TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#DIREDAWA

በድሬዳዋ ተከስቶ የነበረውን ሁከትና ብጥብጥ ተከትሎ ለጠፋው የሰው ሕይወትና ንብረት ተጠርጥረው በተያዙ ሰዎች ላይ ክስ ለመመስረት ምርመራ መጀመሩን በኢፌድሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የጽህፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ ረድኤት ግርማ እንደተናገሩት ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ እጃቸው አለበት የተባሉ 51 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል የተቀናጀ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።

https://telegra.ph/ETH-11-04

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ!

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክቡር አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ዛሬ ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ላይ በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዋና መ/ቤት መስብስቢያ አዳራሽ በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ውስጥ እና በአዲስ አበባ ከተማ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ/ም በክልሉ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና በፀጥታ አካላት እንዲሁም በመከላከያ ጄኔራሎች ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች ዙሪያ አንድሁም ስለተቋሙ ሌሎች የሥራ እንቅስቃሴ አሰመልክቶ ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ይስጣሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ60 ዓመቷን አዛውንት የደፈረው ግለሰብ ተቀጣ!

በአዲስ አበባ ከተማ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ፖሊስ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ60 ዓመቷን አዛውንት አስገድዶ የደፈረው የ 18 ዓመት ወጣት በ18 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት ተቀጣ።

መኪና በመጠበቅ ሥራ ላይ የተሰማራው ግለሰቡ ድርጊቱን በፈጸመበት እለት ሐምሌ 8 ቀን 2009 ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ላይ፤ ማደሪያ የሌላቸው፣ ሸራ ወጥረው ጎዳና ላይ የሚኖሩና በዛም ላይ ሳንባ በሽታ ያለባቸውን አዛውንት ከሚጠብቀው መኪና በአንዱ ውስጥ በተኙበት ድብደባ በመፈፀም እና ራሳቸውን መካላከል እንዳይችሉ በማድረግ ጥቃቱን አድርሷል።

የግል ተበዳይም አንድ የሚያውቁት የመኪና ባለቤት ብርድ በሚሆን ጊዜ በመኪና ውስጥ እንዲያድሩ በነገራቸው መሰረት ለመኪኖቹ ጠባቂ በማሳወቅ በሰጣቸው ፈቃድ መሰረት ወደ መኪናው ያመራሉ። ብርድ ልብሳቸውን ይዞ እንዲሔድ ቀድመው ሰጥተውት የቀረ ልብሳቸውን ይዘው የተከተሉት አዛውንት መኪና ውስጥ ገብተውም የያዙትን ልብስ ደራርበው ለብሰው ይተኛሉ።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-04-2

(አዲስ ማለዳ ጋዜጣ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀብሩ ወረዳ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተማሪዎች ማጣት ሊዘጋ ነው!

ሰሜን ወሎ ዞን በሀብሩ ወረዳ የተገነባው አንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተማሪዎች ማጣት ምክንያት ሊዘጋ መቃረቡን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ገልጿል።

ትምህርት ቤቱ እንዳይዘጋ ህብረተሰቡና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በመፍትሔው ዙሪያ እየመከሩ ነው ተብሏል።

የሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸጋው አገሸን እንደገለፁት በሀብሩ ወረዳ በ5 ሚሊዮን ብር ተገንብቶ በ2009 ዓም ስራየጀመረው የአረሪት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተማሪዎች ማጣት  ትርጉም ያለው አገልግሎት ሳይሰጥ የመዘጋት አደጋ ተጋርጦበታል።

በአካባቢው እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ የሚያስተምሩ 7 መጋቢ ትምህርት ቤቶች ታሳቢ በማድረግ የተከፈተ ቢሆንም ህብረተሰቡ 8ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት ባለመላኩ ምክንያት ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዳልቻለ አስረድተዋል ።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-04-3

@tsegabwolde @tikvahethiopia
IBSA GAADDISA HOOGGANSA OROMOO

"ብዝሃነትን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝምን ለማጠናከርና በህዝቦች መካከል አንድነትና እኩልነት እንዲኖር ይሰራል":- ጋድሰ ሆገንሰ ኦሮሞ

በጋድሰ ሆገንሰ ኦሮሞ ስር የተደራጁ የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ብዝሃነትን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝምን ለማጠናከርና በህዝቦች መካከል አንድነት፣ እኩልነትና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲኖር ይሰራሉ፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች አሁን የምንወስዳቸው እርምጃዎች ለቀጣይ የኦሮሞና የአገሪቱ ህዝቦች ዕጣ ፋንታ ወሳኝ ናቸው ብለዋል፡፡

ፓርቲዎቹ በአጠቃላይ በኦሮሚያ ክልል እየታዩ ባሉ የጸጥታ ችግሮችና ሰሞኑን በክልሉ በተከሰተው የጸጥታ ችግር መሰረታዊ መንስኤዎች ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት የስራ ክፍፍል ማድረጋቸውም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

በአገሪቱ የሚደረገው ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞራሲያዊ እና ፍትሓዊ እንዲሆን መደረግ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ጥናት ከተደረገ በኋላ ጥልቀት ያለው ውይይት ተደርጎ ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥም ፓርቲዎቹ ወስነዋል፡፡

ፓርቲዎቹ በመካከላቸው ያሉትን ልዩነቶች በውይይት ለመፍታት ተስማምተዋል፡፡ በአገሪቱ የመጣው ለውጥ አስተማማኝ መሰረት እንዲኖረው ለማድረግ በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ድርሻ ካላቸው ሁሉም አካላት ጋር ቀጣይነት ያለው ውይይት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ምንጭ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርስቲ በቃሉ ወረዳ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ለሁለተኛ ጊዜ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ዳይሬክተሮች እና የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ከ8 በላይ በሚሆኑ አውቶቢሶች ከ900 በላይ ተማሪዎች በመያዝ ከደጋን እስከ 17 ኪሎሜትር በእግር በመጓዝ የሰብል ስብሰባ እና የአንበጣ መከላከል ስራ እየተሰራ ይገኛል።

ምንጭ፦ ወሎ ዩኒቨርስቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ ከሁለት ቀናት በኋላ እንደሚጀመር የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፦

ህዳር 10 ፣2012 ለሚካሄደው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጠት የሚፈልጉ ከጥቅምት 26 እስከ ህዳር 6 ፣2012 ባሉት 10 ቀናት መመዝገብ እንደሚኖርባቸው ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡ ቦርዱ በድምጽ ሰጭነት ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶችም አስቀምጧል፡፡ በዚሁ መሰረት፦

• በሲዳማ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ውስጥ ነዋሪ የሆነ/የሆነች

• ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሆነ/የሆነች፣

• በምዝገባው ዕለት ዕድሜው 18 አመት እና ከዚያ በላይ የሆነ/የሆነች፣

• በቀበሌው 6 ወር የኖረ/የኖረች ናቸው፡፡

ቦርዱ በድምፅ ሰጪነት ሊመዘገቡ የማይችሉ አካላትንም አሳውቋል፡፡ በዚህም፦

• ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያልሆነ/ያልሆነች፣

• በምዝገባው ዕለት ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች የሆነ/የሆነች እና በድምፅ መስጫ ጣቢያው ከ6 ወር በታች የኖሩ

• በአዕምሮ ህመም ምክንያት የመወሰን አቅም የሌለው መሆኑ ስልጣን ባለው አካል የተረጋገጠበት/የተረጋገጠባት ሰው

• የመምረጥ መብቱ በህግ ወይም አግባብ ባለው ህግ መሰረት በፍርድ ቤት ውሳኔ የተገደበበት/የተገደበባት ሰው ናቸው፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-04-5
"መደመር መፅሐፍ" በፒዲኤፍ ተሰርቆ መውጣቱ ተሰማ!

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተፃፈው መደመር የተሰኘው መፅሐፍ ከቀናት በፊት በኤሌክትሮኒክ ቅጅ ወይም በፒዲኤፍ ተሰርቆ ወጥቷል ተብሏል፡፡

መፀሐፉ በዚህ መልኩ ለአንባቢ መድረሱ የተያዘለትን እቅድ ከግብ ለማድረስ ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ መፅሐፉ ሽያጭ ላይ ግን ያን ያክል ጉዳት አያደርስም ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ዮናስ ዘውዴ ለአሐዱ ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

አቶ ዮናስ ዘውዴ እንዳሉት መፅሐፉ በውስጡ ከያዘው ሃሳብ ባሻገር በሽያጭ ገቢው ሊሰራ የታቀደውን ዓላማ ከዳር ከማድረስ አኳያ፤ ድርጊቱን አውግዘውታል፡፡ ይሁን እንጅ የታቀደውን ዓላማ ከዳር ለማድረስ መፅሐፉ በፒዲኤፍ መውጣቱ የሚገዙትን ሰዎች እንደማያግዳቸው አማካሪው ገልፀዋል፡፡

