TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#AAU

አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2013 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርዓት ነገ ያከናውናል።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮችና መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 6 ሺህ 163 ተማሪዎች ነገ መስከረም 29/2014 ዓ.ም ያስመርቃል።

ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 3 ሺ 604ቱ በመጀመሪያ ዲግሪ የሚመረቁ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ 2 ሺህ 559 ተማሪዎች የድህረ ምረቃ ተመራቂዎች ናቸው።

155 ተማሪዎች በሦሥተኛ ዲግሪ (PhD) የሚመረቁ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ዳይሬክተር ጥላሁን ተስፋዬ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

የምረቃ ስነ ስርዓቱ በሸገር ፓርክ የወዳጅነት አደባባይ እንደሚከናወን ታውቋል።

ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦች የትምህርት ተቋማትን ብቻ ትኩረት አድርጎ መረጃ የሚልክላችሁን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገፅ መቀላቀል ትችላላችሁ : https://yangx.top/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ካለባቸው አካባቢዎች የመጡና የተመረቁ ተማሪዎቹ በታኅሳስ መጨረሻ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበ፡፡

እነዚህ 41 የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪዎች፣ ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ አካባቢ፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን እና ከትግራይ ክልል የመጡ ሲሆኑ፣ የመጡበት አካባቢ የፀጥታ ችግር በመኖሩ ከተመረቁ በኋላም በዩኒቨርሲቲው ለመቆየት ማመልከቻ አስገብተው ነበር፡፡

ተማሪዎቹ ከተመረቁ በኋላ በግቢው ውስጥ ሆነው የመኝታና የምግብ አገልግሎት ሲያገኙ መቆየታቸውን የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና የተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ማቲዮስ ኤርሳሞ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ ግን ተማሪዎቹ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ማሳሰቢያ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡

አንዳንድ ተመራቂዎቹ አዲስ አበባ ውስጥ ሥራ ካገኙ በኋላም በግቢው መኖር ቀጥለዋል ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ ተማሪዎቹ የመጡበት አካባቢ በትክክል የፀጥታ ስጋት ያለበት ስለመሆኑ ማረጋገጥ አለመቻሉን ገልጸዋል።

ከትግራይ ክልል የመጡት ተመራቂዎች በጊዜ ሂደት ሥራ በማግኘታቸውና ወደ መኖሪያቸው በመመለሳቸው አሁን ላይ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያሉ ከትግራይ የመጡ ተማሪዎች ቁጥር 'ጥቂት' መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

''ተማሪዎች ከተመረቁ በኋላ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ያላቸው ሕጋዊ ውል ይቋረጣል'' ያሉት ኃላፊው፤ ዩኒቨርሲቲው ለተመረቁ ተማሪዎች ወጪ የማውጣት ሥልጣን እንደሌለው ገልጸዋል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን መስከረም 30/2014 ዓ.ም ማስመረቁ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahuniversity