TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ሩሲያ ኢንተርኔትን ለማቋረጥ እያሰበች ነው‼️

ሩሲያ እራሷን #በኢንተርኔት አማካይነት ከሚፈጸም ጥቃት ለመከላከል በምታደርገው ዝግጅት ለአጭር ጊዜ እራሷን ከዓለም አቀፉ የኢንትርኔት ትስስር #የማቋረጥ አማራጭን እያጤነች ነው።

ይህም ማለት የኢንትርኔት ግነኙነት በሃገር ውስጥ ብቻ የተገደበ ይሆናል። በዚህም ሩሲያዊያን የሚልኩት እና የሚቀበሉት መረጃ እርስ በርሳው እንጂ ከተቀረው ዓለም ጋር አይሆንም።

ለሙከራው የተቆረጠ ቀን ባይኖርም በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚከናወን ይጠበቃል።

የተቀሩት የዓለም ሃገራት ሩሲያን ከዓለም አቀፉ የኢንተርኔት አገልግሎት ቢያገሏት በእራሷ መቋቋም የሚያስችላት ረቂቅ አሰራር እየተገበረች ነው።

የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ከዚህ ቀደም ሩሲያ #የሳይበር_ጥቃቶችን ታደርሳለች በማለት ማዕቀብ እንደሚጣልባት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

ሩሲያ እንዴት ከተቀረው ዓለም የኢንተርኔት ትስስር እራሷን በማግለል በሃገሪቱ ውስጥ ብቻ የኢንተርኔት አገልግሎትን ማኖር ትችላለች? የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው።

የዘርፉ በለሙያዎች ሲያስረዱ፤ "ኢንተርኔት የሚሰራበትን መንገድ መረዳት ይገባናል" ይላሉ። "በሺህዎች የሚቆጠሩ መረጃዎች የሚተላለፉባቸው ዲጂታል ኔትዎርኮች አሉ። እንዚህ ኔትወርኮች 'ራውተር' በሚባሉ መዳረሻዎች ይገናኛሉ። ሩሲያ ያቀደችው በራውተሮች በኩል ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ እና የሚወጡ ዳታዎችን መቆጣጠር ነው።"

ይህን አካሄድ በመጠቀም ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ መረጃዎችን በመቆጣጠር ረገድ ቻይና ውጤታማ ስለመሆኗ ይነገራል።

ሆን ተብሎም ባይሆን ሃገራት በተለያዩ አጋጣሚዎች ከተቀረው ዓለም ጋር የሚኖራቸው የኢንተርኔት አገልግሎት ከዚህ ቀደም ተቋርጧል። ባህር ውስጥ ያለ የኢንተርኔት ገመድ በመቋረጡ ከዚህ ቀደም አፍሪካዊቷ ሃገር ሞሪታኒያ ለሁለት ቀናት ከተቀረው ዓለም ተነጥላ ነበር።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia