አብዲ ኢሌ‼️
የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ #አብዲ_መሐመድ የቀረበባቸው ክስ “የተቀነባበረ ውሸት ነው” አሉ። አቶ አብዲ ይህን ያሉት ጉዳያቸውን እየተመለከተ ላለው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ነው።
ችሎቱ ለዛሬ ቀጠሮ ይዞ የነበረው አቶ አብዲን ጨምሮ በ47 ተጠርጣሪዎች ላይ የቀረበባቸውን ክስ በንባብ ለማሰማት ነበር። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በይፋ ክስ የመሰረተው ባለፈው ረቡዕ ጥር 22 የነበረ ቢሆንም የተከሳሽ ጠበቆች በችሎት ባለመገኘታቸው የክስ ንባቡ ለዛሬ ተላልፏል። ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተከሳሾቹ በሐምሌ 2010 ዓ. ም. በሶማሌ ክልል 59 ሰዎች እንዲገደሉ እና 412 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት እንዲወድም አድርገዋል በሚል ነው ክሱን ያቀረበው።
በዛሬው የችሎት ውሎ ክሳቸውን ያደመጡት አቶ አብዲ ክሱን ተረድተውት እንደሆነ በመሐል ዳኛው ሲጠየቁ “ሆን ተብሎ የተቀነባበረ #ውሸት መሆኑ ገብቶኛል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። የእርሳቸውን ምላሽ ተከትሎ ችሎቱን ሞልተው የነበሩ ታዳሚዎች በሹክሹክታ ሲጠያየቁ እንደነበር በስፍራው የተገኘው የጀርመን ራድዮ ዘጋቢ ታዝቧል። ፍርድ ቤቱ ከአቶ አብዲ ውጭ የሌሎችን ተከሳሾች ምላሽ ያላደመጠ ሲሆን ከክስ መቃወሚያ ጋር ደርቦ ለመስማት ለመጪው የካቲት 20 ቀጠሮ ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎው የተከሳሽ ጠበቆች በክሱ ላይ ያቀረቡትን አቤቱታም አድምጧል። በክሱ ውስጥ የምስክሮች ዝርዝር አለመካተቱን ያነሱት የተከሳሽ ጠበቆች በተገቢው ሁኔታ “እንድንከላከል አያስችለንም” ሲሉ ተቃውመዋል። አቃቤ ህግ ምላሹን በጽህፈት ቤት በኩል እንዲያስገባ ያዘዘው ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ብይን ለመስጠት ለየካቲት 6 ቀጥሯል።
በዛሬው ችሎት አብዛኞቹ ተከሳሾች በአካል አለመቅረባቸውን ዘጋቢያችን ተመልክቷል። ፍርድ ቤቱ ባለፈው ሳምንት ባስቻለው ችሎት ፖሊስ ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እንዲያውል የአምስት ቀናት ጊዜ ፈቅዶ ሰጥቶ ነበር። የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ለፖሊስ የደረሰው ከትላንት በስቲያ መሆኑን አቃቤ ህግ ዛሬ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል። “ከቦታው ርቀት አንጻር በቂ ጊዜ ይሰጠን” ሲልም በዛሬው ችሎት አመልክቷል።
ምንጭ:- የጀርመን ድምፅ ራዲዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update ትናንት ምሽት በህገ ወጥ መንገድ ከአገር ሊወጣ የነበረ 7 ኪሎ ግራም ወርቅና የተለያየ መጠነ ያለው 60 ሚሊዮን ብር የሚገመት የ8 አገራት ገንዘቦች በቶጎ ዉጫሌ ኬላ መያዙን የገቢዎችና ጉምሩክ አስታውቋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጸመ‼️
የኮሎኔል #ታደሰ_ሙሉነህ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ፡፡ ኮሎኔል ታደሰ ከወይዘሮ አዛለች ጥሩነህ እና ከአቶ ሙሉነህ ሃምሌ 16/1944 ዓ.ም በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ እንደተወለዱ ከትግል አጋሮቻቸው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትም በ67 ዓመታቸው ነው፡፡ ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ የአራት ሴቶችና የሁለት ወንድ ልጆች አባት ነበሩ፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸውም በማህደረ ስብሀት መርዓዊ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ተፈጽሟል፡፡
በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ላቀ አያሌው፣ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ እና የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር አባላት ተገኝተዋል፡፡ የአበባ ጉንጉንም አስቀምጠዋል፡፡
ምንጭ፦ አብመድ

