#DrLiaTadesse
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ ደረጃቸውን የጠበቁ የፊት ጭንብሎች በአገር ውስጥ በስፋት ለማምረት እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል።
በሥራቸው ባህሪ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች የፊት ጭንብል እና ጓንት አዘውትረው እንዲጠቀሙ ምኒስትሯ ምክረ ሃሳብ ለግሰዋል።
ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደተናገሩት ፤ ደረጃቸውን የጠበቀ የፊት ጭንብል በአገር ውስጥ እንዲመረት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እየተሰራ እንደሆነ አሳውቀዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

በጅቡቲ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 150 ደረሱ!
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 341 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አስር (10) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በሀገሪቱ ያሉ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች አንድ መቶ ሀምሳ (150) ደርሰዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 341 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አስር (10) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በሀገሪቱ ያሉ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች አንድ መቶ ሀምሳ (150) ደርሰዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኬንያ 10 ተጨማሪ ሰዎች አገገሙ!
ባለፉት 24 ሰዓት 504 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አምስት ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በሀገሪቱ የተመዘገቡ የኮሮና ቫይረስ ኬዞች 189 ደርሷል።
በተጨማሪ 10 ተጨማሪ ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸው ተገልጿል። አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 22 ደርሷል።

በባህር ዳር የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተጀምሯል!
በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መጀመሩ ተገልጿል። የኮሮና ቫይረስ ምርመራው በክልሉ የማህበረሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ውስጥ ነው የተጀመረው።
መመርመሪያ መሳሪው ካለው የሰው ሀይል አንፃር በቀን የ100 ሰዎችን ናሙና በመውስድ የሚመረምር መሆኑን በምክትል ርዕስ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ሙሉነሽ አበበ ገልጸዋል።
ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ

#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የታክሲ ትራንስፖርት ታሪፍ ማስተካከያ ማድረጉን አስታውቋል።
በተስተካከለው ታሪፍ መሰረት ዝቅተኛው ሶስት (3) ብር ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ 12 ብር ከ50 ሣንቲም ሆኗል። በመመሪያው መሰረት ታክሲዎች ከመጫን አቅማቸው 50 በመቶ ብቻ እንዲጭኑ ይገደዳሉ።
መመሪያውን ተላልፎ የተገኘ አሽከሪካሪ የ5 ሺህ ብር ቅጣት የሚጠብቀው ሲሆን በወንጀልም ተጠያቂ ይሆናል። ተሳፋሪዎች እጥፍ ታሪፍ ከፍለው እንዲጓዙ በመመሪያው ተደንግጓል።
በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ሕገ ወጥ ተግባራት ሲያጋጥሙ ጥቆማ የሚሰጥበት የጥሪ ማዕከል ተዘጋጅቷል።
በተጨማሪም በታክሲ አገልግሎት የሚያጋጥሙ ሕገ ወጥ ተግባራትን ተከታትለው እርምጃ የሚወስዱ ከ100 ያላነሱ ሞተር ሳይክሎች ተሰማርተዋል።

የኮሮና ቫይረስ ምርመራ በኢትዮጵያ!
የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ምርመራ ለማድረግ የሚያስችል ቤተ ሙከራ አዘጋጅቷል።
ኢንስቲትዩቱ ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር ምርመራውን በጥቂት ቀናት ውስጥ መጀመር የሚያስችለው ዝግጅት ማጠናቀቁን አሳውቋል።
ቤተ ሙከራው የመጀመሪያ ምዕራፍ ሥራውን ሲጀምር በቀን 50 ናሙናዎችን መርምሮ ውጤቱን የማሳወቅ አቅም ያለው ሲሆን በ2ኛው ምዕራፍ እስከ 100 ናሙናዎችን መመርመር ይችላል ተብሏል።
የኢኖቬኝና የቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ አብረሃም በላይ (ዶ/ር) መንግሥት ቫይረሱን የመርመር አቅምን ለማሳደግ የተለያዩ ተግባራትነ እየከወነ ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጣሰው ወልደሃና (ፕ/ር) ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት ቫይረሱን በመርመር ረገድ በርካታ ስራዎች እንደሚቀሯት ገልጸው ምርመራው ሊጠናከር ይገባልም ብለዋል።
ምንጭ፦ አሐዱ ቴሌቪዥን

በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 3 ደረሰ!
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ፦
"በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት በሀገራችን በዛሬው እለት #ሦስተኛው ሰው ህይወት ማለፉን ስገልጽ በከፍተኛ ሀዘን ነው። ታማሚዋ በለይቶ ማቆያ ከመጋቢት 28 ጀምሮ ህክምና ሲደረግላቸው የነበርና ከገቡበት ቀን ጀምሮ በጽኑ ህሙማን ክፍል ክትትል ላይ የነበሩ ናቸው። በዚህም የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በእራሴና በጤና ሚንስቴር ስም እየገለጽኩ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅዘመዶቻቸው ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ።"

ሁሴን ሞል - ሀዋሳ!
ይህን ፈታኝ ወቅት በመገንዘብ ፣ እንደማህበረሰብ መተጋገዝ ና መደጋገፍ እንዲጠናከር እና ለማድረግ የመጋቢት እና የሚያዚያን (ሁለት ወር) የኪራይ ክፍያ ነፃ አድርጓል።

እናት ፓርቲ 'የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን' አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የፃፈው ደብዳቤ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ውድ ቤተሰቦቻችን በሀሰተኛ ገፆች እንዳትታለሉ!
በኢትዮ ቴሌኮም ስም እንዲሁም በጤና ሚኒስቴር ስም የተለያዩ ሀሰተኛ የቴሌግራም ገፆች ተከፍተዋል።
በዚህ ፈታኝ ወቅት አንዳንድ አካላት አጋጣሚውን በመጠቀም ለማጭበርበር እየሞከሩ ነው። ሌሎች ደግሞ ተከታይ ለማፍራት ሲሉ የማያደረጉት ነገር የለም።
በመሆኑም መላው የቲክቫህ አባላት በሀሰተኛ መረጃ እና በሀሰተኛ ገፅ እንዳትታለሉ ለማሳውቀ እንወዳለን። ጤና ሚኒስቴር የቴሌግራም አድራሻዬ ይሄ ነው ብሎ በይፋ ያሳውቀው ነገር የለም።

አ/አ 22 አካባቢ በአቶ ደግፌ ኮሬ እና በወ/ሮ አሰፋች ድራጋ የሚተዳደርው 'ፀጋ የገበያ ማዕከል' ለ130 ተከራዮቹ የሚያዚያ ወር ክፍያን ነጻ አድርጓል። የሕንጻው ወርሀዊ ገቢ ከ1,020,000 ብር ነው።
በተጨማሪም ለከተማው አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገው ድጋፍ ለማጠናከር 100,000 ብር አስተዋፅኦ አድርገዋል።
#NewayTsegaye
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በተጨማሪም ለከተማው አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገው ድጋፍ ለማጠናከር 100,000 ብር አስተዋፅኦ አድርገዋል።
#NewayTsegaye
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሌላኛው ፈተና...
የበረሐ አንበጣ መንጋ አሁንም በኢትዮጵያ ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ አሳሳቢ መሆኑን የዓለም የእርሻና የምግብ ድርጅት አስጠንቅቋል።
የአንበጣ መንጋው በበረታባቸው ኢትዮጵያ ፣ ኬንያ፣ሶማሊያ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ዩጋንዳና ታንዛኒያ 20 ሚሊዮን ሰዎች እንዲሁም በየመን 15 ሚሊዮን ሰዎች ብርቱ የምግብ ዋስትና እጦት እንደገጠማቸው ገልጿል።
በመጋቢት ወር የሚጠበቀው ዝናብ በመጪዎቹ ወራት በምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ የአንበጣ መንጋ እንደሚፈጥር የገለጸው ድርጅቱ ከኬንያ ወደ ደቡብ ሱዳን እና ዩጋንዳ እንደሚዛመት አስጠንቅቋል።
ከምሥራቅ አፍሪካ በተጨማሪ አዳዲስ የአንበጣ መንጋ እየተፈለፈለ በሚገኝባቸው በኢራን እና በየመን አሳሳቢ እንደሚሆን የዓለም የእርሻና የምግብ ድርጅት በትናንትናው ዕለት ያወጣው መግለጫ ይጠቁማል።
ድርጅቱ እንዳለው በኮቪድ-19 ሳቢያ በአገራቱ በሰዎች እና አስፈላጊ ቁሳቁሶች እንቅስቃሴ ላይ ገደብ መጣሉ የአንበጣ መንጋን ለመከላከል ፈተና ሆኗል።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ

#StateofEmergency
ባልተረጋገጡ ወሬዎች እንዳትረበሹ!
የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅን በተመለከተ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተሰጠ ማሳሰቢያ፦
የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በሚኒስትሮች ም/ቤት የታወጀዉን የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ በዛሬው ዕለት አጽድቋል፡፡
በአዋጁ አንቀጽ 4 ንዑስ ቁጥር 1 እና 2 መሰረት የሚጣሉ የመብት እገዳዎች፣ እርምጃዎች እንዲሁም ግዴታዎችን በተመለከተ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ነገ ቅዳሜ ሚያዚያ 3 ቀን 2012 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ መግለጫ ይሰጣል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰባችን ከአሰቸኳይ አዋጁ ጋር በተያያዘ ያልተረጋገጡ ወሬዎችን እና መረጃዎችን ከመሰማት እንዲቆጠብ እናሳስባለን።
በአዋጁ መሰረት ከሚዉጡ ህጎች ጋር በተያያዘ ማብራሪያ የመሰጠት ኃላፊነት በተሰጠዉ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በኩል እስከሚሰጥ ድረስ በትዕግስት እንድትጠባበቁን በአክብሮት እንጠይቃለን። ዝርዝር መግለጫው የሚሰጥበትን ሠዓት ነገ አሰቀድመን የምናሳወቅ ይሆናል ፡፡
ሚያዚያ 2 ቀን 2012 ዓ.ም
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

#FightCOVID19
ወጣቱ ባለሃብት ዮሃንስ ሀይሌ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ ማለትም 150 ኩንታል በቆሎ ዱቄት 50 ኩንታል ሩዝ 50 ኩንታል ፉርኖ ዱቄት ለወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የተቸገሩ ወገኖች የሚዉል ድጋፍ ማደረጉን ሰምተናል። የከተማው አስተዳደርም ወጣቱ ባለሀብት ላደረገው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና ማቅረቡ ተገልጾልናል።

አንድ፣ ሁለት ብሎ የጀመረው የቤት ኪራይ ነፃ የማድረግ በጎ ተግባር አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው!
አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኘው 'የአይመን ንግድ ማዕከል' በህንፃው ተከራይተው ለሚሰሩ ነጋዴዎችና ድርጅቶች በሙሉ የአንድ ወር ኪራይ (የሚያዚያን) ነፃ አድርጓል።