የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ!
ከሰኔ 3-5/2011 ዓ.ም የተሰጠው የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ መስከረም 02/2012 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ይፋ ይደረጋል፡፡ ተፈታኝ ተማሪዎች ውጤታቸውን በኤጀንሲው ድረ-ገጽ app.neaea.gov.et በመግባት Admission በሚለው ሳጥን ውስጥ የመፈተኛ ቁጥራቸውን (Registration Number) በማስገባትና display የሚለውን አንዴ click በማድረግ እንዲሁም በSMS 8181 ላይ ID የሚል እንግሊዝኛ ፊደላትን በመጻፍ፣ አንድ ጊዜ ስፔስ በመስጠትና የመፈተኛ ቁጥራቸውን /Registration number/ በዚህ መልክ (ID 123XXX) ጽፎ በመላክ ውጤታቸውን መመልከት የሚችሉ መሆኑን ኤጀንሲው ያስገነዝባል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ለመላው ለ2011 የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች #መልካም_እድል እንዲገጥማችሁ TIKVAH-ETHIOPIA መልካም ምኞቱን ይገልጻል!
TIKVAH-MAGAZINE በመቀላቀል ስለውጤታችሁ አዳዲስ መረጃዎችን መከታተል ትችላላችሁ👇
https://yangx.top/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በጅዳ አውሮፕላን ማረፊያ ችግር ገጠመው!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 767 በሳኡዲ ዐረቢያ ጅዳ ንጉስ አብዱላዚዝ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለመነሳት በማኮብኮብ ላይ ሳለ ከዐስሩ ጎማዎቹ ውስጥ ስምንቱ በመፈንዳታቸው ሳይነሳ ቀርቷል። የገጠመውን ችግር ተከትሎም የማኮብኮቢያ ሜዳው ዝግ እንዲሆን ተደርጎ ነበር።
ትናንት መስከረም 1/2012 በጅዳ ችግር የገጠመው ኢትዮጵያ አውሮፕላን ከማኮብኮቢያው ሜዳ ጥገና ወደ ሚያገኝበት ስፍራ እስኪወሰድ ድረስ ማኮብኮቢያው ሜዳ ለስምንት ሰዓታት ተዘግቶ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። አውሮፕላኑ በሰዓቱ ከጅዳ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ነበር።
Via #አዲስማለዳ

አቶ መለስ የአስቴርን ሙዚቃ አብዝተው የሚወዱት ለምን ነበር? የተለየ ምክንያት ነበራቸው?
ወ/ሮ አዜብ መስፍን፦
መለስ ሙዚቃ ማዳመጥ ይወዳል። አዳማጭ ብቻ አይመስለኝም። የሙዚቃ መሣሪያዎቹ እንዴት እንደገቡና የሚሰጡትን ድምፅ ለይቶ ማውጣት ይችል ነበር። ግጥሞቹን፣ ትርጉማቸውን፣ ቅኔያቸውን ያውቃቸዋል። በጣም ትልቅ ዋጋ ይሰጣቸዋል።
ከትግርኛ ዘፈኖች የታጋይ እያሱ በርሄን ሙዚቃዎች በጣም ያደንቅ ነበር። የእርሱ ትግርኛ ብዙዎቻችን ሳይገባን መለስ ይገባዋል- ቅኔው ውስጥ ላይ ያለው። ይዘቱን የመተንተን፣ ሙዚቃዎችን የማወቅ፣ የመረዳት ችሎታ ነበረው መለስ። እንግሊዝኛም ሲሰማ እንደዛው ነው።
አቶ መለስ ያንጎራጉሩ ነበር?
አዎ በጣም! ጠዋት ጠዋት ሲነሳ . . . አሊያም ማታ ሲገባ ያንጎራጉር ነበር። ያው ድምፅ የለውም ግን ግጥሞቹ ይወጣሉ።
-------------------------------------------------------------------
ቢቢሲ የአማርኛው ክፍል የቀድሞውን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍንን አነጋግሮ ነበር፤ቢቢሲ ከወ/ሮ አዜብ ጋር ያደረገውን ቃለምልልስ ይህን ተጭነው የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-13-3

#GONDAR
የጎንደር ዩንቨርሲቲ የመጥፋት አደጋ የተጋረጠበትን የግእዝ ቋንቋ ለመታደግ በአዲሱ የትምህርት ዘመን በመጀመሪያ ዲግሪ የቋንቋ ትምህርት ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡ የዩንቨርሲቲው የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዘዳንት ዶክተር ካሳሁን ተገኘ ለኢዜአ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የግእዝ ቋንቋ ባለቤት ብትሆንም ለቋንቋው ማደግና መስፋፋት የተሰጠው ትኩረት አነስተኛ ነው፡፡ “በዚህም ሳቢያ ቋንቋው የመጥፋት አደጋ የተጋረጠበት ከመሆኑም በላይ በግዕዝ ቋንቋ የተጻፉ በርካታ የብራና መጻፍትን ለጥናትና ምርምር ስራ ለማዋል አልተቻለም “ብለዋል፡፡
Via #ENA

የ10ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ተፋደርጓል! መልካም ዕድል!
TIKVAH-MAGAZINE በመቀላቀል ውጤታችሁ እንዲታይላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ👇
https://yangx.top/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-MAGAZINE በመቀላቀል ውጤታችሁ እንዲታይላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ👇
https://yangx.top/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አርዓያ ገብረእግዚአብሄር፦
•ከተፈታኞቹ መካከልም ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎች አራት ነጥብ አምጥተዋል።
•75 ነጥብ 5 በመቶ ያህል ተፈታኞች ሁለት እና ከዚያ በላይ ነጥብ ያመጡ ናቸው።
•ሁለት ነጥብ እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡት ተማሪዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ብልጫ አለው።
•ከተፈታኞቹ መካከል ወንዶች 682 ሺህ 572 ሲሆኑ 572 ሺህ 997 ሴቶች ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል 894 ሺህ 318 በመደበኛ፣ 354 ሺህ 782 በግል እና 6 ሺህ 469 ደግሞ በማታው ክፈለ ጊዜ ተፈታኞች ነበሩ።
በዘንድሮው የ10ኛ ክፍል ፈተና ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ለፈተና መቀመጣቸውን የኤጀንሲ መረጃ ያመላክታል። ባለፈው አመት ሁለት እና ከዚያ በላይ ነጥብ ያስመዘገቡት ተፈታኞች 71 በመቶ መሆናቸው የሚታወስ ነው። ተማሪዎች ውጤታቸውን በኤጀንሲው ድረ ገጽ http://
app.neaea.gov.et ወይም www.neaea.gov.et እንዲሁም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት 8181 ላይ ID- ብለው የአድሚሽን ቁጥራቸውን በማስገባት መመልከት ይችላሉ።
Via #FBC

የመስከረም 4ቱ ሰልፍ ተራዝሟል!
በኢትዮጵያ ኦርቶዳክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት እየደረሰ ነው በሚል መስከረም 4 ቀን ሊካሄድ ታስቦ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ መራዘሙ ተገልጿል። የሰልፉ አስተባባሪዎች ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው። ሰልፉም ወደ ጥቅምት 30 ቀን 2012 ዓ.ም መዘዋወሩን አዘጋጅ ኮሚቴው አስታውቋል።
ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
ፎቶ: ፋይል

#ADDISABEBA
በአዲስ አበባ በተለምዶ አፍንጮ በር በሚባለው አካባቢ ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ግንብ ተደርምሶ በመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት አደረሰ። አደጋዉ ሁለት መኖሪያ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ዉጭ ያደረገ ሲሆን ሌሎች 6 የሚሆኑትን ደግሞ በከፊል እንደጎዳ ነዋሪዎች ለኢዜአ ተናግረዋል። በወረዳው 88 ቤቶች ለአደጋ ተጋላጭ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
በአደጋው ቤታቸውና ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙን ወይዘሮ አዜብ ሞገስ የተባሉ ነዋሪ ገልፀዋል። አደጋ ከመድረሱ በፊት በአካባቢው የአደጋ ስጋት መኖሩን ከወረዳ እስከ ክፍለ ከተማ በተደጋጋሚ አቤቱታ በማቅረብ ከቦታው ተነስተው ተለዋጭ ቤት እንዲሰጣቸው ጠይቀው እንደነበርም ተናግረዋል። አክለውም መንግስት የደረሰባቸውን ችግር በመረዳት ቤተሰባቸውን የሚያኖሩበት ቤት እንዲሰጣቸዉና ለእለት ፍጆታ የሚሆን የምግብ እርዳታ እንደያደርግላቸውም ጠይቀዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-13-4

ለ10ኛ ክፍል ተማሪዎች፦
የ2011 ዓ/ም የ10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት የወጣ ሲሆን ተማሪዎች ወይም ወላጆች ውጤታቸውን ቀጥሎ በተመለከተው የድህረ ገፅ አድራሻ መሠረተ ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
www.app.neaea.gov.et ቀጥሎ student result የሚለውን ይጫኑ ቀጥሎ Click here for Grade 10 result የሚለውን ይጫኑ!
1ኛ. የተማሪዉ/ዋ/ን መለያ ኮድ ወይም አድሚሽን ቁጥር ማስገባት
ማሳሰቢያ፦
የተማሪዉ/ዋ/ን ውጤት ለማወቅ የሚያስፈልጉ መረጃዎች፦
A ማለት 4 ነጥብ ነው
B ማለት 3 ነጥብ ነው
C ማለት 2 ነጥብ ነው
D ማለት 1 ነጥብ ነው
F ማለት 0 ነጥብ ነው
2ኛ. ከተዘረዘሩት የትምህርት አይነቶች ውስጥ የግድ መያዝ ያለባቸውን፦ #የmaths , #english & #civics ውጤቶችን በመመዝገብ እና ተጨማሪ 4 የተሻሉ የትምህርት አይነት ውጤቶችን መመዝገብ በአጠቃላይ 7 የትምህርት አይነት ይሆናሉ ማለት ነው።
3ኛ. ከላይ በተዘረዘረው የነጥብ አሰጣጥ መሰረት የ7ቱን የትምህርት አይነቶች አጠቃላይ ድምር ማግኘት አና ለ7 ማካፈል ነው።
#TIKVAH_ETHIOPIA

TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ከቡራዩ ጥቃት ጋር ተያይዞ 22 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። ከቡራዩ ጥቃት ጋር ተያይዞ የኦነግ- ሸኔ አባላትና ሌሎች ከእነሱ ጋር ትስስር ያላቸው 22 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን EBC የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃን ጠቅሶ ዘግቧል። @tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ዳውድ ኢብሳ...
"እነማን እንደተያዙ አናውቅም። መረጃውን እንደሁሉም ሰው ከሚድያ ነው የሰማሁት። እርግጥ ነው በየግዜው ተያዙ እየተባለ ይወራል፣ እኛም ለመለየት አስቸጋሪ ሆኖብናል። ስለዚህ ስለተባለው ነገር አላውቅም።"
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/AP/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እነማን እንደተያዙ አናውቅም። መረጃውን እንደሁሉም ሰው ከሚድያ ነው የሰማሁት። እርግጥ ነው በየግዜው ተያዙ እየተባለ ይወራል፣ እኛም ለመለየት አስቸጋሪ ሆኖብናል። ስለዚህ ስለተባለው ነገር አላውቅም።"
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/AP/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከህንድ የተላከ...
"ትላንት እና ከትላንት በስትያ ከሀገር ውጪ በህንድ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን በማርዋዲ ዩኒቨርስቲ ተሰባስበን እንዲ በደማቅ ሁኔታ በአሉን ከህንዳውያን፣ ኢንዶኔዥያ፣ ኔፓል፣ ባንግላዴሽ፣ ስሪያ፣ አፍጋኒስታን እና ሌሎች አፍሪካን ሀገራት ጋር በሕብረት አክብረናል። መልካም አዲስ አመት!" #BINI

#update በኢንፎርሜሽ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ከዚህ ቀደም ሹመት የነበረው የመካከለኛ ደረጃ ኃላፊነት ምደባ በውድድር እንዲሆን ማድረጉን ኤጀንሲው አስታውቋል። ሰራተኞች በፈለጉበት ቦታ መስራት የሚችሉበትንም አሰራር መፍጠሩን ያለፈውን ዓመት ኤጀንሲው ያከናወናቸውን ተግባራት በገመገመበት ወቅት ገልጿል።
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መስከረም 2 ቀን 1967⬆️
"ደርግ ንጉሱን ለማውረድ ከሰኔ 21፣ 1966 እስከ መስከረም 1፣ 1967 ድረስ 56 ቀናት ያህል ወስዶበታል።" ሌ/ኮሎኔል ፍስሐ ደስታ/አብዮቱና ትዝታዬ/
በወቅቱ የነበራችሁ የቤተስባችን አባላት ምን ትዝ ይላችኃል?? ሁኔታውን እንዴት ታስታውሱታላችሁ?? @tsegabwolde

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከዛሬ መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ/ም ጀምሮ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ከስልጣናቸው ወርደዋል። #ETHIOPIA
አዋጅ ቁጥር 1/1967
1ኛ. ይህ አዋጅ የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1/1967 ዓ/ም ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።
.
.
ይህ አዋጅ እስከፀናበት ድረስ "ኢትዮጵያ ትቅደም" የሚለውን አላማ የመቃወም አድማ የሚያደርግ፤ ስራ የሚያቆም፤ ያለ ፍቃድ ሰላማዊ ሰልፍ እና ስብሰባ የማድረግ በጠቅላላው የህዝቡን ፀጥታና ሰላም የሚነሳ ተግባር መፈፀም ክልክል ነው።
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዋጅ ቁጥር 1/1967
1ኛ. ይህ አዋጅ የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1/1967 ዓ/ም ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።
.
.
ይህ አዋጅ እስከፀናበት ድረስ "ኢትዮጵያ ትቅደም" የሚለውን አላማ የመቃወም አድማ የሚያደርግ፤ ስራ የሚያቆም፤ ያለ ፍቃድ ሰላማዊ ሰልፍ እና ስብሰባ የማድረግ በጠቅላላው የህዝቡን ፀጥታና ሰላም የሚነሳ ተግባር መፈፀም ክልክል ነው።
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#US_EMBASSY
አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በጋምቤላ ክልል ሁለት የግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች የገደሉ ታጣቂዎችን መንግሥት በአፋጣኝ በቁጥጥር ሥር አውሎ ለሕግ እንዲያቀርብ ጠየቀ። አክሽን አጌይንስት ኸንገር የተባለው ዓለም አቀፍ የግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ጥቃት የተፈጸመባቸው በጋምቤላ ክልል ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች ከሚኖሩበት ኙንዬል ከተባለ የመጠለያ ጣቢያ (Nguenyyiel Refugee Camp) ሥራቸውን አጠናቀው በመጓዝ ላይ ሳሉ እንደነበር ድርጅቱ አስታውቋል። በጥቃቱ የመስክ ሰራተኛ እና አሽከርካሪ ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአሜሪካ ኤምባሲ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የግብረ-ሰናይ ሰራተኞች መሆኑን የሚጠቁም ምልክት በነበረው ተሽከርካሪ ላይ ባለፈው ሳምንት የተፈጸመውን ጥቃት አውግዟል።
Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በጋምቤላ ክልል ሁለት የግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች የገደሉ ታጣቂዎችን መንግሥት በአፋጣኝ በቁጥጥር ሥር አውሎ ለሕግ እንዲያቀርብ ጠየቀ። አክሽን አጌይንስት ኸንገር የተባለው ዓለም አቀፍ የግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ጥቃት የተፈጸመባቸው በጋምቤላ ክልል ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች ከሚኖሩበት ኙንዬል ከተባለ የመጠለያ ጣቢያ (Nguenyyiel Refugee Camp) ሥራቸውን አጠናቀው በመጓዝ ላይ ሳሉ እንደነበር ድርጅቱ አስታውቋል። በጥቃቱ የመስክ ሰራተኛ እና አሽከርካሪ ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአሜሪካ ኤምባሲ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የግብረ-ሰናይ ሰራተኞች መሆኑን የሚጠቁም ምልክት በነበረው ተሽከርካሪ ላይ ባለፈው ሳምንት የተፈጸመውን ጥቃት አውግዟል።
Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
mwfellows.info/apply
በመጪው የአውሮፓ ዓመት ለሚካሄደው የ2020 የማንዴላ የወጣት አፍሪካዊያን መሪዎች ዋሽንግተን ፌሎውሽፕ መርሐ ግብር ምዝገባ ተጀመረ።
‘የማንዴላ ዋሽንግተን ፌሎውሽፕ’ የተባለው መርሃ ግብር ወጣት አፍሪካዊያንን በመመልመል በአሜሪካን አገር በሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለ6 ሳምንት የሚዘልቅ የአመራርነት ስልጠና የሚሰጥበት ነጻ የትምህርት እድል ነው።
በኢትዮጵያ የአሜሪካን ኤምባሲ ዛሬ በሰጠው ማብራሪያ በአውሮፓዊያን ቀመር በመጪው ዓመት ለሚሰጠው መርሐ ግብር ምዝገባው ትናንት ተጀምሯል። ምዝገባም እንደ አውሮፓ አቆጣጠር አስከ ጥቅምት 9 ቀን 2019 ይቆያል ተብሏል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-13-5

#FAKE የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቅያ ወይም የመሰናዶ መግቢያ #መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ ሚሰራጨው። በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው ተማሪዎች ውጤት ብቻ ነው። የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አልተደረገም። በሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጀዎች እንዳትታለሉ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ከዕገታው ጀርባ የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ እንደሚኖር ጥርጣሬያቸውን ገልፀዋል!"
ሐሰን ጃበር የተባሉ ሊባኖሳዊ የንግድ ሰው በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀናት ትራንዚት በሚያደርጉበት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ታግተው እንደተወሰዱ እና የደረሱበት እንዳልታወቀ ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል።
በዕለቱ ከአፍሪካዊቷ አገር ጋቦን በመነሳት በአዲስ አበባ አድርገው ወደ ሊባኖስ ቤሩት በማምራት ላይ የነበሩት ሐሰን አዲስ አበባ ደርሰው ቀጣዩ ጉዟቸውን ለማድረግ በሚሰናዱበት ወቅት ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ዕገታ እንደተፈፀመባቸው እና ሊሰወሩ እንደቻሉ የተገለፀው። የግለሰቡ ቤተሰቦች ከሊባኖስ ጋዜጣ አል አክበር ጋር ባደረጉት ቆይታ ከዕገታው ጀርባ የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ እንደሚኖር ጥርጣሬያቸውን ገልፀዋል።
እንደ ጋዜጣው ዘገባ ግለሰቡ ከዓመታት በፊት በፈረንጆች 2017 ከሒዝቦላህ ጋር ግንኙነት አለው በሚል በጋቦን የፀጥታ አካላት ምርመራ የተደረገባቸው መሆኑን አውስቷል። ይሁን እንጂ ሐሰን ከሒዝቦላህ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል።
በአሁኑ ሰዓት ሊባኖሳዊው ግለሰብ የት እና በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የሚታወቅ ነገር የለም። ስለጉዳዩ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ምንም የሚያውቀው ነገር አለመኖሩን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
የሊባኖስ የወጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በኩል የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት በጉዳዩ ላይ ግልፅ ምላሽ እስከ መጪው ሰኞ መስከረም 5/2012 ድረስ እንዲሰጥበት አሳስበዋል። ካልሆነ ግን ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ የሊባኖስ መንግስት አስጠንቅቋል።
Via #AddisMaleda

በደንብ ተመልከቱ⬆️
እኛ እንዲህ ነን፤ ተያይዞ፣ ተቻችሎ፣ ተዋዶ መኖር ካልቻልን ተያይዞ መጥፋት ነው የሚሆነው፤ አንዱን ጠጠር ብታነሱት ሁሉም ይፈርሳል፤ ለሁሉም መኖር የአንዱ መኖር ወሳኝ ነው።
#እንዋደድ #እንከባበር #እንፋቀር #ሰላም #ፍቅር #ተስፋ
ሀሳቡ ከማህበራዊ ሚዲያ ተወሰደ!
🚪መስከረም 2 ቀን 2012 ዓ/ም