ይህን መሰል ድርጊት የሚጠበቅ ነው ያሉት አቶ ዮናስ ምንም እንኳን በገቢ መሰብሰብ ላይ ተፅዕኖ ቢኖረውም መፅሐፉ በአጭር ጊዜ ለብዙ አንባቢዎች መድረሱም ትልቅ አውንታዊ ጎን አለው ብለዋል፡፡ አማካሪው አክለውም መፅሐፉ የተያዘለት ዓላማ በሀገሪቱ የገጠር ክፍሎች የሚገኙ ታዳጊዎችን ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመጡ ለማድረግ በመሆኑ ዜጎች መፅሐፉን እንዲገዙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ምንጭ፦ #AhaduTelevision
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀያት ቲቺንግ ሆስፒታል በሕገወጥ ውህደት ተቀጣ!

•የታዋቂው ቢሊዮነር ዲንቁ ደያሳ እናት ያለፈቃድ ድርሻ ገዝተዋል ሲል ችሎቱ በይኗል


የሸማቶች ጥበቃ እና የንግድ ውድድር ባለሥልጣን አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ሀያት ቲቺንግ ሆስፒታል የቀድሞ ባለቤቶች የአክሲዮን ድርሻቸውን ለሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት ድንቁ ደያሳ እና ወላጅ እናታቸው ዳንሳ ጉርሙ ለባለሥልጣኑ ሳያሳውቁ መሸጣቸው ሕገወጥ ውሕደት ነው በሚል ጥፋተኛ አደረጋቸው።

የባለሥልጣኑ አቃቤአን ሕጎች የመጀመሪያ ደረጃ የአስተዳደሩ ችሎት፣ ተከሳሾቹን በነፃ ማሰናበቱ አግባብ አይደለም በሚል ያቀረበውን አቤቱታ የተመለከተው ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ፤ ማንኛውም ነጋዴ ከ 30 ሚሊዮን ብር በላይ ግብይት በሚፈፅምበት ወቅት ለባለሥልጣኑ ማሳወቅ ይገባዋል፣ የስር ፍርድ ቤቱ ሺያጩ በድርጅቶች መካከል የተደረገ ሲሆን ብቻ ለባለሥልጣኑ ማሳወቅ ያስፈልጋል በሚል የሰጠው ውሳኔም አግባብ አይደለም ሲል ሽሮታል።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-04-7

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#INSA በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (INSA) የተዘጋጀው የመጀመሪያው ብሄራዊ የሳይበር ደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የስብሰባ አዳራሽ በይፋ ተጀመረ፡፡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንቱ "ትኩረት ለሳይበር ደህንነት" በሚል መሪ ቃል ነው የሚከበረው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking የኬንያ የ2019 ብሄራዊ የህዝብ ቆጠራ ውጤት ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ተደርጓል። አጠቃላይ የኬንያ የህዝብ ቁጥር 47.6M፤ ወንድ 23.6M እንዲሁም ሴት 24M

Kenya's population is 47.6M;
23.6M male and 24M female


@tsegabwolde @tikvahethiopia
አል በሺር ለICC ተላልፈው ቢሰጡ እንደማይቃወም የሱዳን የነጻንትና የለውጥ ኃይሎች ቡድን አስታወቀ!

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሺር በዳርፉር እልቂት ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይ ሲ ሲ) ተላልፈው ቢሰጡ እንደማይቃወም የሱዳን የተቃዋሚዎች ቡድን አስታወቀ።

የቡድኑ መሪ ኢብራሂም አል ሼይክ ለሪፖርተሮች እንዳሉት “ሁሉም የነጻነት እና የለውጥ ኃይሎችም በጉዳዩ ላይ ተስማምተዋል።” አል በሺር በአሁኑ ጊዜ በካርቱም በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ ሲሆኑ በሱዳን መንግሥትም የሙስና ክስ ቀርቦባቸዋል።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-04-8

(አልጀዚራ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
[URGENT] በቀጠር ዩንቨርስቲዎች ለመማር ለምትሹ፦

በቀጠር የሚገኙ ሁለት ዩንቨርስቲዎች (Qatar University & Hamad bin Khalifa University) እ.ኤ.አ ለ 2020 የትምህርት ዘመን ለሁሉም አገራት ዜጎች ነጻ (Fully Funded) የትምህርት እድሎችን አመቻችተዋል። ስለሆነም የሚከተሉትን ሊንኮች በመጫን ዝርዝር መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።

