TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
አክሱም ዩኒቨርሲቲ👆

√ባዶ ህንፃ ሆስፒታል ኣይኸውንን!!

√We are the poorest physician in the world with no Health insurance!

√Save the health system and hospitals ,we will save lives.

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ጋር በዛሬው እለት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በውይይቱ የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ደረጀ እና ምክትል ቢሮ ሃላፊው ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ ተገኝተዋል፡፡ የቢሮው ሃላፊ ዶክተር ደረጃ ዱጉማ የክልሉ መንግስት በጤና ባለሙያዎች እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎችን ከፌደራል መንግስት ጋር በመሆን መፍትሄ ለመስጠት እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡ ሃላፊው በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የጤና ባለሙያዎች ጥያቄወቻችን አልተመለሱም በማለት ስራ ለማቆም የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ተገቢነት የለውም ብለዋል፡፡ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ ዶክተር አብዱልቃድር በበኩላቸው፥ መንግስት ባለፉት ዓመታት የጤና ተደራሽነት እና ጥራትን በክልሉ ለማስጠበቅ በርካታ ስራዎች ሲያከናውን መቆየቱንም ተናግረዋል፡፡ ከህዝብ ቁጥር መጨመርና በሌሎች ምክንያቶች ጋር ተያይዞም በጤና ባለሙያዎች እና በህብረተሰቡ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲነሱ እንደቆዩም አስታውሰዋል። የጤና ባለሙዎች በበኩላቸው በሚያነሷቸው ጥያቄዎች ላይ የሌሎች አካላት እጅ አለ የሚለው አስተያየት ቀርቶ መንግስት ተገቢውን መፍትሄ ሊሰጥ እንደሚገባ አንስተዋል። ባለሙያዎች ከዚህ ውጭ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ለfbc ገልጸዋል፡፡ ይህ ውይይት በነገው ዕለት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት የሚቀጥል ይሆናል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ👆የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሀኪሞች #ሰልፍ እያደረጉ ይገኛሉ። #JimmaUniversity

@tseganwolde @tikvahethiopia
ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ...

"ሰልፍ ስላልፈቀዱልን ግቢ ውስጥ ብቻ ለማድረግ አስበን ነበር ልክ እንደ ጀመርን በ10 ደቂቃ ውስጥ የዞን ፖሊስ ከቦን አቁሙ ብሎ አስገደደን፤ በዚህ ምክንያት ሰልፉን ለማቆም ተገደናል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር እያስከተለ ያለው ቀውስ ከፋ ያለ ነው፤ የመገናኛ ብዙሃንም ትኩረት ሊሰጡበት ይገባል ተብሏል…
#update የጤና ባለሙያዎች ሰልፍና ስብሰባ በአንዳንድ ከተሞች። ያቀረቧቸው ጥያቄዎች እንዲመለሱ ሲጠይቁ የነበሩት የጤና ባለሙያዎች በተለያዩ ከተሞች ውስጥ ሰልፍና ስብሰባ እያደረጉ ነው።የጤና ባለሙያዎቹ በመላው ሃገሪቱ በዛሬው ዕለት ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ውስጥ ግን እስካሁን የተካሄደ ያለ ስብሰባም ሆነ ሰልፍ እንደሌለ የቢቢሲ ዘጋቢዎች ገልጸዋል።

በአማራ ክልል በባሕር ዳር እና ጎንደር ከተሞች የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄያቸውን በመያዝ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን በመቀሌ ከተማ የሚገኙ ባለሙያዎች ደግሞ ከክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳርድ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ጋር ውይይት እያደረጉ ነው።ቀደም ሲል የጤና ባለሙያዎቹ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር ከተወያዩ በኋላ አጥጋቢ ምላሽ እንዳላገኙ በመግለጽ ሰልፍና የሥራ ማቆም አድማ ሊያደርጉ እንደሚችሉ በስፋት ሲነገር ቆይቶ ነበር።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ👆

"Hi Tsegsh #Debretabor doctors n other health professional were planning to have a peaceful demonstration today but we were stopped by #police_force from going out of the hospital."

@tsegabwolde @tikvahethiopia