TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#ባልደራስ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከፍተኛ አመራሩ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በባህር ዳር ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቋል። ፓርቲው አመራሩ በአንደኛ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩን ነው ያመለከተው። አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከጥቂት ወራት በፊት ከረጅም ጊዜ እስር መለቀቃቸው የሚዘነጋ አይደለም። @tikvahethiopia
#Update

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራር አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከታሰሩ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ፍርድ ቤት አልቀረቡም

አቶ ስንታየሁ በባህር ዳር አንደኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኙ።

ባልደራስ ፓርቲ አመራሩ በእስር ቤት ውስጥ የሚደርስባቸውን የመብት ጥሰት በመቃወም ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም. የርሃብ አድማ መጀመራቸውን ገልጿል።

ፓርቲው ፤ " በባሕር ዳር አንደኛ ፖሊስ ጣቢያ ታግቶ የሚገኘው የአደረጃጀት ጉዳዮች ኃላፊ ስንታየሁ ቸኮል፣ እጅግ አሰቃቂ በሆነ ክፍል ውስጥ መታሰሩን የገለጿል፤ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት በአካል ተገኝተው የእስር ቤቱን ሁኔታ እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርቧል " ሲል ፅፏል።

አቶ ስንታየሁ እስከ ሞት የሚደርስ ጉዳት ሊደርስባቸው እንደሚችል እና በእስር ቤቱ ውስጥ እየተዛተባቸው መሆኑን መናገራቸውን ፓርቲያቸው ገልጿል።

ከታሰሩ 11 ቀናት ቢቆጠሩም እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውንም ፓርቲድ አሳውቋል።

የጣቢያው ፖሊስ አባላት የአቶ ስንታየሁን ቸኮል ፍርድ ቤት አለመቅረብ ለአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ቢያሳውቁም፣ " እናንተ አያገባችሁም " የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው አረጋግጫለሁ ብሏል ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ።

" አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ባልደራስ ሀገራዊ ፓርቲ ለመሆን የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ተከትሎ በባሕር ዳር ሕዝባዊ የድጋፍ ፊርማዎችን እያስፈረመ በከተማዋ ሲንቀሳቀሰሰ መቆየቱ፣ ከአረፈበት ሆቴል መኝታ ክፍል ውስጥ መታፈኑ ይታወሳል " ሲልም ፓርቲው አክሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ችሎት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ የ10 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ በፍርድ ቤት ተፈቀደላቸው። የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝና ሰለሞን ሹምዬ እያንዳንዳቸው የ10 ሺ ብር ዋስትና በማስያዝ ከእስር እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ፤ ፖሊስ በጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ እና በመስከረም አበራ ላይ እያደረገው ለሚገኘው ምርመራ…
#Update

ፍርድ ቤት በዋስ ከእስር እንዲፈቱ የወሰነላቸው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ እና ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ ከእስር አልተለቀቁም።

ዛሬ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት፣ 3ቱ ጋዜጠኖች በ10 ሺ ብር ዋስ እንዲለቀቁ መወሰኑ ይታወሳል።

ነገር ግን መርማሪ ፖሊስ ይግባኝ ለማለት ለ8 ሰዓት ቀጥሮ ነበር ሆኖም ችሎቱን የሚመሩት ዳኛ ባለመኖራቸው ለነገ ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተቀጥሮ ወደ ታሰሩበት ጣቢያ እንዲመለሱ ተደርጓል።

Via Eden Tilahun / Gabriela

@tikvahethiopia
" ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ የስራ መልቀቂያ አላስገቡም ፤ በመደበኛ የስራ ገበታቸው ላይ ናቸው " - አማራ ፖሊስ

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ የስራ መልቀቂያ እንዳላስገቡ ፤ ሰሞኑን እሳቸውን በተመለከተ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን አስገነዘበ።

ሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩን በሚመለከት ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ መመልከቱን ኮሚሽኑ ዛሬ ገልጿል።

" በእርግጥ ስለ ተቋማችንም ሆነ ከፍተኛ አመራሮቻችን በተመለከተ በተደጋጋሚ ሀሰተኛ መረጃዎች ሲፈበረኩ ይህ አዲስ ባይሆንም አወናባጆቹ የተቋሙን የዓላማ አንድነት ለማናጋት የሚፈጥሩትን ብዥታ ለማጥራት ትክክለኛውን ማሳወቅ ያስፈልጋል " ብሏል።

አክሎም ፤ " ኮሚሽነሩ ተቋሙ በአደረጃጀት፣ በሰው ሀይል ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ በአጠቃላይ ዘመኑን የዋጀ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ የሚችል አደረጃጀት እንዲኖረው ከባልደረቦቻቸው ጋር በትጋት የለውጥ/ሪፎርም/ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ " ሲል ገልጿል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን " ሀሰተኞች ህዝቡን ለማደናገር እንደሚሉት ኮሚሽነሩ የስራ መልቀቂያ አላስገቡም በመደበኛ የስራ ገበታቸው ላይ ናቸው " ሲል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ኢትዮ ቴሌኮም ከሀገር ውጭ ባሉት ከፍተኛ ባንድዊድዝ ተሸካሚ የኢንተርኔት መገናኛ መስመሮች ላይ ባገጠመው ችግር ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎቱ በመጠባበቂያ መስመሮች ብቻ እየሰራ መሆኑን አሳውቋል።

በዚህም የኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥ ወይም የፍጥነት መቀነስ ሊያጋጥም እንደሚችል ከይቅርታ ጋር ገልጿል።

ድርጅቱ ፤ አገልግሎቱን በፍጥነት ለማስቀጠል ባለሙያዎቹ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጾ እስከዚያ ድረስ ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ/ም !

" ኢህአዴግ " ስልጣን ከያዘ በኃላ ለ3ተኛ ጊዜ የተካሄደውን #የ1997ቱ ሀገር አቀፋዊ ምርጫ ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ ሳቢያ ሰኔ 1/1997 በመንግስት የተገደሉ ዜጎች ዛሬ 17ኛ ዓመት መታሰቢያቸው ነው።

በወቅቱ "ኢህአዴግ" ይህን መሰሉ አንባገነናዊ ተገባር የፈፀመው ስልጣኑን ለማስጠበቅ ፣ ስልጣኑን የሚያስጠብቀውም በመሳሪያ ኃይል እንጂ በህዝብ ድምፅ እንዳልሆነ የተቀናቃኝ ፖለቲካ ኃይሎች በተለያየ ጊዚያት ተናግረዋል።

ሰኔ 1 ቀን 1997 በግፍ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የተገደሉ ዜጎች ለነፃነት፣ ለዴሞክራሲ፣ ለፍትህ፣ ለሀገራዊ አንድነት ዋጋ የከፈሉ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፤ በየዓመቱም በዚህ ቀን ይታሰባሉ።

ፖለቲከኞች ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾ ይህን የሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም ክስተት ለሁሉም ትምህርት የሚሰጥ እና መቼም ቢሆን ሊደገም የማገባው ብዙ ትምህርትም ሰጥቶ ያለፈ እንደሆነ ይናግራሉ።

በወቅቱ (ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም) በግፍ የተገደሉ ፣ የቆሰሉ፣ ለእስርና እንግልት የተዳረጉ ዜጎች ኢትዮጵያን ያስተዳደር በነበረው "ኢህአዴግ" በሚባለው ፓርቲ ወቅት ሲሆን ፓርቲው ከ2 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ምድር ህልውና እንዳይኖረው ተደርጎ፣ ከስሟል።

በውስጡ የነበሩ ድርጅቶችም ከአንዱ (#ህወሓት) በቀር አንድ ላይ ተዋህደው ውህድ ፓርቲ ፈጥረው ኢትዮጵያን እያስተዳደሩ ነው።

Video Credit : Biniyam Hirut

@tikvahethiopia
በአማራ ክልል በዋግህምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ ከግንቦት 9 ጀምሮ እስካኩን ምንነቱ ያልታወቀ ወረርሽኝ መከሰቱ ሪፖርት ተደርጓል።

ነገር ግን ተከሰተ ለተባለው ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት የሄደ አካል የለም።

የዞኑ ጤና መምርያ የችግሩን ምንነት ለማወቅ በርካታ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ተቋማት ሄደው የተመለሱ ቢሆንም ነገር ግን ለችግሩ መፍትሔ ለመስጠት ጥረት ያደረገ የለም ብሏል፡፡

ተቋማቱ በርቀት መረጃ ሰብስበው ከመመለስ ባለፈ፣ ችግሩ ወደ ደረሰበት አበርገሌ አለመንቀሳቀሳቸው ተመልክቷል፡፡

የተመድ አካላት፣ ዓለም አቀፍ የረድኤት ተቋማትና ኤጀንሲዎች የወረርሽኙ ሪፖርት እንደ ደረሳቸው ከጤና ሚኒስቴር ቡድን ጋር ወደ ሰቆጣ ሄደው ነበር።

ወረርሽኙ ተከሰተ የተባለበት አበርገሌ ወረዳ በሕወሓት ቁጥጥር ሥር የሚገኝ በመሆኑ፣ ዓለም አቀፍ ተቋማቱ ምላሽ እንዲሰጡ ተጠይቀው እንደነበር ተገልጿል፡፡

ተቋማቱ ጥያቄውን ቢስማሙበትም ነገር ግን ስለሁኔታው በርቀት ሰምተው ከመሄድ ባለፈ ለተጨማሪ ማጣራትም ሆነ ምላሽ ለመስጠት አልተመለሱም።

የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ኪዳት አየለ ስለወረርሽኙ ምንነትና ስለደረሰው ጉዳት ተጠይቀው፤ " 3 ሕፃናት የዕብድ ውሻ በሽታ ዓይነት ምልክት ባለው ሕመም መሞታቸውን፣ እንዲሁም 5 ተጨማሪ ሰዎች የተለየ ምልክት ባለው ሕመም መሞታቸው ሪፖርት ተደርጎልናል " ብለዋል፡፡

ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ ማስመለስና የአፍ መድረቅ የሕመም ምልክቶች የሚታይባቸው በጥቅሉ 8 ሰዎች መሞታቸውን ሪፖርት መደረጉን ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ በተጨማሪ የሕክምና ምርመራ እስካልተረጋገጠ ድረስ ሕመሙን "የዕብድ ውሻ በሽታ ወይም ሌላ ዓይነት ወረርሽኝ ነው ብለን ልንደመድም አንችልም" ሲሉ አክለዋል፡፡

ያንብቡ : telegra.ph/RE-06-08-2

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
#ICRCEthiopia

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት በግጭት ለተጎዱ አርሶ አደሮች ድጋፍ ሰጥቷል።

በደቡብ ወሎ ዞን በተሁለደሬ እና በአምባሰል ወረዳዎች ለሚገኙ 10,000 አባወራዎች 10 ኪሎ ግራም የጤፍ ዘር እንዲሁም የእርሻ ግብዓቶችን ለሟሟላት የሚጠቅም የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

#ICRCEthiopia

@tikvahethiopia
#WFP

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በአፋር ክልል እስከ 1.2 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ለረሃብ የመጋለጥ አደጋ እንዳንዣበበባቸው አመልክቷል።

ድርጅቱ ፤ በክልሉ ላሉ 630,000 ሰዎች ወሳኝ የምግብ አቅርቦት ስርጭት እያካሄደ መሆኑን ገልጿል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም " አምስተኛውን ዙር የምግብ እርዳታ ለሁሉም ማድረስ ጨርሰናል እና ቀጣዩን ዙር በቅርብ ጊዜ ለመጀመር በዝግጅት ላይ ነን " ሲል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#USA #ETHIOPIA

አሜሪካ በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የተቸገሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ወጥትነት ባለው መልኩ የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲያገኙ በማድረጉ ሂደት ውስጥ የታየውን እድገትና ለውጥ በደስታ እንደምትቀበል ገለፀች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ትላንት መግለጫ አሰራጭተዋል።

ሚኒስትሩ በትላንት መግለጫቸው ባለፉት 7 ቀናት ውስጥ ከ1,100 በላይ የጭነት ተሽከርካሪዎች ትግራይ ክልል መግባታቸውን አመልከተዋል።

ተሽከርካሪዎቹ ህይወት አድን ምግብ፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ላለባቸው የሚሆን አቅርቦት፣ አስፈላጊ የጤና አቅርቦቶችን እና ሌሎች አስፈላጊ የእርዳታ ቁሳቁሶችን ለችግር ተጋላጭ ወገኖች ለማድረስ የገቡ መሆኑና ይህም የሆነው ሁሉም የሰብአዊ እርዳታ ሰጭ አካላት ባደረጉት ሕይወትን ማዳን ርብርብ መሆኑን ገለፀዋል።

ብሊንከን በተለይም የኢትዮጵያ መንግስት፣ የአፋር ክልል ባለስልጣናት እና የትግራይ ክልል ባለስልጣናት እርዳታ እንዲደርስ የሚያደርጉትን ትብብር እንዲሁም የተመድ ኤጀንሲዎች ፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የአሜሪካ መንግስት አጋሮች እና ግብረሰናይ ድርጅቶች በመላው ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጥረት እናደንቃለን ብለዋል።

ሁሉም ተዋናይ ወገኖች ይህን ግስጋሴ አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ እና በዘላቂነት ግጭት እንዲቆም ወደ ንግግር እንዲገቡ እናበረታታለን ብለዋል ብሊንከን።

አንቶኒ ብሊንከን ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያሉ አስፈላጊ አገልግሎቶች በአስቸኳይ እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ደህንነት እና ብልጽግና እንዲሰፍን ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት አሜሪካ እንደምትደግፍ ገልፀዋል። በሁሉም ወገኖች ለሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂነት እንዲኖርም ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia