TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update ኦምሃጀር⬆️

የሰቲት #ሑመራ የልኡካን ብዱን ከ20 አመታት በኋላ ዛሬ ወደ #ኤርትራ ኦምሃጀር ከተማ አቅንተዋል።

የልኡካን ብዱኑ ኣባላት ከሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ወጣቶችና ሴቶች የተውጣጡ ሲሆን፥ ቁጥራቸው ከ50 በላይ መሆኑን ተገልጿል።

ነዋሪዎቹ የተከዜ ድልድይ በመሻገር በኦምሃጀር ከተማ ከሚገኘው ከኤርትራ ህዝብና ከሀገሪቱ የሰራዊት ሃይል ጋር ዛሬ ጠዋት ተገናኝተዋል።

📌ጉዞው ከኤርትራ ህዝብ ጋር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ተነገሯል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ⬇️

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ በ73ኛ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ለአካባቢው ሰላም እና ዘላቂ ልማት ተግታ የምትሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ እንደ ተመድ መስራች አባል ሀገር ለባለብዙ ወገን መድረክ ትኩረት በመስጠት የተ.መ.ድ መርህ እንዲከበር እንዲሁም ተግዳሮቶች እና ስጋቶች እንዲወገዱ በጋራ ትሰራለች ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የተካሄደው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ለሀገሪቱ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ክስተት አዲስ ምዕራፍ የከፈተ እንዲሁም ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ተሰፋው እንዲፈነጥቅ ያደረገ መሆኑንም ዶ/ር ወርቅነህ አውስተዋል፡፡

የህግ የበላይነት እንዲከበር፣ ፍትህ እንዲሰፍን፣ የአገር ኢኮኖሚ በአግባቡ ለማስተዳደር እንዲቻል፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ የብዙሃኑ ተሳትፎ እንዲረጋገጥ እንዲሁም ዴሞክራሲ እንዲያብብ ለማድረግ መንግስት በስፋት እና በጥልቀት እየሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ
ተናግረዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመራው መንግስት በሁሉም አቅጣጫ የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት እና እንደ ሙስና፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ መልካም አስተዳደር ያሉትን የእድግት ማነቆዎች ለመቅረፍ በርካታ ተግባራት እየከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በቀጠናው የሰላም አየር እንዲነፍስ ያበረከተቸውን አስተዋጽኦም አብራርተዋል።

ለ20 አመታት ያክል በግጭት ላይ የነበሩት ኢትዮጵያና ኤርትራ አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ መክፈታቸው፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ እንዲሁም #ጅቡቲ እና #ኤርትራ ችግሮቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ የተደረገው ጥረት ከቀጠናው አልፎ ለአፍሪካ ሰላም ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ
መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ጁሴፔ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር #ጁሴፔ_ኮንቴ መኪና በመገጣጠም የሚታወቀውን የአምቼ ኩባንያን ጎብኝተዋል።

ኩባንያው 70 በመቶ በጣሊያን መንግስት 30 በመቶ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግስት ድርሻነት የተቋቋመ ነው፡፡

የጣሊያኑ ጠ/ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ #ኤርትራ አቅንተዋል፡፡

ጠ/ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ በጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየው በቦሌ አየር ማረፊያ ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

ፎቶ፦ ጠቅላይሚንስትር ፅ/ቤት
ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና #ኤርትራ!

#ለኤርትራ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከተቀመጡ 16 ሺሕ ተማሪዎች 40.8% ማለፋቸውን የአገሪቱ የማስታወቂያ ምኒስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር አስታውቀዋል። ፈተናውን ያለፉ የዲግሪ፣ ዲፕሎማና የሰርተፍኬት ትምህርታቸውን ይቀጥላሉ ተብሏል።

Via Yemane G.Mekel,እሸት በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
4 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመገንባት የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ ነው!

አራት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመገንባት የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ገለጸ። ኮርፖሬሽኑ በፓርኮች ግንባታና ምርት ዙሪያ ከምሁራን፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የሙያ ማህበራት ጋር ተወያይቷል። ውይይቱ በኢትዮጵያ በመስኩ እየተካሄደ ያለው እንቅስቃሴ፣ እየተገኙ ያሉ ውጤቶችና ችግሮች ላይ ያተኮረ ነው።

የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ሺፈራው ሰለሞን እንደተናገሩት፤ አሁን ካሉት ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተጨማሪ አራት ፓርኮችን ለመገንት የሚያስችል ጥናት እየተከናወነ ነው። አሶሳ፣ አረርቲ፣ አይሻና ሰመራ ከተሞች ላይ ለመገንባት እንደታቀደ ጠቁመው፤ በተለይ #ሰመራ ላይ #የኢትዮጵያና #ኤርትራ ግንኙነት መሻሻልን ተከትሎ የወደብ አማራጭ በመኖሩ የተሻለ እንቅስቃሴ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።

አሶሳ ላይ ደግሞ የቀርከሃ ምርት በስፋት በመኖሩ ለቢሮ፣ ለቤት እቃዎችና መርከብ ግንባታ የሚሆን ግብዓት ለማምረት የሚያስችል የኢንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት እየተጠና መሆኑን ጠቁመዋል። በቀርከሃ ምርት ለመሰማራት ቻይናዊያን ባለሃብቶች ከፍ ያለ ፍላጎት ማሳየታቸውን ገልጸዋል። ”የጥናት ሂደቱ እንደተጠናቀቀ በውጤቱ መሰረት ወደ ግንባታ ይገባል” ብለዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TiffanyHaddish

የ41 ዓመቷ አሜሪካዊት ተዋናይትና ኮሜዲያን ቲፋኒ ሀዲሽ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ስላለው ግጭት በሰጠቻቸው አስተያየቶች/በምታጋራው መልዕክቶ ምክንያት ከፍተኛ ተቃውሞ እየቀረበባት ነው።

የምታጋራው መልዕክቶች በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን አስቆጥቷል።

ቲፍኒ ሀዲሽ ፥ "በትግራይ ላይ የሚፈፀውን የንፁሃን ግድያ ፣ የሴቶች መደፈር፣ የህፃናት ሞት ክዳለች ፣ በትግራይ ጉዳይ ጦሯን ላሰማራቸው #ኤርትራ በተለይም አምባገነን ለሆነው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ድጋፍ ትሰጣለች" በሚል ነው ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገደች የምትገኘው።

ቲፍኒ ሀዲሽ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትግራይ ስላለው ሁኔታ በትዊተር ገጿ የተለያዩ መልዕክቶችን እያስተላለፈች ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አንዱ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ የሚሰራጩ #ሀሰተኛ መረጃዎች የሚመለከት ነው።

በተጨማሪ፥ በአንድ ሪትዊት ላይ የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን "ጦርነቱ የህዝብ መሆኑን ህፃናትም የዚህ አካል ስለመሆናቸው" ተናግረውበታል የተባለውን የእሳቸውን ንግግር አጋርታለች።

ከተቃዋሚዎቹ በተቃራኒው ደግሞ የምታጋራቸውን መልዕክቶች ትክክል እንደሆኑ የሚገልፁ በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ታይተዋል።

ቲፍኒ ሀዲሽ በ1979 እ.አ.አ. በሎስ አንጀለስ የተወለደች ሲሆን አባቷ ፀሃዬ ረዳ ሀድሽ በወቅቱ የኢትዮጵያ አካል የነበረችውን ኤርትራን ጥለው የተሰደዱ ስደተኛ ነበሩ።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ቲፋኒ ሀዲሽ ከኤርትራና ከመሪዋ ኢሳያስ አፍወርቂ ጋር ጥሩ የሚባል ወዳጅነትንና ቅርርብ ስለመፍጠራቸው ይነገራል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ኤርትራን የጎበኘችው እ.ኤ.አ. በ2018 ሲሆን በወቅቱ የአባቷን ህልፈት ተከትሎ በእሳቸውን የቀብር ስነስርዓት ላይ ለመገኘት ነበር።

@tikvahethiopia