TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
በትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በሰበታ ከተማ በዛሬው እለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

የትራፊክ አደጋው በዛሬው እለት ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ መድረሱን የሰበታ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

አደጋው በሰበታ ከተማ ዲማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተለምዶ ሀይሩፍ ተብሎ የሚጠራ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ከሲኖ ትራክ ጋር በመጋጨቱ የተፈጠረ ነው።

በአደጋውም የ11 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ ፤ 7 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የመቁሰል አደጋ መድረሱን የሰበታ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱራዛቅ አህመድ መናገራቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ArbaMinch

በነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ ዙሪያ በአርባምንጭ ከተማ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

በብሄራዊ ፓርኩ ችግሮች እንዲሁም መፍትሄዎች ዙሪያ በቅንጅት መስራት የሚያስችል ስምምነት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የፌዴራል የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ባዘጋጀው በዚሁ መድረክ ላይ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ተገኝተዋል።

በመድረኩ ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፣ በኦሮሚያ ክልል በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ፣ በምክትል ርዕስ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉበት እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Response to the Ethiopian Refugees UNFPA Sudan.pdf
4.3 MB
በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የተካሄደውን ጦርነት ሸሽተው ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን የሚመለከት ወቅታዊ ዝርዝር ሪፖርት በ #UNFPA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ፊሊፖ ግራንዴ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ (UNHCR) ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ የተመራ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ይገኛል።

የልዑካን ቡድኑ ዛሬ ከሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፍሪሃት ካሚል ጋር መወያየቱ ተገልጿል።

ሚኒስትሯ ለኮሚሽነሩ በሰብዓዊ ዕርዳታና ስደተኞች ጉዳይ ላይ በሀገሪቱ እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራት ማስረዳታቸውን በሰላም ሚኒስቴር በኩል ይፋ የተደረገው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#update

የነጭ ሣር ብሔራዊ ፓርክን ከአደጋ ለመታደግ እና በዘላቂነት ለማስጠበቅ ያለመ የባለድርሻ አካላት የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ።

በፓርኩ ክልል ውስጥ ለሰፈሩ ሰዎች አማራጭ ቦታ የመለየት ስራ እየተከናወነ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ገልጿል፡፡

በአርባ ምንጭ ከተማ ዛሬ በተካሄደው የባለድርሻ አካላት የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሚያ ስነ -ሥርዓት ላይ እንደተገለጸው የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

በተለይም በፓርኩ ውስጥ የሚካሄደው ህገ-ወጥ ሰፈራና ልቅ ግጦሽ ለችግሩ መባባስ በዋናነት የሚጠቀስ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አባያና ጫሞ ሐይቆች በደለል የመሞላት አደጋ የተጋረጣባቸው ሲሆን በህገ- ወጥ መንገድ የሚካሄደው የዓሳ ማስገር ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የመግባቢያ ሰነዱ ዋና ዓላማ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው በመስራት ለፓርኩ ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት እና በአዋሳኝ የሚኖሩ ህዝቦችን የኑሮ ሁኔታ ለመለወጥ ያለመ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ቀጣዩን ያብቡ : https://telegra.ph/Gamo-01-29

መረጃውን ያደረሰን የጋሞ ዞን መንግስት ኮሚኒኬን ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Ethiopia

በሀገራችን ከ2 ወር በኃላ ከፍተኛው የኮቪድ19 ኬዝ ባለፉት 24 ሰዓት ተመዝግቧል።

ከተደረገው 7,011 የላብራቶሪ ምርመራ 771 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል።

በ24 ሰዓት ይህን ያህል ሰው በቫይረሱ መያዙ ሲረጋገጥ ከ62 ቀን በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በሀገራችን የሁለት ሰዎች ሞት ሲመዘገብ 127 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ 136,365 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ ከነዚህ መካከል የ2,087 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 121,987 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

አሁን ላይ 228 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

#Tikvah #Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የሲዳማ ክልል የ8ኛ ክፍል ውጤት እስከሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ይፋ ይደረጋል።

በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ የ2012 ዓ.ም የ8ተኛ ክፍል የፈተና ውጤት በቅርቡ እንደሚሰጥ የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ ዛሬ ገልጿል።

ፈተናው የሲዳማ ህዝብ በክልልነት ከተደራጀ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠጠ ነው።

በአሁኑ ወቅት ፈተናው ታርሞ የተጠናቀቀ ሲሆን እስከሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ድረስ ውጤቱ ለተማሪዎች እንደሚሰጥ በክልሉ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊና መማ/ማስ/ምዘና ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታፈስ ገ/ማርያም አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Report

በዓለም ኣቀፍ ደረጃ የኮቪድ-19 የ24 ሰዓታት ሪፖርት፦

- በመላው ዓለም 14,996 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ በኮቪድ-19 ሳቢያ ሞተዋል፡ 589,158 ሰዎች በቫይረሱ መያቸው ተረጋግጧል።

- አሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓት የ3,652 ዜጎቿን ህይወት ስታጣ፤ 169,033 ሰዎች ለቫይረሱ መጋለጣቸው ተረጋግጧል።

- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 1,245 ሰዎች ሲሞቱ፤ 29,079 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል።

- ብራዚል 1,099 ዜጎቿን በ24 ሰዓት ውስጥ በኮቪድ-19 ስታጣ ፤ 58,691 ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል።

- ሜክሲኮ 1,506 ዜጎቿ ባለፉት 24 ሰዓት ሞተዋል፤ አጠቃላይ በሀገሪቱ የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር 155,145 ደርሷል።

- በኮቪድ-19 የሚሞቱባት ዜጎች ቁጥር እየጨመረ በመጣው ጀርመን ባለፉት 24 ሰዓት 832 ሰዎች ሞተዋል።

- ሩስያ 534፣ ፈረንሳይ 510 ፣ ስፔን 513 ፣ ጣልያን 477 ዜጎቻቸው በ24 ሰዓት ውስጥ ካጡ ሀገራት መካከል ናቸው።

- በደቡብ አፍሪካ የሟቾች ቁጥር በእጅጉ ጨምሯል፤ባለፉት 24 ሰዓት የተጨማሪ 528 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል። ባለፉት 5 ቀናት ብቻ 2,759 ሰዎች ሞተዋል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ሪፖርት እንደሚያስረዳን 102,635,253 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፥ የ2,216,418 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 74,329,277 ሰዎች አገግመዋል።

ውድ የቲክቫህ አባላት ከወረርሽኙ እራሳችሁን፣ ቤተሰባችሁን ትጠብቁ ዘንድ አደራ እንላለን ፤ በሽታው ሳናውቀው በርካቶችን ከጎናችን እንዳያሳጣን እንጠንቀቅ ! ዘውትር የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ(ማስክ) ማድረጎን፣ የእጆን ንፅህና መጠበቆን፣በየትኛውም ቦታ ርቀቶን መጠበቆን፣ሰዎች በብዛት ከሚሰበሰቡበት ቦታ መራቆን አይዘንጉ።

#Tikvah #Purpose

@tikvahethiopia
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው።

የደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲ የሰባተኛ ዙር ተማሪዎቹን ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው እያስመረቀ የሚገኘው በ39 ትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 518 ተማሪዎችን ነው።

ከተመራቂዎች ውስጥም 40 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።

የምረቃ ስነስርዓቱ በአማራ ቴሌቪዥን በቀጥታ እየተሰራጨ ይገኛል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም ተመራቂዎችን ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለተመራቂ ተማሪዎች ከተዘጋጀው መድረክ ውጪ የተመራቂ ወላጆች እና ወዳጅ ዘመዶች በተለመደዉ መንገድ በመመረቂያ አዳራሽም ሆነ በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ተገኝተው ምርቃቱን መታደም አልቻሉም።

ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በኢ.ቲ.ቪ ቋንቋዎች እና በኢ.ቲ.ቪ መዝናኛ ቻናሎች በቀጥታ ስርጭት እየተላለፈ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#update

የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን እያስመረቁ ነው።

መቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው በተለያየ የትምህርት መስክ ትምህርታቸውን የተከታተሉ 2,896 ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

በተመሳሳይ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለ7ኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 59 ተማሪዎችን ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል።

በሌላ በኩል ፦ በዛሬው ዕለት የኒውጄኔሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅም ተማሪዎችን በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia