TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የስራ ጊዜ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን ያካሂዳል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልልና ህዝበ ውሳኔ ውጤትን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ @tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች የክልልነት ሕዝበ ውሳኔ ውጤት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በደብዳቤ ባሳወቀውና በአካል ቀርቦ ማብራሪያ በስጠው መሰረት ምክር ቤቱም ውይይት በማድረግና በተቀመጠው ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችና አግባብነት ባላቸው ሕጎች አንጻር መርምሮ እንዲያጸድቅ አፈ ጉባዔው በጠየቁት መሰረት ሕዝበ ውሳኔው በምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡

Via House of Federation of Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba : በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መሳለሚያ እህል በረንዳ አካባቢ አማኑኤል ጸጋ አብ ህንጻ ላይ የእሳት አደጋ ደርሷል። የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር እና ወደ ሌሎች እንዳይዛመት በእሳትና ድንገተኛ አገልግሎት ባለሙያዎች ፣ፖሊስ አባላት እና የአካባቢው ወጣቶች እየተረባረቡ ይገኛሉ ብሏል። የእሳት አደጋውን መንስኤ በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት እና ተያያዥ…
ፎቶ : ዛሬ ከሰዓት የእሳት አደጋ የደረሰበት መሳለሚያ እህል በረንዳ አካባቢ የሚገኘው አማኑኤል ጸጋአብ ህንጻ።

አደጋው ከሰዓታት በፊት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን አደጋው ለመቆጣጠር እና ወደ ሌላ ቦታ እንዳይሰፋ የአካባቢው ወጣቶችና ነዋሪዎች፣ የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የእሳትና ድንገተኛ አገልግሎት ባለሙያዎች ፣የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ርብርብ ማድረጋቸው ተገልጿል።

የእሳት አደጋውን መንስኤ ፣ በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት እና ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ይገልፃሉ ተብሏል።

Credit : AAPS

@tikvahethiopia
#US : አሜሪካ TPLF ከአማራ እና አፋር ክልሎች እንዲወጣ በድጋሚ አሳሰበች።

ዛሬ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ከአማራ እና አፋር ክልል እንዲወጣ፤ ወደ ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተማ የሚያደርገውን ግስጋሴ እንዲገታ አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ TPLF በከተሞች ላይ ከባድ መሳሪያዎችን ከመተኮስ እንዲቆጠብ ያሳሰበ ሲሆን ሁሉም ወገኖች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁም እንዲያደርጉ እና ድርድር እንዲጀምሩ ጥሪ አድርጓል።

መንግስት በመቐለ እና በሌሎች የትግራይ አካባቢዎች የፈፀማቸውን የአየር ድብደባዎች የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወገዘ ሲሆን አሜሪካ በትግራይ፣ በአማራ፣ በአፋር ሰብዓዊ ድጋፎችን ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗንም አሳውቋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚደርሰው የሰብዓዊ ድጋፎች እንዳይቆራረጡ፤ የሲቪሎች ደህንነት እንዲጠበቅና መብቶች እንዲከበሩና አጥፊዎች እንዲጠየቁም ጠይቋል።

* የሚኒስቴሩ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SUDAN : የሱዳን የፀጥታ ሀይሎች ተቃውሞዋቸውን በሰላማዊ መንገድ ለማሰማት አደባባይ በሚወጡ ዜጎች ላይ የሀይል እርምጃ እንዳይወስዱ አሜሪካና ብሪታኒያ አስጠነቀቁ። በዛሬው እለት የሱዳን ጦር በሲቪል አስተዳደሩ ላይ የወሰደውን እርምጃ በመቃወም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሲዳናውያን አደባባይ ወጥተው ተቃውሞዋችን እንደሚያሰሙ ይጠበቃል። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፤ የሱዳን የፀጥታ ሐይሎች…
ዛሬ የሱዳን ጦር 2 ሰልፈኞችን ገደለ።

በሱዳን የተካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በመቃወም በ100 ሺ የሚቆጠሩ ሱዳኒያውያን ዛሬ አደባባይ ወጥተው ነበር።

ሰልፉን ጠርተው የነበረው የዴሞክራሲ ተሟጋች ቡድኖች ናቸው።

በመላ ሀገሪቱ እንዲካሄድ ዛሬ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ የጀመረው ኦምዱርማን በተባለችው ከተማ ሲሆን ካርቱም ያሉ ሰልፈኞች ወዲያው ሰልፉን በመከተል የሲቪል አስተዳደሩ ወደ ቦታው እንዲመለስ ጠይቀዋል።

የሱዳን የሀኪሞች ህብረት እንዳስታወቀው አምዱርማን ከተማ ውስጥ 2 ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች በጥይት ተገድለዋል።

የሱዳን የፀጥታ ሀይሎች ተቃውሞዋቸውን በሰላማዊ መንገድ ለማሰማት አደባባይ በሚወጡ ዜጎች ላይ የሀይል እርምጃ እንዳይወስዱ አሜሪካና ብሪታኒያ ማስጠንቀቃቸው አይዘነጋም።

Credit : DW/AFP/Al Jazeera

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 14 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,458 የላብራቶሪ ምርመራ 384 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 425 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" እስካሁን ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት ደርሷል "- የአዲስ ከተማ ፖሊስ መምሪያ

መሳለሚያ እህል በረንዳ አካባቢ በአማኑኤል ህንፃ ላይ በተከሰተው የእሳት አደጋ እስካሁን 8 ሚሊዮን 370 ሺ 280 ብር የሚገመት ንብረት እንደወደመ የአዲስ ከተማ ፓሊስ መምሪያ አሳውቋል።

የእሳት አደጋውን መንስኤ እና ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ በቀጣይ ምርመራ ተደርጎ ይገለፃል ተብሏል።

@tikvahethiopia
#ጥቅምት24

የኢትዮጵያ የመንግስት ጥቅምት 24 የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) በሰሜን እዝ ላይ የተፈፀመው ጥቃት ታስቦ እንደሚውል አሳውቋል።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ዕለቱ “አልረሳውም፥ እኔም የኢትዮጵያ ሰራዊት ነኝ” በሚል መሪ ቃል ታስቦ እንደሚውል አሳውቋል።

ዕለቱ የሀገር መከላከያ ሰራዊቱ እየከፈለ ያለውን መስዋዕትነት ለማሰብ፣ ሁሉም ህዝብ የሀገሩ ጠባቂ እና ሰራዊት መሆኑን እንዲሁም ከመከላከያ ጎን መሆኑን የሚያሳይበት ይሆናል ተብሏል።

በተጨማሪ ፤ " ጥቅምት 24 በሚኖረው ስነ ስርዓት መስዋዕት የሆኑ የሰራዊት አባላትን እና የቡድኑን ክህደት ለማስታወስ በዕለቱ ጠዋት 3 ሰዓት ጀምሮ ሁሉም ህዝብ ለ45 ሰኮንዶች እጃቸውን ደረታቸው ላይ በማድረግ ይቆያሉ " የመንግስት ኮሚኒኬሽን ገልጿል።

የሻማ ማብራትና ደሙን እየገበረ ላለው ሰራዊት የደም ልገሳ መረሃ ግብር ይከናወናል ተብሏል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba : የኑሮ ዉድነትን ለመቀነስ "የእሁድ ገበያን" በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች መጀመራቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሳውቀዋል።

ገበያዎቹ በየሳምንቱ እሁድ የተለያዩ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን ለከተማው ነዋሪ በአነስተኛ ዋጋ አንደሚቀርቡም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።

በዚህም በአምራቾችና በሸማቾች መካከል ቀጥተኛ እና አጭር የግብኝት ግንኙነት እንዲኖር ማድረግ ይቻላል ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዋናነትም ህገ ወጥ የዋጋ ጭማሪና ሰዉ ሰራሽ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር አስቀድሞ መከላከል ያስችላል ብለዋል ።

በሁሉም የከተማው አቅጣጫ የሚገኙ ነዋሪዎች በእረፍት ቀናቸው በአቅራቢያቸድ ወዳሉት የእሁድ ገበያዎች በመሄድ መገበያየት እንደሚችሉ ወ/ሮ አዳነች አሳውቀዋል።

Credit : AAPS

@tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

" የተርባይኖቹ ሃይል ማመንጨት ተከዜና ጣና በለስ ግድቦችን በአንድ ጊዜ የማጠናቀቅ ያህል ነው " - ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ

የታላቁ የህዳሴ ግድብ 2 ተርባይኖች ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት መጀመር ተከዜንና ጣና በለስ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦችን በአንድ ጊዜ የማጠናቀቅ ያህል መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ አባል ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ገለጹ።

ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፥ በጣና በለስና በተከዜ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦች የሚመረተው የኤሌክትሪክ ሃይል የህዳሴው ግድብ ሁለቱ ተርባይኖች ከሚመነጩት ኤሌክትሪክ ሃይል እኩል ነው ብለዋል።

ሁለቱ ተርባይኖች ተጠናቀው ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት መጀመር ሁለት ግዙፍ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክቶች በአንድ ጊዜ እንደማጠናቀቅ ይቆጠራል ሲሉም ገልፀዋል።

ፕሮፌሰሩ ፥ ጣና በለስና ተከዜ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦች እንደቅደም ተከተላቸው 460ና 300 ሜጋ ዋት ሃይል እንደሚያመነጩ አውስተው፤ የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሃይል ማመንጫ ግድብ ሁለት ተርባይኖች ስራ መጀመር 750 ሜጋ ዋት ሃይል ስለሚያመነጩ ሁለት ትልልቅ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦችን የማጠናቀቅ ያህል ነው ብለዋል።

Credit : EPA

@tikvahethiopia