TIKVAH-ETHIOPIA
#Freedom_and_Equality ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን በትናንት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች በተገኙበት አካሂዷል። ጉባኤው የተሻሻለውን የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። የተጓደሉ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትንም ምርጫ አካሂዷል፡፡ ቀደም ሲል በነበረው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት 35 የነበረው ማዕከላዊ ኮሚቴ ብሄራዊ ምክር ቤት በሚል…
#Freedom_and_Equality
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ መጋቢት 18 ካካሄደው አንደኛ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ በኃላ ባለ10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
ነእፓ በዚህ የአቋም መግለጫው ላይ ካነሳቸው ጉዳዮች ቀዳሚዎቹ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና በሌሎች አካባቢዎች ያሉ የፀጥታ ችግሮች ናቸው።
ፓርቲው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ላይ የተለኮሰው የጦርነት እሳት ሙሉ ለሙሉ ይቆም ዘንድ ሁሉም አካላት ግጭቱን ለማስቆም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪውን አቅርቧል።
መንግስት በቅርቡ ለትግራይ ክልል ተጨማሪ ሰብአዊ ድጋፍ ከወትሮው በተሻለ መጠን እና ስፋት እንዲደርስ ለማድረግ ያሳየውን ተነሳሽነት እንደሚያደንቅ የገለፀው ነእፓ ውሳኔው በተቻለ ፍጥነት ተግባራዊ ይሆን ዘንድ የሚመለከታቸው አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።
ነእፓ ፤ ምንም እንኳን በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ያለው ግልጽ እና ሰፊ ጦርነት የተለየ ትኩረት ያገኘ ቢሆንም፣ በሀገራችን የተለያዩ ግጭቶች እንዳሉ ይታወቃል ያለ ሲሆን በእነዚህ ግጭቶች ምክንያት በሰላማዊ ዜጎች ላይ ግድያ፣ መፈናቀል እና የንብረት ውድመት ዛሬም ድረስ ሊቆም አልቻለም ብሏል።
መንግስት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ላይ የተፈጠረውን ችግር እልባት ለመስጠት ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ጎን ለጎን በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ ዜጎችን ሰላም እና ደህንነት ለመጠበቅ በቂ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ሲል አሳስቧል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

#Freedom_and_Equality ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ መጋቢት 18 ካካሄደው አንደኛ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ በኃላ ባለ10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። ነእፓ በዚህ የአቋም መግለጫው ላይ ካነሳቸው ጉዳዮች ቀዳሚዎቹ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና በሌሎች አካባቢዎች ያሉ የፀጥታ ችግሮች ናቸው። ፓርቲው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ላይ የተለኮሰው የጦርነት እሳት ሙሉ ለሙሉ ይቆም ዘንድ ሁሉም አካላት…
" የኢኮኖሚ ቀውሱን ለማስተካከል መንግስት አፋጣኝ የማሻሻያ እርምጃዎች ይውሰድ " - ነእፓ
መንግስት እየናረ የሚገኘውን የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠር እና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ።
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ካካሄደው አንደኛ ጠቅላላ ጉባኤ በኃላ ባወጣው የአቋም መግለጫ መንግስት በየጊዜው እየናረ የሚገኘውን የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠር እና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስስ አፋጣኝ እና ተገቢ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሊያደርግ ይገባል ብሏል።
ፓርቲው የዋጋ ግሽበቱን ከሚያባባሱት ኢኮኖሚያዊ እና አስተዳደራዊ ምክንያቶች መካከል ፦
👉 በመረጃ እና እውቀት ላይ ያልተመሰረቱ ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች፣
👉 ወጥነት የጎደለው እና ያልተቀናጀ የመንግስት አሰራር፣
👉ሙስና ይገኙባቸዋል ብሏል።
በሀገራችን በፍጥነት እያደገ ለሚሄደው የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት ዋነኛ ተጠያቂ መንግስት ነው ያለው ነእፓ የተፈጠረውን አጠቃላይ የኢኮኖሚ ቀውስ ለማስተካከል መንግስት አፋጣኝ የማሻሻያ እርምጃዎች እንዲወስድ አሳስቧል።

#AddisAbaba🪧
በአዲስ አበባ ከተማ ህገወጥ የውጭ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች እየተነሱ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ዛሬ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02፣ 08፣ 10 እና 13 በህገ ወጥ መንገድ መሰረተ ልማት አውታሮች እና የዋና መንገድ ኤልክትሪክ ፖሎች ላይ የተሰቀሉ ህገ ወጥ የውጭ ማስታውቂያ ማንሳቱን አስታውቋል።
ህገ ወጥ የውጭ ማስታወቂያዎች የተነሱባቸው ቦታዎች ፦
👉 ከሳህሊተ ምህረት እስከ የተባበሩት ግራ እና ቀኝ ፣
👉 ከተባበሩት እስከ ፍየል ቤት ፤
👉 ከፍየል ቤት እስክ ፊጋ
👉 ከተባበሩት እስከ አያት አደባባይ
👉 ከአያት አደባባይ እስከ ጣፎ አደባባይ ድረስ በግራና በቀኝ በኩል ተሰቅለው የነበሩ ህገ ወጥ የውጭ ማስታወቂያ ሙሉ በሙሉ መነሳቱን አሳውቋል።
በቀጣይም በሌሎች ክፍለ ከተሞች የተሰቀሉ ህገወጥ የውጭ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች የማንሳት ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።
መረጃው የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ነው።

#EthioTelecom
ኢትዮ ቴሌኮም ለተማሪዎች ልዩ ጥቅል ማቅረቡን ገለፀ።
ኢትዮ ቴሌኮም ለኮሌጅ እና ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልዩ የሆነ የተማሪ ጥቅል ማቅረቡን አሳውቋል።
በዚህም :
ወርሃዊ ፦
• ዋጋ 👉 34 ብር ፤ ጥቅል 👉 180 ደቂቃ (ጥሪ) ፤ ስጦታ 90 ደቂቃ (ጥሪ) + 100 መልዕክት ፤
• ዋጋ 👉 64 ብር ፤ ጥቅል 👉 360 ደቂቃ (ጥሪ) ፤ ስጦታ 200 ደቂቃ (ጥሪ) + 150 መልዕክት ፤
• ዋጋ 👉 42 ብር ፤ ጥቅል 👉 1 GB (ዳታ) ፤ ስጦታ 512 MB (ዳታ) + 100 መልዕክት ፤
• ዋጋ 👉 82 ብር ፤ ጥቅል 👉 2 GB (ዳታ) ፤ ስጦታ 1.1 GB (ዳታ) + 150 መልዕክት ፤
ሳምንታዊ ፦
• ዋጋ 👉29 ብር ፤ 3 GB (ዳታ) መሆኑ ተገልጿል።
ኢትዮ ቴሌኮም ፤ ሳምንታዊው የዳታ ጥቅል እና ለደንበኞች የቀረቡት ስጦታዎች የሚያገለግሉት ከለሊቱ 6 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት መሆኑን አሳውቋል።
ተማሪዎች ተማሪነታቸውን የሚገልፅ " መታወቂያ " በመያዝ በኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከሎች በመቅረብ ጥቅሎቹን መግዛት ይችላሉ ተብሏል።

