TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#NewsAlert

ከደቂቃዎች በፊት በአልጄሪያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ሞት ተመዝግቧል። በሀገሪቱ ዛሬ የተመዘገቡ 4 ኬዞችን ጨምሮ 24 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አቶ ጌታሁን አብዲሳን የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አድርጎ ሾሟል፡፡ የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው የ5ኛ 5 ዓመት 5ኛ የሥራ ዘመን 5ኛ አስቸኳይ ጉባዔው አቶ ጌታሁን አብዲሳን የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር እንዲሆኑ እንዲሆኑ የቀረበውን ሹመት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን በአዲስ መልክ ለማዋቀር በወጣው አዋጅ መሠረት ለተቋሙ የቦርድ አባልነት የቀረቡ አዳዲስ እጩ ተሿሚዎችን በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

በዚሁ መሠረት፦

1. አወሉ አብዲ - ሰብሳቢ
2. አበበች ሺከታ
3. ዶ/ር አጋረደች ጀማነህ
4. ማንያዘዋል እንደሻው
5. ዳንኤል ክብረት
6. ኦባንግ ሜቶ
7. ዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ
8. ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ
9. ጌትነት ታደሰ አባል

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አዲሱ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽነር!

አቶ ፀጋ አራጌ የሥነ–ምግባርና ጸረ–ሙስና ኮሚሽነር ሆነው ዛሬ ጥዋት ተሹመዋል። ሹመታቸው 11 ተቃውሞ 6 ድምጸ ተዓቅቦ ገጥሞታል። የሰሜን ወሎ አስተዳዳሪ፣ የአማራ ከልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ኃላፊ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪ ነበሩ።

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ውዝግብ ያስነሳው የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሹመት!

ዛሬ የምክር ቤት አባላት ምክር ቤቱ ሹመት በመስጠትና በመንፈግ ላይ መጠመዱን በማንሳት ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ቦርድ አባልነት የቀረቡት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አሰምተዋል።

ለኢትዮጵያ የፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባል ሆነው ከቀረቡ ዘጠኝ ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ቅሬታ ያቀረቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እንዳሉት ከሆነ ግለሰቡ የሀይማኖት እኩልነት ላይ የማያምኑ፣ በዜጎች መካከል ክፍፍል እንዲፈጠር የሚሰሩ፣ በማለት በሕዝብ የሚነሱባቸው ቅሬታ ወደ ጎን በመተው መቅረብ አልነበረባቸውም በሚል አባልነታቸውን ተቃውመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት መላውን ኢትዮጵያ የሚያገለግል በመሆኑ በእርሳቸው የቦርድ አባልነት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባል ሆነው ከቀረቡት አባላት መካከል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ቅሬታ በመቅረቡ ለብቻው ጉዳያቸው ታይቶ ድምጽ እንዲሰጥ ከተደረገ በኋላ በ148 ድጋፍ በ126 ተቃውሞ እና 24 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ የዲያቆን ዳንኤል የቦርድ አባልነት ፀድቋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በድሬዳዋ የጅብ መንጋ ጉዳት አሳሳቢ ሆኗል!

በከተማዋ ገንደ ሮቃ በተባለው አካባቢ የሰፈረውን የጅብ መንጋ ለማባረር የተቀናጀ ርብርብ እየተካሔደ ቢሆንም መንጋው አሁንም እያዘናጋ በጨቅላ ህፃናት ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በዚሁ አካባቢ ባለፈው የካቲት ወር አንድ የሶስት ዓመት ህፃን የወሰደው የጅብ መንጋ፤ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 1ሰዓት ላይ ሌላ የሁለት ዓመት ህፃን በመውሰድ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉንም ነዋሪዎች ገልፀዋል።

የጅብ መንጋውን ከአካባቢው ለማባረር በሰፈሩ የሚገኙ ጥሻና ዋሻዎችን የማፅዳት ስራ ከተጀመረ አንድ ወር የሞላው ቢሆንም መንጋው ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ ችግር እየፈጠረ ነው ተብሏል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዓለም አቀፍ መረጃ፦

- በዓለም ላይ ከ126,500 በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተዋል።

- በመላው ዓለም 4,637 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል።

- በ24 ሰዓት ውስጥ 7,000 አዲስ ኬዞች ተመዝግበዋል።

- በUS ብቻ 1,280 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፤ 38 ሰዎች ሞተዋል።

- በኮሮና እየታመሰች በምትገኘው የአውሮፓ ሀገር ጣልያን 827 ሰዎች ሞተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፓስፖርት በ1 ወር ጊዜ ውስጥ መሰጠት ሊጀመር ነው!

የፌደራል ኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ከመጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ፓስፖርት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መስጠት ሊጀምር መሆኑን ገለጸ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጅብ ጀማል እንደገለጹት፥ ከዚህ ቀደም አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት ሁለት ወር ከ15 ቀን በላይ ይወስድ የነበረው ጊዜ ወደ አንድ ወር ዝቅ እንዲል ተወስኗል።

በአዲሱ አሰራር መሰረት ፓስፖርት በአስቸኳይ ለማውጣት እስከ አምስት ቀን ብቻ እንደሚወስድም ተናግረዋል።

ካለፈው ዓመት የካቲት ወር ጀምሮ በፓስፖርት ወረቀት እጥረት ምክንያት የአዲስ ፓስፖርት መስጫ ጊዜ ከአንድ ወር ወደ ሁለት ወር ከ15 ቀን መራዘሙ ይታወሳል።

በአሁኑ ሰዓት ኤጀንሲው ከ270 ሺህ እስከ 300 ሺህ ፓስፖርት እንዳለው የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፥ በቀጣይ 500 ሺህ ፓስፖርት ለማስገባት ስምምነት መደረሱን ገልፀዋል።

#ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PASSPORT

በአሁኑ ሰዓት ከ270,000 - 300,000 የሚደርስ ፓስፖርት እንዳለው የፌደራል ኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ገልጿል፤ በቀጣይ 500 ሺህ ፓስፖርት ለማስገባት ስምምነት መደረሱም ተሰምቷል።

ኤጀንሲው ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር 'አዲስ ፓስፖርት' ለማውጣት ተመዝግበው ከሁለት ወር እስከ ሶስት ወር የሆናቸው 90,000 ተገልጋዮች እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

የፌደራል ኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ መሰል ችግሮችን ለማስወገድም ከፊታችን መጋቢት 10 ቀን ጀምሮ አዲስ አሰራር ተግባራዊ ያደርጋል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PASSPORT

የINVEA 10 ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል!

በአስቸኳይ ፓስፖርት ለማውጣት የሚጠየቁ መስፈርቶችን ያላሟሉ እና መደበኛውን ፓስፖርት ያለአግባብ ሲሰጡ የነበሩ ሰራተኞች እንደነበሩ በዛሬው ዕለት ተገልጿል።

ያለአግባብ መስፈርቱን ላላሟሉ እና ለውጭ ዜጎች ፓስፖርት የሰጡ 10 ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። በተደረገው የማጣራት ስራ ሰራተኞቹ ከውጭ ዜጎቹ ከ5 ሺህ ዶላር በላይ መቀበላቸውን ተገልጿል፤ 77 የሚሆኑ ፓስፖርቶች በህገ ወጥ መልኩ ተሰርተው መገኘታቸውንም ተሰምቷል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ፓስፖርቶቹ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ለኢንተርፖል ማሳወቅ እና ሰዎቹን ተጠያቂ የማድረግ ስራ መስራቱ የፌደራል ኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ገልጿል።

#FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሁለት ሹመቶችን ሰጥተዋል። በዚህ መሰረት ፦

1.ወይዘሮ ህይወት ሞሲሳ- የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር እና

2.ሜጀር ጀኔራል አህመድ ሀምዛ - የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾመዋል።

ሹመቱ ከመጋቢት 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተሰጠ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

#PMOEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

በመከላከያ ምክትል የኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የተመራ የልዑካን ቡድን በሱዳን የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ መሆኑን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤንባሲ አስታውቋል።

የልዑካን ቡድኑ በጉብኝቱ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብደላ ሐምዶክ፣ ከሱዳን መከላከያ ሚኒስትር ጄኔራል ጀማለዲን ኦማር እና ከሱዳን ኤታማዦር ሹም ጄኔራል መሃመድ ኡስማን አልሃሰን ጋር ውይይቶችን አካሂዷል።

በሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ የተቃጣውን የግድያ ሙከራ ያወገዙት የልዑካን ቡድኑ አባላት፣ እንዲህ ባለው አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ከሱዳን ጎን እንደምትቆም አረጋግጠዋል።

[በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የሚቃጣ ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት እና አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነው" - የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት

የFDRE ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ጀኔራል አደም መሃመድ ፣ የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ይልማ መርዳሳ እና የሰራዊቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ እና የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎችም ተሳትፈዋል።

በጉብኝታቸውም በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ርብርብ እየተገነባ ያለውን የህዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደት ተዘዋውረው መመልከታቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ሹመቱ የትግራይ ተወላጆችን ያገለለ ነው!" - ዛሬ ሹመቱን ከተቃወሙ የምክር ቤት አባላት

የዛሬው የአራቱን ሚኒስትሮች ሹመት 21 የሕወሓት አባላት ተቃውመውት ነበር፡፡ ሹመቱ የትግራይ ተወላጆችን ያገለለ እንደሆነ፣ ላለፉት 27 ዓመታት ሕወሓት ያፈራውን ሀብት ለመቀራመት የሚደረግ ሹመት ነው የሚሉ ተቃውሞዎችም ተሰምቷል፡፡

