TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የኮሮና ቫይረስ በሽታን #COVID19 ለመከላከል እና ለማከም የሚረዱ መድሃኒቶች አሉ?

- ምንም እንኳን መድሃኒት ለማግኘት ብዙ ምርምሮች እየተሰሩ ቢሆኑም እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ ለኮሮና ቫይረስ በሽታ ህክምና የሚውል መድሃኒት የለም።

- የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ማንኛውም አይነት መድሃኒት መውሰድ እና የመከላከል አቅምን ለመጨመር በሚል ከአንድ በላይ የፊት ማስክ ደራርቦ መጠቀም አይመከርም።

#ጤናሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የኮሮና ቫይረስ [#COVID19] መተላለፊያ መንገዶች እንድታውቋቸው፦

የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የመተንፈሻ አካል የሚያጠቃ በሽታ ነው። ዋናው የመተላለፊያ መንገድ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በሚያስሉበት እና በሚያስነጥሱበት ወቅት ትንፋሽ ጋር በሚወጡ ፈሳሾች ጋር በሚደረግ ንክኪ ነው።

እንዴት መከላከል ይቻላል?

- በሚያስነጥሱበት ወይም በሚያስሉበት ወቅት አፍና አፍንጫዎን በክንድ ወይም በሶፍት መሸፈን

- አይን፣ አፍንጫ እና አፍን ባልታጠበ እጅ አለመንካት

- በውሃ እና በሳሙና መታጠብ፣ አልኮል ነክ በሆኑ የንፅህና መጠበቂያዎች እጅዎን በአግባቡ ማሸት

- የተጠቀሙበትን ሶፍት በፍጥነት በጥንቃቄ መክደኛ ወዳለው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ መጣል

#ጤናሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia