TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.2K photos
1.58K videos
216 files
4.31K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጥንቃቄ

የወገኖቻንን ህይወት እየቀጠፈ ፤ ንብረትም እያወደመ ያለው የጎርፍ አደጋ !

በያዝነው ክረምት በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በጎርፍ አደጋ የወገኖቻችን ህይወት እያለፈ ንብረትም እየወደመ ነው።

ለአብነት በአዲስ አበባ በተለያየ ጊዜ ህፃናት በጎርፍ አደጋ ህይወታቸው አልፏል ንብረት ወድሟል፣ በአማራ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች በደረሰ የጎርፍ አደጋ የሰው ህይወት ጠፍቷል ፣ የአርሶ አደሮች ንብረትም እንዳልነበር ሆኗል።

ከትላንት በስቲያ ደግሞ ከወደ ኦሮሚያ ክልል፣ ጅማ ዞን ማና ወረዳ ሃሮ ቀበሌ እንደተሰማው የአንድ ቤተሰብ አባላትን የሆኑ ወገኖቻችን በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸው አልፏል።

ከወረዳዋ ከተማ የቡ ተነስተው ሃሮ ወደተባለች ቀበሌ 3 ልጆቻቸውን ይዘው ሲጓዙ የነበሩ ቤተሰብ አንድ የ13 ዓመት እና ህጻን ልጅ በደራሽ ጎርፍ ሲወሰዱ አንድ ታዳጊ በህይወት ማግኘት ተችሏል።

በጎርፉ ከተወሰዱት የቤተሰብ አባላቱ የአባት አስከሬን በዕለቱ ሲገኝ፤ የሟች እናትና ሁለት ልጆች አስከሬን ትላንት ጠዋት ተገኝቷል።

የቤተሰብ አባላቱ ፤ በጎርፉ የተወሰዱት ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ ወደ ስፍራው ሲያቀኑ በነበረበት መሆኑን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ የወረዳውን ኮሚኒኬሽን ዋቢ አደርጎ ዘግቧል።

በአማራ ክልል በአምባሰል ወረዳ ወገኖቻችን በጎርፍ አደጋ እና በመሬት መንሸራተት ከቤታቸው ተፈናቅለዋል ፤ ንብረታቸው ወድሟል።

በአጠቃላይ 150 አባወራዎች እና እማወራዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በትምህርት ቤቶች፣ በቀበሌ ማዕከል፣ በገበሬ ማሰልጠኛዎችና በዘመድ ቤት ተጠልለው ይገኛሉ ብለዋል።

በወረዳው በቂ ለድጋፍ የሚሆን ሐብት ባለመኖሩ ለተጎጅዎች የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከሰሞኑን በአፋር ክልል በጎርፍ አደጋ የወገኖቻችን ህይወት ጠፍቷል ፤ ወገኖቻችን ተፈናቅለዋል፤ ከፍተኛ የሀብት ጥፋትም ደርሷል።

በሠመራ ከተማ ብቻ ጎርፍ ባስከተለው አደጋ በትንሹ የሶስት ሰዎች #ህይወት_አልፏል

በኤሊደአር  ወረዳ  ዶቢ ቀበሌ ደግሞ በጎርፍ አደጋ ከ3 መቶ ሺ ኩንታል በላይ የጨው ምርት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

በአካባቢው ላይ ከ300 በላይ የሚሆኑ ባለሀብቶች በጨው ምርት ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን አሁን ላይ ሁለት መቶ  የሚሆኑት አምራቾች በጎርፉ ምክንያት ኪሳራ ደርሶባቸዋል።

በተጨማሪም ጨው ለማምረት ተዘጋጅተው የነበሩ የጨው ማምረቻ ቦታወችም በጎርፉ ምክንያት ተበላሽተዋል።

አንድ አምራች የምርት ቦታዎችን ለማዘጋጀት ከ200 ሺ ብር በላይ ሊያወጣ ይችላል የተባለ ሲሆን ባጠቃላይ አምራቾች ላይ የደረሰው ኪሳራ ቀላል ሊባል የሚችል አይደለም።

በተጨማሪም ፤ በአሳይታና አፋምቦ ወረዳ ወገኖቻችን በአዋሽ ወንዝ ሙላት ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቤት እና ንብረቶቻቸው ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አሳይታ በርጋ ቀበሌ የሚኖሩ ወገኖቻችን በጎርፍ አደጋ እንስሳቶቻቸው ሞተውባቸዋል፣ ቤታቸው እንዳልነበር ሆኗል ፣ ሁለት ሺህ ሄክታር መሬት እርሻ ላይ ጉዳት አድርሶባቸዋል።

በአሁን ሰዓት ከቤታቸው ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ ናቸው።

የመንግስት፣ ማህበራዊ አገልግሎት ሚሰጡ ተቋማት በውሃ ውስጥ ናቸው ያሉት።

በተመሳሳይ ፤ በአፋምቦ ወረዳ ወገኖቻችን በአዋሽ ወንዝ ሙላትና በከባንድ ዝናብ ሳቢያ ቤት ንብረታቸው በጎርፍ አደጋ እንዳልነበር ሆኗል እነሱም ተፈናቅለዋል ፤ እንስሳቶቻቸው ሞተውባቸዋል ፤ እነኚህ ወገኖቻችን የመንግስት ድጋፍ እንፈልጋለን ብለዋል።

በዚሁ ወረዳ 6 ሺህ ሄክታር የጥጥ እና ሰሊጥ እርሻ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ደርሷል።

መረጃዎቹ የተሰባሰቡት ፦ ከአፋር ብዙሃን መገናኛ ፣ ከኤሊዲአር ወረዳ ኮሚኒኬሽን፣ ከዶቼ ቨለ ሬድዮ ፣ ከአምባሰል ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጥንቃቄ

በአዲስ አበባ ከባድ ዝናብ የጣለ ነው። በዚህም ሳቢያ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ፈታኝ ሆነዋል።

አሽከርካሪዎች ፤ በእንደህ ያለው ወቅት ባለማሽከርከር የራሳችንን እና የሌሎችን ወገኖች ደህንነት ማስጠበቅ ይገባናል።

ቪድዮ : አብዱራህማን መኪ - ከደቂቃዎች በፊት ፒያሳ
አካባቢ (Tikvah Family)

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጥንቃቄ

የዘንድሮው ክረምት ተጠንክሮ በመቀጠሉ በሁሉም አካባቢ ያላችሁ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ጥንቃቄ ማድረጋችሁን እንዳትዘነጉ።

በተለይ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ያላችሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ ለማስታወስ እንወዳለን።

የመኪና አሽከርካሪ የሆችሁ ቤተሰቦቻችንም በየአካባቢው እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ ጉዞ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ የራሳችሁን እና የሌሎችንም ወገኖች ደህንነት ልታስጠብቁ ይገባል።

ሌላው ልጆች ያላችሁ የቤተሰባችን አባላት ልጆቻሁን ጠብቁ ፤ በተቻለ መጠን ከባድ ዝናብ ሲጥል ቤት ውስጥ እንዲቀመጡ በማድረግ ወቅቱን ማሳለፍ ይገባል። እጅግ አስፈላጊ ቦታ የሚሄዱ ከሆነም እንዲጠነቀቁ ማሳሰብ እንዳትዘነጉ።

#መልዕክት : ክረምት ሲመጣ ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ወገኖቻችን ምን ያህል እንደሚሰቃዩ ይታወቃል ፤ በግለሰብ ደረጃ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ባንችልም አንዳንድ የሚለበሱ ለብርድ የሚሆኑ አልባሳትን በመስጠት እንደሁል ጊዜው በበጎ ስራችን እንቀጥል።

ቪድዮ : AN ከአዲስ አበባ (አዳዋ ድልድይ) ቲክቫህ ቤተሰብ

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከባድ ያለ ዝናብ የጣለ ነው።

ዛሬም በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ጥሏል።

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የሆናችሁ አሽከርካሪዎች በዚህ ወቅት ስታሽከረክሩ የአየር ሁኔታውን ታሳቢ አድርጋችሁ እንዲሆን አደራ እንላለን።

ወላጆችም ልጆቻችሁን ጠብቁ። በተለይም ደግሞ ወቅቱ የትምህርት ሰዓት እንደመሆኑ ከቤት ወደ ከትምህርት ቤት ሲሄዱና ሲወጡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ልጆቻችሁን አሳስቡ። የአየር ሁኔታውን ታሳቢ በማድረግ የሚደረብ ልብስም እንዲይዙ አድርጉ።

የትምህርት ተቋማት በዚህ በዝናብ ወቅት ለልጆች ደህንነት ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጉላቸው።

በአጠቃላይ ውድ የአ/አበባ ቤተሰቦቻችን በተለይ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ያላችሁ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እንላለን።

በአዲስ አበባ ከትናንት በስቲያ ምሽት በጣለው ዝናብ እናት እና ልጆችን ጨምሮ አራት ሰዎች በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸው ማለፉ ይታወቃል።

ፎቶ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia