TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በሱዳን ወታደራዊውን መንግስት ለመቃወም በወጡ ሰልፈኞች ላይ ጦሩ በወሰደው እርምጃ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ስድስት (6) መድረሱን የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ አስታወቀ። ዛሬ በነበረው ሰልፍ የተገደለው 6ኛ ሰው በባህሪ ከተማ ሲሆን ህፃን ልጅ እንደሆነና ከጀርባው በጥይት ተመቶ እንደተገደለ ኮሚቴው ገልጿል። እስካሁን ድረስ የሱዳንን ወታደራዊ መንግስት መቃወም ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ (ጥቅምት…
#Update

ሱዳን ዛሬም በተቃውሞ ስትናጥ ውላለች።

ትላንት በመዲናይቱ ካርቱም በፀጥታ አስከባሪዎች የተገደሉ ሰልፈኞችን ለመቅበር የተሰበሰበዉ ሕዝብ የቀብሩን ስርዓት ወደ ተቃዉሞ ሰልፍ ቀይረውት ከተማዋ በተቃውሞ ስትናጥ ውላለች።

ፀጥታ አስከባሪዎች በካርቱም እና በሌሎች ከተሞች የነበረውን ሰልፍ ለመበተን ለመበተን በከፈቱት ተኩስ እስካሁን በተረጋገጠው 9 ሰዎች ተገድለዋል።

የሱዳን ፖሊስ ሰልፈኞቹ 96 ፖሊሶችና 129 ወታደሮች አቁስለዋል በማለት የሰልፉን አደራጆች ከሷል።

ትናንት የተገደሉትን ሰልፈኞች ለመቅበር ዛሬ የታደመዉ በርካታ ለቀስተኛ ከሐገሪቱ ፕሬዝደንታዊ ቤተ-መንግስት አጠገብ ተሰልፎ ወታደራዊዉ ጁንታ ስልጣን እንዲለቅ ሲጠይቅና ሲያወግዝ ውሏል።

በሌላ በኩል ፤ ባለፈዉ እሁድ ዕለት በፀጥታ አስከባሪዎች ጥይት የቆሰለ አንድ ሰልፈኛ ግን ዛሬ ህይወቱ አልፏል።

የአፍሪካ ህብረት ፣ ኢጋድ ፣ ተመድ እና አሜሪካ የሱዳን ወታደራዊ ገዢዎች በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የሚወስዱትን የኃይል ርምጃ እንዲያቆሙ ጠይቀዋል።

በሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አልቡርሃን የተመራውን መፈንቅለ መንግስት በማውገዝ እና ወታደሩ ስልጣኑን ወደ ሲቪል መንግስት እንዲያሸጋግር ለመጠየቅ ሰልፍ ወጥተው የተገደሉ ሰዎች 113 ደርሰዋል።

መረጃው ከአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ፣ ዶቼ ቨለ እና ከሱዳን ዶክተሮች ማዕከላይ ኮሚቴ የተውጣጣ ነው።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Tigray , #Mekelle 📍

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) የህክምና ቁሳቁሶችን እና የተለያዩ እንደ የጤፍ ዘር እንዲሁም መሰረታዊ የሆኑ የቤት ቁሳቁሶችን ያካተተ ሰብዓዊ እርዳታውን ይዞ መቐለ፣ ትግራይ ዛሬ ገብቷል።

#ICRCEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በዋስ ከእስር እንዲፈታ የተወሰነለት ጋዜጠኛ በቃሉ አለምረው ከእስር መፈታቱን ለማወቅ ተችሏል። 🔻 በሌላ በኩል ፦ አቃቤ ህግ በ “ፍትሕ” መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መስርቷል። ዐቃቤ ህግ በተመስገን ላይ የክስ መዝገብ የከፈተው፤ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የህግ መንግስት እና የሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት መሆኑን…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" በድሃ ጎኔ ያሳደኩት ልጄ ነው "

ከቀናት በፊት ማንነታቸውን እስካሁን መለየት ባልተቻሉ አካላት የተወሰደው ገጣሚ በላይ ቀበለ ወያ እስካሁን ያለበት እንደማይታወቅ ቤተሰቦቹ አመልክተዋል።

እናት ፦

" ልጄን በሰላም መልሱልኝ የወሰደ አካል፤ መንግስትም ይሁን ሌላም አካል ከሆነ ልጄን በሰላም መልሱልኝ።

በድሃ ጎኔ ያሳደኩት ነው። በደሃ ጎኔ ነው ያሳደኩት ጥፋት ካለው አይጠየቅ አይደለም ፤ ጥፋት ካለው አይታሰር አይደለም ፤ መንግስትም ሆነ ሌላ አካል ልጄን በሰላም ይመልስልኝና የሚጠይቀውን ይጠይቅ።

አፋልጉኝ ፤ ሀገር ወገን ህዝብ አፋልጉኝ ልጄን " ሲሉ ተማፅነዋል።

በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ያሉት ቤተሰቦቹ ልጃቸውን የወሰደው አካል በሰላም ወደቤቱ እንዲመልስላቸው ፤ መንግስትም አስሮት ከሆነ ያለበትን እንዲያሳውቃቸው ጠይቀዋል።

ገጣሚው በአዲስ አበባ ከተማ ፤ ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ሲቪል በለበሱ ሰዎች እንደተወሰደ ከተሰማ ዛሬ 4ኛ ቀኑ ነው።

@tikvahethiopia
#ቹ_የቋንቋ_ትምህርት_ቤት

በዓለም በስፋት (በተናጋሪ ብዛት) ከሚነገሩ ቋንቋዎች በአንደኝነት የሚቀመጠውን፣ የተባበሩት መንግስታት የስራ ቋንቋ የሆነውን፣ ቻይንኛ ቋንቋን ይማሩ!!

