TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የWFP ሪፖርት ምን ይላል?

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜን ኢትዮጵያ የከፋ ረሃብ ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቋል።

#ትግራይ

በትግራይ ክልል ውስጥ 40 በመቶ የሚጠጉ ሰዎች በከፍተኛ የምግብ እጥረት ውስጥ ናቸው።

በትግራይ ክልል በተደረገው አስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዋስትና ግምገማ 83% የሚሆነው ሕዝብ የምግብ ዋስትና ችግር አጋጥሞታል።

በዚህ ሳቢያ የተለያዩ ቤተሰቦች ያላቸውን ምግብ ሁሉ አሟጠው በመጨረሳቸው ጥራጥሬ ብቻ መመገብና የሚመገቡትን የምግብ መጠን ለመቀነስ ተገደዋል።

ከተመጣጣነ ምግብ አንጻር ግምገማው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ትግራይ ውስጥ ከሚገኙ ልጆች መካከል 13% እና ከነፍሰጡር ሴቶች ግማሽ ያህሉ እንዲሁም ጡት የሚያጠቡ እናቶች ለተለያዩ ችግሮች በሚያጋልጥ ሁኔታ የተመጣጠነ ምግብ ችግር ገጥሟቸዋል።

#አማራ

በአማራ ክልል በቅርቡ በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ባለፉት 5 ወራት የረሃብ ሁኔታ ከእጥፍ በላይ ጨምሯል።

በዚህ ሳቢያ ከ5 ዓመት በታች ከሆኑ ህጻናት መካከል 14%ና አንድ ሦስተኛ የሚሆኑ ነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶች የተመጣጣነ ምግብ ችግር አጋጥሟቸዋል።

#አፋር

በአፋር ክልል በጦርነት በተከሰቱ መፈናቀሎች ምክንያት ረሃብና የተመጣጠነ ምግብ ችግር መጠን ከፍ ብሏል።

በቅርቡ የተሰበሰበ መረጃ በክልሉ ከ5 ዓመት በታች ከሆኑ ህጻናት መካከል 28 በመቶው የተመጣጠነ ምግብ ችግር አጋጥሟቸዋል።

#ሰሜንኢትዮጵያ- WFP በተያዘው የፈረንጆች ዓመት በሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ከ9 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች እርዳታ ማቅረብ ያስፈልጋል ብሏል።

በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ኃይሎች የእርዳታ አቅርቦት እንዲጓጓዝ እንዲፈቅዱ ጠይቋል፥።

ሙሉ ሪፖርት www.wfp.org/news/severe-hunger-tightens-grip-northern-ethiopia?s=09

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert መንግስት የህወሃት ቡድን ለሚፈፅመው ትንኮሳ የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የክልል ጸጥታ ሃይሎች በጥናት ላይ ተመስርተው እርምጃ የሚወስዱበትን አቅጣጫ ማስቀመጡን ዛሬ አስታወቀ። ይህ የተሰማው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተመራው የፌደራል ጸጥታ ም/ቤትና የክልል ርእሳነ መስተዳደሮች በሀገራዊ ጸጥታ ሁኔታ ላይ በተወያዩበት ወቅት ነው። በውይይቱ ላይ የህወሃት ቡድን የሚያደርገውን…
"ኢመደበኛ አደረጃጀት"

የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ስለ " ኢ-መደበኛ አደረጃጀት " ምንድነው ያሉት ?

አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፦

" ... ኢመደበኛ አደረጃጀት ያልናቸው አንዳንዶች በጦርነቱ ወቅት በጣም ከፍተኛ የሆነ ድርሻ የነበራቸው አሉ። አንዳንዶች ግን ጦርነቱን የሆነ ከተማ ውስጥ ሆነው በፌስቡክ፣ በዩትዩብ፣ ልክ እዛ ሆነው ምሽግ እንደሰበሩ የሚያሳዩ።

አሁንም ደግሞ ልክ ትላልቅ እጀባዎች የሚመስል ሰራዊት እያስከተሉ የሚንቀሳቀሱ አካላት አሉ። ነገር ግን በጦርነቱም በውጊያውም ምንም አይነት ተፅእኖና ይሄን አደረጉ ብሎ ለመናገርም ሚያሳፍሩ ብድኖች፣ ግለሰቦች እየተፈጠሩ ነው ያሉት።

እነዚህ ማህበረሰቡ አስታግሱልን የሚል እና ቀስ በቀስ በወደዝርፊያም ወደሌላም ጉዳዮች የሚሄዱ ናቸው ከውጭም ከውስጥም እነዚህን በገንዘብ የሚደግፍ ኃይል አለ፤ ልክ እንደተገዳዳሪ ነገር ለመቁጠር የመፈለግ ነገር አለ።

ኢመደበኛ አደረጃጀት መንግስት ተዳከመ በሚል እሳቤ የሚፈጠሩ ናቸው በብዛት።

እናም በእነዚህን ጉዳዮች ህብረተሰቡም ያነሳው ጥያቄ አለ አስታግሱልን የሚል ስለዚህ እነዚህ ስርዓት እንዲይዙ ይሰራል።

እነዚህ ኃይሎች መንግስትን በማጥላላት እና እንገዳደራለን በሚል ብቻ ሳይሆን ከመጋረጃ ጀርባ ደግሞ በመሳሪያ ንግድ ፣ በተተኳሽ ንግድ በጣም ከፍተኛ የሆነ ስራ የሚሰሩ ፣ ገንዘብ ለማከማቸት የሚፈልጉ ፣ ያለ አግባብ ግብር በነጋዴዎች ላይ የሚጥሉና ህብረተሰቡን የሚያስቸግሩ አካላት ናቸው።

በጥናት ላይ ተመስርቶ የክልል የፀጥታ ኃይሎች ፣ የክልል የፀጥታ አስተዳደር መዋቅሮች እነዚህን ኃይሎች መከላከል እና ስርዓት ማስያዝ አለባቸው የሚል ተነጋግረናል ፤ አቅጣጫም ተቀምጧል "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines " የማክስ አውሮፕላናችንን ዳግም ወደ በረራ ለመመለስ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውናል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፌዴራል አቪዬሽን አድሚኒስትሬሽን /FAA/ ፣ የአውሮፓ ህብረት አቪየሽን ደህንነት ኤጀንሲ /EASA/ ፣ CAAC ፣ ECAA እንዲሁም ሌሎች በርካታ የአቪየሽን ተቆጣጣሪ አካላት በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ላይ ጥልቅ ምርመራና ፍተሻ ካደረጉና ዳግም ማረጋገጫ…
#Update

እንሆ ከ3 ዓመት በኃላ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ወደ በረራ ተመልሷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ3 ዓመታት በኋላ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የመጀመሪያ የሙከራ በረራ በተሳካ ሁኔታ ማከናወኑን አስታውቋል።

የሙከራ በረራውን ያከናወነው ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ባካሔደው የደርሶ መልስ በረራ ነው።

ለሙከራ በረራው እ.አ.አ በ2018 የቦይንግ አውሮፕላን በረራ መቆጣጠሪያ ክፍሉ ላይ በታየው የቴክኒክ ችግር ምክንያት አደጋ ከተከሰተ በኋላ የበረራ አገልግሎት እንዳይሰጡ ከታገዱት አውሮፕላኖች መካከል ቦይንግ 737 ET-AVI ET 9201 የተባለ አውሮፕላን መጠቀሙ ተገልጿል።

#ENA

@tikvahethiopia
#Afar

የአፋር ህዝብ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ህወሓት ከጥር 15 አንስቶ በከባድ መሳሪያ በመታገዝ በመጋሌ፣ አብአላ፣ በራሃሌ፣ ኮነባ፣ ኢሬብቲ ወረዳዎች ላይ መጠነ ሰፊ ወረራ እያካሄደ ነው ሲል አሳውቋል።

ፓርቲው ፥ ቡድኑ በትግራይ ህዝብ ላይ ዘመን የሚሻገር ጠባሳን የሚያስቀር እና ለረጅም ዘመናት አብሮት የኖረውን ወንድምና ጎረቤት የሆነውን የአፋር ህዝብ ጋር የሚያቃቅር ስራ እየሰራ ይገኛል ብሏል።

የትግራይ ህዝብም ይህን ኃይል አስቁሞ መሰረታዊ ጥያቄ መጠየቅ እንዳለበት አስገንዝቧል።

ፓርቲው ፥ የህወሓት ቡድን በአሁን ሰዓት አንዴ " የቀይ ባህር አፋሮች ፣ አንዴ የኤርትራ ወታደሮች " ወገኙ በሚል ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ዓለምን ለማደናገር እየሞከረ ነው ብሏል።

ህወሓት በአፋር ላይ ግልፅ የዘር ማጥፋት ዘመቻ እየፈፀመ ነው ያለው የአፋር ህዝብ ፓርቲ ይህንን የዓለም በተለይ የአፋር ህዝብ እንዲገነዘበው ፣ በዛው ልክ እራሱን ለመከላከል መዘጋጀት አለበት ብሏል።

ፓርቲው በመግለጫው የህወሓት ቡድን ከያዛቸው የአፋር አካባቢዎች እስካልወጣና ከባድ መሳሪያዎቹ ለአፋር ሕዝብ ስጋት ወደ ማይሆኑበት ደረጃ እስካልወረደ ይህም ደግሞ እስኪረጋገጥ ድረስ ከዚህ ቡድን ጋር የሚደረግ ወይንም ሊደረግ የታሰበ ድርድር ካለ የአፋር ሕዝብ ይህንን አካሄድ የማይቀበል መሆኑን ገልጿል።

ይህ ድርጊትም እንደ ሀገራዊ ክህደት የሚቆጥር መሆኑን አሳስቧል።

በተጨማሪ ፓርቲው ለህወሓት ጥብቅና ቆመዋል ላላቸው አንዳንድ ሀገሮች እና አለም አቀፍ ድርጅቶች ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

የአፋር ህዝብ በዚሁ ቡድን እየተገደለ ባለበት በአሁን ሰዓት ለቡድኑ ድጋፍ እየሰጡ የሚቀጥሉ ከሆነ የአፋር ሕዝብ ለዚህ እኩይ ተግባር ምንም አይነት ትብብር አንደመይሰጥ ፓርቲው በመግለጫድ አሳስቧል።

ከዚህ ባለፈ ፓርቲው ፌዴራል መንግሰት አውጆት የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማንሳት ያቀረበው ሀሳብ የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ያላገናዘበ በመሆኑም በተለይ በአፋር እና አማራ ክልሎች ላይ እንዲቆይ አሳስቧል።

ህዝቡ ራሱን እንዲከላከል አስፈላጊ እገዛ እንዲደረግለት እና በሰላም ስም ማዘናጋቱ አንዲቆም ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ስላለ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጠውም አሳስቧል።

በመንግስት መግለጫዎች ላይ የአፋርን ችግር ችላ ለማለት ሲሞከር እየተስተዋለ በመሆኑ ይህ ጉዳይ በአስቸኳይ ሊታረም እንደሚገባውም የአፋር ህዝብ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ አስገንዝቧል።

@tikvahethiopia
#WolloUniversity

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተቋርጦ የቆየውን የ2014 ዓ.ም የአንደኛ ሴሚስተር #የኤክስቴሽን ትምህርት ከየካቲት 05/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለማስቀጠል ወስኗል።

በመሆኑም ቀደም ሲል የተመዘገቡ ነባር የመጀመሪያ እና የ2ኛ ዲግሪ የኤክስቴሽን ተማሪዎች ምዝገባ ያደረጉበትን ስሊፕ በመያዝ ሪፖርት እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

አዲስ መመዝገብ የሚፈልጉ የመጀመሪያ እና የ2ኛ ዲግሪ የኤክስቴሽን አመልካቾች ጥር 28 እና 29/2014 ዓ.ም ያለቅጣት መመዝገብ እንደሚችሉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

@tikvahuniversity @Tikvahethiopia
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር በጦርነት ምክንያት የወደሙ እና የፈረሱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ከ1ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ መመደቡን አሳውቋል።

በአማራ እና አፋር ክልሎች ሙሉ በሙሉ የወደሙ 1 ሺህ 93 ትምህርት ቤቶች ሲሆኑ እነዚህ ትምህርት ቤቶች ተመልሰው እንደሚገነቡ ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Woldia

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እና ለአማራ ክልል መንግሥት ጥያቄዎችን ማቅረቡን ገልጿል።

ከተማ አስተዳደሩ ቀደም ሲል የተጀመረውና ኅብረተሰቡ ለጤና እክልና ለተለያዩ ችግሮች እያደረገ ያለው የከተማዋ የአስፋልት መንገድ ግንባታ በፍጥነት ወደ ሥራ የሚገባበትን መንገድ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለ ስልጣን አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጠው ጥያቄውን አቅርቧል።

በተመሳሳይ ሁኔታ የኅብረተሰቡን የመልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በተገቢው መንገድ ምላሽ ለመስጠት ወቅቱን የሚዋጅ አደረጃጀት መፍጠር የሚያስችለውን የከተማዋን የሪጅዮ ፖሊታንት መዋቅር ጥያቄ ለክልሉ መንግሥት በድጋሜ በጽሑፍ አቅርቧል።

ከተማ አስተዳደሩ ለከተማዋ መልማት ከፍተኛ ሚና ያላቸውን ተገቢ ጥያቄዎች የከተማዋን እድገት የሚመኝ ሁሉ ጉዳዮቹን አጀንዳ በማድረግ ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረቡን ከወልዲያ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#Hossana

የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሀዉልት ነገ እሁድ በሆሳዕና ከተማ ይመረቃል።

ለዚህ የምረቃ ስነስርዓት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ወደ ሆሳዕና ከተማ ይገባሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

የሀዲያ ዞን አስተዳደር ወደ ከተማው የተጋበዙትን እንግዶች በሠላማዊ መንገድ ለመቀበልና ለማስጎብኘት እንዲያስችል መላዉ የዞኑና የከተማዉ ነዋሪዎች የአካባቢዉን ሠላምና ፀጥታ በመጠበቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል።

በሌላ በኩል የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስን ጀግንነት የሚዘክር የፎቶ ኤግዚቢሽን ዛሬ በሆሳዕና ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

መረጃው ከሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
አጭር ማስታወሻ ፦

1ኛ. በአዲስ አበባ በጊዜያዊነት ታግዶ የነበረው መሬት ነክ አገልግሎት አሁን ላይ እግዱ ተነስቶ አገልግሎቱ በየክፍለ ከተማው እየተሰጠ ነው። ታግደው ከነበሩ አገልግሎቶች መካከል ጊዜያዊ እግድ የተነሳላቸው አገልግሎቶች ዝርዝር በዚህ ይመልከቱ : https://yangx.top/tikvahethiopia/66990?single

2ኛ. ተቋርጦ የቆየው የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭ ሆነ በስጦታ የማስተላለፍ ውል ከሰኞ ጥር 23/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ይጀምራል። አገልግሎቱን ለማግኘትና የጉዳይ መከታተያ ቁጥር በኦንላን ለማግኘት www.dars.gov.et ይጠቀሙ።

3ኛ. ዩኤኢ (UAE) ኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ላይ ጥላው የነበረው የጉዞ እገዳ ከዛሬ ቅዳሜ ጀምሮ ተነስቷል። በተያያዘ ማስታወሻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛሬ ጀምሮ የዱባይ በረራውን ይቀጥላል።

4ኛ. በወሰን ማስከበር ምክንያት ሳይጠናቀቅ የቆየው የገርጂ ሮባ ዳቦ -መብራት ኃይል (አዲስ አበባ) አስፓልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቆ ሙሉ ለሙሉ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል።

5ኛ. በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ማስክ ያላደረጉ አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች ከተገኙ ብር 1 ሺህ ይቀጣሉ ፤ ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪ በሚጭኑበት ወቅት ደግሞ በአንድ ሰው 500 ብር ይቀጣሉ።

6ኛ. የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ የመታሰቢያ ሀዉልት ነገ እሁድ በሆሳዕና ከተማ ይመረቃል።

@tikvahethiopia
#UAE

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዩኤኢ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ አቡ ዳቢ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር የጋራ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
መነጋገሪያ የሆነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ?

የኢትዮጵያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በተረጋገጠ የፌስቡክ ገፁ ላይ ዛሬ ያጋራው የአንድ ግለሰብ የፌስቡክ መልዕክት መነጋገሪያ ሆኗል።

የተረጋገጠው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌስቡክ ገፅ ከአንድ ሰዓት በፊት ያጋራው እና እስካሁን ያልተነሳው " Musa Gobena " በሚል ስም የሚጠራ የግል አካውንት የተሰራጨ መልዕክት ነው።

መልዕክቱ " የፊንፊኔ ከተማ ቦታዎች የጥንት መጠሪያ እና አሁን ተቀይረው የሚጠሩበት ስም " የሚል ዝርዝር ነው።

ምክር ቤቱ በተረጋገጠው አካውንቱ ባጋራው መልዕክት ላይ ከላይ ምንም አይነት ተጨማሪ ማብራሪያ ያልሰጠበት ሲሆን እስካሁን ድረስ ከ290 በላይ የተለያዩ ይዘት ያላቸው አስተያየቶች ተሰጥተዋል።

ከ170 በላይ ሰዎች የፌዴሬሽን ምክር ቤቱን መልዕክት ለሌሎች አጋርተዋል። ከ567 በላይ ሰዎች ስሜታቸውን በተለያዩ ምልክቶች 👍❤️😡😁😱 ገልፀዋል።

ይበልጥ ይህንን ጉዳይ መነጋገሪያ ያደረገው መልዕክቱን ያጋራው ግለሰብ አካውንት ይዘት እራሱ መንግስትን ሚቃወሙ መልዕክቶች የሚጋሩበት መሆኑ ነው።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በተረጋገጠ የፌስቡክ አካውንቱ ስለወጣው መልዕክት በራሱ ገፅ ሆነ በሌላ የሚዲያ አማራጭ የሰጠው ማብራሪያ የለም።

@tikvahethiopia
#DStv የደስ ደስ!

ሊያመልጥዎ የማይገባ እድል ከዲኤስቲቪ ፤ ከጥር 2 እስከ መጋቢት 21 ድረስ ብቻ የሚቆይ!

በየወሩ የሜዳ ፓኬጅ 550 ብር ሲከፍሉ ባለ 1,300 ብር የሜዳ ፕላስ ፓኬጅ ስጦታ ያገኛሉ። በተመሳሳይ የሜዳ ፕላስ ፓኬጅ በ1,300 ብር ሲከፍሉ ባለ 2,600 ብር የፕሪምየር ፓኬጅ ስጦታ ያገኛሉ።

በእድሉ ፈጥነው ይጠቀሙ። ከከፈሉት የዲኤስቲቪ ፓኬጅ በላይ ያግኙ።

ክፍያ ለመፈፀም፣ፓኬጅዎን ለመቀየር እንዲሁም ሌሎች የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ : https://bit.ly/2WDuBLk

የዲኤስቲቪን ቤተሰብ ይቀላቀሉ! https://bit.ly/3D2O1t4