TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በሩሲያ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 10,028 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 242,271 ደርሰዋል።

- በኢራን ባለፉት 24 ሰዓት 1,958 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል (ከሚያዚያ 2 በኃላ የተመዘገበ ከፍተኛ ኬዝ ነው) ፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 112,725 ደርሷል።

- በቻይና ባለፉት 24 ሰዓት 7 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በደቡብ ኮሪያ ባለፉት 24 ሰዓት 26 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ 1 ሰው ሞቷል።

- በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት 184 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 27,104 ደርሷል።

- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 494 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል ፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 33,186 ደርሷል።

- ሊባኖስ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት ማንም ሰው ከቤቱ እንዳይወጣ ደንግጋለች - #BBC

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ83,000 በላይ ሆኗል።

- በኳታር ባለፉት 24 ሰዓት 1,390 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 26,539 ደርሷል።

- በሳዑዲ አረቢያ በ24 ሰዓት 1,905 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 9 ሰዎች ሞተዋል።

- እስካሁን ኮቪድ-19 ያልተገኘባት አፍሪካዊቷ ሀገር #ሌሴቶ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ በሀገሪቱ እንደተገኘ አሳውቃለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrFawziyaAbikar

በሱማሊያ ተጨማሪ 49 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 49 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 1,219 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አራት (4) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 130 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ሱዳን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 203 ደረሱ!

በደቡብ ሱዳን በዛሬው ዕለት የ108 የላብራቶሪ ምርመራ ውጤት ይፋ ተደርጓል ፤ ዘጠኝ (9) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ወደ 203 ከፍ አድርጎታል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
COVID_19_Prevention_and_Control_Job_Position_selected_Applicant.pdf
8.5 MB
ከደቡብ ክልል ጤና ቢሮ !

የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት የሚያግዙ የጤና የባለሙያ ቅጥር ለመፈጸም ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት (በPDF በምታገኙት) ደብዳቤ መሰረት እስከ ግንቦት 12/2012 ዓ.ም ድረስ በተደመደባችሁበት ዞንና ልዩ ወረዳ በአካል በመቅረብ ቅጥር እንድትፈፅሙ አሳስቧል።

#SHARE #ሼር

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#FicheChambalala

ፊቼ ጫምባላላ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭትን ለመከላከል በአደባባይ እንዳይከበር የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች ወስነዋል። የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች/አያንቶዎች በዓሉ ግንቦት 12 እና 13 ተከብሮ እንዲውልም ቀን ቆርጠዋል።

ወረርሽኝ፣ ጦርነት እና ርሀብ እንዲሁም የታላቅ ሰው ህልፈት ሲከሰት ፊቼ ጫምበላላ በዓል በአደባባይ የማይከበር መሆኑ ታሪካዊ አመጣጥ ያለው መሆኑን የገለፁት አያንቶዎቹ በዓሉ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመከላከል ዘንድሮ አደባባይ እንዳይከበር ወስነዋል፡፡

በኮሮና ወረርሽኝ አማካኝነት ሊከሰት የሚችለውን ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባት በታላቁ (ሶሬሳ) ጉዱማሌም ሆነ በወረዳ እና በቀበሌ ደረጃ በዓሉን በአደባባይ ማክበር የማይቻል እንደሆነም የሀገር ሽማግሌዎች ገልፀዋል።

#fbc
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#BorisJhonson

275 የጤና ባለሞያዎች ህይወታቸውን አጥተዋል!

በዩናይትድ ኪንግደም 275 የጤና ባለሙያዎች በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ኮሮና ቫይረስ በዩናይትድ ኪንግደም 144 የጤና ባለሙያዎችንና 131 የማህበረሰብ ክብካቤ (ሶሻል ወርክ) ሰራተኞችን ህይወት እንደቀጠፈ ገልጸዋል - #AlAin

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#COVID19

የኢትዮጵያና የጎረቤት ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 1,818፣ ሞት 90፣ ያገገሙ 198

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,268፣ ሞት 3 ፣ ያገገሙ 900

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 1,219፣ ሞት 52 ፣ ያገገሙ 130

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 737፣ ሞት 40 ፣ ያገገሙ 281

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 263 ፣ ሞት 5 ፣ ያገገሙ 108

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 203 ፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 2

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 38

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ውድ ቤተሰቦቻችን ከኮቪድ-19 በተጨማሪ ሀገራዊ ጉዳዮችን በ @tikvahethmagazine ታገኛላችሁ!