ቹ * ቻይንኛ እና ቻይንኛ ብቻ የሚማሩበት የከተማችን የቋንቋ ት/ቤት ነው፡፡
*ለተማሪዎች በክረምት ወቅት የሚሰጥ ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅተናል።

አድራሻ፡
*ቦሌ፡ ፋንቱ ሱፐር ማርኬት አካባቢ፣ ሳይ ኬክ ቤት ያለበት ህንጻ፣ 1ኛ ፎቅ
*ስታድየም፡ ትንሸዋ ስታድየም ጀርባ፣ ናሽናል ታወር ፣ 3ኛ ፎቅ
*አያት 49 የአየር መንገድ ቤቶች ፊት ለፊት ማይ ፕላዛ ህንጻ፣ 1ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ በ 0947202020 ይደውሉ፡፡
Congratulations !

ዛሬ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን አስመርቀወል።

ዛሬ ፦

- ጅማ ዩኒቨርሲቲ ➡️ 2 ሺህ 509 ተማሪዎች

- መቱ ዩኒቨርሲቲ ➡️ ከ1 ሺህ በላይ ተማሪዎችን

- ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ➡️ 997 ተማሪዎች

- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ➡️ 1 ሺህ 495

- ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ➡️ ከ1 ሺህ 800 በላይ ተማሪዎች

- አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ➡️ 1 ሺህ 400 በላይ ተማሪዎችን

- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ➡️ ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን

- አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ➡️ ከ2 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን

- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ➡️ 334 የህክምና ተማሪዎችን

- ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ➡️ 1510 ተማሪዎችን

- ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ➡️ 204 ተማሪዎችን

- አምቦ ዩኒቨርሲቲ ➡️ ከ4 ሺህ 400 በላይ ተማሪዎችን አስመርቀዋል።

ተጨማሪ : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ መደበኛ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች የክረምት የእረፍት ጊዚያቸውን በተቋሙ ለመቆየት ካቀረቡ ውስጥ ከግማሽ በላይ ለሚሆኑት ምላሽ መስጠቱን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

"ዩኒቨርሲቲው ጥያቄ ካቀረቡ 102 ተማሪዎች ለ58ቱ ምላሽ በመስጠት በግቢው እንዲቆዩ መፍቀዱን" የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ማቲዎስ እንሰርሙ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

"አሁንም እያንዳንዱን ጥያቄ ኬዝ በኬዝ በማየት ምላሽ እየሰጠን ነው" ያሉት ም/ፕሬዝዳንቱ፤ "በተጨማሪም አካል ጉዳተኛ ለሆኑ እና የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው ተማሪዎችም ምላሽ እየተሰጥ ነው" ብለዋል።

"ሌሎች ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው በሚሄዱበት ጊዜ እና ሲመለሱ የፀጥታ ችግር እንዳይገጥማቸው ዩኒቨርሲቲው ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር የትብብር ደብዳቤ ማዘጋጀቱንም" ገልጸዋል።

"አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም የደህንነት እጀባ ለተማሪዎቹ ይደረጋል" ብለዋል።

የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች ማለትም ከምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ፣ ከትግራይ ክልል፣ ከአማራ-ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች በሙሉ በግቢው እንደሚቆዩ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።

በድጋሜ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ/ም ከግቢው ውጡ ስለተባሉ ተማሪዎች ኃላፊውን ጠይቀናል።

"ግቢውን ለቃችሁ ውጡ የተባሉት ከትግራይ የመጡና ከተመረቁ በኋላ ከአንድ ዓመት በላይ በግቢው የቆዩ ተማሪዎች መሆናቸውን" ገልጸዋል።

"ከነዚህ ተማሪዎች መካከል ግማሽ ያህሉ ወጥተዋል" ያሉት ኃላፊው፤ "የተቀሩትም ከዚህ በላይ በግቢው መቆየት አይችሉም" ብለዋል።

Tikvah University https://yangx.top/+RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EZEMA የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ሰኔ ወር ላይ በሚያካሄደው 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለፓርቲው ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች የሚወዳደሩ እጩዎችን የአስመራጭ ኮሚቴውን ዛሬ ይፋ አደርገ። ፓርቲው የምርጫ አመልካቾችን ከሚያዚያ 25 እስከ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ሲቀበል ቆይቷል። ለዕጩ ተወዳዳሪዎች ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም ውጤታቸው በየግላቸው እንደተገለፀላቸው የጠቆመው…
#Update

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ገባኤውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።

ፓርቲው ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ ነው።

ዛሬ እና ነገ በሚቆየው የፓርቲው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የፓርቲውን መሪ ጨምሮ ለከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪ ጉባኤው በተለያዩ ጉዳዮች ተወይያቶ ውሳኔ ያሳልፋል ፤ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይም ይመክራል ተብሏል።

ፎቶ ፦ Melkamu Outa

@tikvahethiopia
ፎቶ ፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ምረቃ ላይ ተገኘተው ቃለምዕዳን ሰጡ፡፡

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ከዲፕሎማ እስከ ሁለተኛ ዲግሪ በተለያየ የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን ደቀ መዛሙርት አስመርቋል።

በምረቃው ስነ ሥርዓት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ተከናውኗል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት

@tikvahethiopia