TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Balderas ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በነአቶ እስክንድር ነጋ የፍርድ ሂደት ችሎት ታድመው የነበሩ 42 የፓርቲው አባላት ታፍሰው ልደታ ክፍለ ከተማ የፖሊስ መምሪያ ከቆዩ በኋላ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው እንዲታሠሩ እንደተደረጉ ገልጿል። ከታሠሩት ውስጥ አስራ ሁለቱ (12) ሴቶች መሆናቸውን ፓርቲው አረጋግጫለሁ ብሏል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ…
#Balderas : ከታሰሩት የባልደራስ አባላት እና ደጋፊዎች መካከል 2ቱ በዋስ ሲለቀቁ 40ዎቹ ለሰኞ ተቀጥረዋል።

የእነ አቶ እስክንድር ነጋን የችሎት ውሎ ለመታደም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በጥቅምት 11/2014 የሄዱ 42 የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በትላንትናው ዕለት በፓሊስ መታሰራቸው መግለፁ ይታወሳል።

ባልደራስ ፓርቲ አባላቱ እና ደጋፊዎቹ የታሰሩት ፥ አቶ እስክንድር በእስር ቤት የደረሰባቸውን ድብደባ በችሎት ከሰሙ በኃላ እያለቀሱ ችሎቱን አቋርጠው ከችሎት ወጥተው በመንገድ ላይ እያኑ ነው ፖሊስ የታሰሩት ብሏል።

ታሳሪዎቹ ዛሬ ጠዋት 4 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ " ችሎት ውስጥ ረብሸዋል፣ ሲወጡ ደግሞ ፍትህ የለም ፣ መንግስት የለም በማለት ሁከት እና ብጥብጥ በመቀስቀስ " ሲንቀሳቀሱ መያዙን ገልጿል።

ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ የምስክሮችን ቃለ ለመቀበል እና ማስረጃቸውን ለማሰባሰብ የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ቆጠሮ ጠይቋል።

የ42ቱ ተጠርጣሪዎች ጠበቆች ፖሊስ ያቀረበው የጊዜ ቀጠሮ አቤቱታ ውድቅ እንዲሆን ጠይቀዋል።

"በችሎት ውስጥ ተፈጸመ ለተባለው ድርጊት ፖሊስ የሚመለከተው ሳይሆን በወቅቱ ችሎቱ በራሱ ትዕዛዝ የሚሰጥበት ነው። ሆኖም ግን ችሎቱ ምንም አይነት ትዕዛዝ ባልሰጠበት ፖሊስ ያቀረበው አቤቱታ ተገቢ አይደለም" ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ " ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀበት ምክንያት በሕግ ምንም አይነት ድጋፍ " የለውም በማለት የጊዜ ቀጠሮው ውድቅ እንዲሆን በመጠየቅ ከእስር እንዲለቀቁ ለፍ/ቤት ጥያቄ አቅርበዋል ።

ያንብቡ : telegra.ph/BALDERAS-10-22

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 17 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,292 የላብራቶሪ ምርመራ 620 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 512 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
ሻንጋይ ፋርማ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ሊያደርግ ነው።

በቻይና ሀገር 2ኛው ግዙፍ የመድሃኒት አምራች እና አካፋፋይ "ሻንጋይ ፋርማ /Shanghai Pharma/ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ ወስኗል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የአዋጭነት ጥናት ካጠናቀቀ በኋላ ነው ኢንቨስት ለማድረግ ውሳኔ ላይ የደረሰው።

የሻንጋይ ፋርማ ኩባንያ ተወካዮች ከአንድ ሳምንት በፊት በቻይና ከኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

የሻንጋይ ፋርማ ኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጆች በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
#Amhara : የአሜሪካ መንግስት ግጭት ባለባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች በችግር ላይ ለወደቁ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ትላንት በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ከአዲሱ የክልሉ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

በውይይቱ ወቅት ዶ/ር ይልቃል የትግራይ TPLF በአማራ ክልል በወረራቸው አካባቢዎች እየፈፀመ ነው ያሉትን ሰብዓዊ ቀውስ በዝርዝር እንዳስረዷቸው ተነግሯል።

ከውይይቱ በኃላ መግለጫ የሰጡ ጊታ ፓሲ ሀገራቸው አሜሪካ በአማራ ክልል ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን እንደምትደግፍ ገልፀዋል።

አምባሳደር ጊታ ፓሲ በመግለጫቸው ይህ ብለዋል፦

"ከአዲሱ የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ጋር በአማራ ክልል ስላለው ሁኔታ በሰብዓዊ ድጋፍ እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።

ሰብዓዊ ሁኔታውን የተመለከተ ግምገማም እንፈልጋለን፤ ከሰብዓዊ ድጋፍ አጋሮቻችን ጋርም ተገናኝተናል፤ በጣም አስፈላጊው ለኔ የማይረሳው በአማራ ክልል ከሚገኙ ተፈናቃዮች ጋር መገናኘት ነው።

ለተፈናቀሉ ወገኖች በሚደረገው ሰብዓዊና በቀጣይ ለማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።

ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ያሉ ሰዎች ሁሉ ስቃይ ላይ ናቸው፤ የግጭቱ አካባቢ የትም ይሁን የትም።

በጦርነት እና በአለመረጋጋት ጊዜ የሚያጋጥም ስቃይ ድንበርን አያውቅም። ከተነጋገርንባቸው ጉዳዮች አንዱም ይሄ ነው።

ስቃዩ እንዲያበቃ ግጭቱ መቆም አለበት፤ ይህ የአሜሪካ መንግስት ብዙ ጊዜ የተናገረው ነው ልደግመው ፈልጋለሁ፤ለችግሩ ወታደራዊ መፍትሄ የለውም፤ የሆነ አይነት ውይይት፣ ስምምነት እና ተኩስ አቁም እንደሚኖር ተስፋ እናደርጋለን።

ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያውያን የትም ይሁኑ የትም አሜሪካ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ናት"

@tikvahethiopia
#GERD : በህዳሴው ግድብ 2ኛ ዙር የደን ምንጣሮ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ከ40 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸው ተገለጸ።

ይህ የተገለፀው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቴክኒክ እና ሙያ ስራ እድል ፈጠራ ኤጀንሲ የስራ አፈጻጸሙን በክልሉ መዲና አሶሳ በገመገመበት ወቅት ነው።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በሽር አብዱራሂም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ተጠቃሚ መሆን ጀምሯል ያሉ ሲሆን በ2ኛው ዙር የግድቡ ውሃ ሙሌት ደን ምንጣሮ ስራ በክልሉ የሚገኙ በ149 ኢንተርፕራይዞች የተደራጁ ከ1 ሺህ 300 በላይ ስራ አጦች ተሳታፊ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አክለውም ፥ የኢንተርፕራዞቹ አባላት 2 ሺህ 736 ሄክታር መሬት የደን ምንጣሮ ስራ ማካሄዳቸውንና በዚህም ከ40 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

ዘጠኝ ሚሊዮን የሚጠጋ ብር በመቆጠብ ወደ ቋሚ ስራ መሸጋገራቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD : በህዳሴው ግድብ 2ኛ ዙር የደን ምንጣሮ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ከ40 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸው ተገለጸ።  ይህ የተገለፀው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቴክኒክ እና ሙያ ስራ እድል ፈጠራ ኤጀንሲ የስራ አፈጻጸሙን በክልሉ መዲና አሶሳ በገመገመበት ወቅት ነው። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በሽር አብዱራሂም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ…
#ተጨማሪ

ሶስተኛውን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት የሚካሄድበት ስፍራ የደን ምንጣሮ ስራ በመጪው ታህሳስ ወር ለማስጀመር ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሠራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ አሻድሊ ሃሰን አሳውቀዋል።

ይህ ያሳወቁት የቴክኒክ እና ሙያ ስራ እድል ፈጠራ ኤጀንሲ የስራ አፈጻጸሙን በገመገመበት ወቅት ነው።

በመጀመያው እና 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት በተከናወነባቸው አካባቢዎች የተመነጠረው ደን እንዲቃጠል መደረጉን አቶ አሻድሊ አስታውሰዋል፡፡

በተያዘው ዓመት የሚካሄደው የደን ምንጣሮ እንደከዚህ ቀደሙ የገቢ ምንጭ ለማድረግ ትኩረት ይሰጠዋል ብለዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ የክልሉን ጸጥታ ወደቀደመ ሁኔታ ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት የክልሉ ፕሬዜዳንት ፥ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
#Tolay : ዛሬ በጦላይ ማሰልጠኛ ማእከል መሰረታዊ የፖሊስ ስልጠና የወሰዱ ምልምል የፌደራል ፖሊስ ሰልጣኞች ተመርቀዋል።

በ20ኛ ዙር የተመረቁት ልዩ የፌደራል ፖሊስ ምልምል ሰልጣኞች በፌደራል ፖሊስ ታሪክ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙና ሃገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር የጠላትን የውስጥና የውጭ ጥቃት ለመመከት በፅንሰ-ሃሳብና በአካላዊ ብቃት በጥራት የሰለጠኑ ናቸው ተብሏል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱአለም እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና ከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው እንደነበር ኢብኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... በራሳቸው ምክንያት ካልሆነ በስተቀር የአየር ድብደባውና የሰብአዊ እርዳታ ጫኝ አውሮፕላን እንቅስቃሴ አይገናኝም " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ዛሬ ሮይተርስ 2 የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የተመድን የሰብአዊ እርዳታ የጫነ አውሮፕላን መንግስት በትግራይ ክልል ባካሄደው የአየር ድብድባ ምክንያት መቐለ ማረፍ አልቻለም ብሏል። ሮይተርስ በዚህ ጉዳይ ሁለት ሰማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ…
#UN

የኢትዮጵየ አየር ሃይል ትላንት በመቐለ የአየር ድብደባ መፈፀሙ ይታወሳል።

የጥቃቱ ኢለማ የነበረው የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር /TPLF የወታደራዊ ማሰልጠኛና ማዘዣ ማእከል የሆነውን የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት ማሰልጠኛ ቦታ እንደነበር የኢትዮጵያ መንግስት መግለፁ አይዘነጋም።

በዚሁ እለት ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት በኩል ፈቃድ የተሰጣቸው 2 የUN የእርዳታ አውሮፕላኖች በመቐለ እንዲያርፉ በስፍራው ካሉ የበረራ ተቆጣጣሪዎች ፍቃድ በመከልከላቸው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው ነበር።

የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፥ ትላንት የUN ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ዱጃሪክ አውሮፕላኖቹ ከፌደራል መንግስት ፈቃድ የተሰጣቸው እንደሆኑና ወደ አዲስ አበባ የተመለሱትም በኤርፖርቱ የበረራ ተቆጣጣሪዎች ፍቃድ በመከልከላቸው ብቻ መሆኑን አሳውቀዋል ብሏል።

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ አንዳንድ የውጭ መገናኛ ብዙሃን የእርዳታ አውሮፕላኖቹ የተመለሱት በየአየር ጥቃቱ ሳቢያ እንደሆነ በማስመሰል የተሳሳተ ዘገባን አውጥተዋል ሲል ወቅሷል።

የኢትዮጵያ መንግስት በመግለጫው ፥ " የአየር ጥቃቶቹ በከፍተኛ ጥንቃቄ የተወሰዱና የሽብር ቡድኑ ለእኩይ አላማ የሚጠቀምባቸውን የመገናኛና የወታደራዊ ማሰልጠኛዎችን ብቻ ኢላማ ያደረጉ ናቸው" ብሏል።

ነገር ግን TPLF የተሳሳቱ መረጃዎቸን በማውጣት ህብረተሰቡን በሃሰተኛ ምስሎች ለማወናበድ እየሞከረ ነው ህብረተሰቡም ይህንን ተገንዝቦ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሲል በመግለጫው መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba: አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው ዕለት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ካቢኔው ባካሄደው 1ኛ ዓመት የመጀመሪያ ስብሰባው በከተማዋ የፕላን ትግበራዎች ላይ የታዩ ክፍተቶችን ለማረም በሚያስችሉ የመፍትሄ ሀሳቦች ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

በተመሳሳይ በህብረተሰቡ ላይ የሚደርሰውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለማቃለል ለተለያዩ ተቋማት የበጀት ድጎማ እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚሁ መሰረት የከተማ አስተዳደሩ ወቅታዊውን የገበያ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ለሸገር ዳቦ ተጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍሎች የ309 ሚሊዮን 337 ሺህ 500 ብር ድጎማ እንዲደረግ ወስኗል፡፡

የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እህት ኩባንያ የሆነዉ ሆራይዘን ፕላንቴሽንም ለተመሳሳይ ዓላማ የ199 ሚሊዮን 837 ሺህ 500 ብር ድጎማ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በተጨማሪም ካቢኔው የተማሪዎች ምገባ የዋጋ ማሻሻያ ሰነድ ላይ ውይይት በማድረግ ለ2014 የትምህርት ዘመን የ1.9 ቢሊዮን ብር ድጋፍ እንዲደረግ ወስኗል።

በተመሳሳይ በከተማዋ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ከ231 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የጤና መድህን ሽፋን አገልግሎት ለመስጠት የ144 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንዲደረግ ወስኗል።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ቡድንን የፋይናንስ አቅም ለማጠናከር የሚያስችል የ70 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንዲደረግ ካቢኔው ውሳኔ አሳልፏል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተሪያት

@tikvahethiopia
#Ethio_Sudan

የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ወቅታዊ ችግር ለመፍታት በተመረጡ የሀገር ሽማግሌዎች ውይይት ተደረገ።

ከሁለቱም ሀገራት የተመረጡ የሀገር ሽማግሌዎች በመተማ ዮሃንስ ከተማ በሀገራቱ መሀል ባለው ችግር ዙርያ ምክክር መደረጉን የመተማ ዮሃንስ ከተማ ኮሚኒኬሽን ማምሻውን አስታውቋል።

ኮሚኒኬሽኑ እንዳስታወቀው ከነበሩት የውይይት አጀንዳዎች መሀል፣
1.ችግሮቻችን ምን ምን ናቸው የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል፣
2. የኢትዮ-ሱዳን ግንኙነትን ለማጠናከር ከኛ ምን ይጠበቃል፣
3. በቀጠናው የሚታዩ ሰው የማገትና ሌብነትን እንዴት እንከላከል፣
4. ድንበሩ ከዚህ በፊት እንደነበረው ግንኙነት እንዲፈጠር ከኛ ምን ይጠበቃል፣
5.ህዝባችን ሰላሙ የተጠበቀ እንዲሆን የሀገር ሽማግሌዎች እስከ ባህር ዳር ድረስ እንዲቋቋምና
ግንኙነቶችን ለማጠናከር ህብረተሰባችን ላይ የግንዛቤ ትምህርት በመስጠት ስራ መስራት እንደሚገባ የሚሉ ሃሳቦች ተገልፀዋል።

ለዚህም የጋራ የሆነ ትብብር 20 ሽማግሌዎችን በመምረጥ ውይይትን ማድረግ እንደሚችሉ ወስነዋል። ሌላው የሁለቱንም መንግስታት ጠንካራ ግንኙነትን በመፍጠር የህብረተሰብን ችግሮች ለመቅረፍ የጋራ ጥንካሬ ያስፈልጋል ሲሉ የሀገር ሽማግሌዎች ገልፀዋል።

Via የመተማ ዮሀንስ ኮሚኒኬሽን / Elias Meseret

@tikvahethiopia