አማራ ባንክ!
በምስረታ ሂደት ላይ ያለው የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የአክሲዮን ሽያጭ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።
ባንኩ በዛሬው ዕለት በሸራተን ሆቴል ባካሄደው ስብሰባ እስካሁን በተከናወኑ ተግባራት፣ ውሳኔ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮችና እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ተወያይቷል።
በውይይቱ ወቅትም የባንኩ አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መላኩ ፈንታ የባንኩ መመስረት በሀገር እና በክልል ያለውን የልማት ፍላጎት ለማስፋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን ተናግረዋል።
ከዚህ ባለፈም የሚመሰረተው ባንክ ኢንቨስትመንት እና የውጭ ምንዛሪ ተቀማጭ እንዲኖርና ዳያስፖራውንም ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አንስተዋል።
በስነ ስርዓቱ ላይ የአደረጃጀት ኮሚቴው የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የሥነ ምግባር ደንብ ይፋ አድርጓል። በዚህ መሰረትም የአንድ አክሲዮን መሸጫ ዋጋ አንድ ሺህ ብር መሆኑ ተገልጿል።
አንድ ሰው መግዛት የሚችለው ዝቅተኛ የዕጣ ብዛት 10 ሲሆን፥ ከፍተኛው ደግሞ 100 ሺህ እንደሆነም ተነግሯል።
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የትብብር ስልጠናው እንዲቋረጥ ተደረገ!
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ABH Partner service PLC. በሚል እየተሰጠ የነበረው የትብብር ስልጠና ከመመሪያ ውጪ በመሆኑ እንዲቋረጥ መደረጉን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።
በበብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ሬዲዮ እየተላለፈ የነበረው ማስታወቂያም ትክክል ባለመሆኑ እንዲቋረጥ መደረጉንም ሚኒስቴሩ አክሎ ገልጿል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሰኔ 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ደብዳቤ መሰረት ማንኛውም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የትብብር ስልጠና መስጠት እንደማይችል እና የጀመሩትም እንዲያቋርጡ የመጨረሻ ማሳሰቢያ ማስተላለፉን አስታውቋል።
Via #EPA

በ4 ቢሊዮን ብር በደብረ ማርቆስ ፣ ሚዛን አማን፤ ጎሬ መቱ፣ በነገሌና ያቤሎ 71 ሰው የሚጭኑ አውሮፕላኖች ማረፊያ ለመገንባት መታቀዱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አስታወቀ፤ ግንባታዎቹን በ2 ዓመት ተኩል ለማጠናቀቅ ታቅዷል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-17-3
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-17-3
በሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ትምህርት ቤት "ወ/ሮ አየለች ዳገፉ መታሰቢያ" ከተመዘገቡት ከፍተኛ ውጤቶች መካከል የነዚህ እንስቶች ውጤት ይጠቀሳል፦
#BERSABEH 600
#ETSUBDINK 612
#BETLHEM 611
#BERUKTAWIT 605
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BERSABEH 600
#ETSUBDINK 612
#BETLHEM 611
#BERUKTAWIT 605
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአንድ ዓመት ነጻ የኩላሊት ዕጥበት አገልግሎት!
የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት 20 ለሚደርሱ ህሙማን የአንድ ዓመት ነጻ ዕጥበት አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ነው ለህሙማኑ አገልገሎቱን መስጠት የጀመረው፡፡
የኢትዮጵያ መድህን ድርጅትም ለህሙማኑ ለአንድ ዓመት ሙሉ የዕጥበት ክፍያ የሚውል የ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሰጥቷል፡፡ የድርጅቱ የቢዝነስ ልማትና ሪስክ ማኔጅመንት ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ መንግስቱ መሃሩ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለማገዝ ሰፊ ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው በማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ የሚያደርገውን ተሳትፎም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በሰጠው የገንዘብ ድጋፍ በዳግማዊ ሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የሚገኙ 20 የኩላሊት ዕጥበት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ለአንድ ዓመት በነፃ እንዲጠቀሙ ተደርጓል ብለዋል፡፡
የአገልግሎቱ ጠቃሚ ህሙማንም በተደረገላቸው ድጋፍ ደስተኞች መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡ ሌሎች የመንግስትና የግል ድርጅቶችም እየጨመረ የመጣውን የኩላሊት ህመም ጉዳት ለመቀነስ እንዲረባረቡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Via ኤ ኤም ኤን

#ጀግኒት
ተማሪ ZEHARA #ከBAHIRDAR 615፣ HILANI ከአዳማ #ODA_SPECIAL_BOARDING 606፣ NEBUS #ከBISHOFTU 607 በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ/የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ያስመዘገቡ እንስቶች ናቸው! #ኢትዮጵያዊት
#BAHIDAR
#BISHOFTU
#ODA_SPECIAL_BOARDING

138 ሞተሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ!
በደቡብ ክልል ሆሳእና ከተማ 138 ሞተር ብስክሌቶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኮማንድ ፖስቱ ዛሬ ገለጸ፡፡ የከተማው ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊና የኮማንድ ፖስት አባል አቶ ዳዊት ኪበሞ ለኢዜአ እንደገለጹት ሞተር ቢስክሌቶቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ለኅብረተሰቡ ደህንነት ስጋት በመሆናቸው ነው፡፡ ሠሌዳ ቁጥር ሳይኖራቸው ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው አገልግሎት እንዳይሰጡ መታገዳቸውን አስረድተዋል። ኮማንድ ፖስቱ የአካባቢዉን ኅብረተሰብ ደህንነት ለስጋት የሚጥሉ ጉዳዮችን በመለየት እርምጃ መውሰዱን እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
Via #ENA

#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ የሱዳን ተቃዋሚዎች ስብስብ ከሆነው የነፃነትና የለውጥ ሀይል አባላት ጋር ተወያዩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የነፃነትና የለውጥ ሀይል አባላት በሱዳን የይቅርታ እና የአንድነት ባህልን እንዲያዳብሩ አበረታተዋል፡፡
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ካርቱም
የሱዳን ሲቪል አስተዳደር የሚሰረትበት ስምምነት የፊርማ ሥነ-ሥርዓት እየተካሔደ ይገኛል። ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማኅማት በሰነዱ ላይ ፈርመዋል።
Via #EsheteBekele

በአክሱም ዩኒቨርስቲ የሽሬ ካምፓስ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን በእርዳታ አገኘ። ካምፓሱ ድጋፉን ያገኘው #ከካናዳ መንግስት የማአድን ዘርፍ ትምህርትና ስጠልና ማጠናከርያ ፕሮጀክት መሆኑን የካምፓሱ ዲን አቶ መአርግ በላይ ገልጸዋል። #ENA
@tsegabwolde @tivahethiopia
@tsegabwolde @tivahethiopia
#ካርቱም
የሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች እና የተቃዋሚ መሪዎች ስልጣን #ለመጋራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በይፋ ተፈራራሙ። ስምምነቱ በሲቪል የሚመራ የሽግግር መንግስት ለመመስረት መንገድ ይጠርጋል ተብሎለታል። በስምምነት ስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የደቡብ ሱዳን አቻቸው ሳልቫ ኪር ተገኝተዋል።
Via #DW

ከመመሪያ ውጪ የትብብር ስልጠና ሲሰጡ የተገኙ የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስልጠናውን እንዲያቋርጡ ተወሰነ!
የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የተላለፈውን ውሳኔ በመተላለፍ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመሆን የሚሰጡትን የትብብርት ስልጠናዎች እንዲቋረጡ ማድረጉን ገለጸ።
የትብብር ስልጠናውን ሲሰጡ የነበሩ ተቀዋማትም ዮም ኢንስቲትዩት ኦፍ ኢኮኖሚ ደቨሎፐመንት ከደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጋር፣ አዲስ ኮንቲነንታል የጤና አጠባበቅ ኢንስቲትዩት ከሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር እና ናሸናል ኮሌጅ ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር ናቸው፡፡
ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በዚሁ መንገድ ተቀብለው ያስመረቋቸውን እና በመማር ላይ ያሉትን የተማሪዎች የተሟላ ዝርዝር መረጃ በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ ለኤጀንሲው እንዲያቀርቡ በማሳሰብ ለዮም ኢንስቲትዩት ኦፍ ኢኮኖሚ ደቨሎፐመንት፣ ለአዲስ ኮንቲነንታል የጤና አጠባበቅ ኢንስቲትዩት እና ለናሸናል ኮሌጅ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

#ታግደዋል
አራት የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከግል ኮሌጆች ጋር በትብብር የማስተርስ ድግሪ መርሃ ግብር እንዳይሰጡ ማገዱን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡ እግዳው የተጣለባቸው፦
√የጅማ ዩኒቨርሲቲ ABH ከሰተኘ ተቋም ጋር፣
√ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከዮም ኮሌጅ ጋር፣
√ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ከናሽናል ኮሌጅና
√ሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ ኮንቲነንታል የጤና ኢንስቲትዩት

ማስታወቂያ09-12-20111.pdf
176.3 KB
#ለደብረ_ማርቆስ_ዩኒቨርሲቲ_ተማሪዎች
በ2011 የትምህርት ዘመን በቴክኖሎጅ ኢንስትቲዩት የማጠቃለያ ፈተና በራሳቸው ፈቃድ ላልወሰዱ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዓመት መደበኛ የቅድመ – ምረቃ ተማሪዎች!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በ2011 የትምህርት ዘመን በቴክኖሎጅ ኢንስትቲዩት የማጠቃለያ ፈተና በራሳቸው ፈቃድ ላልወሰዱ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዓመት መደበኛ የቅድመ – ምረቃ ተማሪዎች!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ...
"....እንደ ተማሪ #ተቀብሎ እናንተን በሙሉ ኃላፊነት የሚጠብቃችሁ፣ መብታችሁንም የሚያስጠብቅላችሁ በ2012 የትምህርት ዘመን ሁለተኛ ሴሚስተር የማጠቃለያ ፈተና ወቅት ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ከዚያ ውጭ ወደ ዩኒቨርሲቲው በመምጣት ከሚደርስባችሁ እንግልት እና አላስፈላጊ ወጭ ራሳችሁን እና ቤተሰባችሁን እድትጠብቁ እንዲሁም ተጨማሪ ተያያዥ ችግሮችን ለመከላከል የበኩላችሁን እንድታደርጉ መረጃዎችን ከዩኒቨርሲቲው ብቻ እንድትቀበሉ በጥብቅ ያስታውቃል።"

የሱዳን ፖለቲከኞች ሥልጣን ለመጋራት በመስማማታቸው ደስታቸውን ለመግለፅ ወደ ኻርቱም ያቀኑ የአትባራ ሰዎች በተጓዙበት ባቡር አናት ቆመው ሰንደቅ ዓላማ ያውለበልቡ ነበር።
Via #Eshete
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #Eshete
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ከዚህ በኃላ ፍትህን ከመንግስት ሳይሆን ከእግዜያብሄር ነው የምጠብቀው"
በሲዳማ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረዉን ሁከት #ቀስቅሰዋል በሚል ተጠርጥረው የተያዙ ዘጠኝ ግለሰቦች በዋስ እንዲፈቱ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የወሰነላቸው ቢሆንም እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ከእስር እንዳልተፈቱ ቤተሰቦቻቸው ለTIKVAH-ETH ተናገሩ። ፍርድ ቤቱ ትላንት በዋለው ችሎት በዋስ እንዲፈቱ ከወሰነላቸዉ ተጠርጣሪዎች መካካል የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስኪያጅ ጌታሁን ደጉዬ ፣ ምክትላቸው አቶ ታሪኩ ለማ እና የጣቢያው የቦርድ አባል የሆኑት በላይ ባልጉዳ ይገኙበታል።
በጉዳዩ ላይ ለTIKVAH-ETH የተናገሩት ከታሳሪዎቹ ቤተሰቦች አንደኛው ይህን ብለዋል፦
"የዋስትና ደብዳቤውን በጊዜ ነው ጨርሰን የሄድነው፤ ፖሊስ ግን ሊፈታቸው ፍቃደኛ አልነበረም። ፖሊስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደብዳቤ አስገብቻለሁ አለን፤ ነገር ግን ሄደን ስናይ ያስገባውና የተፈቀደለት እግድ የለም ነገር ግን ልጆቹን አልሠጣችሁም አለን። የፖለቲካ እስረኞች ናቸው ህጉ የሚፈታው አይደለም። ...እዚህ አገር ላይ ከፍርድ ቤትና ከህግ የሚበልጠው እላይ ያለው ደውሎ ልቀቅ የሚል ሰው ነው ይህ እኛ እንደተረዳነው የፖለቲካ ጉዳይ ነው። በሚዲያ ቀርቦ የምናገኘው ፍትህ የለም። ለውጥ የሚባል ነገር የሌለበት ሀገር ላይ ነው ያለነው። ፍትህን ከእግዚያብሄር ጠብቀን እንኖራለን። አሁንም ቢሆን የሲዳማ ህዝብ ልጆቹ ይለቀቃሉ ብሎ ጠብቆ ነበር። በቦታው የነበረው ሰው ሀላሌ ይፍታልን ብሎ ነው የሄደው። የሲዳማ ህዝብ ሲዳማ ብቻ ስለሆኑ የታሰሩ ልጆች ላይ የሚደረገውን ጭቆና አይቶ አሁንም ቢሆን መንግስት ፍትህን ይሰጣል ብሎ አይጠብቅም፤ አይጠይቅም። ከእግዚያብሄር ነው ፍትህን የሚጠብቀው ይህ ህዝብ"
#ቲክቫህ