#MinjarShenkora📍
በምንጃር ሸንኮራ በተፈፀመ ጥቃት የሰው ህይወት አለፈ።
በወረዳው " አሞራ ቤት ቀበሌ " ላይ ታጣቂዎች ፈፀሙት በተባለው ጥቃት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።
ጥቃቱ ከኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በሆነዉ አሞራቤት ቀበሌ " አዉራ ጎዳና መንደር ትናንት ከሰዓት የተፈፀመ ሲሆን የሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ከሚል መረጃ ውጭ ምን ያህል የሚለው አልታወቀም።
ወረዳው ጥቃቱን ያደረሱ ታጣቂዎች ምናልባት ማንነታቸው ያልታወቁ " የፀረ ሰላም ኃይሎች " ሊሆኑ ይችላሉ ብሏል።
የምንጃር ሸብኮራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ቦሰት ጥቃቱን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ፦
" ትላንትና መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ ከኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ አዋሳኝ በሆነዉ አሞራቤት ቀበሌ ልዩ ቦታዉ አዉራ ጎዳና ተብሎ በሚጠራ መንደር ላይ ታጣቂዎች በተደራጀ እንዱሁም በቡድንና በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ባደረሱት ጥቃት የሰዉ ህይወት ሲያልፍ በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል " ብለዋል፡፡
በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸዉ ግለሰቦች በአረርቲ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልና ወደ አዲስ አበባ ከተማ ተልከዉ ህክምና እየተደረገላቸዉ መሆኑንም ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል።
" አካባቢዉ ለዓመታት የተለያዩ ትንኮሳዎች ይስተዋልበት ነበር ያሉት " አቶ ታደሰ ፤ " የትናንቱ ግጭት ግን መነሻዉ በግልፅ የማይታወቅ ፤ ምናልባትም ማንነታቸዉ በግልፅ ያልታወቁ ፀረ ሰላም ኃይሎች አቅደዉበት እና አካባቢዉን በማዉደም ነዋሪዎችን ለማፈናቀል አልመዉ የመጡ ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል " ብለዋል፡፡
አቶ ታደሰ ቦሰት " ለጊዜዉ ማንነታቸዉ ያልታወቁ ታጣቂዎቹ ጥቃት ማድረሳቸዉን ተከትሎ ንፁሀን እንዳይጎዱ በተለይ ሴቶችን ህፃናትንና ነፍሰጡሮቹን ከስፍራዉ የማዉጣት ስራ ተሰርቷል " ያሉ ሲሆን " ቤት ንብረታቸዉን ትተዉ ወደ ጫካ የሸሹ በመኖራቸዉና ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ የስልክ ግንኙነት ባለመኖሩ ተጨማሪ የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ ማወቅ እንዳልተቻለ ገልፀዋል።
" ትናንትና አመሻሽ ከ12፡00 በኋላ በአካባቢዉ የፌደራል ፖሊስ በመግባቱና የማረጋጋት ስራ በመሰራቱ አሁን ጥቃቱ በቁጥጥር ስሮ ዉሏል " ብለዋል።
" የአካባቢዉን ሰላም ለማናጋት ከሁሉም ወገን የፀረ ሰላም ኃይሎች ሊኖሩ ይችላሉ " ያሉት አቶ ታደሰ ፤ " በማጥራት እና የጋራ ምክክር በማድረግ የአካባቢዉን ሰላም በዘላቂነት ለማስፈን በቀጣይ በትኩረት ሊሰራ የሚገባ ጉዳይ ነዉ " ብለዋል።
ወረዳው በትላንትናው ጥቃት አድራሾቹ " የማይታወቁ ፤ ፀረ ሰላም ኃይሎች " እያለ መጥራቱ ቅሬታ ያሳደረባቸው አካላት እንዲህ ያለው መሸፋፈን ይበልጥ ችግሩን ከማወሳሰብ በዘለለ ምንም አይነት ፋይዳ እንደሌለው አስገንዘበዋል።
ከዚህ በፊት በተለያዩ የሀገሪቱ ቦታዎች ለሚፈፀሙ ጥቃቶች " ማንነታቸው ያልተረጋገጠ፣ ፀረ ሰላም ኃይሎች " የሚሉ ቃላትን መጠቀም የተለመደ ነው።

#ZHAddis
እጆላይ ያለው ካሜራ ጊዜ በሄደ ቁጥር የሚሰጠው ጥቅም ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ዝቅ እንደሚል ያቃሉ ከማይፈለግ እቃጋ ሳይመደብ አሁኑኑ እኛ ዘንድ ይዘው ይምጡ እንዳይቆጩ አርገን በጥሩ ዋጋ እንገዞታለን።
ይደውሉልን : 0911156257 ከታች ያለውንlink በመጫን የቴሌግራም አባል ይሁኑ https://yangx.top/joinchat/AAAAAEUTeB3LSYVFukiuQw
ቦሌ ወሎሰፈር HMM ህንፃ 2ኛ ፍቅ205

#TikvahSport
ቲክቫህ ስፖርት እና ዘራፍ ቶርናመንት ከጋስት ኢንተርቴመንት እንዲሁም ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር #በጋስትሞል ላይ ያዘጋጁት " #FIFA 22 " ውድድር ምዝገባው ተጀምሯል ።
ውድድሩ ለመጫወት ምቹ በሆነው ጋስት ሞል በPS4 የሚካሄድ ይሆናል። የውድድሩ ተሳታፊዎች በተለያዩ ዙሮች በርካታ ሽልማቶችን ይሸለማሉ።
የውድድሩ የፍፃሜ ተጫዋቾቻችን ውድድራቸውን በኩሪፍቱ ሪዞርት ላይ ያካሂዳሉ።
ለመመዝገብ እንዲሁም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት https://zeraftournament.com/ ወይም በቴሌግራም @Zeraf_Tournament ላይ ማግኘት ይችላሉ።
ቻናል :- https://yangx.top/ZerafTournament

#ETHIOPIA
የዩክሬንና ሩስያ ጦርነት በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና የገቢ እቃዎች ማጓጓዝ ላይ ጫና ፈጥሯል።
ይህንን ጫና ለማቅለል አማራጭ እየተፈለገ መሆኑን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ማስታወቁን ኢዜአን ዋቢ አድርጎ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።
አንድ ወር ያለፈው የዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት በዓለም ሀገራት ላይ ዘርፈ ብዙ አሉታዊ ተፅእኖዎችን እያሳደረ ሲሆን የነዳጅ፣ የምግብ ፣ የምግብ ዘይት እና ሌሎች ምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እንዲፈጠር አድርጓል።
ጦርነቱ በባህር ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ከባድ ፈተናን መደቀኑን የገለፁት የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የባህር ትራንስፖርት ዘርፍ ም/ስራ አስፈፃሚ ወንደሰን ካሳ ፤ የኢትዮጵያ መርከቦች የአገልግሎት ወጪ እየጨመረ ይገኛል ሲሉ አሳውቀዋል።
በተለይ ደግሞ የነዳጅ ወጪ ካለፈው 6 ወራት ወዲህ የ42% ጭማሪ ሊያስከትል ይችላል ብለዋል።
አቶ ወንደሰን ፤ ዩክሬን እና ሩስያ ከአውሮፓ እና ኤዥያ ሀገራት መተላለፊያ በመሆናቸው በተለይ በባቡር ለሚጓጓዙ ምርቶች ከፍተኛ ችግር መሆኑን ገልፀዋል።
በ2021 ላይ 1.5 ሚሊዮን ኮንቴነሮች በባቡር መጓጓዙን ተናግረው በዚህ ዓመት የሚቋረጥ ከሆነ ከ5% - 8% እቃዎች ወደ ባህር ትራንስፖርት ሊመጡና ጫና ሊፈጠር ይችላል ፤ በዚህም ጦርነቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የባህር ትራንስፖርት እጥረት እና በባህር በሚጓጓዙ እቃዎች ላይ የጭነት ዋጋ ጭማሪ ሊያስከትል እንሰሚችል ገልፀዋል።
ያንብቡ : telegra.ph/Ethiopia-03-30

የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ተፅእኖ በስፔን !
በስፔን ሀገር በ37 ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የዋጋ ግሽበት ተመዘገበ።
በሀገሪቱ በመጋቢት 9.8 % ግሽበት የተመዘገ ሲሆን ይህም በ37 ዓመት የታየ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት ነው።
የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ፤ ጦርነቱን ተከትሎ በሩስያ ላይ እየተጣሉ ያሉ ማዕቀቦች፣ ሩስያም ማዕቀብ በሚጥሉባት ላይ እየጣለች ያለው ማዕቀብ በበርካታ ሀገራት ላይ በግልፅ የሚታይ ተፅእኖ እሳደረ ይገኛል።
በስፔን በ37 ዓመታት ውስጥ የተመዘገበው ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት በሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የኢነርጂ ዋጋ መጨመሩን ተከትሎ ሲሆን በሀገሪቱ መንግስት ላይ ጫና ፈጥሯል ተብሏል።

የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ተፅእኖ በስፔን ! በስፔን ሀገር በ37 ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የዋጋ ግሽበት ተመዘገበ። በሀገሪቱ በመጋቢት 9.8 % ግሽበት የተመዘገ ሲሆን ይህም በ37 ዓመት የታየ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት ነው። የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ፤ ጦርነቱን ተከትሎ በሩስያ ላይ እየተጣሉ ያሉ ማዕቀቦች፣ ሩስያም ማዕቀብ በሚጥሉባት ላይ እየጣለች ያለው ማዕቀብ በበርካታ ሀገራት ላይ በግልፅ…
ከፍተኛ የተባለ የዋጋ ግሽበት በጀርመን እና ቤልጂየም ተመዘገበ።
በጀርመን በመጋቢት ወር 7.3% የሆነ የዋጋ ግሽበት የተመዘገበ ሲሆን ይህም ከ30 ዓመት በኃላ (ከጀርመን ውህደት በኃላ) የተመዘገበ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት ነው።
በቤልጂየም ደግሞ 8.31% የዋጋ ግሽበት የተመዘገበ ሲሆን ይህም ከ39 ዓመታት በኃላ የተመዘገበ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት ነው።
እስካሁን ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ መፍትሄ ያላገኘው የዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት በዓለም ሀገራት ላይ እያሳደረ ያለው ተፅእኖ እየከፋ ነው፤ ጦርነቱ መቋጫ ካላገኘ ተፅእኖው አሁን ካለውም እጅግ ሊከፋ ይችላል ተብሎ ይገመታል።
በታዳጊ ሀገራት ላይ ይዞት እየመጣው ያለው መዘዝም ከባድ ነው።

#ETHIOPIA #KENYA
ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገር ኬንያ ጋር በሰላምና የደህንነት ጉዳዮች ለመተባበር ተስማምታለች።
ዛሬ የኢፌዲሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የኬንያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሮበርት ኪቢቹ ኬንያ፣ ናይሮቢ ውስጥ ተወያይተዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከኬንያ አቻቸው ጄኔራል ሮበርት ኪቢቹ ጋር ባደረጉት ምክክር ሁለቱ አገሮች በሁለትዮሽና በአካባቢያዊ የፀጥታ ጉዳይ ለመተባበር ተስማምተዋል፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያና ኬንያ በሠላም እና ደህንነት እንዲተባበሩ የተመቻቸ ሁኔታ እና ዕድል እንዳለ ገልፀዋል፡፡
ጄኔራል ኪቢቹ ፤ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በኬንያ ቆይታ በማድረጋቸው መደሰታቸውን ጠቅሰው '' አገሮቻችን የረⶵም ጊዜ ወዳጅ ናቸው ይህንን የበለጠ ማጠናከር ይገባናል '' ብለዋል፡፡
የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹምቹ ፦
👉 በስልጠና፣
👉 በሠላምና ደህንነት ማስከበር ዘርፎች ለመደጋገፍ ከመግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡
ኢትዮጵያና ኬንያ አባል የሆኑበትንን የምስራቅ አፍሪካ የተጠንቀቅ ኃይልን ለማጠናከር በግንባር ቀደምትነት ለመስራት ተስማምተዋል።
መረጃው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#ETHIOPIA ኢትዮጵያ ከሳዑዲ ተመላሽ ዜጎቿን መቀበል ጀምራለች። በዛሬው ዕለትም 157 ህፃናት እና 314 ሴቶች በድምሩ 498 ዜጎች በሰላም ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። በቀጣይ ከ7 እስከ 11 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ ዜጎችን ለመመለስ እቅድ ተይዟል። Via @tikvahethmagazine
#Update
ከሳኡዲ አረቢያ በሁለተኛ ዙር 438 ወገኖቻችን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።
ዛሬ ከሰዓት በሁለተኛው ዙር በረራ 438 ወገኖቻችን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ዛሬ ማለዳ በመጀመሪያ ዙር 498 ወገኖቻችን ወደሀገር መግባታቸው ይታወሳል።