“ህብረተሰቡ ለእኛ ያለው #አመለካከት ሊሻሻል ይገባል”- የቀድሞ የኢትዮጵያ የሰራዊት አባላት‼️
ህብረተሰቡ ለእኛ ያለው አመለካከት ሊሻሻል ይገባል ሲል በቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት የተቋቋመው የድጋፍና የልማት ማህበር ጥሪ አቀረበ፡፡
ማህበሩ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሰራዊቱ ህብረተሰቡ ለእኛ ያለው አመለካከት ሊቀየር ይገባል፤ ልክ እንደ ጨፍጫፊ ነው የሚመለከተን፤ ይህ አመለካከት ሊቀር ይገባል ብሏል፡፡
ማህበሩ ለቀድሞ የኢትዮጵ ሰራዊት አባላትንና ቤተሰቦቻቸው የድጋፍና እገዛ ስራዎችን ለመስራት ታልሞ የተቋቋመ ማህበር መሆኑን በመግለፅ የማህበሩ ዋና አላማ ማህበረሰቡ ለሰራዊቱ ያለውን መጥፎ አመለካከትን ማስቀየርና የተጎዱ የሰራዊቱን አባላት በመርዳት እንደሆነ መቶ አለቃ ሰለሞን ገልፀዋል፡፡
ማህበሩ ስራውን በሁለት አባላት የጀመረ ሲሆን አሁን ላይ 1 ሺህ 200 ደርሷል፤ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ሶስት ወርሀዊ ጉባኤዎችን አካሂዷል ተብሏል፡፡
የቀድሞ የኢትዮጵያ የሰራዊት የድጋፍና የልማት ማህበር በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ እየተፈጠረ ያለውን የኢትዮጵያዊነትንና የአንድነትን ስሜት እንደ አንድ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ ሰፋፊ ስራዎችን ለማከናወን አቅዶ ወደ ስራ መግባቱን መቶ አለቃ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡
የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት የድጋፍና የልማት ማህበር ባሳለፍነው ጥቅምት ወር መመስረቱ ይታወሳል፡፡
ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ

#update ከሰዓት አዲስ አበባ የገቡትን የጊኒ ፕሬዝዳንት #አልፋ_ኮንዴን በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በተደረገ የእንኳን ደህና መጣችሁ ስነስርአት ላይ በመገኘት ተቀበሏቸው። ሁለቱ ወገኖች የካቲት 3 ቀን 2011 ከሚጀምረው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን #የሁለትዮሽ ስብሰባዎች እንደሚኖራቸው ይጠበቃል።
ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) ለፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ የ9 መቶ ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ፡፡ አብቁተ ከዚህ በፊት ለጣና እንክብካቤ የሚውል 2 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉም ይታወሳል፡፡
Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በሙሉ፦
1000273509497
#ሼር_ሼር_ያድርጉ!!
ጥር 26 በእስቴ መካነ እየሱስ ቀበሌ 03 የተቃጠለውን መስጊድ በአንድነት ተባብረን ለማሰራት ኮሚቴ ተቆቁሞ የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ተጀምሮል በገንዘብ መደገፍ ለምትፈልጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ [Este M/E/Yetekatelu Mesgede Yerdata][የእስቴ መ/እ/የተቃጠለው መስጊድ የእርዳታ]የሂሳብ ቁጥር 1000273509497 ደብተሩ በሶስት ግለሰቦች ስም ተከፍቶል....
#1)አህመድ አሊ
#2)ሀጅ ኡስማን አሊ
#3)ሁሴን መሀመድ
©ሀብታሙ ካሴ

በእስቴ ወረዳ የተቃጠሉትን #መስጊዶች
አንድ ላይ ተባብረን በጋራ #እናሰራ!
1000273509497 የሂሳብ ቁጥር [Este M/E/Yetekatelu Mesgede Yerdata][የእስቴ መ/እ/የተቃጠለው መስጊድ የእርዳታ]
#TIKVAHETHIOPIA #ቲክቫህኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አንድ ላይ ተባብረን በጋራ #እናሰራ!
1000273509497 የሂሳብ ቁጥር [Este M/E/Yetekatelu Mesgede Yerdata][የእስቴ መ/እ/የተቃጠለው መስጊድ የእርዳታ]
#TIKVAHETHIOPIA #ቲክቫህኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንቢ እንበላቸው‼️
በብሄር ከፋፍለው #ሊያፋጁን የሚጥሩትን የሰይጣን ቁራጮች እንቢ እበላቸው፤ በዘር ለይተው እንድንፋጅ የሚጎተጉቱንን የሰላም ፀሮች እንቢ እንበላቸው፤ #በሀይማኖት ከፋፍለው ሊያጫርሱን የሚፈልጉትን እንቢ እንበላቸው!! ሰላም፣ አንድነት፣ ፍቅር የሁሉም ነገር መሰረት ነው!!
ሰላም እደሩ!!

