TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Nekemte

በነቀምቴ ከተማ ባለፈው አንድ ዓመት ገደማ ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት የንግድና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ጫና በማሳደሩ አንዳንድ ባለሃብቶች ወደ ሌላ ቦታ እየሄዱ እንደሚገኙ ከከተማው ነዋሪዎች መካከል ገልፀዋል።

የኢንተርኔት አገልግሎትም በከተማው መቋረጡና በአብዛኛው የወለጋ ዞኖች የስልክ አገልግሎት አለመኖርም ሥራቸው ላይ እንቅፋት መሆኑን እንዳንድ በንግድ ሥራ የሚተዳደሩ ሰዎች ለቪኦኤ ተናግረዋል።

የነቀምቴ ከንቲባ አቶ በሪሶ ተመስጌን ከተማዋ በአሁኑ ሰዓት ተረጋግታለች፣ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዋም እንዲቀላጠፍ ውይይት እናደርጋለን ብለዋል።

#የአሜሪካድምፅሬድዮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia