TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዓለም አቀፍ የቁርዓን ውድድሩ ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል። ዓለም አቀፍ የቁርአን ውድድሩ በነገው እለት ጥዋት በአዲስ አበባ ስቴዲየም እንዲካሔድ በመንግስት ፍቃድ መሠጠቱ ተሰምቷል። በዚህም መሠረት ነገ ሰኔ 6 ቀን 2014 ፕሮግራሙ እንደሚካሔድ አዘጋጆቹ ማሳወቃቸውን ሀሩን ሚዲያ ዘግቧል። @tikvahethiopia
#መልዕክት

ዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር ፦

" የኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ የቁርአን ሂፍዝ ውድድር ሽልማት በዛሬው ዕለት ይደረግ የነበረው ወደ ሰኞ 06/10/14 ተቀይሯል።

ህዝባችን ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በመምጣት ፕሮግራሙን እንድትታደሙ በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

ለተፈጠረው ክፍተት ሕዝባችንን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መልዕክት ዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር ፦ " የኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ የቁርአን ሂፍዝ ውድድር ሽልማት በዛሬው ዕለት ይደረግ የነበረው ወደ ሰኞ 06/10/14 ተቀይሯል። ህዝባችን ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በመምጣት ፕሮግራሙን እንድትታደሙ በአክብሮት እንገልፃለን፡፡ ለተፈጠረው ክፍተት ሕዝባችንን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ " @tikvahethiopia
#መልዕክት_2

(ነገ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቁርዓን ሂፍዝ ውድድር)

- ፕሮግራሙ ከጠዋቱ 1 ሰዐት ጀምሮ ስለሚካሄድ በጊዜ አዲስ አበባ ስታዲየም እንገኝ።

- በ500 ብር ትኬታ የቆረጠ ሁለት ሰው ሆኖ መግባት ይችላሉ። ትኬት ያልገዙ ሰዎች በ200 ብር በር ላይ እንዲገዙ ተመቻችቷል።

- ሴቶች ከወጋገን ባንክ ፊት ለፊት ያሉትን በር ቁጥር 8፣ 9 እና 11ን ብቻ ተጠቀሙ። የVIP እንግዶችም በVIP በኩል መግባት ትችላላችሁ።

- ሁሉም የራሱን መስገጃ ይዞ መገኘት አይዘንጋ

- የተጠቀምናቸውን ውሀና ብስኩቶች የምናነሳበትን ፌስታል መያዝ አይዘንጉ። በመሃል ሌባ ሊኖር ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ያድርጉ።

- አቅመ ዳካማዎችን፣ታላላቆችንና ሴቶች የተሻለ ቦታ እንዲያገኙ አድርጉ

- ለአስተናጋጆች፣ ለኻዲሞችና ለፀጥታ አካላት ፍፁም ታዛዥ ይሁኑ።

ከፕሮግራሙ አዘጋጆች ፦ ዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር

Via ኡስታዝ አህመዲን ጀበል

@tikvahethiopia
#DawitNega

በትግርኛ የሙዚቃ ስራዎች በእጅጉ የሚታወቀው አርቲስት ዳዊት ነጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰማ።

አርቲስት ዳዊት ህመም አጋጥሞት ያለፉትን ቀናት በአዲስ ህይወት ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደነበር ተነግሯል።

የአርቲስት ዳዊት ነጋ የሙዚቃ ስራዎች የትግርኛ ቋንቋ ከሚያደምጡ ሰዎች ባለፈ ቋንቋውን በማያዳምጡትም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበሩ ናቸው።

ከሙዚቃ ስራዎቹ መካከል ፦ ባባ ኢለን፣ ዘዊደሮ፣ ወዘመይ፣ ቸቸኮላታ፣ ኣጆኺ ትግራይ፣ ቕዱስ ፀባያ የሚሉት ይጠቀሳሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መልዕክት_2 (ነገ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቁርዓን ሂፍዝ ውድድር) - ፕሮግራሙ ከጠዋቱ 1 ሰዐት ጀምሮ ስለሚካሄድ በጊዜ አዲስ አበባ ስታዲየም እንገኝ። - በ500 ብር ትኬታ የቆረጠ ሁለት ሰው ሆኖ መግባት ይችላሉ። ትኬት ያልገዙ ሰዎች በ200 ብር በር ላይ እንዲገዙ ተመቻችቷል። - ሴቶች ከወጋገን ባንክ ፊት ለፊት ያሉትን በር ቁጥር 8፣ 9 እና 11ን ብቻ ተጠቀሙ። የVIP እንግዶችም በVIP…
ፎቶ ፦ በአሁን ሰዓት በ አዲስ አበባ ስታዲየም " ዓለም ዓቀፍ የቁርአን ሂፍዝ ውድድር " እየተካሄደ ይገኛል።

ፕሮግራሙ በርካታ ህዝበ ሙስሊም በተገኘበት ነው እየተከናወነ የሚገኘው።

በዚህ ዓለም አቀፍ የቁርዓን ውድድር ኢብራሒም አብዱራህማን ኢብራሒም ሀገራችን #ኢትዮጵያን 🇪🇹 ወክሎ የውድድሩ ተሳታፊ ነው።

ፕሮግራሙ እንደተጠናቀቀ ተጨማሪ መረጃዎችን የምንልክላችሁ ይሆናል።

@tikvahethiopia
#አስቸኳይ

ሰኔ 4 ቀን 2014 ዓ/ም በአማራ ክልል፣ ሰሜን ሜጫ ወረዳ በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

በሰሜን ሜጫ ወረዳ ቆለላ ቀበሌ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ፦
- ጋፈራ፣
- አውጣ
- ባችማ
- ተክለድብ በተባሉ ቀበሌዎች 1409 በሚደርሱ የአባወራ ቤቶች ላይ ከባድና ቀላል የንብረት ጉዳት ደርሷል።

በእስሳት እና አትክልት፣ ፍራፍሬ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ ለተጎዱ 5 ቀበሌዎች #አስቸኳይ_ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

አጠቃላይ የደረሰው ጉዳት ዝርዝር በዚህ ተያይዟል ፦ https://telegra.ph/North-Mecha-06-13

#ሰሜን_ሜጫ_ወረዳ

@tikvahethiopia