Audio
የስራ ማቆም አድማ‼️
የቡርጂ ወረዳ መንግሥት ሰራተኞች የሥራ ማቆም አድማው በማንነታቸው “ይደርስብናል” ካሉት ጥቃትና የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች መታሰርን ተከትሎ ነው "የቡርጂ ብሄረሰብ ተወካዮች ነን” የሚሉ ቁጥራቸው 70 የሚሆኑ ሰዎችና የሀገር ሸማግለዎች በደል ደርሶብናል ሲሉ ወደ ክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ በመምጣት አቤቱታ አቅርበዋል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ታመነ ተሰማ በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች ለምን ታሰሩ ብሎ ሥራ ማቆም ተገቢነት የለውም ብለዋል፡፡

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መከላከያ ሰራዊት‼️
በደቡብ ክልል የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን ከመቆጣጠር አንፃር የመከላከያ ሠራዊት የመሪነት ሚናውን በመወጣት ላይ መሆኑ ተገለፀ፡፡
Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በደቡብ ክልል የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን ከመቆጣጠር አንፃር የመከላከያ ሠራዊት የመሪነት ሚናውን በመወጣት ላይ መሆኑ ተገለፀ፡፡
Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባለሀብቶች #የቴሌኮም ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅድ የህግ ረቂቅ ቀረበ‼️
የቴሌኮም አገልግሎት ረቂቅ አዋጅ በሚል ስያሜ የተዘጋጀው ሰነድ ኢትዮጵያን በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ለፈለገ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ባለ ሀብት ክፍት የማድረግን የመንግስትን ፍላጎት ይፋ አድርጓል። ረቂቅ አዋጁ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባለፈው አመት በቴሌኮም ዘርፉ እንዲተገበር ከወሰነው ሰፋ ባለሁኔታ ዘርፉን ለገበያ ክፍት የሚያደርግ ነው። ቀድሞ ተነግሮ የነበረው መንግስት የኢትዮ ቴሌኮምን አብላጫ ድርሻ ይዞ ቀሪውን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች ድርሻ የመሸጥ ነበር።
ዋዜማ ራዲዮ የተመለከተችው ረቂቅ አዋጅ እንደሚያሳየው ግን ሀገሪቱ የቴሌኮም ዘርፏን ሰፋ አድርጋ ለገበያ እንደምትከፍት የሚያሳይ ነው። በረቂቅ አዋጁም ላይ ፣ በሌላ ህግ የተደነገገ አዋጅ ወይንም ደንብ ቢኖርም ማንኛውም የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብት የቴሌኮም አገልግሎት ፣ የቴሌ ኮሚኒኬሽን ኦፕሬሽን እና የቴሌ ኮሚኒኬሽን ኔትወርክ ባለቤትነት ፍቃድ የማግኘት መብት እንዳለው ተደንግጓል። እስካሁን ለቴሌኮም ዘርፉ ግልጋሎት ላይ የዋሉ የቴሌኮም አዋጅ፣ የብሮድካስት አገልግሎት አዋጅ፣ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ እና የፖስታ አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ ህጎች እንዲሻሩም በረቂቅ አዋጁ ላይ ተቀምጧል።
#የቴሌኮም_ዘርፉን እንዲቆጣጠርም የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ተቆጣጣሪ ባለስልጣን እንዲቋቋም የሚያደርግ ሰፊ አንቀጾችም በረቂቅ ህጉ ተካቷል።
በረቂቅ ህጉ መሰረት በርካታ የቴሌኮም ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ በመሆኑ ካልተገቡ የገበያ ውድድሮች ከመቆጣጠር አንስቶ፣ የቴሌኮም አገልግሎት ፍቃድን መስጠትና በርካታ ስልጣኖች ተሰጥተውታል። የቴሌ ኮም ዘርፍ ቢሊየን ዶላሮችን የሚያንቀሳቅሱ ኩባንያዎች ያሉበት በመሆኑ ባለስልጣኑ ጠንካራና ጥቅማ ጥቅሞቻቸው የተጠበቁላቸው ሰራተኞች ሊኖሩት እንደሚገባ ባለሙያዎች ይመክራሉ።
ረቂቅ አዋጁ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ተግባራዊ ከሆነ የኢትዮጵያን የቴሌ ኮሚኒኬሽን ዘርፍ በብዙ መልኩ የሚያሻሽልና ለሀገሪቱም የውጭ ምንዛሬን በስፋት እንደሚያስገኝ እንዲሁም ነገሩ በጥንቃቄ ከተያዘ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚም መልካም መሆኑን መንግስት ያስረዳል።
አሁን በብቸኝነት አገልግሎት እየሰጠ ያለው ኢትዮ ቴሌኮምም ጠንካራ ውድድር ከፊቱ እንደሚመጣበት ይጠበቃል። ይህን የመንግስት ውሳኔ አስተዋይነት ይጎድለዋል ሲሉ የሚተቹ ባለሙያዎችም አሉ።
ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