የስፖርት ወዳጆች ከሆናችሁም ስፖርታዊ ጉዳዮችን በ @tikvahethsport ማግኘት ትችላላችሁ!

ቲክቫህ ኢትዮጵያ!
@tikvahethmagazine @tikvahethsport
ሱዳን ውስጥ በአንድ ቀን የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ!

የሱዳን ጤና ሚንስቴር ባወጣዉ መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓት የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን አሳውቋል ፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 90 ደርሷል።

ከዚህ በተጨማሪ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዙ ሰዎች 1,818 ደርሰዋል ፤ በ24 ሰዓት ውስጥ 157 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በሌላ በኩል ትላንት ሃያ አምስት (25) ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው (ኮቪድ-19) አገግመዋል ፤ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 198 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠው የቤተክርስቲያን አገልግሎት ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መወሰኑን #ኢቢሲ ዘገበ።

ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ እንደገለፁት በቤተክስትያኗ አጥቢያዎች የሚሰጠው አገልግሎት መቋረጡ በምዕምኑ መንፈሳዊ ህይወት ላይ ችግር ማስከተሉን አብራርተዋል፡፡

እናም ፍፁም ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ አገልግሎቱ እንዲቀጥል ሲኖዶሱ መወሰኑን ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#WHO

የኮሮና ቫይረስ ከዓለማችን ላይ እስከወዲያኛው ላይወደገድ እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ ህክምናዎች ዳይሬክተር ዶክተር ማይክ ረያን በትናንትናው እለት በሰጡት ማብራሪያ፥ ቫይረሱ የሚያበቃበትን ጊዜ መተንበይ ትክክል እይደለም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ሁላችንም የኮሮናቫይረስ በዓለም ማህበረሰብ ዘንድ ሌላኛው ወረርሽኝ ሆኖ እስከወዲያኛው ሊቆይ ይችላል የሚለውን ከግምት ማስገባት አለብን ያሉት ዶክተር ረያን፥ ቫይረሱ እስከወዲያኛው አብሮን ሊኖርም ይችላል ብለዋል - #BBC

#AlJazeera
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን!

ከግንቦት 4 - ግንቦት 6 ድረስ የተካሄደው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አስመልክቶ ከቅዱስ ሲኖዶሱ የተሰጠ መግለጫ!

Via @tikvahethmagazine

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,580 ላቦራቶሪ ምርመራ 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 272 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 5 ወንድ እና 4 ሴት እንዲሁም እድሜያቸው ከ17 እስከ 66 ዓመት የሆኑ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 5 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ 4 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) ነው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 4

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 3

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 2

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ማዳጋስካር ?

ማዳካስካር ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።

የማዳስካር ጤና ሚኒስቴር ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ 18 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አሳውቋል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 230 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል ትላንት አንድ (1) ሰው ከበሽታው ማገገሙን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 108 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 ኢኮኖሚውን ክፉኛ እያዳከመው ነው!

በአዲስ አበባ የኮከብ ደረጃ የተሰጣቸው ሆቴሎች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በወር በአማካይ እስከ 35 ሚሊዮን ዶላር እያጡ መሆኑን የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር አስታውቋል።

ኮቪድ 19 የዓለም ወረርሸኝ በመሆን የተለያዩ አገራት የጤና ቀውስ ከመሆንም ባለፈ ኢኮኖሚያቸውን ክፉኛ እያዳከመ ይገኛል።

ቫይረሱ ዓለም አቀፍ መፍትሄ እስካላገኘ ድርስ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ አገሮች ላይም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሱ መበርታቱ የማይቀር መሆኑ ይገመታል።

በኢትዮጵያ አሁን ላይ በተለይ የቱሪዝምና የመስተንግዶ ዘርፉ፣ ግብርናው፣ አምራች ኢንዱስትሪውና የውጪ ንግዱ ክፉኛ እየተጎዳ መሆኑን ጥናቶች እያመላከቱ ነው - #ENA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia