TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ExitExam 

የህግ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam ) ከዛሬ ጀምሮ መውሰድ ይጀምራሉ።

በኮቪድ ምክንያት የትምህርት ተቋማት ከተዘጉ በኋላ ወደ 2013 የተዛወረው ፈተና ቀጥሎም በሀገሪቱ በተፈጠረው የጸጥታ ስጋት ምክንያት ዳግም ሊራዘም ችሏል።

በዚህ ምክንያት በትግራይ ክልል ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በትግራይ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፈተናውን አይወስዱም።

በአስፈታኝ ዩኒቨርሲቲዎች ለማስፈተን አመቺ ሁኔታዎች ከሌሉ በአጭር ጊዜ የድጋሚ ፈተና በልዩ ሁኔታ በማዘጋጀት እንዲፈተኑ ይደረጋል ተብሏል።

የፍትሕ እና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢኒስትቲውት ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ ፈተናው ከታህሳስ 13-16 ባለው ጊዜ ውስጥ እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወሳል።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የትምህርት ሚኒስቴር " የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና አፈፃፀም መመሪያ " ን በማጸደቅ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አሰራጭቷል። በ2015 የትምህርት ዘመን ገቢራዊ የሚሆነው መመሪያው፤ የከፍተኛ ትምህርት የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተናን በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የሚያስችል ስርዓት ለመዘርጋት ወሳኝ ነው ተብሏል። መመሪያ ቁጥር 919/2014 ሆኖ በፍትህ ሚኒስቴር የጸደቀውን መመሪያ የከፍተኛ…
#ExitExam

ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥለው ዓመት 2015 ትምህርት ዘመን የሚጀምረውን የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የአፈፃፀም መመሪያን በማጸደቅ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማሰራጩት ይታወቃል።

ለመሆኑ መመሪያው ምን ይላል ?

- የመውጫ ፈተናው የመጀመሪያ ዲግሪ የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ይመለከታል።

- መመሪያው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እና ሀገሪቱ የምትፈልገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ከሚከወኑ የማስፈፀሚያ ስልቶች አንዱ ነው።

- የመውጫ ፈተናውን ወስዶ 50 በመቶ ውጤት ማምጣት ያልቻለ ተማሪ መመረቅም ሆነ ከተማረበት ዩኒቨርሲቲ የዲግሪ ሰርተፊኬት ማግኘት አይችልም።

- በመውጫ ፈተና 50 በመቶ ማምጣት ያልቻለ ተጨማሪ ጊዜ ወስዶ በአግባቡ አጥንቶ ፈተናውን 50 በመቶ እና ከዛ በላይ አምጥቶ ማለፍ እንዲችል ለሁለት ተጨማሪ ጊዜ የመፈተን እድል ይሰጠዋል። ተፈታኙ እድሉን መጠቀም ያለበት የመጀመሪያውን ፈተና ከወሰደ በ3 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው።

- አንድ ተማሪ ለምርቃት ብቁ የሚሆነው የመውጫ ፈተናውን ካለፈ ብቻ ሲሆን 3 ጊዜ ተፈትኖ የማለፊያ ነጥብ ያላገኘ ተፈታኝ ከብሄራዊ የብቃት ማዕቀፍ ተገቢው ማስረጃ ይሰጠዋል።

- የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና እንደየትምህርት ፕሮግራሙ ባህሪ በዓመት ሁለቴ እና ከዛም በላይ ሊሰጥ ይችላል።

- የመውጫ ፈተና የሞያ ማህበራት ተጠናክረው የሞያ ፍቃድ ፈተና መስጠት እስከሚጀምሩ በትምህርት ሚኒስቴር ወይም ውክልና በሚሰጠው ተቋም ይዘጋጃል።

መውጫ ፈተና ላይ ሚካተቱ ኮርሶችን በተመለከተ በመጪው ጊዜ በየትምህርት መስኩ በሚዘጋጁ የማስፈፀሚያ ዝርዝር መመሪያዎች ይለያል መባሉን ሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ትምህርት ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ካሰራጨመው ዘገባ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ExitExam

የትምህርት ጥራት #ፈተና_በመስጠት ብቻ ይረጋገጣል ?

ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ የመውጫ ፈተና መሰጠት እንደሚጀመር ይታወቃል።

ለመሆኑ ፈተና በመፈተን ብቻ የትምህርት ጥራት ማምጣት ይቻላል ? ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ጉዳይ ምላሽ አለው።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢቲቪ) የተናገሩት ፦

" የትምህርት ጥራት ፈተና ብቻ በመስጠት የሚሳካ ፤ የሚረጋገጥ ነገር አይደለም።

በአጠቃላይ ግን በትምህርት እና ስልጠና ዘርፉ በተለይም በትምህርቱ ዋና ችግር አለ ተብሎ የተለየው ዋና የትምህርት ሴክተሩ ስብራት ነው ተብሎ የተለየው ትምህርታችን ጥራትም ተገቢነትም ጎሎታል።

ስለዚህ አስመርቀን የምናስወጣው በሙሉ ባይባልም የጥራት ፣ የብቃት ችግር አለበት ይሄንን መፍታት ያስፈልጋል።

ለዚህ የሚሆን በሁሉም ደረጃ ከግብዓትም ጋር ከሂደቱም ጋር የሚያያዝ እንደዚሁም ውጤቱን ከማረጋገጥ ጋር የሚያያዝ ስራዎች መሰራት አለባቸው ተብሎ በመንግስት ቁልፍ የሪፎርሞች ተጀምረዋል አንደኛው ከመውጫ ፈተና ጋር የሚያያዝ ነው።

ይሄ የመውጫ ፈተና በዋናነት የሚመለከተው የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃንን ነው ሁለተኛ ዲግሪ እና ሌሎችን አይመለከትም የሚጀምረው በ2015 ሰፋ ብሎ ነው እንጂ ከዚህ በፊትም የተጀማመሩ ስራዎች አሉ የተጀመሩ ፕሮግራሞች አሉ።

ዋናው ቁም ነገሩ በግብአት ደረጃ ጥራቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል የምሩቁን ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን የመማር ማስተማር ሂደቱ ጥራትን በሚያረጋግጥ መልኩ መምራት እና መስጠት ያስፈልጋል።

በጥሩ ግብዓት ከተደገፈ እና ጥሩ ሂደት ካለው በውጤቱ ማረጋገጥ ይገባል ከሚል መነሻ የተጀመረ የሪፎርም ስራ ነው "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ExitExam

በ2015 የትምህርት ዘመን ከሚጀምረው የመውጫ ፈተና (ለመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃን ብቻ) ጋር በተያያዘ ከፈተናው በፊት ሊቀድሙ የሚባቸው ነገሮች አሉ በሚል የተለያዩ ሃሳቦች ይነሳሉ።

የግብዓት አቅርቦት ችግር ባለበት ሁኔታ ፣ የትምህርት ተቋማት አቅም በሚፈለገው ደረጃ ባልሆነበት ፣ የመምህራን ብቃት በራሱ ሳይመዘን / መምህራን ሳይመዘኑ ተማሪዎችን መመዘን እንዴት ይሆናል ፤ እንዴትስ ውጤት ያስገኛል በሚል ጥያቄ የሚያነሱ አሉ።

የትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ላይ ምላሽ አለኝ ብሏል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢቲቪ) ከተናገሩት ፦

" አቻ ምሳሌ ላይሆን ይችላል ግን አንድ ምሳሌ ላንሳ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች አሉ ከሺህ በላይ የሚሆኑ በሁሉም ት/ቤቶች ያለው አቅም ፣ የመምህራን፣ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መሰረተ ልማት አቅም እና መምህራኑ የተመዘኑ / ምዘናውን ያለፉ መሆን አለመሆናቸው ያለው ምጣኔ በጣም የተለያየ ነው። እንደዛም ሆኖ ግን አንድ ወጥ የሁለተኛ ደረጃ ፈተና ያስፈልገናል እንደ ሀገር።

የ2ኛ ደረጃ ፈተና የምንሰጠው አንድ ሰው በሁለተኛ ደረጃ የሚሰጠውን ትምህርት በእርግጥ አጠናቋል ለሁለተኛ ደረጃ አጠናቃቂ ነው ተብሎ በቅቷል ወይ ለማለትና ለመለካት ነው።

ይሄ ፈተና ስታንዳርድ ፈተና ነው። በየሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች አቅም አይደለም የሚዘጋጀው ፣ በሁለተኛ ደረጃ ያሉ መምህራንን አቅም ብቻ አይደለም ታሳቢ የሚያደርገው፤ እንደ ሀገር ሁለተኛን ደረጀን የጨረሰ ሰው ምን አይነት እውቀት እና ስብዕና ሊኖረው ይገባል የሚለውን የሚፈትሽ ነው።

መምህራኑ ሁሉም ተፈትነው ብቁ ሆነው እስኪያልፉ ፣ ያለን መሰረተ ልማት በትምህርት ቤቶች ወይም በዩኒቨርሲቲዎች ያለን አቅም ተመጣጣኝ እስክናደርግ ድረስ አንድን ሪፎርም አንጀምርም ካልን ዝንተዓለም ያንን ሪፎርም አናደርግም።

ሪፎርሙ መጀመር አለበት የሆነ ጊዜ ላይ መጀመር አለበት የተባሉ ጉድለቶች እንዳሉ አውቃለሁ፤ እንደ ትምህርት ሴክተርም እንደትምህርት ሚኒስቴርም እንገነዘበዋለን።

የመምህራኖቻችንን ብቃት ለማሳደግ በየአመቱ ከልማት አጋሮችም ፣ ከመንግስትም ግምጃ በሚሊዮኖች እያፈሰስን መምህራን በ2ኛ ፣ 3ኛ ዲግሪ እናስተምራለን።

እንደሚታወቀው መንግስት ለትምህርት በሰጠው ልዩ ትኩረት በሀገራችን 4ኛው ትልቁ በጀት የሚመደብለት ሴክተር ነው ሰፊውን የሚወስደው የከፍተኛ ትምህርት ነው የውስጥ መሰረተ ልማታቸውን፣ አደረጃጀታቸውን ለማሳደግ የሚውል ሀብት አለ እነዚህ ቁርጠኝነቶች በመንግስት በኩል የውስጥ ችግሮችን ለመፍታት የሚውል ነው።

መምህራኖቻችን በቀጣይነት እያበቃን መሄድ አለብን እርግጥ ነው እንደዛም ሆኖ ግን ይሄ ስራ መጀመር አለበት ፤ አሁን ካልጀመርነው ከበቂ በላይ ጉዳት ደርሷል የትምህርት ጥራቱ ላይ።

በፈተና ብቻ አይደለም ዩኒቨርሲቲዎችን በተልዕኮ በትኩረት በመለየት ፣ ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ በማድረግ ፣ የሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ፈተና በጥራት በመስጠት ፣ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን አነስተኛውን መስፈርት በፖሊሲው መሰረት 50 ፐርሰንት በማድረግ እነኚህ ሪፎርሞች መምህራን ልማት ላይ የምንሰራውን ፤ የዩኒቨርሲቲ ማስፋፊያን ገድበን የወሰድናቸውን ሪፎርሞች ድምር ውጤት ለትምህርት ጥራት ወሳኝ ነው ፤ ይሄንን ማድረግ ተገቢ ነው ጊዜው አሁን ነው ብለን ነው የገባንበት። "

@tikvahethiopia