TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update አዲስ አበባ⬇️

ሰሞኑን ወደ መሬት ባንክ እንዲመለሱ ውሳኔ የተላለፈባቸው የአዲስ አበባ ሰፋፊ ቦታዎች ዳግም በሕገ-ወጥ መንገድ እንዳይወረሩ #ጥበቃ እንዲደረግላቸው ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡ የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽህፈት ቤት ለቦታዎች ጥበቃ እንዲያደርግ ለደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት በደብዳቤ ትዕዛዝ አስተላልፏል ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል...

በሕገ-ወጥ መንገድ #የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የያዙ አካላትን #በማጋለጥ ጥቆማ እንዲሰጥ የከተማው ነዋሪ ጥሪ ቀርቦለታል፡፡ ጥሪውን ያቀረበው የአዲስ አበባ አስተዳደር ቤት ኖሯቸውም የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የወሰዱ ካሉ፣ ነዋሪው እንዲጠቁመው ይፈልጋል፡፡ የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት በፌስቡክ ገጹ እንዳስረዳው፣ ታጥረው የቆዩ የከተማዋን መሬት ወደ መንግስት እንደመለሰው ሁሉ በጋራ መኖሪያ ቤቶችም ላይ ምርመራውን ቀጥሏል፡፡ የቤት ችግር ላለባቸው ነዋሪዎች ታስቦ የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በህገ-ወጥ መንገድ በያዙት ላይ፣ በተደረገው #ፍተሻ የተገኘውን ውጤት እንደሚገለፅም ተጠቁሟል፡፡
እስከዚያው ነዋሪዎች፣ ሰው ሳይገባባቸው የቆዩ፣ በህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ ቤቶችን እንዲጠቁሙ አሳስቧል፡፡

ምንጭ፦ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መግለጫ⬆️የኦሮሞ ሕዝብ አንድነት እና አንገብጋቢ የወቅቱ ጉዳዮችን አስመልክቶ ኦነግ፣ ኦፌኮ፣ የተባበሩት ኦነግ፣ የኦሮሚያ ነፃነት አንድነት ግንባር እና የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር #የጋራ መግለጫ አውጥተዋል። ፓርቲዎቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ አምስት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ አተኩረዋል። እነርሱም፦ የኦሮሞ ማንነትን ለማጥፋት እየተደረገ ያለው ሙከራ፣ አዲስ አበባ ጉዳይ፣ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ሚድያዎች፣ በሃገሪቱ እየታየ ያለው ለውጥን እና በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ፌዴራሊዝምን የሚመለከቱ ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia