TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
በኢፌዴሪ አየር ሀይል የሰሜን አየር ምድብ የሰራዊት አባላት በትግራይ ክልል የተከሰተው የአንበጣ መንጋ የመከላከል ስራ አከናውነዋል።

የሰራዊት አባላቱ በክልሉ ደቡብ ምስራቅ ዞን እንደርታ ወረዳ ውስጥ ነው የአምበጣ መንጋውን ጉዳት ለመቀነስ በባህላዊ የመከላከያ ዘዴዎች እገዛ ያደረጉት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን :

- በሽብር ፤
- በመንግስት ተቋማት ዝርፊያና ፤
- በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በሀገር ውስጥ እንዲሁም በውጭ በልዩ ክትትል ሲፈለጉ የነበሩ 95 ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ይህን ያሳወቀው በዛሬ ዕለት የሩብ አመቱ አፈጻጸሙ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫው ላይ ነው። (ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ፦

- በአማራ ክልል የገንዘብ ቅያሬው ተግባራዊ ከሆነ ጀምሮ ከ800 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖት በቁጥጥር ስር ውሏል።

- ከ800 ሺህ ሀሰተኛ ብር 600 ሺህ የሚሆነው የአዲሱ ገንዘብ ኖት ነው ፤ ቀሪው አሮጌው የብር ኖት ነው።

- ፖሊስ በክትትል የገንዘብ ማባዣ ማሽን በቁጥጥር ስር አውሏል ፤ ሀሰተኛ የገንዘብ ኖት ስርጭቱንም ከምንጩ ለማድረቅ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እያደረገ ነው። (etv)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት !

አቶ ልደቱ አያሌው ህገመንግስቱ ለመናድ በማሰብ የተለያዩ ህገ መንግስቱን የሚቃረኑ የሽግግር ሰነዶችን አዘጋጅተዋል ተብለው በቀረበባቸው 2ኛው ክስ ላይ ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ዛሬ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ችሎት የአቶ ልደቱ አያሌው አራት ጠበቆች ተገኝተው ነበር።

ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠው ዐቃቤህግ በማስረጃነት ለፍርድ ቤቱ የያዘውን ሲዲ ከክሱ ጋር ለተከሳሽ ባለመስጠቱ ምክንያት ነው።

የተከሳሽ ጠበቆች ሲዲው ደርሶን ተመልክተንና ተዘጋጅተን እንቅረብ ሲሉ ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ተቀብሏል።

ፍርድ ቤት የተከሳሽ ጠበቆች ሲዲው ደርሷቸው ተዘጋጅው ክሱን በችሎት ለማንበብ ለጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። (ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጥቅምት 6/2013 ዓ/ም

የኢትዮጵያ ኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 137 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 35 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 606 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 115 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የ1 ሰው ህይወት አልፏል (ከጎንደር)

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 560 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 101 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ1 ሰው ህይወት አልፏል።

#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 185 የላብራቶሪ ምርመራ 12 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 94 የላብራቶሪ ምርመራ 05 ሰዎች በቫረረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

* ላልተካከቱ የክልል ሪፖርቶችን ቆየት ብላችሁ ይህንኑ ፖስት ተመልከቱ !

@tikvahethiopiaBOT
#UPDATE

ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23 እስከ ጥቅምት 30/2013 ዓ/ም ባለው ጊዜ ውስጥ ተመራቂ ተማሪዎችን ብቻ መቀበል እንደሚችሉ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በሀዋሳ በተጀመረው የማጠቃላይ መድረክ ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

- ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ዝግጁነታቸውን በሥራ አመራር ቦርድ ገምግመው ከጥቅምት 23/2013 በፊት ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቅ አለባቸው፡፡

- ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ዝግጁነታቸው ሳይረጋገጥ ጥሪ የሚያቀርብ ዩኒቨርሲቲ አይኖርም፡፡

- በተካሄደው ግምገማ መሰረት ቢጫ እንዲሁም ቀይ የተሰጣቸው ዩኒቨርሲቲዎች በአስቸኳይ ማስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች አስተካክለው ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡

- የዩኒቨርስቲዎችን ጥሪ በሚመለከት መርኃ ግብሩ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡

- የትራንስፖርት አቅርቦትን በተመለከትም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ (MoSHE) የማመቻቸት ሥራ የሚሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የጥንቃቄ_መልዕክት

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲና አካባቢው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የበረሀ አንበጣ በአሁኑ ሰዓት በዛፎች ላይ በማረፉ ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 7 ከጠዋቱ 12፡00 - 2፡00 ባለው ሰዓት በአውሮፕላን የፀረተባይ መድኃኒት ይረጫል።

በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው ዙሪያ በ3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኙ ነዋሪዎች በተጠቀሰው ሰዓት ከቤታችሁ እንዳትወጡ እና ጥንቃቄ እንድታደርጉ የጥንቃቄ መልዕክት ተላልፏል።

#SHARE #ሼር

(ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,569
• በቫይረሱ የተያዙ - 665
• ህይወታቸው ያለፈ - 12
• ከበሽታው ያገገሙ - 640

በአጠቃላይ በሀገራችን 87,834 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,337 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 41,628 ከበሽታው አገግመዋል።

301 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SavetheChildren

የህፃናት አድን ድርጅት (Save the Children) ይፋ ያደረገው መረጃ በዓለማችን መካከለኛና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚኖሩ ቤተሰቦች የተገኙ ወደ 594 ሚሊዮን የሚጠጉ ህፃናት ኮቪድ-19ን ለመቋቋም የሚያፈልጋቸውን የገንዘብ እርዳት ከሃገሮቻቸው መንግስታት እንዳላገኙ ያሳያል።

ከSave the Children የተላከልልን ሙሉ መረጀ ከላይ ይመልከቱት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Emirates

ኤሚሬትስ አዲሱን የዓለም አቀፍ "ይህ ቅጣት ነው" የተሰኘው ዘመቻ አካል የሆነ "ሕገወጥ ሰዎች ዝውውር ምንድነው?" የተሰኘ ፊልም ከታዋቂው አይርላንዳዊ ፊልም አክተር ሊያም ኒሰን ጋር በትብብር ያዘጋጀውን አጭር ፊልም ይፋ አድርጓል።

አዲሱ አጭር ፊልም በዓለም ዙሪያ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ብዝበዛ ዙሪያ የሚስተዋሉ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ለመቀየር እና ማስተማር አላማ ያለው ነው።

ከጥቅምት ወር ጀምሮ በሁሉም በረራዎች ውስጥ ከሚኖሩት የመዝናኛ ቪዲዮች አንዱ አካል በማድረግ ይህን ልዩ መልእክት በማስተላለፍ ኤሚሬትስ ስለዚህ ዓለም አቀፍ ችግር ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ብሎም በረካታ ስለ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ምንነት የተሻለ መረጃ ያስጨብጣል ብሎ ተስፋ አድርጓል።

ይህ አንቅስቃሴም ከፍተኛ ግንዛቤ በመፍጠር ብዙ ህገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪ ተጠርጣሪዎች ተለይተው ሪፖርት ስለሚያስችል ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑትን ከአደጋ ለመከላከል ያስችላል ተብሎ ይታመናል።

#251communication

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የባህር ዳር ደም ባንክ ተሸለመ !

በኢትዮጵያ ካሉት 40 የደም ባንክ አገልግሎት የባህርዳር ደም ባንክ የ2012 ዓመት ምርጥ 1ኛ በመሆን ተሸለመ።

ትላንት ጥቅምት 6/2013 ዓ/ም በጎንደር ሀይሌ ሪዞርት የተዘጋጀውን የእውቅና የዋንጫ እና ምስክር ወረቀት ተቀብሏል።

የባህር ዳር ደም ባንክ የተሸለመው ፦

- በክልሉ በደም እጥረት እንዳይኖር በማድረግ
- አውቶማቲክ እና በኢትዮጵያ ብቸኛ ሶፍትዌር በመስራት
- አለማቀፋዊ ጥናታዊ ጹሁፍ በማሳተም
- ሌሎችን ደም ባንኮች በማገዝ ነው።

የደም ባንኩ ከሽልማቱ በኃላ አብረውት ለነበሩ በጎ ሰዎች፣ በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች፣ የባህር ዳር ከነማ ደጋፊዎች ፣ የደም ባንክ ክበባት እና ሰራተኞች ፣ ደም ልገሳ አስተባባሪዎች፣ ደም ለተጠቃሚዎቹ ፣ የባህርዳር ከተማ አስተዳደር እና ነዋሪዎች ፣ ለማህበራዊ ድረ ገጽ ጸሀፊዋች ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE በአርሜኒያ እና አዛርባጃን መካከል ተደርጎ የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት ከአንድ ቀን በላይ መዝለቅ አልቻለም። አዛርባጃን በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀችው የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ ከአንድ ቀን በኋላ ለዛሬ እሁድ አጥቢያ የአርሜኒያ ኃይሎች በሰነዘሩት ጥቃት 7 ሰዎች ተገድለዋል። ጥቃቱ የተሰነዘረው በአዛርባጃንዋ የጋንጃ ከተማ የመኖርያ መንደሮች ላይ ነው ተብሏል። በጥቃቱ…
#UPDATE

የአዘርባጃን ባለስልጣናት በዛሬው ዕለት እንዳስታወቁት በጋንጃ ከተማ ላይ በኤርሜንያ በተፈፀመ የሚሳኤል ጥቃት 12 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል።

ከ40 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መቁሰላቸው ተገልጿል።

በአርሜኒያ እና አዘርባጃን መካከል በሩሲያ የተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ከተጣሰ በኃላ በ2ቱ ሀገራት መካከል ያለው ጦርነት ተባብሶ መቀጠሉ እየተገለፀ ይገኛል። በጦርነቱ እስካሁን በርካቶች አልቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#LIVE

የሴቶች ማራቶን መካሄድ ጀምሯል !

#ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በጉጉት የሚጠበቁበት የግማሽ ማራቶን ውድድር ከ ጀመረ ጥቂት ደቂቃዎችን ተቆጠርዋል።

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን!

@tikvahethsport