ሌሎቹ የምክር ቤት አባላት ደግሞ በተሿሚዎቹና በሹመቱ ላይ የቀረበውን ትችት ያስተባበሉ ሲሆን ፣ ‹‹ሚኒስትሮቹ የሚሾሙት ላለፉት ዓመታት የተዘረፈ ሀብትን ለማስመለስ ነው፤›› ሲሉ ወ/ሮ ብርቱካን ታደሰ የተባሉ የምክር ቤቱ አባል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባል የሆኑት አቶ ተስፋዬ ዳባ ደግሞ ዶ/ር ሊያ ከትግራይ ብሔር መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አቶ ተስፋዬ ከዚህ ቀደም ሚኒስትሮችን ለመሾም የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ቡራኬ ያስፈልግ እንደነበር ገልጸው፣ አሁን ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕገ መንግሥቱ የሰጣቸውን መብት ተጠቅመው ሹመት መስጠት በመጀመራቸው ምክንያት የቀረበ ተቃውሞ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የከሚሴው ግጭት ተከሳሾች ክስ ተቋረጠ!

በአማራ ክልል ኦሮሚያ ልዩ ዞን በከሜሴ የተለያዩ ወረዳዎች ተነስተው በነበሩ ግጭቶች ተከሰው የነበሩ ግለሰቦች ክስ መቋረጡን አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቶባቸው ከነበሩ ከ80 በላይ ግለሰቦች ውስጥ የእድሜ፣ የጤና እና የወንጀል ተሳትፎን በመመልከት ቁጥራቸው 14 ለሚጠጉ ተከሳሾች ሰኞ የካቲት 30/2012 ክስ አቋርጧል፡፡

በተመሳሳይም በአማራ ክልል በእስር ላይ የነበሩ አምስት የወረዳ አመራሮች ክሳቸው መቋረጡን አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam

ጄኔራል አደም መሃመድ፦

"የመከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱ ህዝቦች ሰላምና ሉዓላዊነት የማስከበር ተልዕኮውን ለመወጣት በላቀ ብቃት ላይ ይገኛል። በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የሚቃጣን ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት እና አስፈላጊውን አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነው። የመከላከያ ሰራዊቱ ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ህዝብና መንግስት የሰጡትን ተልዕኮ በላቀ ብቃት እየተወጣ ይገኛል። ሰራዊቱ ግድቡ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በየወሩ ከደመወዙ በመቆጠብ የዜግነት ድርሻውን እየተወጣ ነው።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam

አየር ሃይል ዋና አዛዥ ሜ/ጀኔራል ይልማ መርዳሳ፦

"የኢፌዴሪ አየር ሃይል በቀጠናው የሚቃጣን የአየር ላይ ጥቃት ለመመከት ብሎም አስፈላጊውን አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነው።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AlJazeeraArabicLive

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአልጀዚራ ቴሌቪዥን አረብኛ ፕራግራም ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ በአሁን ሰዓት እየተሰራጨ ይገኜ። ቃለምልልሱ ለተከታታይ ለአራት ቀናት ይተላለፋል።

ቃለምልልሱን ለመከታተል በኢትዮጵያ አቆጣጠር፦

1. ዛሬ ሀሙስ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓም ከምሽቱ በ1:00 ሰዓት ጀምሮ እየተላለፈ ይገኛል።

2. በድጋሜ ነገ አርብ መጋበት 4 ቀን 2012 ዓም ከጧቱ በ5:30 ይቀርባል፣

3. ቅዳሜ ከቀኑ በ7:30 ይደገማል፣

4. በድጋሜ እሁድ ከሌሊቱ በ10:30 ይቀርባል፣

https://youtu.be/ueliG2kthek

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam

ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ያላትን አቋም ለማስረዳት በተለያዩ አገራት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን በመላክ ላይ ትገኛለች።

በዚሁ መሰረት በኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ዛሬ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓም ኬንያ ናይሮቢ በመገኘት ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ያላትን ግልጽ አቋም ለፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አስረድቷል።

ሁለቱ መሪዎች ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ያደረጉትን ውይይት ተከትሎም የጋራ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።

በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሚመራው የልኡካን ቡድን በቀጣይም በሌሎቹ የአባይ ተፋሰስ አገራት ተመሳሳይ ጉብኝት በማድረግ ለአባል አገራቱ መሪዎች የኢትዮጵያን አቋም እንደሚያስረዳ ይጠበቃል።

#EPA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam

በቀደሞው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ከዛሬ ጀምሮ በአውሮፓ በመገኘት ከአውሮፓ ህብረት ፕሬዝዳንት ፣ ከፈረንሳይ እንዲሁም ከሌሎች የህብረቱ አባል አገራት መሪዎች ጋር በመገናኘት ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያን አቋም ለማስረዳት ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia