#CommanderDerartuTulu
ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው በዛሬው ዕለት ተመረጡ።
ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው በ27 ድምፅ በ1 ተቃውሞ ነው የተመረጡት።
ለቀጣይ አራት ዓመት ፌዴሬሽኑን ይመራሉ።
ምንጭ፦ EAF
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#TikvahFamily
ከ1 ወር በላይ ተቋርጦ የቆየው የቲክቫህ ማስታወቂያ ከነገ ጀምሮ ይቀጥላል።
ህጋዊ የንግድ ፍቃድ አውጥታችሁ የምትንቀሳቀሱ የቲክቫህ አባላት የድርጅት ባለቤቶች ፓኬጁን : @Tikvahpromo / +251942293508 #ብቻ ማግኘት ትችላላችሁ።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#MetekelZone
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ቡለንና ድባጤ ወረዳ ነዋሪዎች ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱ እንደሆነ አሳውቀዋል።
ከባለፈው ረቡዕ አንስቶ በቡለን ወረዳ 2 ቀበሌዎች ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ከ4 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።
ከትላንት በስቲያ በቆንጢ ቀበሌ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 2 ሰዎች ሲገደሉ 3 ሰዎች ቆስለዋል፤ በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል።
ታጣቂዎቹ በተለያየ ስፍራ ጥቃት ፈፅመው ከስፍራው እንደሚሸሹ ነዋሪዎች ከዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።
አንድ የቡለን ወረዳ ነዋሪ በስልክ ለዶቼ ቨለ ሲናገር እንደተደመጠው ፥ ከሶስት ቀን በፊት ከፌዴራል ፣ ከክልል እና ከዞን አመራሮች በተሰጠው አቅጣጫ ህብረተሰቡ ወደ ሰብል መሰብሰብ ቢመለስም ጥቃት ተፈፅሞበታል።
በጥቃቱ ባል እና ሚስት ፣ ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ህይወታቸውን አጥተዋል፤ ከ4-8 ሰዎች ቆስላው ሆስፒታል ይገኛሉ።
'ዶሽ' በተባለ የቡለን ቀበሌ ሰሞኑ የአካባቢው የፀጥታ ኃይል በመምሰል እና የደንብ ልብስ በመልበስ ጥቃት ተፈፅሟል። በዚህም የሰዎች ህይወት ማለፉን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በቡለን በተፈፀሙት ጥቃቶች ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት ስብሰባ ላይ ነን በሚል ለሬድዮ ጣቢያው ምላሽ አልሰጡም።
የፀጥታ ኃይል እርምጃ ለመውሰድ ሲንቀሳቀስም ታጣቂዎቹ ወደ ጫካ እንደሚሸሹ ነው የተነገረው።
የዞኑ ኮማንድ ፖስት በትላንትናው ዕለት ባወጣው መረጃ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ባልተወጡ 66 አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጿል፤ ከነዚህ መካከል የፖሊስ አባላት ይገኙበታል።
በወታደራዊ አሰሳም 50 ሰዎች መማረካቸውን 43 የሚሆኑ እጅ መስጠታቸውን ኮማንድ ፖስቱ መግለፁን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,778
• በበሽታው የተያዙ - 473
• ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,335
አጠቃላይ 117,242 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,809 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 95,225 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
297 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

#Mekelle
ICRCና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር #መቐለ የደረሱ የህክምና ቁሳቁሶችን እያከፋፈሉ ነው።
ቀድሚያ የተሰጣቸው አይደር ሆስፒታል እና የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ እንዲሁም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ፋርማሲዎች ነው።
ሰብዓዊ አገልግሎቱ ከመቐለ ውጭም በሌሎች አካባቢዎች እንደሚቀጥል ተገልጿል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ICRCና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር #መቐለ የደረሱ የህክምና ቁሳቁሶችን እያከፋፈሉ ነው።
ቀድሚያ የተሰጣቸው አይደር ሆስፒታል እና የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ እንዲሁም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ፋርማሲዎች ነው።
ሰብዓዊ አገልግሎቱ ከመቐለ ውጭም በሌሎች አካባቢዎች እንደሚቀጥል ተገልጿል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#EndertaWoreda
በትግራይ ክልል እንደርታ ወረዳ ሚሊሻዎች በሰላማዊ መንገድ ትጥቅ ማስረከባቸውን መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።
ሚሊሻዎቹ አምስት መቶ (500) እንደሚሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከመከላከያ፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሃይማኖት አባቶች ጋር በመወያየት ነው ትጥቅ ያስረከቡት።
የሁለተኛ ኮማንዶ አዣዥ ሻለቃ አለባቸው አምባቸው ትጥቅ የፈቱት ሚሊሻዎቹ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን መጀመሪያ ቢጠራጠሩም አሁን ላይ ግን እምነት እያደረባቸው በመምጣቱ ትጥቅ ለማስፈታት ትችሏል ብለዋል።
የልዩ ኃይል ዘመቻ 2ተኛ ብርጌድ 2ተኛ ሻለቃ ምክትል አዛዥ ደረጀ ደበሳ ፥ የተፈታውን ትጥቅ መከላከያ ሰራዊት እንደማይወስደው ተናግረው ፤ ትጥቁን እዛው ያሉ ነዋሪዎች በሚመርጡት/በሚያምኑት ሰዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ እንደሚደረግ አስገንዝበዋል።
የሀገር ሽማግሌዎች በየጫካው ፣ በየበረሃው በመሄድ ሚሊሻውን በማምጣትና በማግባባት ትጥቅ እንዲፈቱ እንዳደረጉ ተናግረዋል ፤ መሊሻዎቹ ያቀረቡላቸውን ጥሪ ስለተቀበሉ አምስግነዋቸዋል።

www.tikvahethiopia.net
የቲክቫህ ኢትዮጵያ (Tikvah Ethiopia) አባላት ሆናችሁ ፦
በምትኖሩበት አካባቢ የሚደርስባችሁ ችግር አለ ?
ማሰራጨት የምትፈልጉት መረጃ አለ ?
ኢፍትሃዊ የሆነ አሰራር አጋጥሟችኃል?
በምትሰሩበት የትኛውም ተቋም የሚደርስባችሁ በደል/ለህዝብ ልታሳውቁት የምትፈልጉት ጉዳይ አለ ?
የፀጥታ እና የደህንነት ችግር አለባችሁ ?
በ www.tikvahethiopia.net በወረዳ ደረጃ መልዕክቶቻችሁን አሰራጩ ፤ መረጃዎቹ ተደራጅተው ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ የቲክቫህ አባላት ይፋ ይደረጋሉ።
ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰዎች ስለማያውቁት አካባቢ ምንም አይነት መረጃ እና መልዕክት እንዳያሰራጩ መረጃዎቹ የሚታዩት ለዛው ወረዳ ነዋሪዎች ብቻ ነው፤ መረጃውንም ማረጋገጫ ያሚሰጡት የዛው ወረዳ ነዋሪዎች ብቻ ናቸው።
በትግራይ ያሉ አባላቶች ከ1 ወር በላይ በኢንተርኔት መቋረጥ ልናገኛቸው አልቻልም ፤ በዚህም ምክንያት በድረገፃችን ላይ ምዝገባ እያከናወኑ አይደለም። የኢንተርኔት አገልግሎት ሲመለስ ከአባላቶቻችን ጋር እንደምንገናኛ ተስፋ እናደርጋለን።
* ከላይ ያሉት የምትመለከቷቸው ምስሎች በድረገፁ ላይ አባላት እንዴት መረጃ እንደሚያሰራጩ የማያስዩ ናቸው።
www.tikvahethiopia.net
#TikvahFamily❤️

#JoeBiden
ጆ ባይደን የፕሬዜደንታዊ ምርጫው ውጤት በኤሌክቶራል ኮሌጅ #ተረጋግጦላቸው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው በይፋ መሰየማቸውን BBC ዘግቧል።