TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#አረንጓዴ_አሻራ በሀገር ደረጃ እስካሁን በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ቀን 232 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ይህንን ያስታወቁት በወላይታ ሶዶ ከተማ ከአካባቢው የህብረተስብ ክፍሎች ጋር እየተወያዩ ባሉበት ወቅት ነው።

#አሁን በደረሰን መረጃ በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት ከተተከሉት ችግኞች ውስጥ በኦሮሚያ 132 ሚሊዮን ፣ በደቡብ 45 ሚሊዮን፣ በትግራይ ስምንት ሚሊዮን 400ሺህ አማራ 38ሚሊዮን እና አዲስ አባባ ከሶስት ሚሊዮን በላይ የተከናወኑ ይገኙበታል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ዛሬ ጥዋት 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ለመትከል የታቀደው 200 ሚሊዮን ቢሆንም እስካሁን የተከናወነው ከዚህ በላይ መድረሱን ነው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ ለማወቅ የተቻለው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሁን

"የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ያልተቋጨ የቤት ሥራ" በሚል ርዕስ በዶክተር በለጠ በላቸው ይሁን ተፅፎ በ "ኢትዮጵያ አካዳሚክ ፕሬስ" የታተመ መፅሐፍ በሂልተን ሆቴል የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ፣ ሙሁራን ፣ የሚዲያ ባለሞያዎችና የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት በመመረቅ ላይ ይገኛል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የመክፈቻና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት የተላለፈ ሲሆን በደንበር ጉዳዮች ዙርያ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች የሚመረምሩና የሚያጠኑ እንዲሁም በተግባር ስራ የሚሳተፉ ባለሞያዎች በመፅሐፉ ዙርያ ግመገማ ቀርቦ ውይይት በመከናዎን ላይ ይገኛል።

Via Bereket H.

@tikvahethiopia