TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ዲላ ሆስፒታል‼️

ዲላ ሆስፒታል በጌድዮ ዞን ለሚገኙ ተፈናቃዮች #ድጋፍ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው እንደሚልክ አስታወቀ።

የዲላ ሆስፒታል ከዞኑ ጤና መምሪያ ጋር በመሆን በጌድዮ ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች ህክምና በሚሰጥባቸው ሆስፒታሎች የጤና ድጋፍ እና እገዛ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎችን ወደ ስፍራው እንደሚልክ የሆስታሉ የህክምናና ተግባር ስልጠና ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ሰላማዊት_አየነ ለኢቢሲ ገልጸዋል፡፡

ከሀኪሞችና ነርሶች የተውጣጣው የባለሞያዎች ቡድን መድሀኒት፣ የህክምና ቁሳቁሶችንና ሌሎች ግብዓቶችን በመያዝ የህክምና እርዳታ ስራ እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ገደብ እና ይርጋ ጨፌ ሆስፒታሎች ለተፈናቃዮች ህክምና እየተሰጡ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ፎቶዋ ሲዘዋወር የነበረችው እናት በዲላ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላት መሆኑም ታውቋል፡፡

ታካሚዋ ላጋጠማት የምግብ እጥረት የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ሲሆን መንቀሳቀስ እንድትችልም የፊዝዮ ቴራፒ ህክምና እያገኘች መሆኗ ተጠቅሷል፡፡

ለእናቲቱ ሌሎች የጤና ምርመራዎችም እየተደረጉላት እንደሆነም ነው የተገለፀው፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀሰት ዜና እና ከጥላቻ ንግግሮች እንቆጠብ፦

በዚህ የለውጥ ወቅት ግጭት በመቀስቀስ እና ብጥብጥ በማንገስ የህዝብ መፈናቀል እና ስቃይን ለማባባስ ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ ነው።

አንዳንድ ሀላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦች በተለይም በማህበራዊ ሚዲያዎች የግለሰቦችን እና የድርጅቶችን የሀስት ስም በመጠቀም እና በምስልም በማጀብ የሀሰት ዜናዎች እና የጥላቻ ንግግሮችን በስፋት በማሰራጨት ስሜት በመኮርኮር ላይ ይገኛሉ።

ይህንን የታቀደ እና የተደራጀ ዘመቻ ዓላማ ያልተረዱ ወገኖች ተነካብኝ ያሉትን ወገን ሳያጣሩ በሚሰጡት አፀፋ ምላሽ ወደ ግጭት ሲያመሩ እና ሲተናኮሱ ይስተዋላል። ይህንን የሚሰሩ እና የሚቆሰቁሱ ደግሞ በሞቀ ቤታቸው ሆነው ሌላ ብጥብጥ ይጠነስሳሉ።

ስለሆነም በግጭት እና ብጥብጥ ፀብ በመፍጠር የአመራሮችን እና የድርጅቶችን ስም በመጠቀም፣ ብሄር፣ ፆታ እና ቦታ በመቀየር የግጭት ድግስ የሚደግሱ የተበራከቱ በመሆኑ ማጣራት፣ መመርመር እና ማስተዋል የወቅቱ የሰላም ቁልፍ ነው።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ውስጥ በተለምዶ ቦሌ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተፈጥሮ የነበረው የጸጥታ ችግር ተራ የቡድን ጸብ እንጂ ከፖለቲካ ግጭት ጋር የተገናኘ እንዳልሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በቡድን ጸቡ ተካፋይ የነበሩትን 231 ተጠርጣሪዎች #በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሎ ባደረገው ማጣራት ከጉዳዩ ጋር ቀጥታ ግንኙነት አላቸው የተባሉ 72 ወጣቶችን በማስቀረት ቀሪዎቹን 159 ወጣቶች በምክር #መልቀቁንም አስታውቋል።

የፖሊስ ኮሚሽኑ የኢንዶክትሪኔሽን እና የህዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር #ፋሲካ_ፈንታ ማምሻውን ለአርትስ ቲቪ እንዳስታወቁት በወጣቶቹ መካከል የተፈጠረውን ጸብ ከቄሮ የወጣቶች ቡድን ጋር በማገናኘት የፖለቲካ ግጭት አስመስሎ የተናፈሰው ወሬ ፍጹም መሰረተ ቢስ ነው። እንደኮማንደር ፋሲካ ገለጻ የጸቡ መነሻ በአንድ የላዳ ታክሲ ሹፌር እና በአካባቢው በነበሩ ወጣቶች መካከል “መንገድ አሳልፈኝ አላሳልፍም” በሚል ጭቅጭቅ የተነሳ አለመግባባት ነው።

ትናንት መጋቢት 8 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ በቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ አንድ ክልል አየርአምባ ትምህርት ቤት ከፍ ብሎ በሚገኘው የጫት መሸጫ ሱቆች አካባቢ ተከስቶ በነበረው በዚሁ ተራ ግጭት ቂም የያዘው የታክሲ ሹፌር ወደሰፈሩ በመሄድ ለጓደኞቹ በአካባቢው ወጣቶች ጥቃት እንደደረሰበት ተናግሮ ለጸብ ሲዘጋጁ ካደሩ በኋላ በዛሬው ዕለት ወደስፍራው በመምጣት አጥቅተውኛል ካላቸው ወጣቶች ጋር ግጭት እንዲፈጠር አድርጓል።

እንደኮማንደር ፋሲካ ገለጻ ፖሊስ አስቀድሞ መረጃ ስለደረሰው ወደስፍራው ሃይል በማሰማራት ጸቡን ለመከላከል ጥረት በማድረግ ላይ እያለ በሁለቱ ሰፈር ወጣቶች መካከል በተቀሰቀ ጸብ በእንቅስቃሴ ላይ የነበሩ ሶስት ተሽከርካሪዎች መስተዋት ሲሰበር በተመሳሳይ በመስተዋት ተሰርተው የነበሩ የጫት መሸጫ ሱቆች እና በአካባቢው በሚገኝ የኦሮሚያ ባንክ ቅርንጫፍ ቢሮ መስተዋት ላይም መጠነኛ ጉዳት ደርሷል።

ፖሊስ በሁለቱም ወገን የጸቡ ተካፋይ ናቸው ያላቸውን 231 በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ማጣራቱንና በቀጥታ በግጭቱ ተሳታፊ ናቸው ያላቸውን 67 ወንዶችና 5 ሴቶች በድምሩ 72
ተጠርጣሪዎች በእስር አቆይቶ ቀሪዎቹን 159 ተጠርጣሪዎች በሙሉ ዳግም በዚህ አይነት ጥፋት ላይ እንዳይገኙ መክሮ መልቀቁን ተናግረዋል።

ኮማንደር ፋሲካ እንዳሉት እውነታው ይኸው ሆኖ ሳለ አንዳንድ አክቲቪስቶች በማህበራዊ ሚዲያ “በቦሌ ቄሮ እና በአዲስ አበባ ወጣቶች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ” በማለት ባሰራጩት የሃሰት መረጃ ያልተገባና ለፖለቲካ አላማ የታቀደ ተግባር በመፈጸም የህብረተሰቡን ደህንነት ስጋት ውስጥ ለመክተት ሞክረዋል። ከተማዋ አለመረጋጋት እንደሌላት በማሰብ ብዙዎች ለደህንነታቸው ስጋት እንዲገባቸውም ምከንያት ሆነዋል። ይህ ተግባር ፍጹም ሃላፊነት የጎደለውና ማመዛዘን ከሚችል አካል የማይጠበቅ ነው ያሉት ኮማንደሩ እንዲህ አይነት የሃሰት መረጃ የሚያሰራጩ ግለሰቦችም በህዝብ ሰላምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ወንጀል እየፈጸሙ መሆኑን ሊገነዘቡና ሊጠነቀቁ ይገባል ነው ያሉት።

ህብረተሰቡም በዚህ አይነት #የፈጠራ_መረጃ እንዳይደናገር ያሳሰቡት የፖሊስ ሃላፊው ለማይበርድ ግጭት የሚዳርጉ የሃሰት ወሬዎችን ባለማራገብ ሰላሙን እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላልፈዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከዚህ ግጭት ምርመራ ጋር ተያይዞ ያሉትን ቀሪ ውጤቶች በቀጣይ ለህዝቡ ይፋ እንደሚያደርግም ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል።

Via ArtsTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቦሌ ክ/ከተማ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት/...

ዛሬ መጋቢት 09/2011ዓ.ም በክ/ከተማችን ውስጥ ወረዳ 1 ልዩ ስሙ ቦሌ ሚካኤል በሚባለው ሰፈር በቄሮዎች እና በአካባቢው ወጣቶች መካከል ግጭት እንደተፈጠረ ተደርጎ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚንሸራሸረው ዜና ሐሰት እንደሆነ በስፍራው በመገኘት ማረጋገጥ ችለናል፡፡ በርግጥ የግለሰቦች ግጭት ነበር፤ የጠቡ መንስኤ የታክሲ ተራ አስከባሪዎች ከጫት ነጋዴዎች ጋር የፈጠሩት አለመግባባት ሲሆን በግጭቱ በአቅራቢያው የነበረ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ የሚገኝበት ሕንጻ መስተዋት መጠነኛ የመሰበር አደጋ ከመድረሱ በስተቀር በሰው ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት የለም፡፡በአሁኑ ሰአትም ሰላማዊ እንቅስቃሴ ነው ያለው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ በቦሌ ስለተፈጠረው ጉዳይ በቦታው የነበሩ አካላትን ማግኘት ከቻልኩ ምን እንደተፈጠረ ጠይቄ ተጨማሪ መረጃ አደርሳችኃለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሳነ ሊቀጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ በደቡብ ሱዳን ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ያላቸውን ድጋፍ ለመግለፅ ያለመ ጉብኝት በሀገሪቱ ሊያደርጉ ነው፡፡ በቫቲካን ከሀገሪቱ ኘሬዝዳንት ሳልቫኪር ጋር የተወያዩት አቡነ ፍራንሲስ ለማድረግ ያለሙት ጉብኝት ለሀገሪቱ ህዝቦች ያላቸውን ቅርበትና የሰላም ሂደቱን ለማበረታታት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የሁለቱ መሪዎች ውይይት በሰላም ሒደቱ፣ የተሰደዱ የሀገሪቱ ዜጎች በሚመለሱበትና በቀጣይ የልማት ዙሪያ ያተኮረ እንደነበር ቫቲካን ገልፃለች፡፡ አቡነ ፍራንሲስ ከ2 አመት በፊት ደቡብ ሱዳን ለመጎብኘት የነበራችውን ዕቅድ በሀገሪቱ በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ማዘግየታቸው ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- አሶሼትድ ኘሬስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም ሚኒቴር‼️

በምንጃር ሸንኮራ እና ፈንታሌ ወረዳዎች አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ተፈጥሮ የነበረው ግጭት በቁጥጥር ስር መዋሉን የሰላም ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ እና በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ መካከል አሞራ ቤት በምትባል ቀበሌ እንስሳትን ውሃ በማጠጣት ሂደት የተፈጠረው ግጭት በዛሬው ዕለት በቁጥጥር መዋሉን በሚኒስቴሩ የግጭት አፈታት ዳይሬክተሩ አቶ ኃይለአብ ጌታቸው ለebc ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ እንዳስታወቁት በአዋሳኝ አካባቢዎቹ መጋቢት 8 ፣2011 የተፈጠረው ግጭት እንሰሳትን ውሃ ለማጠጣት በሚል ምክንያት ተጀምሮ ለሁለት ሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል፡፡

በግጭቱ በሁለቱም ወገን ከሞቱት ሁለት ሰዎች በተጨማሪ በሰባት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

የመከላከያ ሠራዊትም ግጭት በተፈጠረበት አካባቢ ገብቶ የማረጋጋት ስራ እየሰራ እንደሆነም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የሁለቱ ዞን አስተዳዳሪዎች ግጭት በተፈጠረበት አካባቢ ዛሬ በመሄድ ህዝቡን በማወያየት ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረጉ መሆኑንም አቶ ኃይለአብ አመልክተዋል።

በእንሰሳት ግጦሽ እና የመጠጥ ውሃ የተፈጠረው አለመግባባት ከዚህ በፊትም እንደሚከሰትና በሁለቱም ወገን በኩል ያሉ አመራሮችና የአካባቢው ማህበረሰብ እንደከዚህ ቀደም ባሉ ውይይቶች ችግሩን እንደሚፈቱት ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአርበኞች ግንቦት ሰባት የውጪ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ነዓምን ዘለቀ ከድርጅቱ ሀላፊነት መልቀቃቸውን አስታወቁ። ኢሳት እንደዘገበው ከኤርትራ የተመለሱ የድርጅቱ ወታደሮች አያያዝ እንቅልፍ ስለነሳኝ ሀላፊነቴን በገዛ ፈቀዴ ለቅቄያለሁ ብለዋል። ከዚህ ቀደምም ከድርጅቱ ለመልቀቅ ሀሳብ እንደነበራቸው ያመለከቱት አቶ ነዓምን ከማናቸውም የድርጅቱ አባላትም ሆነ አመራሮች ጋር የግል ቅራኔ የለኝም ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን ትላንት መጋቢት 9 ቀን 2011 ባካሄደው ስብሰባ አራተኛዉን የህዝብና ቤት ቆጠራ ለማካሄድ የተደረገዉን ዝግጅት በመገምገም የዉሳኔ ሃሳቦች ኣሳልፏል::
በዚህም መሠረት:-

• የሕዝብና ቤት ቆጠራው እንዲቀጥል በቴክኒክ ደረጃ በቂ ዝጅግት የተደረገ መሆኑንና ኮሚሽኑና ማእከላዊ እስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሰፊ ስራ የሰሩ መሆኑን፤

• የካርታ እና ተያያዥ ስራዎች እየተገባደዱ መሆኑን፤

• ሌሎች ዝግጅቶችም እየተደረጉ መሆኑን ግንዛቤ ወስዶ የቆጠራውን አላማና ግብ በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሳካት የሚያስችሉ ተግባራት የተሟሉ ባለመሆናቸው ማለትም በየአካባቢው ለስራው መሳካት በተገቢው ሁኔታ መጠናቀቅ የሚገባቸው ተግባራት ባለመጠናቀቃቸው እና ተጨማሪ ግዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ፤

• ምንም አንኳን ለቆጠራ የቀሩን ቀናት ጥቂት ቢሆንም በተለያዩ ገጭቶች ምክንያት የትፈናቀሉ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ወገኖች ወደነበሩበት ቀዬ የመመለሱ ስራ በበቂ ሁኔታ ባለመሰራቱ አሁንም በርካታ ዜጎች በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ በመሆኑ እነዚህ ወገኖች ትርጉም ባለው ደረጃ ወደ ነበሩበት ቦታ እስኪመለሱ ድረስ ተጨማሪ ጊዜ በማስፈለጉ ቆጠራው እንዲራዘም የውሳኔ ሃሳቡን ለተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች እንዲቀርብ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ ክልል ም/ፕሬዝዳንት ወ/ሮ #ጠይባ_ሀሰን በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ሕገ ወጥ ግንባታዎች ከፈረሱባቸው የማህበረሰቡ አካላት ጋር በትላንትናው ዕለት ውይይት አድርገዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዲላ ዩኒቨርሲቲ🔝

#የዲላ_ዩኒቨርሲቲ በጎ አድራጎት ክበብ በጌዴኦ ዞን ለሚገኙ የተፈናቀሉት ወገኖች ገቢ ማሰባሰቢያ የሶስት ቀን ዜር ፎር (የስጋ አቅርቦት) ለማስቀረት ዛሬ የፒቲሽን ማሰባሰብ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ የተቋሙ ተማሪዎችም ትብብር እድታደርጉላቸው ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia