የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት‼️
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመከላከያ ሰራዊት አዋጅ 28 አንቀፆችን #ሊያሻሽል ነው።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 8ኛ መደበኛ ስብሰባው አዋጅ ቁጥር 809/2006 ላይ ያሉ 28 አንቀጾች እንዲሻሻሉ የመከረው በአገሪቷ የተፈጠረውን ለውጥ ተከትሎ #ሰራዊቱ አገራዊ ግዴታውን በተሻለ ብቃት እንዲወጣ ለማስቻል መሆኑም ተገልጿል።
የአገራዊ ደህንነት ስጋቶችና የጦርነት አይነቶች፣ ባህሪያትና ውስብስብነትንም ከግምት ውስጥ በማስገባት የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ደግሞ የሪፎርሙ አንድ አካል ነው።
በዚህ መሰረት ከተሻሻሉት አንቀጾች ውስጥ የሰራዊቱ አደረጃጀት ቀደም ሲል ከነበረው በተጨማሪ በባህር ሃይል፣ በስፔስና በሳይበር ሃይሎችም እንደሚደራጅ በረቂቅ አዋጁ ተጠቅሷል።
የሰራዊቱ ምልመላ፣ ቅጥር፣ ወታደራዊ ስልጠና፣ የአባላት ግዴታ፣ ማበረታቻ፣ የውትድርና አገልግሎት የሚቋረጥበት ሁኔታ፣ የአገልግሎት ካሳና ጡረታም በአዋጁ ከሚሻሻሉ አንቀፆች ወስጥ ይጠቀሳሉ።
የምክር ቤቱ አባላትም በሚሻሻሉ አንቀፆች ላይ ያላቸውን አስተያየት ከሰጡ በኋላ አዋጁ በዝርዝር እንዲታይ ለውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።
በተያያዘ ዜና ምክር ቤቱ በዛሬ ስብሰባው የህዝብና ቤት ቆጠራ አባላትን ለመመደብ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
አዲስ የተመረጡት የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን 20 አባላት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ አማካኝነት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
በሌላ በኩል ምክር ቤቱ በመንግስትና በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለልማት ፖሊሲ ፋይናንስ ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማፅደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅንም መርምሮ ለገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ መርቷል።
ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የአዲስ አበባ ወጣቶች🛫ሀዋሳ
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን #ለማጠንከር ወደ ሐዋሳ ያቀናሉ፡፡
በነገው እለት ወደ ሐዋሳ የሚያቀኑት፥ በአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር #ታከለ_ኡማ የሚመራ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ናቸው፡፡
በምክትል ከንቲባው የሚመራው እና በሐዋሳ የሁለት ቀናት ቆይታ የሚያደረገው ይህ የሉኡካን ቡድንም ከሐዋሳ እና አካባቢው ነዋሪዎች
ጋር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በሚያጠናክሩ አጀንዳዎች ዙሪያ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች በባህር ዳር የሶስት ቀን ቆይታ አድርገው መመለሳቸው የሚታወስ ነው።
ምንጭ፦ eprdf addis abeba

#Update በዚሁ አመት ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው የህዝብና ቤት ቆጠራ 20 አባላት ተመደቡለት፡፡ ከፌዴራል ሚኒስትሮችና ከክልል ደግሞ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችን ጨምሮ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና ከንቲባን ያካተተ 20 አባላትን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለኮሚሽኑ መድቧል፡፡ የሰላም ሚኒስትር፣ የገንዘብ ሚኒስትር፣ የትራንስፖርት ሚኒስትርና ሌሎችንም ያካተተው የኮሚሽኑ አባላት በሕዝብና ቤት ቆጠራ ወቅት ፖለቲካዊ አመራርና አስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲሰጥ ይጠበቅበታል ተብሏል፡፡ አባላቱ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ ፈፅመው ሀላፊነታቸውን ተረክበዋል፡፡ አምና መካሄድ የነበረበት የህዝብና ቤት ቆጠራ በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ለዚሁ አመት መራዘሙ ይታወቃል፡፡ ቆጠራው የሚካሄድበት ወር ግን አልተቆረጠም፡፡
ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ🔝የተቋሙ ተማሪዎች ከፌደራል መንግስት ከሚመጡ ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከነገ ጀምሮ ውይይት ያደርጋሉ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ኦነግ አዲስ ፓርቲ አይደለሁም፤ እንደገና መመዝገብ #የለብኝም ሲል ያቀረበውን አቤቶታ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ወድቅ አድርጎታል፡፡ የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ ዳባ ግን ግንባሩ በ1983 ዓ.ም በሕግ ስለተመዘገበ አሁን ድጋሚ አይመዘገብም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ ኦነግ ይህንኑ አቋሙን ለቦርዱ ማሳወቁንም ገልጸዋል- ቃል አቀባዩ፡፡
©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ነባር አመራሮችን በወጣቶች ተክቶ በሀገሪቱ የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ወደ ክልሉ በማውረድ ለማሳካት እንደሚሰራ የድርጅቱ ሊቀመንበር አስታወቁ፡፡ #በሰመራ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአብዴፓ ድርጅታዊ ኮንፈረንስ የአቋም መግለጫ በማውጣት ትናንት ተጠናቋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሹመት‼️
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለተለያዮ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች #ሹመት ሰጥተዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መግለጫ መሰረት፦
1.ዶክተር አምባቸው መኮንን፦ የጠቅላይ ሚንስትሩ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት አማካሪ ሚንስትር
2.አቶ ገብረእግዚአብሔር አርአያ፦ በሚንስትር ዴኤታ ማዕረግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ
3.አቶ ጫኔ ሽመካ፦ በሚንስትር ዴኤታ ማዕረግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ
4.አቶ ጫላ ለሚ፦ በሚንስትር ዴኤታ ማዕረግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ
5.አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ፦ የጠቅላይ ሚንስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር ዴኤታ
6.ብርጋዴል ጄኔራል አህመድ ሀምዛ፦ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር
7.አቶ ሞቱማ መቃሳ፦ የጠቅላይ ሚንስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር ዴኤታ
8.አቶ ከበደ ይማም፦ የአካባቢ ጥበቃ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር
9.አቶ አዘዘው ጫኔ፦ የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር
10.አቶ አወል አብዲ፦ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር
11.አቶ ሙሉጌታ በየነ፦ የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር
12.ዶክተር ፅጌረዳ ክፍሌ፦ የብሔራዊ ኤች. አይ. ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር
13.ወይዘሮ ያምሮት አንዱዓለም፦ የአርማወር ሐሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር
14.ዶክተር ሚዛን ኪሮስ፦ የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር
15.አቶ ሀሚድ ከኒሶ፦ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር
16.አቶ ከበደ ጫኔ፦ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር
17.ወይዘሮ ምስራቅ ማሞ፦ የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።
ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት

ጥረት‼️
• በየዓመቱ 100 ሚሊዮን ብር ሲከስር ነበር፡፡
• የባንክ ዕዳውም 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡
በቀድሞው ኢህዴን (አዴፓ) በዘላቂ በጎ አድራጎት ወይም ኢንዶውመንት ቁመና ይዞ የተመሠረተው ጥረት ኮርፖሬት 20 ኩባንያዎች አሉት። ከእነዚህ ውስጥ ከሰባቱ በየዓመቱ 100 ሚሊየን ብር አካባቢ ይከስራል።
የጥረት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አምላኩ አስረስ እንደሚሉት በቀደመው አመራር ጥረት 11 ቢሊዮን ብር ጥሬ ሀብት አለው ተብሎ ሪፖርት የተደረገውም ስህተት ነው። የጥረት በአሁኑ ወቅት ያለው ጥሬ ሀብት 5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ሲሆን 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን አካባቢ የባንክ ዕዳ አለበት። ከዚህም በተጨማሪ ካሉት 20 ኩባንያዎች በሰባት ኩባንያዎች በየዓመቱ 100 ሚሊዮን ብር ይከስራል።
ጥረት በትራንስፖርት ዘርፉ የተሠማሩ 500 ተሽከርካሪዎች አሉት እየተባለ ሪፖርት ሲደረግ ቢቆይም በተግባር ያሉት ተሸከርካሪዎች ግን 348 ናቸው። ከዚህ ውስጥ 48ቱ ብቻ ዓመት እስከ ዓመት ይሠራሉ፤ ሌሎቹ የተበላሹ ናቸው። ጥረት ከኪሳራው ለመውጣት አዲስ ፍኖተ ካርታ እያዘጋጀ ሲሆን የመዋቅር እና የአመራር ለውጥም እያደረገ እንደሆነ ዶክተር አምላኩ አስረድተዋል። አጥፊዎችም #በሕግ የሚጠየቁ ይሆናል ብለዋል።
ምንጭ፦ አብመድ

#Update ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ እናቶችን ያቀፈ 22 አባላት ያሉት #የሰላም_አምባሳደሮች ቡድን መቀሌ ገብቷል፡፡ ቡድኑ ከሁሉም ክልሎች እና ከአዲስ አበባ እና ድሬደዋ የተውጣጣ ነው፡፡ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደብረ ጺዮን ገብረ ሚካዔል ቡድኑም ሲቀበሉ ባደረጉት ንግግር ለሰላም ተልዕኮ የመጣችሁበት ትግራይ ክልል ሰላማዊ ነው ብለዋል፡፡ ቡድኑ በቆይታው ከተለያዩ ኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ከክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር ይወያያል፡፡
©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትግራይ ክልል‼️
የትግራይ ክልል ለ3 ሺህ 231 ታራሚዎች #ይቅርታ አደረገ። የክልሉ የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እንዳስታወቀው፥ ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች መካከል 72ቱ #ሴቶች ናቸው።
ታራሚዎቹ የይቅርታ ህግን ያሟሉ መሆናቸውን ተከትሎ ነው በይቅርታ እንዲለቀቁ መደረጉን የቢሮው ሀላፊ አቶ #ተኪኡ_ምትኩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
ታራሚዎቹ ከህዳር 20 ቀን 2011 ጀምሮም ወደ ህብረተሰቡ እንደሚቀላቀሉም ተመልክቷል።
የክልል መንግስት ባለፈው ዓመት የግንቦት 20 በዓልን ምክንያት ለ2 ሺህ 206 ታራሚዎች ይቅርታ አድርጎ አንደነበር ይታወሳል።
ምንጭ፦ fbc

ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል‼️
ባለፈው ሳምንት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ያሶ ከተማ በፈፀመ ጥቃት #ስምንት የአንድ ቤተሰብ አባላት #መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ህዳር 11 ቀን 2011 ማታ ከሶስት ሰዓት በኋላ ታጣቂዎች የቤተሰብ አባላቱን በጥይት ገድለው ቤታቸውንም እንዳቃጠሉ በጥቃቱ ባለቤታቸውንና የባለቤታቸውን ወንድሞች ያጡት የስምንት ልጆች እናት ወ/ሮ #ልኪቱ_ተፈራ ይናገራሉ።
"መጀመሪያ ተኩስ ከከፈቱብን በኋላ ቤት ውስጥ ጭድ ጨምረው እሳት ለኮሱብን። እኔና ልጆቼ በጓሮ በር በኩል አመለጥን። ሌሎቹ ግን እዚያው ተቃጠሉ" በማለት ሁኔታውን ያስታውሳሉ።
ልጃቸው አቶ ወጋሪ ፈይሳ በመኖሪያ ቤታቸው በወቅቱ ሃያ አንድ የቤተሰብ አባላት እንደነበሩና ቤታቸውም ፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያ በመሆኑ ደህንነት ተሰምቷቸው እንደነበር ይናገራል።
ነገር ግን ያልጠበቁት ነገር መከሰቱንና በተፈጠረው ነገርም ህፃናት ልጆች ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ እንዳሉም ይገልፃሉ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሳ አህመድ ከተማው ውስጥ ግድያ ስለ መከሰቱ መረጃ እንዳላቸው ነገር ግን ዝርዝር ጉዳዮችን እንደማያውቁ ገልፀዋል።
ከጥቃቱ የተረፉ የቤተሰቡ አባላት ሸሽተው የተጠለሉበት አዋሳኝ የምሥራቅ ወለጋ ሃሮ ሊሙ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጋሮማ ቶሎሳ ግድያው ስለመፈፀሙ ማረጋገጫ እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።
"አባቴ ፈይሳ ዲሳሳ፣ ወንድሙ ዲንሳ ዲሳሳን ጨምሮ ስምንት የአጎቶቼ ልጆችን አጥተናል። ግድያው በጣም አሰቃቂ ነበር" ይላሉ አቶ ዋጋሪ።
በተመሳሳይ እለት የቤተሰብ አባላቱን ግድያ ጨምሮ በያሶ ከተማ በተፈፀመ ጥቃት አርባ የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን ኗሪዎችና የአዋሳኝ ወረዳ አስተዳዳሪው ቢናገሩም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊው አቶ ሙሳ ግን አስር ሰው ብቻ ስለመገደሉ መረጃ እንዳላቸው ይገልፃሉ።
ሆኖም ግን ጉዳዩን በሚመለከት ተጨማሪ መረጃ እንደሚያስፈልጋቸው "መንገድ በመዘጋቱ ነገሮችን በቅርበት ማጣራት አልቻልንም" በማለት ተናግረዋል።
አቶ ሙሳ እንደሚሉት የረቡዕ ጥቃት ከመፈፀሙ ከጥቂት ቀናት በፊት ሁለት የመንግሥት ሰራተኞች ተገድለዋል። አርብ እለትም ደግሞ በካማሼ ሌሎች ሦስት ሰዎች መሞታቸውንም ገልፀዋል።
በያሶ ጥቃቱን የፈፀሙት ታጣቂዎች ከመሆናቸው በዘለለ ስለታጣቂዎቹ እስካሁን ምንም የተረጋገጠ መረጃ እንደሌለ አቶ ሙሳ ይናገራሉ።
'ያፈነገጡ የኦነግ ታጣቂዎች' ለአካባቢው ስጋት እየሆኑ እንደሆነ አቶ ሙሳ ቢናገሩም ያነጋገርናቸው ኗሪዎች እና የአዋሳኝ ወረዳ ሃላፊዎች ግን በአካባቢው #የኦነግ ታጣቂ እንደሌለ ገልፀዋል።
በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ አራት የካማሺ ዞን ሃላፊዎች አሶሳ ከተማ ስብሰባ ቆይተው ወደ ካማሺ በመመለስ ላይ ሳሉ በተከፈተባቸው ተኩስ ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ብዙዎች መገደላቸውንና ወደ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ከቀያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል።
በአሁኑ ወቅት ግን ነገሮችን #ለመቆጣጠር በያሶ ከተማ ፌደራል ፖሊስ፤ በካማሽ ደግሞ መከላከያ ሠራዊት እንደገባ አቶ ሙሳ ገልፀዋል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ🛫
ኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ7ኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካ የምርጥ አየር መንገድ ሽልማትን #አሸነፈ።
አየር መንገዱ ሞሮኮ ራባት ላይ እየተካሄደ በሚገኘው 50ኛው የአፍሪካ ታላላቅ አየር መንገዶች ማህበር አመታዊ ጉባኤ ላይ አሸናፊ መሆኑ የተበሰረው።
የእውቅናው ሽልማቱ ለአየር መንገዱ በፋይናንስና ትርፋማነት አፈጻጸም ላይ ባሳየው የላቀ ደረጃ ምክንያት እንደተበረከተለት ተነግሯል።
ምንጭ፦ FBC

#UpdateSport ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ውጤት፦
ጅቡቲ ቴሌኮም 1-3 ጅማ አባጅፋር
⚽ አስቻለው ግርማ
⚽ ማማዱ ሲዲቤ
⚽ ማማዱ ሲዲቤ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅቡቲ ቴሌኮም 1-3 ጅማ አባጅፋር
⚽ አስቻለው ግርማ
⚽ ማማዱ ሲዲቤ
⚽ ማማዱ ሲዲቤ
@tsegabwolde @tikvahethiopia