1. ሃማድ ቢን ኸሊፋ ዩንቨርስቲ (በዲግሪ፣ በማስተርስ እና በፒ.ኤች.ዲ)
https://opportunitiescorners.info/hammad-bin-khalifa-university-scholarship-2020/

2. ቀጠር ዩንቨርስቲ (በማስተርስ እና በፒ.ኤች.ዲ)
https://opportunitiescorners.info/qatar-university-scholarship/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅዱስ ሲኖዶስ በሁሉም ቋንቋ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ማሰልጠኛ ማዕከል እንዲከፈት ወሰነ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሁሉም ቋንቋ "የአፍ መፍቻ ቋንቋ" ማሰልጠኛ ማዕከል እንዲከፈት ወሰነ፡፡ ከጥቅምት 12 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ዛሬ 14 ያህል ነጥቦችን ያካተተ መግለጫ አውጥቷል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ በመክፈቻ ንግግር የቀረበው መልዕክት ለቀጣይ የቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ተልዕኮ ጠቃሚ መሆኑን በማመላከት ማጽደቁንም አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ሠላም ዙሪያም መግለጫ የሰጠው ሲኖዶሱ “በኢትዮጵያ እየታዬ ያለው የሰው ሕይወት መጥፋትና የዜጎች ንብረት መውደም ቅዱስ ሲኖዶሱን ያሳዘነ ሲሆን፣ መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ሠላም እንዲያስከብር፣ የዜጎች ደኅንነት እንዲጠበቅ እንዲያደርግ፣ የተፈናቀሉትም ወደ ቀያቸው እንዲመለሱና ለጠፋው ንብረታቸው ማቋቋሚያ እንዲደረግላቸው፤ በተለይም በክርስቲያኖችና አብያተ ክርስቲያናት ላይ እየደረሰ ያለው ስደትና መከራ ጎልቶ እየታዬ በመሆኑ የጥፋቱ መልዕክተኞችን መንግሥት በሕግ እንዲጠየቁ እንዲያደርግ” ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የተለያዬ ቋንቋ ተናጋሪዎች በብዛት እንደሚገኙ ያመለከተው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ “የቤተ ክርስቲያኒቱን ተከታዮች በቋንቋቸው ማስተማርና ማገልገል እንዲቻል በየአህጉረ ስብከቶቹ የሚገኙ የአብነት ትምህርት ቤቶችን ማጠናከር፣ ከልዩ ልዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች አገልጋዮችን ማፍራት እንዲቻል ለትምህርት ቤቶች ማጠናከሪያ የሚሆን ቋሚ በጀት እንዲመደብ፤ በቀጣይም በሁሉም አፍ መፍቻ ቋንቋ በማዕከል ማሰልጠኛ እንዲቋቋም” ብሏል፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-04-9

@tikvahethiopia @tsegabwolde
በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ የመንግስት ሰራተኞችና የፓሊስ መርማሪ በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ምድብ ጽ/ቤት ከክፍለ ከተማው ፓሊስ መመሪያ እና ከህብረተሰቡ ጋር በተቀጀ ክትትል ሁለት የመንግስት ሰራተኞችንና አንድ የፓሊስ የምርመራ ኃላፊ ጉቦ በመቀበል የሙስና ወንጀል ሲፈፅሙ እጅ ከፍንጅ ተይዙ፡፡ ሁለቱ ተጠርጣሪ ግለሰቦች የቦሌ ክፍለ ከተማ ሰራተኞች ሲሆኑ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ.ም በተደረገ የኦፕሬሽን ስራ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ውስጥ እየተገነቡ የሚገኙ ቤቶችን ከመቆጣጠርና ከመሰል ስራዎች ጋር ኃላፊነት ተሰጥቷቸው በማከናወን ላይ በሚገኙበት ጊዜ አላግባብ የግል ተበዳይ ከሆኑት ግለሰብ ላይ ከፊኒሽንግ ስራ ጋር በተያያዘ ፍቃድ ወይም ስራ ለመስጠት በሚል አስር ሺ ብር በመጠየቅና በመደራደር ስምንት ሺ ብር ጉቦ ሲቀበሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሰሞኑን በሀገሪቱ ከነበረው ግጭት ጋር ተያይዞ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሚገኙ ተገልጿል!

የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር ሰሞኑን በሀገሪቱ በተከሰቱ ግጭቶች ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በየደረጃው ካሉ የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከአባ ገዳዎች፣ ከወጣቶች፣ ከሴቶች እና ችግሩ ከተፈጠረባቸው አካባቢ አመራሮች ጋር በመሆን ግጭቱ የብሔር መልክ እና የሃይማኖት መልክ ይዞ እንዳይስፋፋ ማድረጉን ገልጿል።

ከብሔራዊ የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን እና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተውጣጡ ግብረ ኃይሎች ለተጎጂዎች እርዳታ እያቀረቡ ነው ብሏል። በዚህም 878 ኩንታል የምግብ፣ 712 ካርቶን ብስኩት፣ እንዲሁም ምግብ ነክ ያልሆኑ 10 ሺህ 280 የቤት ቁሳቁሶች ተደራሽ መሆናቸውን ነው የተጠቀሰው።

የሰላም ሚኒስቴር በህዝቦች መካከል መተማመን እንዲኖር መጣር፣ የሀሳብ ልዩነቶችን በጠረጴዛ ዙሪያና በህግ ስር መፍታት አስፍላጊ መሆኑን ተናግሯል። ሚኒስቴሩ ሰሞኑን የተከሰተው ግጭት እንዳይባባስ የድርሻቸውን አዎንታዊ አስተዋፅኦ ያበረከቱትን በማመስገን ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

ViaFBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስር አለቃ መሳፍንት ከሆስፒታል መውጣቱ ተሰማ!

ሰኔ 15 ጀነራል ሰአረ መኮንን ላይ ግድያ እንደፈፀመ የተጠረጠረው ጠባቂ ህክምናውን ጨርሶ ከጦር ሀይሎች ከሆስፒታል እንደወጣ ተሰማ። ጋዜጠኛው ኤልያስ መሰረት አገኘሁት ባለው መረጃው ተጠርጣሪው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ምሽት ከሆስፒታል ወጥቷል። ነገር ግን ወዴት እንደተወሰደ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። እንደ መረጃው ምንጮች ግምት ግን ወደ እስር ቤት ሳይወሰድ እንዳልቀረ ተጠቅሷል። በጉዳዩ ላይ የፌደራል ፖሊስ መረጃው እንደሌለው አሳውቋል። ግለሰቡ በአራት የፌደራል እና አራት መከላከያ አባላት ጥበቃ ተደርጎለት ህክምና እየተከታተለ እንደነበር ከዚህ በፊት ተገልጾ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ንግግር እና እንቅስቃሴ ማድረግ መጀመሩ ይታወቃል።

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሳሜክ ሽኩሪ🛬ዋሽንግተን ገብተዋል!

የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሳሜህ ሽኩሪ ለኅዳሴ ግድቡ የሦስትዮሽ ውይይት ዋሽንግተን ገቡ፡፡ ረቡዕ ጥቅምት 26 ይጀመራል ተብሎ በሚጠበቀው ውይይት ከኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በተጨማሪ የዓለም ባንክ ኃላፊዎችም ይታደማሉ ተብሏል፡፡

ግብፅ በግድቡ ላይ በሚደረግ ድርድር ዓለም ዐቀፍ አሸማጋይ እንዲገባ በይፋ የጠየቀችው በጥቅምት መጀመሪያ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ሦስተኛ ወገን እና አደራዳሪ የሚባልን ጉዳይ እንደማይቀበለው ሲገልፅ ቢቆይም፤ በመጨረሻ በዋሽንግተኑ መድረክ እንደሚሳተፍ ባለፈው ሳምንት ማረጋገጡ ይታወሳል፡፡ የዋሽንግተኑ መድረክም ውይይት ብቻ እንደሚሆን መግለፁ አይዘነጋም፡፡

ምንጭ፦ #AhaduTelevision
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ገዱ🛫ወደ ዋሺንግቶን አቀኑ!

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጥቅምት 26 ቀን 2012 ዓም አሜሪካ በጠራችው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውይይት ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ማምሻውን ወደ ዋሺንግተን ዲሲ ተጉዘዋል። ክቡር አቶ ገዱ ወደ ዋሽንግተን የተጓዙት የአሜሪካ የገንዘብ ተቋም ኃላፊ ስቴቨን መንቺን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ውይይት እንዲያደርጉ ባደረጉት ግብዣ መሰረት ነው። በዋሽንግተን ዲሲ በሚካሄደው ውይይት ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ያላትን አቋም እንደምታስረዳ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia