TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray #Mekelle

ተጨማሪ ፎቶዎች፦ ዛሬ በመቐለ ከተማ ለፌዴራል መንግስት ልዑካን ቡድን የተደረገለት አቀባበል።

Photo Credit : Tigrai Television & Demtsi Weyane

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #Mekelle ተጨማሪ ፎቶዎች፦ ዛሬ በመቐለ ከተማ ለፌዴራል መንግስት ልዑካን ቡድን የተደረገለት አቀባበል። Photo Credit : Tigrai Television & Demtsi Weyane @tikvahethiopia
#Mekelle

መቐለ የሚገኘው የፌዴራል መንግስት ልዑክ ፦

- በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጨፎ የተመራ ነው።

- ልዑኩ ከ50 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን ሚኒስትሮች፣ የፌደራል መስርያ ቤት ዋና ኃላፊዎች እና ዲፕሎማቶች ይገኙበታል።

- በልዑካን ቡዱኑ የጠ/ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ፣ #የኢትዮ_ቴሌኮም ዋና ስራ ስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሪት ፍሬህይወት ታሙሩ ፤ #የባንክ_ኃላፊዎች በርካታ ሚኒስቴሮች ይገኙበታል።

- የፌዴራሉ መንግሥት ልዑክ ፤ ዛሬ መቐለ መግባቱ የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊነት እንደሚያጠናክረው ታምኗል።

Credit : Demtsi Weyane

@tikvahethiopia
#safaricom

በቴሌኮም ዘርፍ የተሰማራዉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎቶቹን ለማስተዋወቅ በመላዉ አዲስ አበባ ለ 10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የመንገድ ላይ ትርዒት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ትርዒቱ የተለያዩ መዝናኛዎችን ያካተተና ሲምካርድ ለሚገዙ ደንበኞቹ የተለያዩ ስጦታዎችን አዘጋጅቷል። ተቋሙ አዲሱን የሳፋሪኮም ኔትወርክ  እንዲቀላቀሉ ጥሪውን  ለደምበኞቹ ያቀርባል።

ታህሳስ 18ና 19/2015 በሳፋሪኮም ሱቆች አካባቢ የመንገድ ላይ ትርዒቱ የሚከናወን ሲሆን ታህሳስ 19/2015 ዝግጅቱ ፍፃሜውን ያገኛል።

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle መቐለ የሚገኘው የፌዴራል መንግስት ልዑክ ፦ - በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጨፎ የተመራ ነው። - ልዑኩ ከ50 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን ሚኒስትሮች፣ የፌደራል መስርያ ቤት ዋና ኃላፊዎች እና ዲፕሎማቶች ይገኙበታል። - በልዑካን ቡዱኑ የጠ/ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ፣ #የኢትዮ_ቴሌኮም…
" በክልሉ ትልቅ ችግር የሆነው የባንክ አገልግሎት በቅርቡ ይፈታል " - አቤ ሳኖ

ዛሬ ወደ መቐለ ያመራው የፌደራሉ መንግስት ልኡክ በክልሉ ያለው የባንክ ችግር በቅርቡ እንደሚፈታ ለክልሉ ህዝብ ማረጋገጡ ተገልጿል።

ልዑኩ ለትግራይ ህዝብ እንዳረጋገጠው ከሆነ  በክልሉ ትልቅ ችግር የሆነው የባንክ አገልግሎት በቅርቡ መፍትሄ ያገኛል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 18 ባለሞያዎችን ወደ መቐለ እንዳሰማራም በዛሬው ዕለት ተገልጿል።

የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ " ባንኩ የሚስተካከሉ የሲስተምና የኦዲት ሥራዎችን በዚህ ሳምንት አጠናቆ አገልግሎት ለማስጀመር እየሰራ ነው " ብለዋል።

" በትግራይ የባንክ አገልግሎት በመቋረጡ ምክንያት ህብረተሰቡ  ለከፋ ችግር እንደተዳረገ እንረዳለን " ያሉት አቤ " ይህንን ችግር  በአጭር ጊዜ ለመፍታት ከዛሬ ጀምሮ ባለሞያዎቻችን ወደ ስራ ገብተዋል " ሲሉ አሳውቀዋል።

የሰላም ጅምሩ እንዲፀና ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ የባንኩ ፕሬዝዳንት መጠየቃቸውንም ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ታህሳስ19

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የኃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓልን ለማክበር ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅ/ገብርኤል ገዳም አምርተዋል።

ቅዱስነታቸው ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመሆን ዛሬ ድሬዳዋ ከተማ ሲደርሱ በከተማው ከንቲባ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በሌላ በኩል ፤ ታህሳስ 19/2015 ዓ/ም በቁልቢ እንዲሁም በሀዋሳ በድምቀት ለሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል የፀጥታ መዋቅሮች በዓሉ ደህንነቱ የተረጋገጠና ሰላማዊ እንዲሆን አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጋቸውን ለመስማት ችለናል።

Photo Credit : EOTC

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

#ቅዱስ_ገብርኤል

የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ መንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም (ቤተመንግሥት ቅዱስ ገብርኤል) በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል።

በዓሉን በደማቅ መልኩ ለማክበር የገዳሙ አስተዳደር ጽ/ቤት ከፀጥታ አካላት ከአከባቢው ምዕመናን ጋር ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

ፅ/ቤቱ የፓርኪንግ ችግር ፈፅሞ እንጋይገጥም አዲሱ የቤተመንግስት ፓርኪንግ መፈቀዱንም አመልክቷል።

ምእመናን ለበዓሉ ሲመጡ መታወቂያ ከእጃቸው ላይ እንዳይለይ መሳሰቢያ ተሰጥቷል።

@tikvahethiopia