TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.9K photos
1.52K videos
215 files
4.17K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#DrLiaTadesse

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 85 ደረሱ!

በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 431 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 85 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ43 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ፤ ከአሜሪካ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 2 - የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 3 - የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
“በቤትዎ ይቆዩ”

ኢትዮ ቴሌኮም “በቤትዎ ይቆዩ” በሚል የጥቅል አገልግሎት የቅናሽ ማሻሻያ አድርጓል። ቅናሽ የተደረገባቸው ዕለታዊ አገልግሎቶች:-

1. በ5 ብር 30 ደቂቃ የድምጽና 20 አጭር መልዕት - ይህም ከቀድሞው አንጻር የ53 መቶ ቅናሽ አለው።

2. በ5 ብር 100 ሜጋ ባይት የኢንተርኔት ዳታና 20 አጭር መልዕክት ወይም በ10 ብር 250 ሜጋ ባይት የኢንተርኔት ዳታና 20 የአጭር የጽሁፍ መልዕክት - ይህም ከቀድሞ አንጻር የ56 በመቶ ቅናሽ አለው፡፡

3. በ15 ብር ደግሞ 30 ደቂቃ የድምጽ፣300 ሜጋ ባይት የኢንተርኔት ዳታና 20 አጭር የጽሁፍ መልዕክት በአንድነት -ይህም ከቀድሞው አንጻር የ45 በመቶ ቅናሽ አለው።

ከጧቱ 12 ሰዓት እሰከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ያለው ትራፊክ መጨናነቁ ሻል ያለ በመሆኑ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት የአገልግሎት ቅናሹ ተደርጓል።

ኢትዮ ቴሌኮም የኮሮናቫይረስን ለመከላከል በሚል በጥቅል አገልግሎቱ ላይ ያደረገው ማሻሻያ ከነገ ሚያዝያ 8፣ 2012 ጀምሮ ለ2 ወራት ያህል እንደሚቆይም አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ ኢቢሲ፣ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጊፍት ሪል እስቴት በላከልን መልዕክት ቃል የገባውን 1,500,000 ብር ለኮቪድ መከላከያ ብሔራዊ ኮሚቴ ማስረከቡን ገልጾልናል።

ይህ ገንዘብ ድርጅቱ ሌሎች ባለሀብቶችን እና የጊፍት መንደር ቁጥር 2 ነዋሪዎችን በማስተባበር በአይነት ካበረከተው ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የምግብ ግብአቶች ድጋፍ በተጨማሪ ድርጅቱ በግሉ ያበረከተው የገንዘብ ድጋፍ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በላከልን መልዕክት ይህን ወቅት በመደጋገፍ ለማለፍ ሀገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሆነ አሳውቆናል። በሌላ በኩል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ገልጾልናል።

ድጋፍ እና እገዛን በሚመለከት ፦

- ድርጅቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከል እና መቆጣጠርን በተመለከት በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።

- ድርጅቱ በሚገኝባቸው ወረዳዎች እና አጎራባች ወረዳዎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ለ400 ሰዎች እገዛ እና ድጋፍ አድርጋል።

- ተቋሙ ለሚያሳድጋቸው 15 ወላጅ አልባ ህፃናት በየወሩ የሚያደርገው ድጋፍ እንደተጠበቀ ሆኖ የዘይትና የዱቄት ድጋፍ አድርጋል።

የእርድ እና የስጋ ስርጭት አገልግሎትን በሚመለከት ፦

- የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው። ቀዳሚ የነበረው ሰራተኞችን ማሰልጠን፣ ግንዛቤ መስጠት፣ በተለይም ሚኒ ሚዲያውን በመጠቀም ተሰርቷል።

- ድርጅቱ የሙቀት መለኪያ አስገብቶ ሰራተኞች ሲገቡ ሙቀታቸው እንዲለካ፣ የእጅ ጋንት፣ ሳኒታይዘር እና ሌሎች የንፅህና መጠበቂየዎች እንዲሰጥ ተደርጓል።

- ተሽከርካሪዎች ከከተማ ሲመጡ የኬሚካል ርጭት እየተደረገ ይገኛል። ኬሚካል ርጭቱ ሊያገኛቸው የማይችሉ የመኪና ክፍል (በተለይም የጎማ ክፍል) 'ማለፊያ ቦታ' ተሰርቶ መኪናዎች ጎማቸው በኬሚካል እንዲፀዳ እየተደረገ ነው።

- እንስሳት ሲገቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጎ እየተሰራ ነው፣ የእርድ ክፍሎች ሴራሚክ ተደርገዋል፤ ክፍሎቹ ፅዳታቸውን በየጊዜው ይጠበቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጊኒ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የፊት ጭምብል መልበስን አስገዳጅ ማድረጓን ገልፃለች፡፡ የጊኒው ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ ትናንት ለህዝባቸው ባስተላለፉት መልዕክት እያንዳንዱ ዜጋ ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ የፊት ጭምብል ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡

ጭምብል መልበስን ግዴታ ያደረገችው ጊኒ ጥሪውን ተቀብለው ተግባራዊ የማያደርጉ አካላት የ 3 ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

ፕሬዝዳንት አልፋ የንግድ ተቋማት፤የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ሌሎች ድርጅቶች ለሰራተኞቻቸው የፊት ጭምብል እንዲያዘጋጁም ጠይቀዋል፡፡ የሚዘጋጀው የፊት ጭምብል ሀገር ውስጥ የሚመረት እና ብዙ ወጪ የማያስወጣ መሆን አለበት ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,988
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 431
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 3
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ያሉ - 65
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 1
• አጠቃላይ ያገገሙ - 15
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 85

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቻይና የህክምና ባለሞያዎችን ወደሀገራችን ልትልክ ነው!

ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የምታደርገው ጥረት የሚደግፉ የህክምና ባለሙያዎችን ቻይና ወደ ኢትዮጵያ ልትልክ ነው።

እነዚህ የቻይና የህክምና ባለሙያዎች ልምዳቸውን ያጋራሉ እንዲሁም የኮሮና ቫይረስን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የሚያስችሉ መመሪያዎችን እና ቴክኒካል ምክሮችን ለጤና ባለሙያዎች እና ለህክምና ተቋማት ያካፍላሉ ተብሏል።

ምንጭ፦ CGTN, ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

የኦሮሚያ ክልል የኮሮናቫይረስ [ኮቪድ-19]ን ለመከላከል የሚውል እስካሁን ከ90 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዝብ ከተለያዩ አካላት ቃል ተገብቶ ገቢ እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

በአጠቃላይ እስካሁን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በክልሉ በአይነትና በጥሬ ገንዘብ  ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መገኘቱን የክልሉ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ገልጿል።
 
የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ዛሬ ባካሄደው አራተኛ ዙር የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ ባለኃብቶችና ድርጅቶች 10 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

(ENA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 435 ደርሷል!

ባለፉት 24 ሰዓት በጅቡቲ በተደረገ 580 የላብራቶሪ ምርመራ ሰባ ሁለት (72) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በዚህም አጠቅላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 435 ደርሷል። በሌላ በኩል ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 71 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነትን ለመቀነስና የተረጋጋ የበዓል ግብይት ለማካሄድ የቁም እንስሳት መሸጫ ቦታዎች ዝርዝር ይፋ ሆነዋል።

1. አቃቂ ወረዳ 8 (የከብት በረት ማዕከል) ውስጥ ሲሆን ይህንን ለማስፋፋትም ወረዳ 8 ፊት ለፊት የሚገኘው ጥምቀተ ባህር ግቢ ውስጥ ግብይት ይፈጸማል፤

2. የካ ወረዳ 12 የነበረውን መገበያያ ወደ ወረዳ 1 በማዛወር ግብይቱ እንዲከናወን ይደረጋል፤

3. ኮልፌ ቀራኒዮ፡- በቀራኒዮ በኩል ወደ ቤቴል በሚወስደው መንገድ (ወረዳ 7) መንዲዳ የሚባል ቦታ ላይ ተዘጋጅቷል፤ ጉለሌ የነበረው ሸጎሌ የቁም እንስሳት መሸጫ ማዕከልን ለማስተንፈስ እንዲያስችል ወደዚህ ስፍራ እንዲዘዋወር ተደርጓል፤

4. ብርጭቆ ወረዳ 13 የነበረውን ደግሞ እዛው ወረዳ ላይ ሶስት ቦታ በማዘጋጀት – ኒኮላ ሜዳ፣ ሻወር ቤት ብርጭቆ አጠገብ ወረዳ 14 ኦሮሚያ ድንበር ላይ ልዩ ስሙ ኦሮሚያ ሜዳ የሚባል ቦታ ላይ ይከናወናል፤

5.ንፋስ ስልክ – ቄራ ከብት በረት ወረዳ 6 ላይ ያለውን በማስፋፋት ወረዳ 5 ላይ በተጨማሪነት እንዲገበያዩ ይደረጋል፤

6. በግ እና ፍየል ወረዳ 2፣ 3፣5፣ 10 ላይ እና (ቫርኔሮ አደባባይ) ለቡ ጀሞ አካባቢ ተዘጋጅተል፤

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'ከብርሃኔ አደሬ ሞል' በተላከልን መልዕክት ድርጅቱ በቦሌ ክፍለ ከተማ ባለው ህንፃ ለሱቅ እና ለቢሮ አገልግሎት ለተከራዩ 162 ተከራዮች የሶስት ወር የቤት ኪራይ 50 % ቅናሽ መድረጉ ተገልጾልናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኬንያ 9 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፣ 1 ሰው ሞቷል!

ባለፉት 24 ሰዓት 800 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ዘጠኝ (9) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 225 ደርሷል። ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡት 9 ሰዎች መካከል አምስቱ (5) ከናይሮቢ አራቱ (4) ከሞንባሳ ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪ ተጨማሪ አንድ ሰው በቫይረሱ በመሞቱ የማቾች ቁጥር 10 ደርሷል። እንዲሁም አስራ ሁለት (12) ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸው በመረጋገጡ አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 53 መድረሱን የኬንያ ጤና ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 ክትባትም ሆነ መድሃኒት የለውም!

በመዘናጋት ከፍተኛ ዋጋ እንዳንከፈል በድጋሚ አደራ ለማለት እንወዳለን። በአሁን ሰዓት ለኮሮና ቫይረስ በሽታ [ኮቪድ-19] ምንም የተረጋገጠ ክትባትም ሆነ መድሃኒት የለውም።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የምትሰሟቸው መረጃዎች በስራ ላይ ያሉ እጅግ በጣም ጊዜ የሚፈልጉ ናቸው። አሁን ያለው ብቸኛው መድሃኒት የጤና ባለሞያዎችን ምክር ማዳመጥ ነው።

ከሰሞኑን በአሜሪካ የጤና ተቋም CDC በኃላፊነት የሚሰሩት ዶክተር ኤርሚያስ በላይ ይህን ማለታቸው አይዘነጋም ፦ "...ለዚህኛው ቫይረስ [ለኮቪድ-19] ክትባት እንደሚገኝለት ተስፋ አደርጋለሁ። ግን ይሄን ክትባት ለማግኘት ብዙ ጊዜ ይወስዳል። ከ8-12 #ወራት ሊወስድ ይችላል።"

በተለያዩ ባልተጨበጡ መረጃዎች ፣ እንዲሁም በሂደት ላይ ባሉ የምርምር ስራዎች ዙሪያ የሚወጡ መረጃዎችን በመስማት የስፔን እና ጣልያን አሁን ደግሞ የአሜሪካ ዜጎች እየከፈለቱ ያለውን ዋጋ እንዳንከፍል አደራ።

እራሳችንን እንጠብቅ፤ የምንባለውን እናድምጥ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia