TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
አቶ ሽመልስና አቶ አዲሱ🛫ደንቢዶሎ🔝

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሰት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ እና የኦሮሞ ዴክራቲክ ፓርቲ ማዕከላዊ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ #አዲሱ_አረጋ ከደንቢዶሎ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ለመወያየት ዛሬ ወደ #ደንቢዶሎ አቅንተዋል፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) በቅርቡ በሱማሊኛ ቋንቋ ስርጭት የሚጀምር መሆኑ ተገለፀ፡፡ ይህ የተገለፀው በኣዳማ እየተካሄደ ባለው የኦሮሚያና የሱማሌ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ መድረክ ላይ ነው፡፡ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በመድረኩ ላይ እንደገለፁት የሁለቱን ክልሎች ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) በቅርቡ በሱማሊኛ ቋንቋ ስርጭት ይጀምራል ብለዋል፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለላፉት ሁለት አመታት ባጋጠማት ህመም በዱባይ ራሺዲያ ሆስፒታል በህክምና ላይ የቆየችው ሰርካለም ታመነ በዱባይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጽ/ቤትና በዱባይ የኢትዮጵያዊያን ኮሚኒቲ ማህበር ድጋፍና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ባደረገው ክትትልና ድጋፍ ትናንት ግንቦት 7 ቀን 2011 ዓ.ም ወደ አገሯ ተመልሳለች፡፡ በራሺድ ሆስፒታል በህክምና ላይ የነበረችው ሶፊያት መሀመድ ሚያዚያ 22 ቀን 2011 ዓ.ም ወደ አገሯ መመለሷ የሚታወስ ነው፡፡ ሶፊያ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ድጋፍ በአቤት ሆስፒታል ህክምናዋን እየተከታተለች ትገኛለች፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia