ፎቶ ፦ የሐዋሳ ሀይቅን የማስዋብ ፕሮጄክትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል አካባቢን ነፃ ማድረግ ስራ መጀመሩን ከተማ አስተዳደሩ ዛሬ አሳውቋል።
የሐዋሳ ሀይቅ የማስዋብ ስራ በከተማዋ በ2014 በጀት አመት በይፋ ከሚጀመሩ ፕሮጄክቶች መካከል አንዱ እንደሆነ ተገልጿል።
ፕሮጄክቱ ሲጠናቀቅ የሐዋሳን ሀይቅ ለዘርፈ ብዙ የቱሪዝም መስህብነት ብቁ የሚያደርገው ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ ገልጿል።
@tikvahethiopia

ችሎት !
በአማራ ክልል፤ ምዕራብ ጎጃም ዞን፤ ጎንጂ ቆለላ ወረዳ ከሦስት ዓመት ግድም በደቦ በተመራማሪዎች ላይ ግድያ የፈፀሙ 32 ተከሳሾች ከ1 ዓመት እስከ 20 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ የባሕር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቅጣት ወሳኔ አስተላለፈ።
በእነ መላኩ አበበ የክስ መዝገብ የቀረቡ 32 ተከሳሾች በጋራ ሰው በመግደል፣ አካል በማጉደል፣ የግድያ ሙከራ በማድረግና ንብረት በማውደም ከጥቅምት 13 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ጀምሮ ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት ሲከታተሉ ቆይተዋል።
ጥቅምት 13 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ተከሳሾቹ "ተመራማሪዎቹ ልጆቻችንን የማይታወቅ መርፌ በመውጋት ለአደጋ አጋልጠዋቸዋል" በሚል ያልተረጋገጠ ወሬ ተነሳስተው፤ ለሦስተኛ ዲግሪ ማሟያ በወረዳው አዲስ ዓለም ከተማ የምርምር ሥራ ይሠራ በነበረ አንድ ተመራማሪ ላይና በሌላ ረዳቱ ላይ የሞት፤ በሌሎች ሦስት የጤና ባለሞያዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳትና በሌላ ግለሰብ ላይ ደግሞ የመግደል ሙከራ እንዲሁም መኪና የማቃጠል ተግባር መፈፀማቸውን የባሕር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት አመልክቷል።
ፍ/ቤቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በዋለው ችሎት በ32ቱ ተከሳሾች ላይ እንደየ ወንጀል ተሳትፏቸው ከ1 ዓመት እስከ 20 ዓመት የሚደርስ የፅኑእ እስራት ቅጣት አስተላልፎባቸዋል።
ሌሎች አምስት ተከሳሾች በወንጀሉ ስለመሳተፋቸው የቀረበ ማስረጃ ባለመኖሩ ቀደም ሲል በነፃ መሰናበታቸውን ፍ/ቤቱ አስታውሷል።
በዛሬው የፍ/ቤት ውሎ በርካታ የፀጥታ አስከባሪ አካላት በፍርድ ቤቱ ቅጽር ግቢ ታይተዋል። በፍርድ ቤቱ ውስጥ የተወሰኑ ጉዳዩን የሚከታተሉ ታዳሚያንም ነበሩ። የፍርድ ውሳኔው ሲሰጥ የማረሚያ ቤት አልባሳት የለበሱ እስረኞች ውሳኔውን ቆመው ተከታትለዋል።
ምንጭ፦ ጀርመን ድምፅ ሬድዮ

#የጤና_ሚኒስቴር_ማስጠንቀቂያ !
የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ፥ የኮቪድ-19 ክትባትን ከመንግስት የጤና ተቋማት ውጪ የሚሰጡ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀ።
በሚኒስቴሩ የብሄራዊ ክትባት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዮሃንስ ላቀው ፥ የኮቪድ 19 ክትባትን በግል እያስከፈሉ የሚሰጡ አካላት ህገ ወጥ በመሆናቸው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ህብረተሰቡም ይሄንን ተከትሎ ራሱን ለአደጋ ማጋለጥ እንደሌለበት ተናግረዋል።
አቶ ዮሃንስ ክትባቶቹ በእርዳታ የገቡ መሆናቸውን አስታውሰው፣ ለህብረተሰቡ በመንግስታዊ ጤና ተቋማት ብቻ በነፃ የሚሰጡ ሆነው ሳለ ክፍያ እየተጠየቀ እንደሚሰጥ ሰምተን እያጣራን ነው ብለዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በህገ ወጥ መንገድ ክትባቶቹን ለመገበያየት መሞከር በአያያዙና በአወሳሰዱ ላይ እክል የሚፈጥር በመሆኑ ጉዳቱ የከፋ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
እስካሁን ለየተኛውም የግል ተቋም የኮቪድ 19 ክትባትን መስጠት እንዲችል ያልተከፋፈለ መሆኑንና ፈቃድም እንዳልተሰጣቸው በማሳሰብ ለወደፊት በግል ጤና ተቋማት መሰጠት ሲጀመር ቀድመን የምናሳውቅ ይሆናል ብለዋል። እስካሁን ግን ክትባት እንዲሰጥ ፈቃድ የተሰጠዉ የግል የህክምና ተቋም የለም ሲሉ አስገንዝበዋል።
መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ነው።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ፥ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አቤቱታ ባቀረበባቸው በደቡብ ክልል በ4 የምርጫ ክልሎች የተካሄደው የክልል ምርጫ ውጤት ተሰርዞ በድጋሚ ምርጫው እንዲካሄድ ውሳኔ ሰጠ፡፡
ኢዜማ በ28 ምርጫ ክልሎች በድምፅ አሰጣጥ ሂደት በድምጽ ቆጠራና በ6 ምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ የዕጩዎቼ ፎቶና ዝርዝር ባለመካተቱ አልተወዳደርኩም ለዚህም 156 ገጽ የሰነድና የምስል ማስረጃ አያይዤ ለቦርዱ ባቀርብም ቦርዱ ማስረጃዬን ሳይመለከት ነው ውሳኔ የሰጠው ሲል ምርጫው እንዲደገም በማለት ተከራክሮ ነበር።
ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ኢዜማ ስርአቱን የተከተለ አቤቱታ አላቀረበም የቀረበው አቤቱታ እንጂ በማስረጃ የተደገፈ አደለም ስድስቱ ጣቢያ ላይዝርዝር ያቀረበ ቢሆንም ሁለቱ ባዶ ናቸው ሲል መከራከራያ ነጥብ አንስቶ ይግባኙን ተቃውሞ ነበር፡፡
ክርክሩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም መርምሮ ሰኔ 14 ቀን በደቡብ ክልል በላስካ መደበኛ ፣ በቁጫ ልዩ ፣ በጉመር ሁለት እና በብርብር ምርጫ ክልል የተካሄደው የክልል ምርጫ የኢዜማ ዕጩዎች በድምፅ መስጪያ ወረቀት ላይ ፎቶዋቸውና ስም ዝርዝራቸው ያልተካተተ በመሆኑ ዕጩዎቹ ሳይወዳደሩ በመቅረታቸው ምርጫው እንዲደገም ወስኗል።
በሌላ በኩል ኢዜማ በሰኔ14 ቀን 2013 ዓ/ም በ22 ምርጫ ክልሎች በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ በድምጽ አሰጣጥ እና በድምጽ ቆጠራ ሂደት ላይ ታዛቢዎቼ እንዳይሳተፉ ተደርጓል ሲል ያቀረበው አቤቱታን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ መርምሮ ጥሰቱ በማን ላይ በየትኛው ጣቢያ መቼ የሚለው ዝርዝር ፍሬ ነገርና ማስረጃ አልቀረበም ሲል የኢዜማን ይግባኝ አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል።
ያንብቡ : telegra.ph/Tarik-Adugna-08-27
የመረጃ ባለቤት : ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

#DrAbiyAhmed
የጀርመኗ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ዛሬ ከሰዓቱን በጠሩት የጂ-20 ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ የተሰኘ ጉባዔ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበይነ መረብ በመታገዝ ተሳትፈዋል።
“ለንግድ እና ለኢንቨስትመንት ማሕቀፋዊ ሁኔታዎች” በሚል ርዕስ የሚካሄደው ጉባዔ የስምምነቱ ፈራሚ የሆኑ ሀገራት ተጨማሪ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን እንዲያገኙ በሚያስችል ሁኔታ ማሕቀፋዊ ሁኔታዎችን ወደ ቀጣይ ርምጃዎች ለመውሰድ የታለመ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር፣ ለሙዐለ ነዋይ ፍሰት ምቹ ነባራዊ ሁኔታ እንዲኖር ለማስቻል በኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አማካኝነት ማክሮ ኢኮኖሚያ፣ መዋቅር እና የዘርፍ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን ገልጸዋል።
#PMofficeEthiopia

#TikvahFamily
የሀገር ውስጥ እና የውጭ ስፖርታዊ ጉዳዮችን በ https://yangx.top/joinchat/VvwzStMNcNHmhK0x (ቲክቫህ ስፖርት) መከታተል ትችላላችሁ።
@tikvahethsport

#ውድ_ቤተሰቦቻችን_ጥንቃቄያችሁን_አጠናክሩ😷
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,458 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ12 ሰዎች ህይወት ደግሞ አልፏል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 9,292 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1,458 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 12 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።
ወደፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ታማሚዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ሲሆን በአሁን ሰዓት 580 ሰዎች በፅኑ ታመው ህክምና ላይ ናቸው።

TIKVAH-ETHIOPIA
"...ምህረት አይኖረንም፤ አንረሳውምም፤ የገባችሁበት ገብተን እናድናችኋለን፤ ዋጋ እንድትከፍሉም እናደርጋለን" - ጆ ባይደን የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ትላንት በካቡል ከተፈፀመው ጥቃት ጋር በተያያዘ ንግግር አድርገዋል። የሽብር ጥቃቱን ለፈጸሙትም ሆነ አሜሪካን ለመጉዳት የሚመኙ አካላትን ጠንከር ባለ ንግግራቸው አስጠንቅቀዋል። ባይደን ፥ "ምህረት አይኖረንም፤ አንረሳውምም፤ የገባችሁበት ገብተን…
#Update
የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል በካቡል አውሮፕላን ማረፊያ ከደረሰውን ፍንዳታ ጀርባ ባለው ቡድን ውስጥ ዕቅድ የሚያወጣ ነው የተባለ ግለሰብ በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) አማካይነት እንደገደለ አስታወቀ።
ISIS-K የተባለው ቡድን የISIS ክንፍ ሲሆን በካቡል አውሮፕላን ማረፊያ ባደሰው ጥቃት ወደ 170 የሚጠጉ ሰዎች ሞተዋል።
ከተገደሉት ሰዎች መካከል 13ቱ አሜሪካውያን ወታደሮች ናቸው።
የማዕከላዊ ዕዝ አባል ካፒቴን ቢል ኧርባን እንዳሉት፤ ፍንዳታ ላደረሰው ቡድን እቅድ የሚነድፈውን ሰው ለመግደል የድሮን ጥቃት የተሰነዘረው #ናንጋሀር በተባለ የአፍጋኒስታን ግዛት ውስጥ ነው።
ኢላማው የISIS አባላት እንደነበሩና ንጹሀን ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ ተገልጿል።
ሪፐር የተባለው ድሮን ከመካከለኛው ምሥራቅ ተወንጭፎ የISIS አባሉ መኪና ውስጥ ከሌላ የISIS አባል ጋር ሳለ መትቶታል።
በናንጋሀር ግዛት በርካታ የISIS-K አባላይ እንደመሸጉ ይነገራል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከሳዑዲው ልዑል ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የመከላከያ ሚኒስትር ሞሃመድ ቢን ሳልማን ቢን አብዱልአዚዝ ጋር በስልክ ተወያዩ።
የሳዑዲው ልዑል በውይይቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ እድገትና ብልጽግና ለጠ/ሚ ዐቢይ ደግሞ ስኬትን ተመኝተዋል።
በውይይታቸው ወቅት በሁለትዮሽና የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ምንጭ፡ Saudi Gazette

#SaudiArabia
በጄዳ የሹሜሲ ዲፖርቴሽን ማዕከል ከገቡ በኃላ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በተለያዩ ሆስፒታሎች ውስጥ ህይወታቸው ያለፈ የኢትዮጵያ ዜጎችን የሚያውቃቸው ቤተሰብ ፣ ዘመድ እና ጎደኞች ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠየቀ።
ከዚህ በታች የሟቾች ስም አስክሬናቸው የሚገኝበት ሆስፒታል የተገለፀ ሲሆን የምታውቋቸው ሰዎች በቢሮ ቁጥር 13 ቀርባችሁ ሪፖርት እንዲያደርጉ በጄዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት አሳውቋል።
- ሂክመት መሀመድ (የአስክሬን መገኛ👉 ሸርቅ ጂዳ ሆስፒታል)
- ከዲጃ ማህመድ (የአስክሬን መገኛ👉ሸርቅ ጂዳ ሆስፒታል)
- ሮዳስ ሙሉ (የአስክሬን መገኛ 👉 ሸርቅ ጂዳ ሆስፒታል)
- ጀማል ከማል (የአስክሬን መገኛ 👉 ሸርቅ ጂዳ ሆስፒታል)
- ቢንያም ምሩፅ ሃጎስ (የአስክሬን መገኛ 👉 ሰግር ሆስፒታል)
- የኢንዲያ ተማም /ህፃን ልጅ/ (የአስክሬን መገኛ 👉 ሰግር ሆስፒታል)
- መሃሪ ኃይሌ (የአስክሬን መገኛ 👉 ንጉስ አብዱላአዚዝ ሆስፒታል)
- ሱልጣን ሙሀመድ (የአስክሬን መገኛ 👉 ንጉስ አብዱላአዚዝ ሆስፒታል)
- በህታ ነጋሲ አፈወርቂ (የአስክሬን መገኛ 👉 ንጉስ አብዱላአዚዝ ሆስፒታል)
- ሰለሞን ሀዱሽ ተካ (የአስክሬን መገኛ 👉 ንጉስ አብዱላአዚዝ ሆስፒታል)
በዚሁ አጋጣሚ በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ስራ ዳግም የተጀመረ መሆኑ ቢታወቅም አሁንም ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ያሉ ዜጎች በርካታ በመሆናቸው ልዩ ትኩረት ሊደረግ ይገባል።

ብሊንከን እንዲከሰሱ ተጠየቀ።
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አንቶኒ ብሊንከን የገቡትን የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ማስበር ባለመቻላቸው እንዲከሰሱ ተጠይቋል፡፡
ሚኒስትሩ እንዲከሰሱ የጠየቁት የሪፐብሊካን ፓርቲን በመወከል ምክር ቤት የገቡ አባላት መሆናቸውን ፎክስ ኒውስ ዘግቧል፡፡
አንቶኒ ብሊንከን ወደ ኃላፊነት ሲመጡ የገቡትን ቃል ማሳካት እንዳልቻሉ የገለጹት አባላቱ በዚህም ምክንያት መከሰስ አለባቸው በሚል የሀገሪቱን ሕጎች እየጠቀሱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ብዙ ሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት በብሊንከን ላይ ጥያቄ ቢኖራቸውም የሚሪላንድ ተወካዩ አንዲ ሃሪስ እና የደቡብ ካሮላይና ተወካዩ ራልፍ ኖርማን ግን የሕግ አንቀጾችን ሳይቀር እያጣቀሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒትሩ መከሰስ እንዳለባቸው መናገራቸው ተሰምቷል፡፡
የአፍጋኒስታን ጉዳይ እንዲሻሻል መሰራት ቢገባውም ይህንን ማድረግ ባለመቻሉ ከፍተኛ መቅሰፍት መድረሱን የምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል ነው የተባለው፡፡
የአፍጋኒስታንን ጉዳይ ማስተካከል በፕሬዝዳንት ባይደን ትከሻ ላይ የወደቀ ቢሆንም በዋናነት ግን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህንን የማማከር ኃላፊነት ነበረባቸው ተብሏል፡፡
ከትናንት በስቲያ በአፍጋኒስታን መዲና ካቡል ሃሚድ ካርዛይ ዓለም አቀፍ አወሮፕላን ማረፊያ ውጭ ላይ በተከሰተው ፍንዳታ 13 የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸው እና ምስቅልቅል የበዛበት ወታደሮችን የማስወጣት ተግባርም አንቶኒ ብሊንከንን ሊያስጠይቅ እንደሚችል የምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ፤ የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት በሚጠበቅባቸው ልክ አለማማከራቸው እና አሜሪካ በአፍጋኒስታን ያላትን ብሐየራዊ ጥቅም በተገቢ ሁኔታ ማሳወቅ አለመቻላቸው ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው ነው የተገለጸው፡፡
ያንብቡ : telegra.ph/AL-AIN-08-28
(አል ዓይን ኒውስ)