረናል።
ስራው ጥሩ ነው፤ በተፋጠነ መልኩ እየሄደ ነው። በሁለቱም ኃይላት በኩል ተግባብቶ የመስራት ሂዘት ጥሩ እየሄደ ነው። "
በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነትን ተከትሎ የትጥቅ መፍታት ሂደትን የአፍሪካ ህብረት የክትትል እና ቁጥጥር ኮሚሽን በማቋቋም እየተከታተለው ይገኛል።
ከላይ የተገለፁት ሁለቱ ተወካዮችም የዚሁ ኮሚሽን አካል ናቸው።
ፎቶ፦ ENA
@tikvahethiopia

ፎቶ፦ ዛሬ የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ " ፊቼ ጫምበላላ " በዓል በሀዋሳ ጉዱማሌ በመከበር ላይ ይገኛል።
Photo Credit : EBC
@tikvahethiopia
Photo Credit : EBC
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
ሱዳን ውስጥ የነበሩ የግብፅ ወታደሮች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ።
የሱዳን ጦር 177 የግብፅ የአየር ኃይል ወታደሮች ወደ ግብፅ መወሰዳቸውን አስታውቋል።
የሱዳን ጦር ባወጣው መግለጫ የግብፅ ወታደሮቹ በአራት የግብፅ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ከሰሜናዊቷ ዶንጎላ ከተማ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል።
ጦሩ ፤ ግብፃውያኑ ሱዳን የነበሩት የጋራ የአየር ሃይል ልምምድ ለማድረግ እንደነበር አመልክቷል።
የግብፅ ጦር የሰራዊት አባላቱ ሱዳንን ለቀው ስለመውጣታቸውን እስካሁን በይፋ ባያሳውቅም ሱዳን ያሉ ወታደሮቹን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ከሱዳን ባለስልጣናት ጋር በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጾ ነበር።
የሱዳን ጦር አሁን መመለሳቸውን የገለፃቸው የግብፅ ወታደሮች ከቀናት በፊት በRSF የተያዙትን እንዳልሆነና በRSF ስር ያሉት 28 ወታደሮች መሆናቸውንና አሁንም በነሱ እጅ እንደሚገኙ ገልጿል።
ትላንት ምሽት ግን የሱዳን ጦር ወደ ግብፅ የተወሰዱት በRSF የተያዙት / የታሰሩ ወታደሮች መሆናቸውን ገልጾ መግለጫ አውጥቶ ነበር ፤ ይህንን መግለጫም ዋቢ በማድረግ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎችን ሰርተው ነበር።
ጦሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የትላንቱ መግለጫው ትክክለኛ እንዳልሆነ አመልክታል። የተያዙት / የታሰሩት በሚል የገባው ቃል ሳይታወቅ በስህተት ነው ብሏል።
አሁን ወደ ግብፅ እንዲመለሱ የተደረጉት ወታደሮች ግጭቱ በተቀሰቀሰበት ወቅት ማራዊ ውስጥ የነበሩ ነገር ግን ከኤርፖርት ውጭ ስለነበሩ በRSF ያልተያዙ ናቸው ሲል አስረድቷል።
የሱዳን ውጊያ በተጀመረበት ወቅት በጄነራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሄሜቲ) የሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሻ (RSF) ሜሮዌ ላይ የግብፅ ወታደሮችን #መማረኩን ማሳወቁ ይታወሳል።
ከቀናት በፊት የግብፁ ፕሬዜዳንት አብድል ፈታህ አል ሲሲ ሱዳን ውስጥ የተያዙት የግብጽ ወታደሮች፣ በዚያ የተገኙት ከሱዳን አቻዎቻቸው ጋራ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ እንጂ ፤ የትኛውንም ወገን ለመደገፍ አለመኾኑን ገልጸዋል።
ይህንን የገለፁት ከግብጽ ከፍተኛ ወታደራዊ ም/ቤት ጋር ስብሰባ በተቀመጡበት ወቅት ሲሆን የወታደሮቹን ደህንነት በተመለከተ ከRSF ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን አስታውቀዋል።

የሱዳን ውጊያ 6ኛ ቀኑን ይዟል።
በተዋጊዎቹ ኃይሎች መካከል ለ2ኛ ጊዜ ትላንት የ24 ሰዓታት ለሰብዓዊት ተኩስ ለማቆም ሙከራ ተደርጎ የነበር ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቶ ውጊያው ቀጥሎ እንደነበር ተሰምቷል።
የተኩስ አቁም እንዲደረግ የተሞከረው ዜጎቻቸውን ከሱዳን ለማስወጣት እየጣሩ ባሉ ሀገራት ግፊት መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል።
ዛሬም በሱዳን የተለያዩ ከተሞች ውጊያ መኖሩ በተለይ በካርቱም የፕሬዜዳንቱ ቤተመንግስት እና የሱዳን ጦር ዋና መስሪያ ቤት አካባቢ ወታደራዊ ግጭት መኖሩ ተመላክቷል።
በርካቶች ያለምግብ፣ውሃ፣ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቤታቸው ውስጥ ዘግተው እንደተቀመጡ ይገኛሉ።
በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቤታቸውን ጥለው ከካርቱም እየሸሹ እንደሚገኙ ተነግሯል።

የሱዳን ውጊያ 6ኛ ቀኑን ይዟል። በተዋጊዎቹ ኃይሎች መካከል ለ2ኛ ጊዜ ትላንት የ24 ሰዓታት ለሰብዓዊት ተኩስ ለማቆም ሙከራ ተደርጎ የነበር ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቶ ውጊያው ቀጥሎ እንደነበር ተሰምቷል። የተኩስ አቁም እንዲደረግ የተሞከረው ዜጎቻቸውን ከሱዳን ለማስወጣት እየጣሩ ባሉ ሀገራት ግፊት መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል። ዛሬም በሱዳን የተለያዩ ከተሞች ውጊያ መኖሩ በተለይ በካርቱም የፕሬዜዳንቱ ቤተመንግስት…
#ሱዳን
" ቤተሰቦቻችን ስላሉበት ሁኔታ ለማወቅ አልቻልንም ፤ጭንቀት ላይ ነን "
በሱዳን እየተካሄደ ያለው ውጊያ ዛሬ 6ኛ ቀኑን መያዙ ይታወቃል።
በሱዳን ያሉ ቤተሰቦቻችን ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ ካርቱም ወዳለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስልክ ብንደውልም ምላሽ አላገኘንም ሲሉ እዚህ ኢትዮጵያ የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መልዕክት ልከዋል።
በሱዳን ያሉ ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ባለመቻላቸው እንደተጨነቁ የገለፁት እንዚሁ አባላት ፤ ማንን መጠየቅ እንዳለብን ግራ ገብቶናል ይህ ጉዳይ የሚመለከተው አካል ምላሽ ሊሰጠን ይገባል ብለዋል።
ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ሁለተኛ ቤት በሆነችው ሱዳን ውስጥ ኢትዮጵያውያን ለስራ እና በቋሚነት ለኑሮ እንደሚገኙ ይታወቃል።
የሰሞኑ የሱዳን ውጊያ ደግሞ እዛ ያሉትን ብቻ ሳይሆን እዚህ ያሉ ቤተሰቦችንም ጭምር ጭንቀት ውስጥ ጥሏል።
ከትላንት በስቲያ በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፤ በሱዳን እየተካሄደ ባለው ውጊያ በርካታ ሲቪሎች ለጉዳት መዳረጋቸውና ህይወትም እየተቀጠፈ መሆኑን በመግለፅ ከእነዚህ መካከል #ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙበት መረጃዎች እንደደረሱት አሳውቋል።
ኤምባሲው ምን ያህል ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ እና እንደተጎዱ በዝርዝር ባይገልፅም ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ለማለፍ ኢትዮጵያዊን የተቻላቸውን ሁሉ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
መረጃ ለመለዋወጥ እና ለምክክር የኤምባሲው ባልደረባ የሆኑትን አቶ ነጅብ አብደላ በስልክ ቁጥር +249911646547 ማነጋገር እንደሚቻልም ገልጿል።

የዒድ አልፈጥር በዓል መቼ ነው ?
የፌዴራል ጠቅላይ ሼሪዓ ፍርድ ቤት ፥ የዒድ አልፈጥር በዓል ጨረቃ ዛሬ ሀሙስ ማታ ከታየች ነገ አርብ ፣ ካልታየች ደግሞ ቅዳሜ ይከበራል ሲል አሳውቋል።
ይህን ያሳወቀው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።
1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ፤ ለኢትዮጵያና ለመላው ዓለም ህብረተሰብ የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞቱን የገለፀው ሼሪዓ ፍርድ ቤቱ ሙስሊሙ ህብረተሰብ በዓሉን ሲያከብር ያጡና የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብና በመርዳት እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል።
#ኤፍቢሲ

RSF የግብፅ ወታደሮችን ለቀይ መስቀል አስረከበ።
የሱዳን ጦርነት በጀመረበት ወቅት በጄነራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ የሚመራው የሱዳን ፋጥኖ ደራሽ (RSF) ኃይል እንደማረካቸው የገለፃቸውን የግብፅ ወታደሮችን ዛሬ ጥዋት ለዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ማስረከቡን አሳውቋል።
RSF ለቀይ መስቀል ያስረከባቸው የግብፅ ወታደሮች በማራዊ ጦር ሰፈር የነበሩና ላለፉት 5 ቀናት ይዞ ያቆያቸው ናቸው ፤ በቁጥርም 27 እንደሆኑ ተነግሯል።
የሱዳን ጦር በማራዊ ከኤርፖርት ውጭ የነበሩና በRSF ያልተያዙ በቁጥር 177 የግብፅ አየር ኃይል አባላትን ወደ ግብፅ እንዲመለሱ ማደረጉን ማሳወቁ ይታወሳል።